Thursday, January 26, 2012

አቡነ ፋኑኤልን በሚዛን


(አንድ አድርገን ጥር 17 ፤ 2004ዓ.ም)፡- ባለፈው ቅዳሜ ጥር ፲፪ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. አባ ፋኑኤል በቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት በአቶ አዲሱ አበበ አማካኝነት  አጭር ቃለ መጠይቅ አድርገው ነበር፣ በቃለ ምልልሱም በርካታ የሆኑ ውሸት አዘል መልዕክቶችን በአቡነ ፋኑኤል  ተላልፈዋል ከቃለ መጠይቁ አለፍ አፈፍ ብለን   ለማቅረብ እንሞክራለን፡፡ በመቀጠል ጥያቄዎችን በተከታታይ እንመልከታቸው ፡፡
 (Jan 21, 2012) ከVOA ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ
(ከ05፡00 ደቂቃ አንስቶ እስከ 25፡00ደቂቃ )-- የ20 ደቂቃ ቆይታ አለው

ጥያቄ: አባታችን አሁን የመጡበት ሹመቶ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው?
መልስ፡ አዎ፣ ከዚህ በፊት መጥቼ ቅዱስ ፓትሪያሪኩንም ነግሬያቸው ነበር እኔ የመጣሁት ሀገሬን ለማገልገል ነው እና በተቻለ መጠን እዚሁ ቢያረጉኝ ብዬ ነበር ነገር ግን በቅዱ ሲኖዶስ ስለታዘዝኩኝ ትዕዛዙን አክብሬ መጥቻለሁ፣ በመቀጠም እራሴው ደብዳቤ ጽፌ ወደ ሀገሬ እንዲመልሱኝ ያለምንም ችግር በመጣሁ በሦስት ወሬ  ወደ ሀገሬ  ተመልሻለሁ ነበር ያሉት።

እርምት: እኛ እስከምናውቀው ድረስ ከዚህ በፊት በመጡበት ወቅት ትልቅ ችግር ተነስቶ እንደውም በቅዱስ ሚካኤል ደብር መቀመጥ እንደማይችሉ ተነግሯቸው፣ እንደዛ ከሆነ የቤቱ ባለቤት እራሴው ነኝ እስቲ የምታደርጉትን እናያለን ብለው ከጥቂት የቤተክርስቲያኑ አባላት ጋር አምባጓሮ ጀምረው በዛው ጊዜ የተጀመረው የፍርድ ቤት ክስ እስከ አሁን ድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለሁለት ከፍሎት ይገኛል፣ ቤተክርስቲያኑንም ለአላስፈላጊ የ$200000 ብር ወጪ ተዳርጓል ለምን ይሄን ሸሸጉ?
ሌላው በዚሁ በመጡበት ጊዜ በተለምዶ እራሳቸውን ገልልተኛ ብለው የሚጠሩ አብያተ ክርስቲያናት ስብስብ ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለንም ብለው በዛው ጊዜ ከገለልተኞች አንድነት የወጡበት እና ባይተዋር የተደረጉበት ጊዜ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

ጥያቄ: እንዴት በድጋሚ ሊመለሱ ቻሉ?
መልስ: "ሕልም ሲደጋግም እውነት ነው እንደሚባለው" አሁን ለሁለተኛ ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ይሄን ሀገረ ስብከት እንዳገለግል ስላክ እውነትም እግዚአብሔር እንዳገለግለው የፈለገው እዚህ መሆን አለበት ፤ መሆን አለበት ብዬ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ ትዕዛዝ ለማክበር ብዬ ተመልሼ መጣሁ።

እርምትእርሳቸው እንዳሉት ሕልም ሲደጋግም የሚሉት ቅዠት ካልሆነ ሕልም እንዳልደገማቸው ብናውቅም ባለፈው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወቅት ከዚህ አደራጅተው በቀሲስ አማረ ካሣዬ መልዕክተኝነት የተላኩትስ? እነሱም በሕልም ነው በዕውን መልሱን ለሳቸው እንተወው እና ከዚህ በፊት ወደዚህ ዋሽንግተን ዲሲ በሕገ ወጥ መንገድ በመጡ ጊዜያት ሁሉ ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ እውቅና ወይም የለሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ እውቅና ሲሾሙ፣ ሲሸልሙ፣ ቤተክርስቲያን ሲባርኩ፣ እንዲሁም የተለያየ ከቀኖና ውጪ ሲሰሩ በነበረበት ጊዜ ሁሉ፣ በተለያዩ በሄዱባቸው ቦታዎች ሁሉ ‹‹የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ እኮ እኔ ነኝ አሁን ያሉት አባት ከተነሱ ቆይተዋል ›› በማለት ይናገሩ የነበረውስ? የቅዱስ ሲኖዶስን ትዕዛዝን አከብራለው ማለታቸው ማንን ሊያታልሉ ነው፣ "ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት" እንዳይሆንቦት እንላለን።
ጥያቄ: ለሁለተኛ ጊዜ ተሹመው ሲመጡ ምን አይነት አቀባበል ተደረገሎት?

መልስ: ለሁለተኛ ጊዜ ተመልሼ ስመጣ በርካታ የዋሽንግተን ዲሲ ካሕናት፣ አስተዳዳሪዎች፣ የቦርድ ተወካዮች፣ ምዕመናን በታላቅ አክብሮት አቀባበል አድርገውልኛል።

እርምትበወቅቁ የተገኙ የዚህ ዝግጅት ተወካዮች እንደገለፁልን የቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያ ቦርድ አባላት ሦስቱ፣ ከካህናት የኪዳነ ምሕረት ቨርጂኒያ፣ ቀሲስ ደረጀ ስዩም፣ ቀሲስ ይስሐቅ፣ የደብረ ምህረት ካህናት በሙሉ፣ በጣም ጥቂት የደብሩ ሰንበት ት/ቤት አባላት ብቻ ነበሩ የተገኙት ፤ ከተገኙት ጥቂት ካህናት ውስጥም ደጅ ጥናት እንደሆነ ይገመታል ለምን እንደመጡም የታወቀ ነው ፤ እንደተለመደው ክፈቱልን ለማለት እንደሆነ የታወቀ ስለሆነ የሚያስገርም አይደለም። ከሁሉ የሚገርመው ግን ‹‹በታላቅ አክብሮት አቀባበል አድርገውልኛል›› ሲሉ መሰማቱ በጣም ያስገርማል። የሚመጡበትን ቀን ሳይቀር በቲፎዞዎቻቸው አሳስተው ሳይጠበቁ በድብቅ ገብተው ማደራቸውን የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ስለሆነ አያስገርምም።

ጥያቄ: ባለፈው አንድ የስብሰባ ጥሪ አድርገው ነበር፥ በመጥሪያውም ላይ የቤተክርስቲያናችሁ ደንብ እንደተከበረ ሆኖ፣ ቀኖና እንዳይጣስ፣ ሥርዓት እንዳይበላሽ እንመካከር ብለው ነበር ለምን? በስብሰባው ላይ ምን ያህሎች ተገኙ? 

መልስ: ባለፈው ታሕሳስ ፯ ባደረግነው ስብሰባ ለ፲፯ ስቴቶች የስብሰባ ጥሪ አድርጌያለሁ፣ ብዙዎች በተለይ እሩቅ ያሉት አንዳንዶች አንድ ካህን ስላላቸው፣ ለእሁድ አገልግሎት ስለማይደረሱ እንደማይመጡ ገልጸውልናል፥ ሆኖም ግን ከአካባቢያችን ፱ የቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች፣ ሁለት የቤተክርስቲያን ተወካዮች በጥቅሉ ፲፩ ቤተክርስቲያኖች ተገኝተዋል ነበር ያሉት። 

ተያያዥ ጥያቄ: በስብሰባው ላይ እኮ በተለይ እራሳቸውን ገለልተኛ ከሚባሉት ሚካኤል ብቻ ነበር የተገኙት እንዴት ነው?

መልስ: አይደለም ከተገኙት መካከል የኪዳነ ምሕረት ቨርጂኒያ አስተዳዳሪ፣ የውድ ብሪጅ ኢየሱስ (በቀሲስ ወርቅነህ ኃይሌ) የተመሠረት (ያለ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ጳጳስ የተባረከ ቤተ ክርስቲያን ሊባል አይችልም ፍትኀ ነገሥት መንፈሳዊ) የልደታ ተወካይ ብለው( ከ፲፩ ውስጥ ሁለቱን ብቻ ነበር የጠቀሱት) ሌሎች ተወካይ ወይም ቦርድ አልተገኙም ማለት ነው (ወይ የውሸት መዓት. . . ስብሃት ለአብ. . . እውነት እኛን መስለው ሊነጥቁ የመጡ መሆናቸውን ሊያሳየን ይችላል)

እርምት: እዚህ ላይ አቡኑ የተናገሩት በሙሉ ውሸት እንደሆነ በአጠቃላይ በቃለ ምልልሱ ላይ ጠቅሰውታል መጀመሪያ አስራ አንድ ናቸው ብለውን ነበር፣ በኃላ ደግሞ ከጠቀሱት ሦስቱ ቤተክርስቲያን ከሚባሉት ሁለቱን ብቻ ነበር የጠቀሱት፣ በአጠቃላይ የአባ ፋኑኤልን ሥራ ልንመለከት ይገባናል የበግ ለምድ ለብሰው የመጡ ነጣቂ ተኩላነታቸውን በሚገባ ያስገነዘቡን ይመስለናል።
የሆነ ሆኖ ፍርዱን ለተመልካች እና ቤተክርስቲያናችንን ልንጠብቅበት የሚገባ ጊዜ ስለሆነ ክርስቲያኖች ሁላችን ነቅተን ልንጠብቅ፣ ሕዝበ ክርስቲያኑን ከነጣቂ ተኩላዎች ልንጠብቃቸው ይገባል ባይ ነን።

በመጨረሻ ለአባ ፋኑኤል መልዕክት አለን 
 ቤተክርስቲያን መቼም አሳድጋ፣ አስተምራ (የተማሩት ካለ ማለታችን ነው)፣ ለክብር አብቅታ በከበሬታ ወንበር ላይ አስቀምጣ ስታበቃ እንደዚህ ቤተክርስቲያንን ለመናፍቃን እና ለፕሮቴስታንቶች አሳልፎ ለመስጠት ምን አደፋፈረዎ፣ ወይስ ቤተክርስቲያኒቱስ ምንን አጎደለችብዎት? ሲሆን እዚህ ላደረሰችዎ ቤተክርስቲያን፣ ነገ ጥለው ለሚሄዱት ዓለም እንዲህ ክርስቲያኖችን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሰጠዎት ሥልጣን ተጠቅመው ከሚያምሱት፥ ለምን ነገ ትውልድ ሊያመሰግንዎ፣ እግዚአብሔርም በምድር ያከበረዎ በሰማይም እንዲያከብርዎ ሥርዓቷን፣ ቀኖናዋን፣ ትውፊቷን ለልጅ ልጅ ለማድረስ አይፋጠኑም በእውነቱ በአሁን ሰዓት ቤተክርስቲያንን ልንታደግ የሚገባ ጊዜ መሆን ሲገባው ለምን ሰድበው ለሰዳቢ ቤተክርስቲያኒቱን ይሰጣሉ? ለምንስ ያለውን እንደነበረው ከአባቶቻችን የተቀበልነውን የሃይማኖት አንድነት ለነገው ማስተላለፍ አቃተን፣ እግዚአብሔርስ እንዴት ይለመነን? እናንተ ካሕናት እኮ ናችሁ ሕዝቡን ወደ ድህነት እንድትወስዱት ሥልጣኑን ካህን፣ ጳጳስ አድርጎ የሾማችሁ ይሄ እንዴት ተረሳችሁ? ምን ጥቅም ዓይንን ቢያውር ለተመረጡለት ክብር መብቃት ደግሞ ከኛ ይጠበቃል እግዚአብሔር እንዳከበረዎ፣ የተሰጠዎትን ቢቀበሉ እንመክራለን፤ ነገር ግን በራሴ ጥበብ በሚሉት ቢሄዱ እጁን መዘርጋቱ አይቀርም "የሲኦል ደጆች አይችሏትም" ነው የተባለላት።

ሲሆን አጠገብዎ የከበብዎትን የተኩላ መንጋ አስወግደው ለክብር ላበቃችዎ ቤተክርስቲያን ለሥርዓቷ፣ ለቀኖናዋ፣ ለትውፊቷ የሚጋደሉ ሕይወታቸውን የሚሰጡትን ወገኖች ሰብስበው ቢሰሩ መልካም ይመስለናል ነገር ግን በኢትዮጵያ እና በተለያዩ ሀገሮች በታወቁት መናፍቃን የፕሮቴስታንት አፈ ቀላጤዎችን ለምሳሌ እንደ
፩ኛ/ አባ ኃይለሚካኤል ቀንደኛ የፕሮቴስታንት ምልምል
፪ኛ/ ኃይለጊዮርጊስ ጥላሁን ተረፈ አርዮሳዊ በምንፍቅናው ከቤተክርስቲያን የተባረረ
ሌሎች ለጥቅም የከበቦዎት ሁሉ፣ ለቤተክርስቲያን ሳይሆን ለግል ጥቅማቸው የሚሯሯጡ፣ አሁን በስም የማንጠቅሳቸው ነገር ግን በቅርብ ዝርዝር ሥራቸውን የምንጠቁማቸው ለከርሳቸው ያደሩ ክህነታቸውን እንደ ኤሳው ለእራፊ ጨርቅ እና ለቁራሽ እንጀራ የሸጡ ከበው ልክ የወደቀ ሥጋ እንዳየ አሞራ ዙሪያ ከበው "ቅዱስ አባታችን" (ቅድስናዎን እርሶ ያውቃሉ) የሚልዎት በሙሉ እውነት ለቤተክርስቲያን መቆማቸውን በቀላሉ ማሳየት ይችላሉ። ለጥቅም የቆሙ እንደሆኑም በተደጋጋሚ በሚሰሩት እና በሚያደርጉት እራሳቸውን ያሳዩ የጥቅም ሰዎች ናቸው።

ለአቶ አዲሱ አበበ
የአሜሪካን ሬዲዮ ጣቢያ አቅራቢ፣ የሠራህው በጣም ጥሩ ሥራና ጊዜውን የጠበቀ ሥራ በመሆኑ ልትመሰገን ይገባሃል። ነገር ግን ሥራህን ሙሉ ሊያደርግ የሚችለው የሚከተሉትን ሚዛናዊ በሆነ የጋዜጠኝነት ሙያ መሰረት ስታቀነባብረው ነው፤

  1.  አባ ፋኑኤል መቼም ያሉት ሁሉ ትክክል ነው ብለህ እንደማትቀበል ሁሉ ሐሰት ነው ልትልም እንደማትል እርግጠኞች ነን፤ እንደ አድማጭ ግን የምንጠቁመው እውነቱን ከሐሰቱ ሊለይ የሚችለው ልክ በአሜሪካን ሀገር (fact checker) እንደሚባሉት በእኛም ሀገር በተለይ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሊቃውንት ጉባኤ እንዳለ ስለምታውቅ የተናገሩትን በሊቃውንቱ ጉባኤ ብታረጋግጥ፣ ቤተክርስቲያኒቱ እንዲህ አይነት አሠራር የላትም ብለው ሲሉ ተቀብለን መሄድ ያለብን አይመስለንም።
  2. በቦታው የነበሩትን አባት አቡነ አብርሃምን ማነጋገር ምናልባት ሚዛናዊ ሊያደርው ይችላል ብለን እናምናለን ስለዚህ በሚገኙበት ቦታ ብታነጋግራቸው ሥራህን ሚዛራዊ ሊያደርው ይችላል ብለን እናምናለን።

ቸር ይግጠመን ብለን ለዛሬ እንሰናበታለን 

ከመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ የተገኝ


 (Jan 21, 2012) ከVOA ራዲዮ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ
(ከ05፡00 ደቂቃ አንስቶ እስከ 25፡00ደቂቃ )-- የ20 ደቂቃ ቆይታ አለው

10 comments:

  1. አንድ አድርገን፣ ደጀ ሰላም፣ ገብረሔር፣ አሃቲ ተዋህዶ እንዲሁም ሌሎች ሌሎች፤ አቤት\\\ አቤት\\\ ሥማችሁ እንደ ግብራችሁ ቢሆን፤ ?

    መጋቢ ሐዲስ በጋሻው ደሳለኝ፣ መምህር አሰግድ ሳህሉ፣ ቀሲስ አሸናፊ ገ\ማርያም፣ ዲያቆን ትዝታው ሳሙኤል፣ መምህር ተረፈ፣ መምህር ታሪኩ፣ ዘማሪት ምርጥነሽ፣ ዘማሪት ዘርፌ፣ ዘማሪ ዕዝራ፣ ዘማሪ ዳግማዊ፣ ዘማሪ ሐብታሙና ሌሎችም የተዋህዶ ወንድሞችና
    እህቶች፤ የክርስቶስ ልብ ያላቸው፣ ወንጌሉ በደንብ የገባቸው፣ የሚያገለግሉ ድንቅ የተዋህዶ ልጆች ናቸው። እግዚአብሔር ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን ፀጋውን አሁንም አሁንም ጨምሮ ያብዛላቸው።

    በዘመናችን የወንጌል ጠላቶች ሆናችሁ የተነሳችሁ፤ የእፉኝት ልጆች ሆይ፤ የወንድምን ሥም ማጥፋትና በቅናት ማሳደድ፡ የክርስትና መንገድ አድርጋችሁ የምትቆጥሩ፣ ካላጣላችሁ ያገለገላችሁ የማይመስላችሁ፣ የመንጋው መብዛት የማያስደስታችሁ፣ ከርስትናን በሥም እንጂ በተግባር ለመግለፅ ያልታደላችሁ፣ የአህዛብን ግብር የምትፈፅሙ፣ ወንድሞችን በድንጋይ የምትወግሩ፤ እናንተ ሆይ፤ እግዚአብሔር ቢዘገይም የሚቀድመው የለም ስለመንጋው ይገደዋልና ሳይፈረድባችሁ ንስሃ ግቡ። ድንጋይ የሆነውን ልባችሁን አውጡና የክርስቶስን ልብ ተቀበሉ። እግዚአብሔር ይርዳችሁ።
    የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን አማላጅነት አይለየን። አሜን።

    ReplyDelete
  2. Who are u to say Aba fanuel lied? who are u to say he is tekula?, while u are full of lies, enante Gibezoche Mejemeria Erasachun Asdu, Keza Yewoendemachun Gudef Tawotalachu. Enanete Mahibre kidusan while u are doing some good job, in the other hand this few ppl working like this website and Dejeselam and someother websites are rewining your good reputations. People are starting to take note of that, Please think about it. We know Everybody makes mistakes, we know Abune Abraham made a good job and he made a mess too, he and Mahibre kudusan are responsible for the situation we are right now in dc (a lot of kififle) not aba fanuel, but you don't see us putting lies in public, we dont lie, but u in other hand has no shame when u put lies, don't you think u will be judged by God for that. If you write just write, write what is true, not ur assumptions or anybody assumptions, just the truth. At the End We want love, forgiving one another, working together, I hope in the future u will work for that, because what u r doing now is dividing us
    Let God have mercy on all of us and forgive us all our sin
    Amen

    ReplyDelete
  3. ውድ አዘጋጆች፣ ከላይ "ቀሲስ አማረ ካሣዬ" ለአቡነ ፋኑኤል ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ መልዕክተኛ ሆነው ስለ መላካቸው የተገለጸ ነገር አንብቢያለሁ። "ቀሲስ" ብላችሁ የገለጻችኋቸው ሰው ማን እንደሆኑ እና ከየትኛው ቤተ ክርስትያን እንደ ተላኩ ብትገልጹልኝ።

    ReplyDelete
  4. the "Anonymous Jan 26, 2012 08:31 AM " I have a question for you.
    Who are you refering when you say, 'US & WE' in this cotted speech-- "but you don't see us putting lies in public, we don't lie", Who are you please. I believe here people are talking about Abune Fanuel deeds, and you are talking about Abune abriham and MK. When you say that it will be nice if you state what kinds of differences made by abune abriham and MK. More than that I don't see MK in between this at all. If you want to talk what MK says you have to visit its legal and known websites. While you are telling the blogger that he is judging without knowing the right thing, you just did by guessing that all these blogs are MK's. It is a little bit confusing. Please people let's discuss ideas not people or organizations.

    ReplyDelete
  5. Bertu Egzer yabertachu manime yefelegewun beel le betkristian yemitekem siran kemesirat weed huala atibelu

    ReplyDelete
  6. amaha,
    በጠየከው መሠረት ቀሲስ አማረ ካሣዬ ማለት በዲሲ ርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም የሚያገለግሉት እና በተለይ በአሁን ሰዓት ቤተክርስቲያኑን ወደ ግል ንብረትነት ለመውሰድ እየተጣጣሩ ያሉት ሰው እራሳቸውን "ዶክተር" ብለው የሚጠሩት ነገር ግን ባለን መረጃ መሠረት ምንም ዓይነት የዶክተርነትም ሆነ ተመሳሳይ ትምህርት የወሰዱበት መረጃዎች ስለሌሉ ቀሲስ ተብለው ይጠራሉ፡ እኚህ ሰው የቅድስት ማርያምን ቤተክርስቲያን በተለያየ ጊዜ ሕዝቡን ከቦርዱ ጋር፣ ወይንም ቦርዱን ከምዕመናኑ ጋር በማጋጨት ከዛም እድሩን ከህዝቡ ጋር እያጋጩ በተለያየ ጊዜ የራሳቸውን ንብረት መዝረፍ እና ሀብት ማከማቸት የተያያዙ ሰው ናቸው ለዚህም በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል
    ፩/ በአለፈው ሦስት ዓመታት ውስጥ የቤተክርስቲያኑን መረዳጃ እድር የቤተክርስቲያኑ መሆን አለበት በማለት ለፍርድ ቤት አላስፈላጊ ወጪ የዳረጉ እና ህዝቡን ከካህናት ከቦርድ ያጋጩ ዋነኛው ተጠያቂ ናቸው
    ፪/ ከጥቂት ጊዜ በፊት በካህናት ማካከል ለተነሳው ግጭት ዋነኛው ተጠያቂ እና ቤተክርስቲያኑን ለሁለት ለመክፈል የተደረሰበት አጋጣሚ ነበር ነገር ግን በአንዳንድ አስተዋይ ሰዎች ምክንያት እርቁ ሊወርድ ችሏል
    ፫/ ከአራት ወይም አምስት ወር በፊት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩትን አቡነ አብርሃም ላይ በማኅበረ ካህናቱ ስብሰባ ላይ ርዕን አንስተው ሊያሰሩን አልቻሉም በሚል የዲሲን ካህናት አስተባብረው ፊርማ አሰባስበው ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወስደው ለሲኖዶሱ አቤቱታ አቅራቢ በመሆን ለአባ ፋኑኤል መንገዶችን በመፍጠር ለዚህም ደግሞ ዋነኛው ምክንያት አባ ፋኑኤል ልባርካችሁ እንጂ ሥርዓት ብለው ጥያቄ ስለሌላቸው እኛኛውን ከሰው እኚህኛውን የግብር ወዳጃቸውን እንዲሾሙ መሳሪያ በመሆን አገልግለዋል። የሚገርመው ግን ሲሄዱ ወደ ኢትዮጵያ የሚያምኗቸውን ቦርድ እንኳ ሳይናገሩ ዘመድ ልጠይቅ የዘመድ ሰርግ ብለው አመካኝተው ከቤተክርስቲያኑ 5000.00 ተቀብለው ነው የሄዱት ነገር ግን ሄደው በማያምኑት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ቀርበው ባለ 7 ገጽ አቤቱታ ካነበቡ በኃላ ኮፒውን ለቅዱስ ፓትሪያሪኩ ሰጥተዋል።
    ፬/ በተለይ ባለፈው የጌታችን የመድኅኒታችን የጥምቀት በዓል በሚከበርበት ጊዜ አብረን ከአባ ፋኑኤል ጋር ካላከበርን ብለው ለቤተክርስቲያን አንድነት ለማፍረስ በቅተዋል፣ በተጨማሪም ቦርዱ እና የካህናት ተጠሪዎች ለምን እንዲህ አደረጉ ብለው ሲጠየቁ ወንድማችን ናቸው ስለዚህ አብረን ማክበር ይገባናል በሚል ትልቅ የከረረ ጸብ ተነስቶ ርዕሰ ደብር አብርሃም እና ሊቀ መዘመር ሞገስ በዓል እንኳ ለማክበር ሳይመጡ ቀርተዋል፥ ለዚህ በተለያየ ጊዜ ለሚነሳው የሥልጣን ሽኩቻ ዋነኛው እና ቀንደኛው ቀሲስ አማረ ሲሆኑ ባለቤታቸው ደግሞ በኪችን በኩል የሴቶች ሀላፊ እና አድራጊ ፈጣሪ ነች እሳቸው ደግሞ በመቅደስ ገብተው እንዲህ ሰው እና እግዚአብሔር እንዳይገናኝ እንቅፋት ሲሆኑ ኖረዋል ለዚህች ደብር የራሷ የሆነ ህንጻ ቤተክርስቲያን መገንባት ትልቅ እንቅፋት የሆኑት እኚሁ ሰው እንደሆነ ለመጠቆም እወዳለው። ብዙ ነበር ግን ምን ያደርጋል ብቻ
    የቤተክርስቲያኑ አባል ነኝ የቦርዱም አባል ነበርኩኝ

    ReplyDelete
    Replies
    1. ስለ ተሰጠኝ መልስ ሳላመሰግን አላልፍም። እርግጠኛ ሳልሆን አስተያየት መስጠት ስላልፈለኩ እንጂ እንደ ጸሐፊው አገላለጽ ዶ/ር አማረ ካሣዬን ለመንካት እንደታሰበ ገብቶኛል። አንድን የተማረ ሰው፣ ለዚያውም በቲዎሎጂ ምሩቅ የሆኑትን አባት እንደ ተራ ሰው ማንቋሸሽ የጤና አይመስለኝም። ብዙውን ጊዜ እንደዚህ ዓይነት አስተያየት የሚሰጡ ሰዎች እራሳቸው ምንም ዓይነት ትምህርት የሌላቸው፣ መላ ጊዜያቸውን በአሉባልታ የሚያሳልፉ፣ አሳዳጊ የበደላቸው የተረገሙ ብቻ ናቸው። አለበለዚያ ደግሞ በቤተ ክርስትያኗ ውስጥ እንደፈለጋቸው ሊፈነጩ ያልቻሉ፣ የሰዎችን ስም በማጥፋት ድብቅ ዓላማቸውን ሊያሳኩ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው።

      ስለ ዶ/ር አማረ ካሣዬ ማንነት የበለጠ ለማወቅ ከተፈለገ ጠቅላይ ቤተ ክህነትን መጠየቅ ይቻላል። አባ ወልደ ትንሣኤ (የዝዋዩ አባት) በሕይወት በነበሩበት ዘመን ከሳቸው ጋር አብረው በኮሚቴ ይሠሩ እንደነበረና መልካም ዝና እንደነበራቸው ምስክርነቱን 2003 ላይ በወጣው (ቁ. 5 እና 6) የ "መለከት" መጽሔት ላይ ለማንበብ ይቻላል። የዚህ ብሎግ አዘጋጆች ወይም ደግሞ የራሳችሁን ማንነት እየደበቃችሁ አስተያየት የምትሰጡ ሰዎች እንደምትሉት፣ ዶ/ር አማረ ካሣዬ ቦርዱን ከሕዝቡ ጋር ወይም ምዕመኑን ከቦርዱ ጋር የሚያጋጩ ሰውም አይደሉም። በሳቸው ላይ ላነሳችሁት ቅሬታ እንደ ቅደም ተከተሉ መልስ እሰጣችኋለሁ። ያቀረባችሁትን ወሬ እና አሉባልታ ለማረጋገጥ ዕድል ለሌላቸው ሰዎች ማብራሪያ ሊሆን ይችላል።

      1/ “የቤተ ክርስትያኗ መረዳጃ ዕድር የቤተ ክርስትያኑ መሆን አለበት” ተብሎ በተነሳው ውዝግብ ቤተ ክርስትያኗን ለአላስፈላጊ ወጪ ዳርገዋል ብላችሁ የኮነናችኋቸው ጉዳይ፣ እውነት እንነጋገር ከተባለ ስሙ እንኳን በግልጽ እንደሚመሰክረው በቤተ ክርስትያኗ ስም የተቋቋመውን ዕድር ከቤተ ክርስትያኗ ለመነጠል ፍርድ ቤት ክስ ያቀረበው ማነው? ጥቂት የዕድሩ ሥራ አመራር አባላት አይደሉምን? እነዚህ ጥቂት የሥራ አመራር አባላት የዕድሩን ገንዘብ ለሌላ ዓላማ ለመጠቀም በማሰብ፣ የቤተ ክርስትያኗ የቦርድ ሊቀ መንበር በአንድ ወቅት የተከሰተ ስህተትን፣ ይህም የቤተ ክርስትያኗ እና የዕድሩ ገንዘብ በአንድ አካውንት የሚቀመጥ በመሆኑ በስህተት ለቤተ ክርስትያኗ ወጪ የሚያስፈልግ ገንዘብ ከዕድሩ ሂሣብ ላይ መነካቱን እና ዕርምት መወሰዱን በግልጽ በመናገራቸው፣ ይህ ጉዳይ እንደ ከባድ ወንጀል ተቆጥሮ አምባጓሮ የፈጠሩትና ፍርድ ቤት የሄዱት አመራሮቹ አይደሉምን? ሕዝቡን ከካህናቱ እና ከቦርዱ ጋር ያጋጩ እነዚህ ግለሰቦች ናቸው ዶ/ር አማረ ካሣዬ አይደሉም።

      2/ በካህናት መካከል መቼም ቢሆን ግጭት ሊነሳ ይችላል። በቅርብ ጊዜ ተነሳ ለሚባለውም ግጭት እያንዳንዱ ካህን የራሱ አስተዋጽኦ አለው። እነዚህ ካህናት የእግዚአብሔር አገልጋይ ሰዎች መሆናቸው መዘንጋት አይገባም። እንደ ማንኛውም ተራ ሰው እነሱም የተለያየ ፍላጎቶችና ችግሮች ይኖራቸዋል። ከምንም በላይ ደግሞ በሰው ላይ የሚያድረው እርኩስ መንፈስ ይፈታተናቸዋል። በተለይ የዶ/ር አማረን ወንበር ዘወትር የሚመኝ ካለ መቼም ቢሆን እንቅልፍ አይኖረውም። በሽምግልና የተያዘውን ጉዳይ እንዲህ በአደባባይ የሚያወጣው እንዲህ ያለ ሰው ብቻ ነው።

      3/ “ከአራት ወይም አምስት ወር በፊት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩትን አቡነ አብርሃም ላይ በማኅበረ ካህናቱ ስብሰባ ላይ ርዕን አንስተው ሊያሰሩን አልቻሉም በሚል የዲሲን ካህናት አስተባብረው ፊርማ አሰባስበው ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወስደው ለሲኖዶሱ አቤቱታ አቅራቢ በመሆን… ወዘተ የተባለው ክስ ዶ/ር አማረ ካሣዬን አይመለከትም። ነገሩ “አህያውን ፈርቶ ዳውላውን” እንደሚባለው ካልሆነ በስተቀር። በመጀመሪያ ደረጃ አቡነ አብርሃምም ሆነ አቡነ ፋኑኤል የዲሲ ርዕሰ አድባራት ቅ/ማርያም ቤተ ክርስትያንን አያስተዳድሩም፤ ደጇም አይደርሱም። ታድያ በምን ሥሌት ይሆን በዚህ ጉዳይ የዶ/ር አማረ ካሣዬ ስም የሚነሳው? ዶ/ር አማረ ካሣዬ ወደ አገር ቤት የሄዱት በቤተ ክርስትያን አባቶች መካከል ለ 20 ዓመታት የዘለቀውን መለያየት እና መወጋገዝ ለማርገብ እና በውይይት ለማስታረቅ በምእመናን በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት ተወክለው እንጂ አስተያየት ሰጪው ባሠፈረው ምክንያት አይደለም። ለዚህ ጉዳይ እኔ ራሴ ምስክር ነኝ። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ውይይቱን ለማዳመጥ ችያለሁና! ቅዱስ ሲኖዶስ ዘንድ መቅረብ ያለበት ካህን መሆን ስላለበት፣ ሌሎቹ ካህናት አገር ቤት ለመግባት የተለያዩ ችግሮች ስለ ነበሩባቸው ፣ ዶ/ር አማረ ያለ ፍላጎታቸው፣ እልህ አስጨራሽ ውይይት ተካሂዶ የሕዝብን (የኮሚቴውን) አደራ ተቀብለው ግዳጃቸውን ተወጥተው ተመልሰዋል። የኮሚቴው ውሣኔ ከደረሳቸውም በኋላ በተዋረድ ለቦርዱም አሳውቀዋል። ለማታውቁቱ ሰዎች ሁሉ፣ ዶ/ር አማረ ካሣዬ ያለ ቦርዱ ፍቃድ በራሳቸው ውሣኔ የሚፈጽሙት ወይም የሚያስፈጽሙት ምንም ጉዳይ የላቸውም።

      4/ “በተለይ ባለፈው የጌታችን የመድኅኒታችን የጥምቀት በዓል በሚከበርበት ጊዜ አብረን ከአባ ፋኑኤል ጋር ካላከበርን” … ጎበዝ! አባ ፋኑኤል የተጠለሉበት ቤተ ክርስትያን የዲሲ ቅ/ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ነው፤ ይህ ቤተ ክርስትያን በሳቸው ስም የተመዘገበ በመሆኑም ጭምር ነው። ያ ቤተ ክርስትያን እንደ ሌሎች አብያተ ክርስትያናት ሁሉ ከደብረ ሰላም ቅ/ ማርያም ቤተ ክርስትያን ጋር አንድነት አለው። እነዚህ አብያተ ክርስትያናት ተጠሪነታቸው ለአባ ጳውሎስ አይደለም፤ የራሳቸው ቦርድ ወይም የሥራ አመራር አላቸው። እነዚህ አብያተ ክርስትያናት ወሳኝ ክብረ-በዓላትን፣ እንደ ጥምቀት እና ደመራ በጋራ ያከብራሉ። በመሆኑም፣ ያሳለፍነው የጥምቀት በዓል በጋራ ኮሚቴያቸው ውሣኔ መሠረት የተከበረው በዲሲ ቅ/ ማርያም ቤተ ክርስትያን እና በዲሲ ቅ/ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ነበር። የቅ/ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን ሥራ አመራር በአባ ፋኑኤል ጉዳይ ለሁለት ተከፍሏል። ምክንያቱ ከላይ የገለጽኩት ነው፤ አባ ጳውሎስን አይቀበልም። ምእመናኑ የማርያም ንግሥ ሲኖር ቅ/ ማርያም ቤተ ክርስትያን ሄደው ያከብራሉ፤ እንዲሁ የቅ/ ማርያም ቤተ ክርስትያን ምእመናን የቅዱስ ሚካኤል ንግሥ ሲኖር ሄደው በጋራ ያከብራሉ። ይኼ ልምድ አባ ፋኑኤል ተሹመው ከመምጣታቸው በፊት ጀምሮ በምእመናኑ ፈቃድ የሚፈጸም እንጂ በማንም ተጽእኖ የሚደረግበት አይደለም።

      በመጨረሻም ላሳስባችሁ የምወደው ነገር ቢኖር፣ የአቡነ አብርሃም ደጋፊዎች ችግራችሁን ከአቡነ ፋኑኤል ጋር ብትፈቱ ይሻላችኋል። ተገልላችሁ ወይም ራሳችሁን አግልላችሁ እንደኖራችሁ ሁሉ “ገለልተኛ ነን፣ የአቡነ ፋኑኤልን አመራር አንቀበልም” ብላችሁ ተለይታችሁ የምትወጡበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን እገምታለሁ። የናንተ ጉዳይ እኛን አይመለከተንምና ሠላማችንን ስጡን። ሩቅ ሆኖ የሰውን ስም ከማጥፋት ይልቅ ቀረብ ብሎ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት ጥረት ማድረግ በተሻለ ነበር። ለነገሩ እናንተ ለማንም የምትመለሱ አይደላችሁም፤ ክርስትያናዊ ሥነ-ምግባር የጎደላችሁ ናችሁና። እግዚአብሔር አስተዋይ ልቡና ይስጣችሁ!

      Delete
  7. amaha,
    በጠየከው መሠረት ቀሲስ አማረ ካሣዬ ማለት በዲሲ ርዕሰ አድባራት ቅድስት ማርያም የሚያገለግሉት እና በተለይ በአሁን ሰዓት ቤተክርስቲያኑን ወደ ግል ንብረትነት ለመውሰድ እየተጣጣሩ ያሉት ሰው እራሳቸውን "ዶክተር" ብለው የሚጠሩት ነገር ግን ባለን መረጃ መሠረት ምንም ዓይነት የዶክተርነትም ሆነ ተመሳሳይ ትምህርት የወሰዱበት መረጃዎች ስለሌሉ ቀሲስ ተብለው ይጠራሉ፡ እኚህ ሰው የቅድስት ማርያምን ቤተክርስቲያን በተለያየ ጊዜ ሕዝቡን ከቦርዱ ጋር፣ ወይንም ቦርዱን ከምዕመናኑ ጋር በማጋጨት ከዛም እድሩን ከህዝቡ ጋር እያጋጩ በተለያየ ጊዜ የራሳቸውን ንብረት መዝረፍ እና ሀብት ማከማቸት የተያያዙ ሰው ናቸው ለዚህም በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል
    ፩/ በአለፈው ሦስት ዓመታት ውስጥ የቤተክርስቲያኑን መረዳጃ እድር የቤተክርስቲያኑ መሆን አለበት በማለት ለፍርድ ቤት አላስፈላጊ ወጪ የዳረጉ እና ህዝቡን ከካህናት ከቦርድ ያጋጩ ዋነኛው ተጠያቂ ናቸው
    ፪/ ከጥቂት ጊዜ በፊት በካህናት ማካከል ለተነሳው ግጭት ዋነኛው ተጠያቂ እና ቤተክርስቲያኑን ለሁለት ለመክፈል የተደረሰበት አጋጣሚ ነበር ነገር ግን በአንዳንድ አስተዋይ ሰዎች ምክንያት እርቁ ሊወርድ ችሏል
    ፫/ ከአራት ወይም አምስት ወር በፊት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩትን አቡነ አብርሃም ላይ በማኅበረ ካህናቱ ስብሰባ ላይ ርዕን አንስተው ሊያሰሩን አልቻሉም በሚል የዲሲን ካህናት አስተባብረው ፊርማ አሰባስበው ወደ ቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ወስደው ለሲኖዶሱ አቤቱታ አቅራቢ በመሆን ለአባ ፋኑኤል መንገዶችን በመፍጠር ለዚህም ደግሞ ዋነኛው ምክንያት አባ ፋኑኤል ልባርካችሁ እንጂ ሥርዓት ብለው ጥያቄ ስለሌላቸው እኛኛውን ከሰው እኚህኛውን የግብር ወዳጃቸውን እንዲሾሙ መሳሪያ በመሆን አገልግለዋል። የሚገርመው ግን ሲሄዱ ወደ ኢትዮጵያ የሚያምኗቸውን ቦርድ እንኳ ሳይናገሩ ዘመድ ልጠይቅ የዘመድ ሰርግ ብለው አመካኝተው ከቤተክርስቲያኑ 5000.00 ተቀብለው ነው የሄዱት ነገር ግን ሄደው በማያምኑት የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ቀርበው ባለ 7 ገጽ አቤቱታ ካነበቡ በኃላ ኮፒውን ለቅዱስ ፓትሪያሪኩ ሰጥተዋል።
    ፬/ በተለይ ባለፈው የጌታችን የመድኅኒታችን የጥምቀት በዓል በሚከበርበት ጊዜ አብረን ከአባ ፋኑኤል ጋር ካላከበርን ብለው ለቤተክርስቲያን አንድነት ለማፍረስ በቅተዋል፣ በተጨማሪም ቦርዱ እና የካህናት ተጠሪዎች ለምን እንዲህ አደረጉ ብለው ሲጠየቁ ወንድማችን ናቸው ስለዚህ አብረን ማክበር ይገባናል በሚል ትልቅ የከረረ ጸብ ተነስቶ ርዕሰ ደብር አብርሃም እና ሊቀ መዘመር ሞገስ በዓል እንኳ ለማክበር ሳይመጡ ቀርተዋል፥ ለዚህ በተለያየ ጊዜ ለሚነሳው የሥልጣን ሽኩቻ ዋነኛው እና ቀንደኛው ቀሲስ አማረ ሲሆኑ ባለቤታቸው ደግሞ በኪችን በኩል የሴቶች ሀላፊ እና አድራጊ ፈጣሪ ነች እሳቸው ደግሞ በመቅደስ ገብተው እንዲህ ሰው እና እግዚአብሔር እንዳይገናኝ እንቅፋት ሲሆኑ ኖረዋል ለዚህች ደብር የራሷ የሆነ ህንጻ ቤተክርስቲያን መገንባት ትልቅ እንቅፋት የሆኑት እኚሁ ሰው እንደሆነ ለመጠቆም እወዳለው። ብዙ ነበር ግን ምን ያደርጋል ብቻ

    ReplyDelete
  8. መቼም ከዘረዘርካቸዉ ባንድ አንዱ ነህ በቤ/ክ ራዕይህና መመዘኛሕ ምንድ ነዉ?

    ReplyDelete
  9. This info is priceless. When can I find out more?
    my site: GFI Norte

    ReplyDelete