Tuesday, February 21, 2012

በ ‹‹እውነትና ንጋት›› የአባ ሰረቀ ስልታዊ ማፈግፈግ

የመፅኀፉ አርዕስ፡- እውነትና ንጋት
የገጽ ብዛት ፡222
ዋጋው 30 ብር
ጸሀፊ ፡- አባ ሰረቀ ወልደ ሳሙኤል ቆሞስ
በተስፋዬ አዳነ
(አንድ አድርገን የካቲት 13 2004ዓ.ም)፡- ይህ መፅሀፍ ሶስት ክፍሎች አሉት ፡፡ ክፍል አንድ ነገረ ማሪያምን መነሻ በማድረግ ‹‹በጥንተ አብሶ›› ላይ የሚያጠነጥን ነው ፡፡ ክፍል ሁለትና ሶስት የመፅሀፉ አዘጋጅ እና ማህበረ ቅዱሳን የገጠማቸው ውዝግብ ያሳየናል ፡ በዛሬው ምልከታዬ እኔን (እናንተን) የሚመለከተው ክፍል ላይ አተኩራለሁ፡፡

የጸሀፊው መግቢያ መልዕክት
የጸሀፊው የመግቢያ መልእክት በሚል ርዕስ ስር ፀሀፊው ለፅሁፋቸው መነሻ የሆናቸውን ሶስት ምክንያቶች በማስቀደም ጀምራሉ፡፡ ሶስቱም ምክንያቶች ወደ አንድ አቅጣጫ ነው የሚያተኩሩት፡፡ በተከፈተባቸው የስም ማጥፋት ዘመቻ ማስተባበል ላይ (እሳቸው እደሚሉት) ፡፡

ፀሀፊው መፅሀፉን ለመፅሐፋቸው መነሻ ምክንያት የሆናቸው በእሳቸው ላይ የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ ሀሰት እንደሆነ ለማስረዳት ሆኖ ሳለ ግራ በሚያጋባ ሁኔታ የነገስታቱን ታሪክ ሲያንቋሽሹ እና አሳፋሪ የሚባለውን ታሪካቸውን ብቻ መርጠው ሲኮንኑ ይታያሉ፡፡ ‹‹የአባቱን ቅምጥ ያገባና ከሁለት እህቶቹ ጋር የግብረ ስጋ ግንኙነት የነበረው›› ብለው የአንድ ንጉስ ታሪክ በማለት ከአንድ ገጽ በበለጠ ያሰፈሩት ይታያል(ገፅ 9 - 11) ምሁራዊ አፃፃፍ የጎደለው እና ኢ-ተአማኒ የሆነ ይህ የመግቢያ ክፍል በርካታ የታሪክ ጉዳዮችን ሲያነሳ (እንደ መፅሀፍ አቅም) አንድም ማጣቀሻ መፅሀፍ አይጠቅስም ፤ ያነሳቸው ሀሳቦች እውነት እንደሆኑ ሰነዶች ያስረዳሉ ፤ መረጃዎች ይጠቅሳሉ ፤ መዛግብት ያሳያሉ ፤ ከማለት ውጪ ለማረጋገጫነት የሚረዳ አንባቢም በነገሩ ላይ እርግጠኛ እንዲሆን የሚያስችል ሰነድ ፤ መረጃ እና መዝገብ አይጠቅስም፤ ይህ አንዳንድ የመንደር ወሬ ፈጣሪዎች ከሌላ የሰሙት ለማስመሰል ‹‹አሉ›› ‹‹ተባለ›› ፤ ‹‹ተደረገ›› ብለው እንደሚያስወሩት ያለ ነገር ይመስላል፡፡


ፀሀፊው ለምን ይቅርብኝ ብለው ያሰቡ ይመስለኛል፡፡ በገፅ 11  ላይ ‹‹የኢትዮጵያ ታሪክ በሚል መፅሀፍ ዋሊስ ባጅ እንዲህ ብሎ ይገልጸዋል ..ገፅ 283›› በማለት የእንግሊዘኛው ፅሁፍ እና የአማርኛው ትርጉም አስቀምጠዋል፡፡ በመሰረቱ የመፅሐፍ ርዕስ ተተርጉሞ አይጠቀስም፡፡ ይሁን መቼም ጸሀፊው የአፃፃፍ መሰረታዊ መርሆዎች አያውቁም ብንል እንኳን ለመፅሀፉ እና ለታሪኩ ተዓማኒነት ሲባል መቼ ? የት ሀገር ? በየት ማተሚያ ቤት? እንደታተመ መገለፅ ነበረበት፡፡ መፃፍ ስለተፈለገ ብቻ ፤ ሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የመፃፍ ነፃነት በመጠቀም ማሳተሚያ ገንዘብ እና አሳታሚ ድርጅቶችን መከታ በማድረግ መጽሀፍ አይፃፍም፡፡ አሁንም ከመፅሀፉ መግቢያ አልወጣሁም ፤ በጣም ያስደነገጠኝ ስለ ፀሀፊው ያለኝ አመለካከት ገና ገመነሻው የለወጡብኝ ሁለት ሀሳቦች ላስነብባችሁ፡፡

‹‹…….በርካታ መነኮሳትም የቤተመንግስቱ ዘብ ጠባቂዎች እና ደጅ ጠኚ መሆን ጀመሩ፣.. በዚህ ምክንያት ነገስታቱ ቤተክርስትያኒቱን ለስልጣናቸው እንደ አንድ ታላቅ መብት አድርገው መጠቀም ቀጠሉ››ገፅ 11 እውነት መነኮሳቶቻችን ምንኩስናቸውን ትተው ወይም አፍርሰው የነገስታቶች ዘብ ጠባቂ ነበሩ ? መቼ ? የት ? እነማን ?  ይህን ልተወው እና ‹‹ የዘአጉዬ (ዛጉዬ) ንግስና ለማፋለስ ከፍተኛ አይነተኛ ሚና የተጫወቱ የሀይማኖት ስራዎች  ርስት ጉልት ወይም ሲሶ መንግስት የሚባል አዲስ ነገር ተፈጠረላቸው ፤ በእንቅስቃሴው የተሳተፉ እና ከፍተኛ ሚና የተጫወቱ የአንዳንድ ታላላቅ አበምኔቶች በቤተ መንግስት ታላቅ ስፍራ ተሰጣቸው ›› ገፅ 18 ይህ ሀሳብ  በማያሻማ ሁኔታ የአቡነ ተክለሐይማኖት ቅድስና  የማይደግፉ ወገኖች የሚሰነዘር ነው፡፡ ጸሀፊው ይህን ለማለት ለምን እንደፈለጉ ወይም ይህን ማለታቸው ሰልፋቸው ከየት ወገን እንደሆነ ፍንጭ ሰጥቶ ወደ ቀጣዩ ክፍል የሚያሸጋግር ድልድይ ነው፡፡

ጥንተ አብሶ(Original Sin)
ክፍል አንድ በዋናነት የሚያተኩረው ‹‹ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ወይም የአዳም በደል አላገኛትም›› በሚል በአቡነ ማቲያስ እና ‹‹ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ነበረባት ፤ ጌታን ስትወልድ መልአኩ ሲያበስራ ነው መንፈስ ቅዱስ ያነፃት›› በሚል ቀሲስ አስተርእየ ፅጌ የቀረበው ትምህርት ላይ ሆኖ ዲሲ ማህበረ ካህናት ለጉዳዩ ዳኝነት ለመስጠት ሲሞከር የሚታይ ክፍል ነው፡፡

ጸሀፊው ራሳቸውን የጉዳዩ ገለልተኛ አድርገው ለዳኝነት እንደቀረቡ በሚናገሩበት በዚህ ክፍል የቀሲስ አስተርእየን ሀሳብ የሚደግፉ (የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ ወይንም የአዳም በደል ነበረባት) በማለት ስድስት ያህል የጽሁፍ ማስረጃሆች እሳቸው ያሉበት የማህበረ ካህናቱ የተቋቋመው ኮሚቴ አቅርቧል፡፡ (ገፅ 30 እና 56 ፤ ማስረጃዎቹን ካቀረቡልን አንፃር በዝርዝር እንመልከተው እና እንመዝነው፡፡
1.      ሐይማኖት አበው ትርጓሜ ወንጌል ፤ መጻህፍተ ቅዳሴ እና ገብረ ህማማት
ጸሀፊውን ጨምሮ የኮሚቴዎች አባላት በግርድፍ በእነዚህ መጻህፍት ላይ ሀሳባቸውን የሚደግፍ ትምህርት አለው ይበሉ እንጂ የትኛው መጽሀፍ ላይ ምን ተብሎ እንደተፃፈ አልጠቀሱም ፡፡ እንዲህ አይነት ነገር ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልእ ‹‹ ገበሬ አስደንግጥ ጥቅስ›› ይሉታል፡፡ ገበሬው በማሳ እያለ ድንጋይ ሲፈነቅል ፤ አልያም ክምር ሲያነሳ ፤ እባብ ያልሆነ ነገር ግን እባብ የሚመስል ፍጡር አፈትልኮ ይሄዳል፡፡ በዚህ ሰዓት ገበሬው እባብ መስሎት ይደነግጣል፡፡ አስተውሎ ሲያይ ግን እባብ እንዳልሆነ እና በከንቱ እደደነገጠ ይረዳል፡፡ አልያም እንደ ከተማ ባህታዊያን ምዕራፍ እና ቁጥር ሳይናገሩ ጌታ በማቴዎስ ወንጌል እንዲህ ብሏል ብሎ እንደመናገር አይነት ነው ፤ የሰዎቹ የመረጃ አገላለፅ ወይም አጠቃቀም፤
2.     የመልክከ ብርሀን አድማሱ ጀንበሬ
እዚህ ጋር ሁለቱን የሊቁን መጻህፍት ጠቅሰዋል ፤ እንደተለመደው ገፅ አይጠቅሱም ‹‹መጽሎተ አሚን›› እና ‹‹ኮከሐ ሃይማኖት›› ፤ በጣም ነው የሚገርማችሁ ሁለቱን መጻህፍት ከዚህ በፊት እና አሁን ይህን ጉዳይ መነሻ በማድረግ አንብቤአችዋለሁ፤ አንድም ቦታ የነሱን ሀሳብ የሚደግፍ ነገር አላየሁም ፤ ያነበባችሁ ካላችሁ ምስክርነት መስጠት ትችላላችሁ ፤ ያላነበባችሁም ሊቁ የሞቱት አባታችን እንጂ መጻህፍቶቻቸው አሉና አንብባችሁ ታዘቡኝ ፤ አይ ሊቁ አባታችን በህይወት ቢኖሩ…
3.  የአለቃ አያሌው መጻህፍት
ሁለት የአለቃ አያሌው መጻህፍት ተጠቅሰዋል ፤ ‹‹የኢትዮጵያ እምነት በሶስቱ ህግጋት›› እና ‹‹ወላዲተ አምላክ በኢትዮጵያ›› ለዚሁ ጉዳይ ይረዳኝ ዘንድ በማለት እነዚህን መፃህፍት አንብቤያችዋለሁ፡፤ ፍፁም አለቃ አያሌው ታምሩ ‹‹ እመቤታችን ጥንተ አብሶ ነበረባት ብለው አይፅፉም ›› እንደ እድል ሆኖ ይህ የቀሲስ አስተርየ ክህደት በተነሳበት ወቅት አለቃ አያሌው በህይወት ነበሩና ለእነሱ ብለው ባዘጋጁት መፅሀፍት (ዜና ህይወት ዘቅድስተ ቅዱሳን እመ አምላክ) ገፅ 1 ላይ እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹ ስሜን ጠርተው ማታለያ ያደረጉኝ ቄስ አስተርየንና ዲያቆን ፅጌን እንዲሁም የዜና ልደታ ጋዜጣ ጸኀፊን እኔን አትጨምሩኝ ፤ ተመለሱ እላለሁ ፤ የቀራችሁት ምዕመን ግን ወደ ስህተት እንዳትገቡ በበደላቸው እንዳትተባበሩ ምክሬን እየሰጠሁ ይህን መፅሀፍ አንብባችሁ እንድትጠቀሙበት አደራ እላለሁ ›› እናም ይህን መፅሀፍ ታነቡ ዘንድ ግብዣዬ ነው፡፡
4.  ከፕሪስተን ዩኒቨርሲቲ የተገኝ የብጹዕ ቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ መፅሀፍ
<<Yet eastern orthodoxy does not share the Roman catholic dogma of the immaculate conception which teaches the virgin’s exemption from origin sin. According to the Eastern Orthodoxy church, the blessed virgin is truly human, shoring the origin sin which is part and parcel of humanity which ultimately  expresses itself in natural death.

ይህን በግርድፉ ወደ አማርኛ ስመልሰው ‹‹ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ድንግል ማርያም ጥንተ አብሶ አልነበረባትም የሚል የኢማኩሌት ኮንሰፕሽን አስተምህሮ የሆነው የሮማ ካቶሊክ ዶግማን አይጋሩትም፡፡ እንደ ምስራቅ ኦርቶዶክስ አስተምህሮ ቅድስት ድንግል ማርያም ሰው እንደመሆኗ በሰው ዘር ላይ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣውን ራሱንም በተፈጥሯዊ ሞት የሚገልጸውን ጥንተ አብሶን ትናገራለች›› ብለው ፅፈዋል፡፡ በዚህ ጉዳይ በቀጣይ የምለው ነገር ቢኖረኝም ለአሁን ትንሽ ልበል፡፡ ይህ የአቡነ ጳውሎስ መፅኀፍ (በአባ ሰረቀ ብርሀን መፅሀፍ ላይ የተፃፈው ብቻ ለማለት ፈልጌ ነው) የሚናገረው ስለ ምስራቅ አብያተክርስያናት ነው፡፡ እኛ ደግሞ የኦሪየንታል ቤተክሰርስትያን አካላት ነን ፡፡  ቢሆንም በእኛ ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ማለት በአስተዳደር ከፍ ያለ ቦታ ላይ የሚቀመጥ ፤ ስልጣነ ክህነቱ ከከፍተኛው ስልጣን (ጵጵስና ) የማይበልጥ ፤ የቤተክርስትያኑ አባል ማለት እንጂ የቤተክርስትያኒቱን አስተምህሮ የሚቀይር ፤ የሚለውጥ የሚሽር የማይሳሳት ማለት አይደለም፡፡ ሊሳሳት ይችላል ፡፡ አቡነ ጳውሎስ ይህንን ሀሳብ ደግፈው ቢፅፉ እንኳን ጽሁፋቸውም ሆነ እሳቤያቸው የሳቸው ማንነት እንጂ የቤተክርስትያኑን አስተምህሮ የሚወክል አይደለም፡፡ ስለሆነም ከጸሀፊውና ከያዘው መልዕክት አንፃር ለአቅመ መረጃ ያልደረሰ የአጯጩሁኝ መረጃ ነው፤ ግን አባ ሰረቀ ይህን መረጃ ለምን በዚህ ሰዓት መጠቀም ፈለጉ
5.     የአራቱ የእህት አብያተክርስትያናት እና የሌሎች ኦርቶዶክሳዊ መጽሀፍት
ከአራቱ እህት አብያተ ክርስትያናት ጋር አንድነት አለን ፤ ይህ ማለት ግን ልዩነት የለንም ማለት አይደለም ፤ ከልዩነታችን ውስጥ ደግሞ ይህ ጥንተ አብሶ ጉዳይ ነው ፤ ሊቁ አባታችን አለቃ አያሌው ይህን የኮሚቴዎች ሀሳብ እና የቄስ አስተርዮን አመለካከት በሚመለከት እንዲህ ብለው ነበር፡፡ ‹‹ ቄስ አስተርየ ከእህት አብያተክርስትያናት መለየት የለብንም ይላል ሌላው ጸሀፊም የእኛ አስተማሪዎቻችን እስክንድራውያን ናቸው ይላል ፡፡ እስክንድራውያን ለቡራኬ የተመረጡ እንጂ የኢትዮጵያ ሊቃውንት የትምህርቱን ወንበር ለሌላ አሳልፈው አልሰጡም (ዜና ህይወተ ዘቅድስተ ቅዱሳን ገጽ 39)

እንደሚታወቀው 1600 ዘመን በላይ ከእስክንድርያ 111 ሊቀ ጳጳስ አስመጥተናል፡፡ ይመጡ የነበሩት ጳጳሳትም ለመባረክ እና ስልጣነ ክህነትን ለመስጠት እንጂ ለማስተማር አልነበረም፡፡ እንኳን ለማስተማር ለመነጋገር እንኳን በአስተርጓሚ ነበር  የሚጠቀሙት ፤ ሀገራችን ኢትዮጵያ ክርስትናን ከተቀበሉ ሀገራት ቀዳሚ ነች ፡ በአፍሪካ ደግሞ ከግብጽም ትቀድማለች ፤ በ34 ዓ.ም ፡፡ ስለሆነም አስተምህሮዋ በቀጥታ ከሐዋርያት የተቀበለችው እና በራሷ ሊቃውንት የተስፋፋ ነው ፡፡

ጸሀፊው የሚገኙበት ኮሚቴ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ‹‹ ጥንተ አብሶ አለባት›› ብሎ ድፍረቱን እና ክህደቱን ያሳየን ከላይ ባየናቸው ምዕራፍና ቁጥር በሌላቸው ‹‹ ገበሬ አስደንግጥ›› ጥቅሶች ነው፡፡


From Anonymous
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም «ጥንተ አብሶ» የሚባል ነገር ፈጽሞ የሌለባት፣ ከአባታችን ከአዳም በሰው ልጆች ሁሉ ላይ የወረደው የውርስ ኃጢአት እርሷን ግን በጭራሽ ያልነካት ያልደረሰባት፣ ይህም የሆነው የሰው ዘር ሳትሆን ቀርታ ወይም ልዩ ሰማያዊ ፍጡር ሆና ሳይሆን ከአባቷ ከቅዱስ ኤያቄምና ከእናቷ ከቅድስት ሃና የተወለደች ሰማይና ምድርን ለፈጠረ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ እናትነት አስቀድማ የተመረጠችና የታጨች በመሆኗ ለዚህ የመረጣት መንፈስ ቅዱስ ገና በእናቷ ማኅፀን ሳለች በዘር ይተላለፍ ወይም ይቆራኝ ከነበረው የውርስ ኃጢአት ጠብቋታል። እንዳይደርስባትም አንጽቷታል /ንፁህ አድርጓታል/። ምክንያቱም ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና። ስለዚህም ከሴቶች ሁሉ የተለየች መሆኗን በቅዱስ ገብርኤል አብሳሪነት በቤተ መቅደስ እያለች ከሦስቱ አካላት አንዱን ወልድን በግብረ መንፈስ ቅዱስ እንደምትፀንስ ተነግሯታል። ተበስሮላታል። በዚያን ሰዓትም የመልአኩን ቃል በመቀበል «እንደ ቃልህ ይደረግልኝ» ስትል ብስራቱን ተቀብላለች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

እንግዲህ የቤተ ክርስቲያናችን ትምህርቱ ከጥንት የመጣው የአባቶቻችንም ምስክርነቱ ዛሬ ደግሞ የእኔም እምነት ይሄ ነው። የማስተምረውም የምመሰክረውም ይህንኑ ነው። ይሁንና ዛሬ ዛሬ እንደሚሰማው «እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን መንፈስ ቅዱስ አንጽቷተል ቀድሷታል» የሚለውን አባባል የግድ ከነጻች ኃጢአቱ ነበረባት ማለት ነው አለበለዚያ ከምን አነፃት? በሚል በማይገባ ስህተት ውስጥ ገብተው ይህንኑም በድፍረት የሚናገሩ ሰዎች አልታጡም። ምንም እንኳ መለኮታዊ ጥበብን በሰው ቋንቋ ለመግለጽ አስቸጋሪ ቢሆንም ለማነጻጸርም ቢያዳግትም ለእኛ በሚገባን መንገድ በቀላል ምሳሌ ለማስረዳት ያህል፦ አንድ ሰው ከመኪና ግጭት አደጋ ለጥቂት ድኗል። ታዲያ ይህን ሰው እግዚአብሔር አዳነው እግዚአብሔር ጠበቀው እንላለን። ሆኖም አድኖታል ጠብቆታል ስላልን የግድ ተገጭቶ ነበር የሚለውን ሃሳብ አያስከትልም። ሳይገጭ እግዚአብሔር ጠብቆታልና። ለመዳን ለመትረፍ መገጨት ወይም ለአደጋው መጋለጥ የግድ የለበትም ፈጦ ከመጣው አደጋ ሊሰወር ይችላልና። ጠበቀው አዳነው ማለት እንችላለን። ነገር ግን አዳነው ስለተባለ ጠበቀው ስለተባለ አለበለዚያ ከምን አዳነው ከምን ጠበቀው ስለደረሰበት ስለተገጨ አይደለም ወይ? ብሎ ማሰብ አለማስተዋል ካልሆነ በቀር ሌላ ሊሆን አይችልም። እንደዚሁም ሁሉ እመቤታችንን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ከአዳም የውርስ ኃጢአት ጠበቃት፣ እንዳይደርስባት አነጻት ስለተባለ ብቻ ያነጸት ስለነበረባት ነው ብሎ ማመን መከራከር ለእኔ ኅሊናዬ የማይቀበለው ነገር ነው። ስለዚህ በትክክለኛው መልክ መሄድ ሲገባ አዲስ ሃሳብና አዲስ ፍልስፍና ማምጣት ትርፉ ውድቀት ነው። ከቶውንስ የፍልስፍና እናቱ መቸገር ነው ተብሎ የለ። ስለዚህ ለሁሉም የሚበጀው በእመቤታችን ላይ ምርምር ማካሄዱ ሳይሆን ይልቁንስ ለአሥራት ሀገሯ ለኢትዮጵያችን ሰላሙን በአማላጅነቷ እንድታወርድልን በረከቷ እንዲበዛልን ፍቅሯ እንዲጨምርልን መማፀን መለማመን እንጂ እግዚአብሔር ያከበራትን ለእናትነት የመረጣትን በማንና በምንም ምሳሌ የማይገኝላትን ንጽሕተ ንጹሐን፣ ቅድስተ ቅዱሳን በሆነች እናታችን ላይ ቃል መናገሩ አስተያየት መሰንዘሩ በራስ ላይ መልሶ ለመጣል ድንጋይ ማንሳት ነውና ከዚህ መቆጠብ ያስፈልጋል። እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።

15 comments:

  1. Would you please write more about this book and Aba Serke. I'd like to know more about it.

    Good perception, God bless you.

    ReplyDelete
  2. Almot bay tegaday... ayee aba

    ReplyDelete
  3. Dear Tesfaye

    God bless u. It is very Knowledgeable way of writing, Good on on.
    It is good information u gave us and amazing the patriarch wrote, very sad "" <>
    That is why Abune Pawlos support, all these tehadesso including Abune Fanuel(who made a big stir at Awassa now starting in America people pls wake up do ur own research) and Getachew Doni , All Begashaw groups and tehadesso etc...

    God Bless for this excellent information dear Tesfaye. Always ONE TEWAHEDO, DINGILE Getachin yetekemetebat Nesihit Nesuhan Tinte Teabeso yalagegnat ,yalderesebat nat Enatchin.

    LONG LIVE FOR ONE TEWAHEDO

    ReplyDelete
  4. Replies
    1. what do you mean by so what?
      you mean I don't care? ............thats you don't like truth!!!!!!!!!!!!

      Delete
  5. mel'eku betam arif new. ye hohiatina yekalat gidifet woim yalitelemedu ena ke Amarigna quanqua sir'at wuch newu yemititsifu. bistekakel melkam new.

    ReplyDelete
  6. Aba Sereke,please,find your place!Our Lady is immaculate.Egziabher senef aydelem maderiawen yemyetebek!!'menfeskidus akeba emkerse emma'
    Glory to the Almighty God.

    ReplyDelete
  7. «ነገር ግን ቃላችሁ አዎን አዎን፥ ወይም አይደለም አይደለም ይሁን፤»
    ማቴ ፭፥፴፰።


    ከሊቀ ኅሩያን ከፈለኝ ወልደ ጊዮርጊስ
                ይህ ቃል፦ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፦ በምንም ነገር ቢሆን መማል ፈጽሞ እንደማይገባ ከተናገረ በኋላ የተናገረው ቃል ነው። እኔም እውነት የሆነውን እውነት፥ ሐሰት የሆነውን ደግሞ ሐሰት ለማለት ይኽንን ሕያው የሆነውን የጌታዬን የአምላኬን የኢየሱስ ክርስቶስን ቃል መነሻ አድርጌያለሁ።
                   ቅዱሳን አባቶቻችን ጥንተ ጠላታቸው ሰይጣን የተለያየ ክብረ ነክ ስድብ ሲሰድባቸው በትእግሥት ያሳለፉት፥ በአኰቴት ይቀበ ሉት ነበር። ስለ ሃይማኖታችው መዋረድ ለእነርሱ ጸጋ ነውና። ቅዱስ ዳዊት ከዙፋኑ ወርዶ ከተርታው ሕዝብ ጋር ተሰልፎ በመዘመሩ ሜልኰል ወለተ ሳኦል አሽሟጣው ነበር፥ እርሱ ግን ሽሙጡን በጸጋ ተቀብሎ ስለ እግዚአብሔር ክብር ገና ከዚህ የበለጠ ራሱን እንደ ሚያዋርድ ነግሯታል። ፪ኛ ሳሙ ፮፥፳-፳፪። የገዛ ልጁ አቤሴሎም አሳድዶት በስደት በሚንከራተትበትም ጊዜ የሳኦል ቤተ ዘመድ የሆነ፥ ሳሚ የሚባል ሰው በሕዝቡና በመኳንንቱ ፊት ሰድቦታል። ይህ በዳዊት ላይ የወረደ ስድብና ውርደት ያሳዘናቸውና ያበሳጫቸው የሶር ህያ ልጆች ሰይፋቸውን መዝዘው ነበር። በዚህን ጊዜ ቅዱስ ዳዊት፦ «ተዉት ይስደበኝ፤ (ይርገመኝ፥ ያዋርደኝ፤)፤» ብሎአቸዋል። በየዘ መኑ የተነሡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንም ስድቡን ብቻ ሳይሆን ሰይፉን፥ እሳቱን፥ ግርፋቱን ሁሉ ታግሠው እስከ ሞት ድረስ ጸንተዋል። «እስከ ሞት ድረስም የታመንህ ሁን፤ የሕይወት አክሊልንም እሰጥሃለሁ።» የተባለውን በተግባር ፈጽመዋል። ራእ ፪፥፲። በሃይማ ኖታቸው ሲመጡባቸው ግን ትእግሥት የላቸውም፥ «መናፍቅ» ሲሉአቸው ዝም አይሉም።
              እኔ ይኽንን መግለጫ ከአምስት ዓመታት በኋላ እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ ለማውጣት የተገደድኩት፥ በ2002 ዓ.ም. በተከበሩ በመምህር ሀብተ ማርያም ተድላ በተጻፈ መጽሐፍ ላይ እና በሰሞኑ ለቅድስት ተዋህዶ ሃይማኖት ለመሠዋት በተዘጋጁ የአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ወጣቶች ለቅዱስ ሲኖዶስ ስለ ተሃድሶ መናፍቃን ባቀረቡት አቤቱታ ላይ «ከኑግ ጋር የተገኘህ ሰሊጥ አብረህ ተወቀጥ፤» ሆኜ በመገኘቴ ነው።
              አባታችን መምህር ሀብተ ማርያም ተድላ፥ በዲሲ እና አካባቢዋ አብያተ ክርስቲያናት ትብብር ተቋቁሞ በነበረው የካህናት ማኅበር፥ በ«ቄስ» አስተርአየ ጽጌ፤ አቅራቢነት ተነሥቶ የነበረውን የሃይማኖት ክርክር 219 ገጽ በሆነው መጽሐፋቸው የማያዳግም ኦርቶ ዶክሳዊ መልስ ሰጥተዋል። ይህም በዘመናቸው ለተነሡ መናፍቃን በአፍም በመጽሐፍም መልስ ከሰጡ ጥንታውያን ሊቃውንት ጋር የሚያሰልፋቸው ነው። በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ዙሪያ፦ «ጥንተ አብሶ ነበረባት፤» በሚሉ ወገኖችና «ጥንተ አብሶ አልነ በረባትም፤» በሚሉ ወገኖች መካከል ዱላ ቀረሽ ክርክር በሚደረግበት ጊዜ እኔም በቦታው ተገኝቼ ነበር። ምክንያቱም በወቅቱ የማገለ ግለው ዲሲ ማርያም ስለነበረ ነው። የጉባኤውም ቃለ ጉባኤ ጸሐፊ ነበርኩኝ። የጉባኤው ሰብሳቢም ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ነበሩ።
              ይህ የሃይማኖት ክርክር በሚደረግበት ወቅት፦ የ«ቄስ» አስተርአየን ሃሳብ የደገፉ ሰዎች ዝርዝራቸው በመጽሐፉ ላይ ተጠቅሷል። ይኽንን ፍጹም የሆነ ክህደት ከተቃወሙት መካከል ደግሞ እኔ እና ርዕሰ ደብር አብርሃም እንገኝበታለን። ይኽንንም በወቅቱ በስደት እዚህ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፥ የሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ የነበሩት አቡነ ማትያስ፥ ያውቁታል። በኋላም ለሀገረ   ስብከቱ ተሹመው መጥተው ለነበሩት ለብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ሁሉንም ነገር አስረድቼ ማስረጃዎችን ሰጥቻቸዋለሁ። ጸሐፊው መምህር ሀብተማርያም ተድላ በመጽሐፋቸው ገጽ 34 ላይ፦ «ለቅዱስ ሲኖዶስ በተላከው በማኅበረ ካህናቱ ጽሑፍ አለመግባባት የተፈጠረበት ምክንያት ከሚለው አርእስት ቀጥሎ የሰፈረው ይነበባል። አንደኛው ወገን፦ < አንጺሖ ሥጋሃ ኃደረ ላዕሌሃ> የሚለውን  ቃል ተቀብሎ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የነቢብ፥ የገቢር፥ የኀልዮ ኃጢአት ያልነበረባት የሌለባት ናት። ነገር ግን በአዳማዊ ዘር በኲል ከሚተላለፈው ውርስ መንፈስ ቅዱስ አንጽቷታል ሲል፤ ሁለተኛው ወገን ደግሞ ገና ሳትወለድ በዘር ይተላለፍ ከነበረው አዳማዊ ውርስ ነጻ ናት የሚል ነው፤» ብለዋል። ይህ ትክክል ነው። ትክክል ያልሆነው ይኽንን የተረጐሙበት መንገድ ነው። «ይህ ከዚህ በላይ የሚነበበው የማኅበረ ካህናት ጽሑፍ የተጣመመና የተዛባ (Distorted) በሆነ አጻጻፍ የተቀመጠ ወይም ለማደናገር ሆን ተብሎ የተደረገ አሻሚ ሁኔታ ይታይበታልና መስተካከል ይኖርበታል፤» ብለዋል። ይህም በወቅቱ «እመቤታችን ጥንተ አብሶ አልነበረባትም፤» ብለን የተከራከርነውን ሰዎች እምነት የነካ ነው። ምክንያቱም «ጥንተ አብሶ አልነበረባትም፤» የሚለው የገባው የእኛን እምነት ለማንጸባረቅ እንጂ ለማደናገር አይደለምና ነው። አባታችን መምህር ሀብተ ማርያም ይኽንን ያደረጉት ሆን ብለው እንዳልሆነ ስለሚገባኝ ለወደፊቱ እንዲስተካከልልኝ በትኅትና እጠይቃለሁ።
              ምንአልባት በወቅቱ ምን እርምጃ ወሰድክ የሚል ጥያቄ ይነሣ ይሆናል፥ ተገቢም ነው። ኅዳር 1 ቀን 1998 ዓ.ም. ስድስት ገጽ የቅሬታና የአቋም መግለጫ በማውጣት በጽሑፍ አሰራጭቻለሁ፥ በሬድዮም አስነግሬአለሁ። በዚህም ምክንያት ከዲሲ ማርያም ከሥራዬ ተባርሬ እስከነ ቤተሰቤ በረሀብ አለንጋ ተገርፌአለሁ። በኋላም ቅዳሜ ቅዳሜ አገለግል ወደነበረበት በሪችመንድ ደብረ መንክራት ልደታ ለማርያም ቤተክርስቲያን ብቻ ተወስኜ በምኖርበት ጊዜ፥ ቤተክርስቲያኗን ወደ እናት ቤተክርስቲያን በማስገባቴ ብዙ ፈተና ደርሶብኛል። ከፈተናውም አንዱ፥ የዲሲ ማርያም አስተዳደር ሪችመንድ ከሚገኘው ቦርድ ጋር በመመሳጠር ፍርድ ቤት ገትረውኛል። ይኽንንም ብፅዕ አቡነ ገብርኤል ያውቁታል። ምክንያቱም ቦርዱ በምስክርነት ጠርቷቸው ፍርድ ቤት ተገኝተው ስለነበረ ነው። መገኘታቸውም በእኔ ላይ ለመመሥከር ሳይሆን የፍርድ ቤቱን ትዕዛዝ ለማክበር ሲሉ ብቻ ነበር። ነገር ግን ከሳሾቼ ምንም ማስረጃ ማቅረብ ስላልቻሉ ክሳቸውን ለማቆም ተገደዋል። ዳኛውም ለእኔ ፈርዶልኝ ፋይሉን ዘግቶታል። የእኔ አቋም በግልፅ የታወቀ በመሆኑ ከአሁን ቀደም ከብፁዕ አቡነ ማትያስና ከብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ጋር አሁንም ከብፁዕ አቡነ አብርሃም ጋር እናት ቤተክርስቲያኔን እያገለገልኩ ነው። ሃይማኖቴም የጠራ ነው። በመሆኑም «መናፍቅ» መባልን እምቢ ብያለሁ፥ ነፍሴ ትጸየፈዋለች። በመሆኑም ከአምስት ዓመታት በፊት ያወጣሁትን አቋሜን ዛሬም እነሆ እላችኋለሁ። እስከ ሞት ድረስም ያው ነው፥ አይለወጥም።  
    ኅዳር 1 ቀን 1998 ዓም

    ReplyDelete
  8. This comment has been removed by a blog administrator.

    ReplyDelete
  9. Thank you for your information, but is the word used by Abune Paulos is ...shoring or sharing the origin sin? If shoring the translation would be different from what you translate.So please tell us the right word what he write.

    Yen

    ReplyDelete
  10. Great article, please publish this in a book format (whether it is short volume or not). Put every necessary documents. Dear Tesfaye for your writing keep the polite way of writing. Just show us the truth we will take it from there. "answering in anger way is not good"

    All the best, GOD be with us,

    ReplyDelete
  11. Eastern and Oriental Orthodox


    Immaculate Conception is presented by artists in Orthodox Church too. Here Holy Mary in Perlez, Vojvodina, Serbia.
    Eastern Orthodox Christians say that Mary was without sin for her entire life, but they object to the dogmatic declaration of her immaculate conception.[57]
    In the tradition of Ethiopian Orthodoxy,, a branch of Oriental Orthodoxy, the Kebra Nagast says:
    He cleansed eve's body and sanctified it and made for it a dwelling in her for adam's salvation. She [i.e., mary] was born without blemish, for He made her pure, without pollution, and she redeemed his debt without carnal union and embrace...Through the transgression of eve we died and were buried, and by the purity of mary we receive honour, and are exalted to the heights (emphasis added).[58] http://en.wikipedia.org/wiki/Immaculate

    ReplyDelete
  12. What about a book by Ejigayehu (Elzabet????????????) yesuama..kikikikikik new

    ReplyDelete
  13. So my question for Tesfaye about immaculate conception is that are you saying that we differ from the oriental orthodox church in the matter of dogmatic issues? if so i have read the book and it shows documents signed by EOTC and coptic church of Egypt that we have the same beliefs (DOGMA) so, are you telling us that we differ from them? this is a new teaching you are telling us i thought our difference is in canonical/ traditional related issues. If you are saying that we differ from them are you saying that we are the same with the Catholics in regards to immaculate conception because the Catholics are the only believers of immaculate conception. So your article is an attack on a person who have tried to write a book that shows the issues that we currently have in our church which needs immediate decision by the holy synod which has slept on it for years. However, from my understanding the book shows that there is an issue that needs decision before it goes farther and confuses the theologians as well as the believers of our church. So why are you cutting peaces off information that the writer probably didn't mean to say????

    ReplyDelete