(አንድ አድርገን የካቲት 28 ፤ 2004ዓ.ም)፡- ከቀናት በፊት በዋልድባ ገዳም አካባቢ መንግስት ላሰበው ትልቅ የስኳር ፋብሪካ ለማቋቋም ስራውን መጀመሩን አስመልክቶ የገዳሙ መነኮሳት ጥያቄያቸውን ይዘው ወደ ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ(ቤተመንግስት) መምጣታቸውን ከደጀ ሰላም ፤ እና ከተለያዩ ጋዜጦች ላይ አንብባችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህ የተባለው ስኳር ፋብሪካን ለመገንባት ብዙ አብያተክርስትያናት እንደሚፈርሱ ለገዳሙ መነኮሳት መረጃ ደርሷችዋል ፤ መንግስት የሚለው ነገር ‹‹ተለዋጭ ቦታ ይሰጣችኋል መንግስት ተለዋጭ ቦታ ሳይሰጥ ምንም አይነት የቤተክርስትያኗ ቦታ ለልማት አያውልም ›› የሚል ሲሆን ፤ መነኮሳቱ ‹‹እኛ ከአባቶቻችን የተረከብነውን የቤተክርስትያ ቅዱሳት ቦታዎችን በገንዘብ እና በሌላ ተለዋጭ ቦታ አንለውጥም›› የሚል ነበር፡፡ እውነት ነው ይህ የቤተክርስትያኗ የእምነት ቦታ በምንም አይነት አላፊ እና ጠፊ በሆነ ነገር አንለውጥም ፤ ደብረሊባኖስ ገዳም እና አካባቢው ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለኃይማኖት በህይወት በኖሩባቸው 98 ዓመታት ብዙ ገቢረ ተዓምራትን በእግዚአብሔር ረዳትነት ያደረጉበት እና እኛም ቦታውን ረግጠን ፤ ቤተክርስትያኗን ስመን ፤ ቦታው ላይ የፈለቀውን ጸበል ጠጥተን እና ተጠምቀን ከስጋ በሽታችን እንድንፈወስ ለእኛ ለሃጥያተኞቹ የተሰጠን ድንቅ ቦታ ነው፡፡ መንግስት እያለ ያለው ይህን የመሰለውን በዋልድባ አካባቢ የሚገኙትን የቅዱሳን ቦታዎችን በሌላ ቦታ ልቀይራችሁ ተመጣጣኝም ብር ልስጣችሁ ነው የሚለው፡፡
ይህ ነገር እንደተሰማ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚታተሙ ጋዜጣ እና መፅሄቶች አንስቶ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚዘጋጀው የአሜሪካ ድምፅ ድረስ መረጃው ሰዎች ዘንድ ለማድረስ ብዙ ጥረት ሲያደርጉ ተስተውሏል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙ ከሸገር 102.1 በቀር ሌሎቹ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለውታል ፤ ለምን ቢባል ነገሩ ከመንግስት የሚያጋጭ ስለሆነ አብዛኞቹም ጣቢያዎች ይህን ለማውራት መረጃውንም ምዕመኑ ዘንድ ለማድረስ ሲጥሩ አልተመለከትንም፡፡ ባለፈው ግብረሰዶማውያን አዲስ አበባ ላይ ስብሰባ ሲያደርጉም ከመንግስት መጣላት ነው ብለው ዝምታቸውን መርጠዋል ፤ የአርሰናል ወይም የማንችስተር ጉዳይ ቢሆን ኖሮ ተጨዋቾቹ የበሉትና የጠጡት ነገር ሳይቀር ይነግሩን ነበር ፤ ይህ ጉዳይ ግን ሚዛን አልደፋም መሰል ጸጥ ብለዋል ዝምታን መርጠዋል ፤ አስተውሎ ለተመለከተው ሀገራችን በኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በኩል አልታደለችም የሚያስብል ነው፡፡ ጋዜጠኛ ጉዳዮችን ሰዎች ዘንድ ካላደረሰ ማን ሊያደርስ ነው ፤
ይህን ጉዳይ ይዘው ከ1000 በላይ ኪሎ ሜትር ጋራ ሸንተረርና ሜዳውን አቋርጠው አዲስ አበባ 4ኪሎ ቤተመንግስት አቤቱታቸውን ለማቅረብ በገዳሙ የተወከሉ ጥቂት መነኮሳት አባቶች በቤተመንግስት በር ላይ ተገኝተዋል፡፡ የበር ዋርድያ (ዘብ) ምን እንደሚፈልጉ እና ማንን ማነጋገር እንደሚፈልጉ ሲጠይቃቸው ‹‹ ክቡር ጠቅላይ ሚኒትር መለስ ዜናዊን ›› ማነጋገር እንደሚፈልጉ ፤ ከየት እንደመጡ ፤ ለምን ጉዳይ እንደሚፈልጓቸው ገለጹላቸው ፡፡ ወዲያው የበር ላይ ዋርድያው ስልኩን ብድግ ያደርግና ወደ ውስጥ ይደውላል ፤ ከቤተመንግስት አንድ ሰው ስልኩን ያነሳና ከየት እደመጡ ጉዳያቸው ምን እንደሆነ ዘቡ ያስረዳላቸውና ስልኩን ይዘጋዋል ፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከቤተመንግስት ከውስጥ አንድ ስልክ ይደወልና ዘበኛው ያነሳዋል ፤ የመጡትንም ባለጉዳዮች እንዲያገናኝው ትዕዛዝ ያዘዋል ፤ የበር ዘቡም ከአባቶች አንዳቸው እንዲመጡ እና ስልኩን እንዲናግሩ ይነግራቸዋል ፤ አባቶችን የሚወክሉ አንድ አባት ወደ ስልኩ ይጠጉና ስልኩን ተቀብለው ‹‹ሀሎ›› ይላሉ ፤ ከወዲያ የሚሰማው ግን ያልጠበቁት ነገር ነበር ፤ ከሰላምታ በፊት የስድብ መዓት ሲወርድባቸው ይሰማሉ ‹‹ እናንተ ደፋሮች ይህን ጉዳይ ብላችሁ የአንድን ሀገር መሪ ለማናገር የፈለጋችሁት ፤ ደፋር በሉ አሁኑኑ ሂዱ ….›› ሌሎችንም ነገሮች በቀጭኑ ሽቦ ተነገራቸው ፤ ሀሳባቸውን ለመስማት ምንም የአየር ጊዜ አልሰጣቸውም ፤ ተናግሮ ሲጨርስ ብቻ ጆሯቸው ላይ ስልኩን ዘጋው ፤ በጊዜው በሰሙት ነገር በጣም ገረማቸው ፤ ያገኙትንም መልስ ተገርመው ምን ማድረግ እንዳለባቸው በመወያየት ከ4ኪሎ ቤተመንግስት በር ፊታቸውን አዙረው ሄዱ፡፡
(ይህን ነገር ቪኦኤ ላይ ስልክ ያናገሩትን አባት የካቲት 23 /2004 ቃለ መጠይቅ አድርገውላቸዋል ፤ ከድምጽ ክምችታቸው ማድመጥ ችላሉ)
(ይህን ነገር ቪኦኤ ላይ ስልክ ያናገሩትን አባት የካቲት 23 /2004 ቃለ መጠይቅ አድርገውላቸዋል ፤ ከድምጽ ክምችታቸው ማድመጥ ችላሉ)
ለዚህ ጉዳይ የመጡት መነኮሳት አባቶች ቤተመንግስት ገብተው ጠቅላይ ሚንትሩን ማነጋገር ባይችሉም እንኳን መልዕክታቸውን በምን መልኩ እሳቸው እጅ እንደሚያደርሱ ጊዜ ወስደው ተወያዩ ፤ በመጨረሻም በፖስታ ቤት አማካኝነት መላክ እንደሚችሉ ተረዱ ፤ የጠቅላይ ሚንስትሩን ቢሮ ፖስታቸውን ለማግኝት ብዙ አልተቸገሩም ነበር ፤ ፖስታውን በመያዝ ቀጥታ ወደ ዋናው ፖስታ ቤት በማምራት በአካል ለመስጠት ያሰቡትን ደብዳቤ ለጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ስማቸውን ፅፈው በአስቸኳይ እንዲደርሳችው 30 ብር ከፍለው ሊልኩ ችለዋል ፤ በመጨረሻም ግልባጩን ለጠቅላይ ቤተክህነት የፓትርያርክ ፅ/ቤት አመሩ ፤ እዚያም ለማስገባት ከጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ ያልተናነሰ ነገር አጋጥሟቸው ደብዳቤውን አስገቡ፡፡
እንደ እኔ እምነት ይህ ደብዳቤ ደርሷልም አልደረሰምም ሳይባል መንግስት ዝም እንደሚል እርግጠኛ ሆኜ መናገር እችላለሁኝ ፤ ከወራት በፊት ጠቅላይ ሚንስትር ቢሮ የሚላኩ ደብዳቤዎች የት እንደሚደርሱ የሚያወሳ የግል ጋዜጣ ላይ አንድ ፅሁፍ ወጥቶ ማንበቤን አስታውሳለሁ ፤ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትራችን ከተላኩ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ደብዳቤዎች ውስጥ ለአንዱም መልስ መስጠት አልቻሉም ፤ ይህ የሚያሳየው የደረሰው ደብዳቤው መልስ ካገኝ እንደ እድለኝነትም ይቆጠራል ፤ እኛ ለማንኛውም ትክክለኛና ፤ ሚዛናዊ መልስ የምንጠብቀው ከላይ ነው ፡፡
በኦሪት ዘመን እግዚአብሔር እንደ ልቤ ያለው ንጉስ ዳዊት ፤ ካንተ በኋላ ሌላ ጠቢብ አይነሳም የተባለው ጠቢቡ ሰለሞን ፤ እና አያሌ ነገስታት ህዝብን ለማስተዳደር እግዚአብሔር ሾሟቸዋል ፤ ጊዜውም ሲደርስ የሾማቸውን ሽሯቸዋል ፤ አሁንም ይህ የመንግስት ወንበር ከዘመናት በፊት ያለፉት ነገስታት ተቀምጠውበታል ፤ ህዝብንም በህግና ከህግ ውጪ አስተዳድረውበታል ፤ እግዚአብሔር በዘመናቸው ሾሞ ፤ ቀብቶ አስቀምቷቸዋል ፤ ዘመናቸው ሲያበቃ አውርዷቸዋል ፤ በእነዚህ ሁሉ ጊዜያት ይህች አሁን ያለችው ቤተክርስትያን እንዳለች አለች ፤ ዛሬ የምናያቸው ባለስልጣናት ጠዋት ታይተው ከሰዓታት በኋላ እደሚደርቁ የሳር ላይ ውሃዎች ናቸው ፡፡ ዛሬ መጥተዋል ነገ ደግሞ ወደ ማይቀርበት ሞት ይነጉዳሉ ፤ አሁንም ግን ቤተክርስትያን እንዳለች ትኖራለች ፤ ነገ ደግሞ የተሻሉት አልያም የባሱት መንግስታት ወንበሩን ስልጣነ መንግስቱን በእጃቸው ሊይዙት ይችላሉ ፤ ቤተክርስትያን ላይም መከራዋን ሊያበዙባት አልያልያ ሸክሟን ሊያወርዱላት ብቅ የሚሉ ሌሎች ሊመጡ ይችላሉ እነሱም ግን እንደ አመጣጣቸው ተመልሰው ይሄዳሉ ፤ የማይሞት ባለስልጣን የማያልፍ መንግስት አላየንምም አልሰማንምም ፤ በእምነታችንና በወንጌል እንተነገረው የማያልፍ መንግስት የምናውቀው በሰማይ ያለውን ብቻ ነው ፤ ይህች ንፅህት አንዲት ቤተክርስትያ ግን ጌታችን መድሀኒታን እየሱስ ክርስቶስ በዳግም እስኪመጣ ድረስ ከነፈተናዋ ሳትጠፋ ትጠብቀዋለች ፤ ትቆያለች፡፡
ከ20ዓመት በፊት አቡነ መርቆርዮስ ከሀገር እንዲወጡ በጊዜው የነበረው ጠቅላይ ሚኒስቴር ታምራት ላይኔ ፊርማ አማካኝነት ከጀርባ በተሰራ ሴራ አማካኝነት ከሀገር እንዲወጡ ማድረጉን ሰውየው ከእስር ከሰነበተበት ከቃሊቲ ሲለቀቅ ራሱ በአንደበቱ መስክሯል፡፡ እሱም አንድ ወረቀት ላይ ሲፈርም የአቡኑን መሰደድ ቀድሞ ሲያውቅ የርሱ ህይወት ወደ ወህኒ እንደሚወርድ አያውቅም ነበር ፤ ለኛ አይመስለንም እንጂ ሁሉን የሚያይ አምላክ ግን ሰው የሰራውን ስራ ፤ በምድር ያደረገውን ግፍ በምድር አጸፋውን ሳይሰጠው እንዳይመለስ አይጠራውም ፤ ቤተክርስትያን ላይ እጃቸውን ያነሱ ካሉበት ቁልቁል ሲንሸራተቱ እንጂ በሞገስ በግርማ ከፍ ሲሉ አላየንም ፤ ቤተክርስትያን ቅዳሴ እንቅልፌን ነሳኝ ያለውም ኮለኔል መንግስቱ ኃ/ማርያም ቤቱን ከአስራዎቹ ዓመት በላይ አልኖረበትም ፤ ሀገር ለቆ ተሰዷል ፤ አጠገቡ ያለውን ቤተክርስትያን ለዓመታት ማዘጋቱን እናስታውሳለን ፤ የህውሐት ከፍተኛ ባለስልጣን ከደደቢት በርሀ ጀምሮ ‹‹የኢትዮጵያ ቤተክርስትያንን ቤተክርስትያንን የማፈራረስ ሴራን›› ከቀናት በፊት አስነብቦን ነበር ፡፡ እኔ የምፈራው ለእናንተው ነው የምትቆፍሩትን ጉድጓድ አታርቁት ማን እንደሚገባበት አይታወቅም፡፡ እኛ ግን ለባለስልጣኖቻችን ሀገርን የሚመሩበት ፤ ህዝብን ያለ አድልዎ የሚያስተዳድሩበት ፤ መልካም አስተዳደርን የሚያሰፍኑበት ፤ ለትውልድ ጥሩ ስራን ሰርተው ማለፍ የሚችሉበት የስልጣን ዘመን ያደርግላቸው ዘንድ ‹‹ለሰለሞን ማስተዋልና ጥበብን የሰጠህ አምላክ ለመሪዎቻችንም ማስተዋሉን አድልልን›› እያልን እንጸልያለን ፤ እግዚአብሔር ማስተዋልን ካላደለ የኛን ማስተዋል ወንዝ እንደማያሻግረን እናውቃለን፡፡ መሪዎቻችን ማስተዋሉን ካደላቸው ሀገር ሰላም ይሆናል ፤ ሰዎች ተከባብረው ይኖራሉ ፤ ቤተክርስትያንና ምዕመኑም የሰላም አየር ይተነፍሳል ፤ በእምነቶች መካከል የመከባበር መንፈስ ይመጣል መጪውም ዘመን ብሩህ ይሆናል ፤ ያለበለዚያ ደግሞ የተገላቢጦሽ……..
ይህን የመሰለ ቤተክርስትናችን ላይ ፤ ገዳሞቻችን ላይ ያጋረጠ አደጋ እያየን ከዚህ በላይ ሌላ አሳሳቢ ጉዳይ ከወዴት ሊመጣ ነው ፤ ይህ ለእኛ እረፍት የሚሰጠ ለነገ የምንለው ጉዳይ አይደለም ፤ በዶዘር የቅዱሳን አባቶቻችን አጽም እየታረሰ እንደ አልባሌ ነገር ወደ ሌላ ቦታ ሲወሰድ እያየን እንቅልፍም አይወስደን ፤ እረፍትም አይሰጠን ፤ ለብዙ መቶ ዓመታት በአባቶቻችን ጽኑ ተጋድሎ እና ጸሎት የቆየው የሰነበተልን ገዳም ሲፈታ እያየን ዝም አንልም ፤ ይህ የዋልድባ ገዳም አባቶች ጉዳይ ብቻ አይደለም ፤ ይህ 4 ኪሎ የሚገኝው የጠቅላይ ቤተክህነት ጉዳይ አይደለም ፤ ይህ በሰሜኑ ክፍል የሚገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ብቻ ጉዳይ አይደለም ፤ ይህ በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚገኝው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች የሁላችን ጉዳይ ነው ፡፡ ይህ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠር የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች ጥያቄ ነው ፤ አቡነ ጳውሎስ ይህን ጉዳይ እንደ ቤተክርስትያኗ የበላይ ሀላፊ ሞግተው ለውጥ ያመጣሉ የሚል እምነት የለንም ፤ ባይሆን ለትራንስፎርሜሽን የ5ዓመት የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ከማድረግ ውጪ ፤ እኛ ሀገሪቱ ላይ ልማት አይካሄድ ፤ ድህነታችን ይሻለናል የሚል አመለካከት የለንም ፤ ነገር ግን ገዳሞቻችን ተፈተው ፤ አብያተክርስትያኖቻችን ፈርሰው ፤ የቅዱሳን አፅም እንደ አልባሌ ሁኔታ በዶዘር ታርሶ ፤ ቅዱሳን ቦታዎችን በብር ለውጠን ከምናመጣው እድገት ይልቅ አሁን ‹‹ያለን እምነት ከድህነታችን ጋር›› አስር እጅ ይሻለናል የሚል ፅኑ እምነት አለን፡፡ ይህችን እምነት አባቶቻችን ሲያስረክቡን የስጋ ድሎት እንድናገኝባት ፤ ስለ አላፊው ምድራዊ ነገር እንድናስብባት ሳይሆን መሰረታዊውን መንግስተ ሰማያትን እንድንወርስባት ነው ፡፡ እምነት እና ገንዘብን ለየቅል ተመልከቱልን ፤ ስለ እምነት ስናወራ ስለ አላፊ ጠፊ ብር አታውሩብን ፤ ስለ ቅዱሳን ቦታዎች ስናወራ ስለ ሌላ ተለዋጭጭ ቦታ አታውሩብን ፤ ይህን የምናይበት አይን የምንሰማበት ጆሮ የለንም፡፡
ኢትዮጵያ እምነት ያለውም የሌለውም መሆኗን ቀዳማዊ ሃይለስላሴ በአንድ ወቅት ተናግረዋል ፤ የአንድ እምነት አይደለም የአንድ ሰው መብት በህገ-መንግስቱ መሰረት መከበር አለበት ፤ ይህ ጥያቄ ግን ግለሰባዊ አይደለም ፤ የአንድ አገር ጠቅላይ ሚኒስቴር እንዲህ ብለው ይናገራሉ ብለን አንገምትም፤ በእንዲህ አይነት ሁኔታ ለጥያቄዎችም መልስ ይሰጣሉ የሚል እምነት የለንም ፤ ከእሳቸው በታች ያሉት ሰዎች ግን በእውቀት ማነስ ተናግረውታል ይሆን ይሆናል ፤እነርሱም ቢሆኑ ቦታውን የሚመጥን መልስ መመለስ አለባቸው እንጂ እንደ መንደር ጎረምሳ መልስ መስጠት የለባቸውም ፤ ይህን የመሰለ ዜና ሰዎች ቢያዳምጡት ለሀገርም መልካም አይደለም ፤ ጥያቄዎቻችን መሰረታዊ ናቸው ፤ መንግስትን የሚወክል መፍትሄ የሚሆን መልስ እንሻለን ፤ አባቶቻችሁ ገዳማትን ሰርተው አቆይተውልናል ፤ እናንተ ልጆቻቸው ገዳሙን የመጠበቅ ታሪካዊ አደራም እንዳለባችሁ አትዘንጉ ፤ ከአስር መቶ አመታት በላይ ተጠብቆ ሲወርድ ሲዋረድ ያለውን ቦታ በልማት ሰበብ ድንበሩን አታፍርሱብን፡፡
ባያውቁት ነው እንጂ ይህች ቤተክርስትያን ስለ ምዕመኗ ፤ ስለ ሀገር ሰላም ፤ ስለ አገልጋዮች ፤ ስለ ሀገር ድንበር ፤ ስለ እሰር ላይ ስለሚገኙ ሰዎች ፤ ስለ ዓለም ሰላም ፤ ስለ ዝናብ ብቻ ስለሁሉም ነገር ሳትጸልይ የኖረችበት ጊዜ የለም ፤ ትላንትና ጸልያለች ፤ ዛሬም ትጸልያለች ፤ ነገም እንደዚያው ፤ ቤተመንግስቱ ዙሪያውን ከበውት የሚገኙት የቅዱስ ገብርኤል ፤ የበአታ ለማርያም ፤ የኪዳነምህረት ፤ የስላሴ ፤ የእግዚአብሔር አብ አብያተ ክርስትያናት የነግህ ኪዳን ፤ የጠዋት ጸሎት ፤ ቅዳሴ ፤ ለሀገር ለህዝበ ክርስትያን እንደሚተርፍ የተረዱት አይመስለኝም ፤ በዱር በገደሉ ያሉ የአባቶች እንባ ለሀገር ሰላም የጀርባ አጥንት መሆኑም አልገባቸውም ፤ አንድ ምሳሌ ብቻ እናንሳ ፤ በ1997 ዓ.ም ሚያዚያ 30 ቀን ቅንጅትን በመደገፍ በመስቀል አደባባይ የተሰበሰበው ሰው (በጊዜው የነበራችሁ ሰዎች ታስታውሱታላችሁ ) እግዚአብሔር ያንን ለተቃውሞ የወጣ ህዝብን በጠራራ ጸሀይ ዶፍ ዝናብ ከሰማይ አውርዶ ባይበትነው ኖሮ ምን ሊፈጠር እንደሚችል አስቦት የሚያውቅ ሰው አለ? የትኛው ጦር ፤ የትኛው ፌደራል ፖሊስ ነው የሚበትነው? ከዚያን ቀን በፊትም ሆነ በኋላ እንደዚያ ያለ ዝናብ አላየሁም፡፡ እንኳን በዝናብ አለፈ ፤ እንኳን ደም ያልፈሰሰ ፤ እግዚአብሔር ይመስገን ፤ ‹‹እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ ሰራተኞች በከንቱ ይደክማሉ እግዚአብሔር ከተማ ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል›› መዝሙረ ዳዊት 127 ፤ 1 ይላል፡፡ እኛ ለዚህ ነው ኢትዮጵያ ሐገረ እግዚአብሔር የምንለው ፤ የእኛ ሀጥያት ቢበዛ የበደላችን ፅዋ ሞልቶ ቢፈስ እንኳን እግዚአብሄር ይችን ሀገር አይተዋትም ፤ እርሱ ለቤቱ ከእኛ በላይ ይተጋል ቤቱንም ይጠብቃል ፤ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው ስለ ሀገር ፤ የሚጸልዩ የአባቶቻችን ባእት ሲፈርስ እያየን ዝም አንልም፡፡ የሰማዕቱን የቅዱስ ጊዮርጊስን የአድዋ ውለታ ሚኒሊክ ከመቃብር ተነስተው ቢናገሩ ደስ ይለን ነበር ፤ በጊዜው የነበሩ የጣልያን ወታደሮችን ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ የመሰከሩት በታሪክ መዛግብት ተፅፎ ተቀምጧል፡፡ አሁን እያልን ያለነው እንደ ቅዱስ ጊዮርጊስ ለሀገራቸው እና ለእምታቸው ሰማዕት የሚሆኑ የአባቶቻችንን ማረፊያ ፤ የቅዱሳንን መናህሪያ አትንኩብን ፤ ለትውልድ የሚተርፍ ስህተት አትስሩ ነው የምንለው፡፡
መሪ ማለት ችግሩ የተፈጠረበት ቦታ ድረስ ሄዶ የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት የራሱን ጥረት ያደርጋል ፤ እንደ አለመታደል ሆኖ እኛ ጥያቄያችንን ከሰሜኑ የሀገራችን ክፍል መሀል አዲስ አበባ ድረስ ስናመጣ መልሳቸው ስድብ ሆነብን ፤ ችግሩን አያውቁትም ብለን አይደለም ጥያቄውን እዚህ ድረስ ያመጣነው ፤ ድምጻችን ቢሰማ መፍትሄ ብናገኝ ብለን እንጂ ፤ ታዲያ ይህችን ሀገር የሚያስተዳድራት ህዝብ በየ5 ዓመቱ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እያደረኩ ህዝቡ 99.6 በመቶ መረጠኝ ለሚለው መንግስት ጥያቄያችንን ከአፈር ከደባለቀብን ሌላ የት ሄደን አቤት ማለት እንችላለን ፤ የእስራኤል አምላክ እንደማይተወን እርግጠኞች ነን ጸሎታችንን አናቋርጥም ፤ እንባችንንም ወደ ላይ እንረጫለን ራሄልን የተመለከተ አምላክ እኛንም ይመለከተናል አንጠራጠርም ፡፡
ከዚህ በላይ ምን ሊምጣ ነው። ይህ መንግስትና ቅዱስ ፓትሪያልኩ ይህችን ቤተክርስቲያ አያደሙ አንዲኖሩ መፍቅድ መቆም ያልበት ይምስለኛል። ዛሬ ህዝበ ክርስቲያኑ በአንድ መንፈስ ሆኖ ለቤተክርስቲያ መቆም ያለበት ሲሆን አነርሱንም በቃችሁ ማለት አለብን። ከፓርቲ በፊት ቤተክርስቲያንን ማስቀድም ያለብን ጊዜ ላይ ደርሰናል በቤተክርስቲያ ላይ ስለሚደርሰው በደል ፍራቻችንን አናስወግድና ሁሉን አንጋፈጥ። የአባቶቻችን አምላክ ይርዳን
ReplyDeletewhat shall we do? ????????????
ReplyDeleteEre gobez ande enebel
አሜን ቸሩ አምላካችን ጸሎታችንን ይስማልን::
ReplyDeleteabetu amlakachin hoy megefatachinin temelket hayilachin mirkuzachin meshashegachin ante nehina hulun neger kewunilin
ReplyDeleteSelam Le'enante yihun
ReplyDeleteMane Tekel Fares!!!
Alfo Ayichew
yihem gize yalf yihon? Amlak hoy ebakh slekedemu degag abatoch bleh Betecrstiyanhn tebkat.
ReplyDeleteNo body opens mails which are sent to the prime minster office. Everyday hundreds of mails are shredded without even seen by the any lower level authorities. Forget about Meles, he will not see any mail. The secretaries are told to do. Do not expect anything from there. I feel so bad for those who paying a lot for the postal service. It would be better to send it as regular mail.
ReplyDeleteየገዳማት ማማ
ReplyDeleteየባህታዊያን ዋሻቸዉ መሸሸጊያ ለቅዱሳን
የምእመናን ተስፋ መጠጊያቸዉ ለቅቡጻን
ዓለምን የናቁ የዓለም መናኛ
አምሳለ ኢየሩሳሌም አንተን መማጠኛ
የገዳማቱ አብነት የቋርፉ መገኛ
ዋልድባም ሊፈታ?… መሬቱ ታረሰ
የቅዱሳንህ አጽም በከንቱ ፈለሰ፡፡
እንዴት በኛ በደል ይጉደፍ እምነታችን?
ቅዱሳን የሰሩት ይጥፋ ታሪካችን?
አንተን ሽተዉ አንተን ለታመኑት
አስብ ቃለዉግዘታቸዉን ፍረድ ለቀደሙት፡፡
ማይ ገባ ሚካኤል የማር ገጽ ጊዮርጊስ
አቡነ አረጋዊ እጣኖ ማርያምን ሁሉንም ለማፍረስ
ልማት ብሎ ሽፋን ሴራ ተሸርቧል
የገዳማት ማማ ዋልድባ ተደፍሯል፡፡
“እንበለ ፈላሲ ኢይባዕ ነጋሲ” እንዳይሻር ዉግዘቱ
ተጋድሎዉ እንዳይነጥፍ እንዳይርቀን በረከቱ
… በከለባት ማህል
ሰሚ ያጣዉ እንባ ወዳንተ ይጮሃል
በል ፍረድ ዝም አትበል ሁሉ ይቻልሃል፡፡
(የካቲት 4, 2004ዓ.ም)
ቅዱሳን ቦታዎችን በብር ለውጠን ከምናመጣው እድገት ይልቅ አሁን ‹‹ያለን እምነት ከድህነታችን ጋር›› አስር እጅ ይሻለናል...
ReplyDeleteበጣም ትክክል!!! የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው!!!
Deleteቅዱሳን ቦታዎችን በብር ለውጠን ከምናመጣው እድገት ይልቅ አሁን ‹‹ያለን እምነት ከድህነታችን ጋር›› አስር እጅ ይሻለናል!!!
ReplyDeletehulum neger abkitual!!! ethiopia azina eyetekezech new.wond tefa! yewelad mekan .enbawan man yitireg?
ReplyDeleteየሃጢያታችንን ብዛት የማይመከት የአባቶቻችን አምላክ እርሱ ያስተካክለው፡፡
Deletecheru egizihabher esu chuhetachinen yemeleketal teyaken beagebabu alememelesachew ayedeneken lelam lelam leyadergu yechilalu ayedenkenm becha lebachewn amlak endikeftlachew entsely anferam menm ayametum yemokrut yehonal gin endayadagimut yehonallu .awun metfiyachew yetekarebe yemeslal ye 5 ametu edget ena transformetion ekid menalbat ye enesu edme lehon yechilal bezu serawit alachew ye werem ye militarim.....hulum yemitay yemitefa kentu fukera !!! yechi betchristianen yemitebku serawits? ylum? yetyalu? becha egna wulle addis honen enji fetenaw gin addis ayedelem yemokrut wetakebalu weyem yetefallu egna tewahedoawiea ansegam enesu wendemochachin gin yasferachewal.mastewalen cheru egizhabher yestachew
ReplyDeleteAre Gobez tebabren Yihen mengist ental, zare nege saybal addis abebame yeyekiflehagru ketemem menesat alebn, lela were yiqrna wede tiglu enamra
ReplyDeleteabet abet yemen yeger esat metaben?kewest esat kewech esat ere amlakachen ande belen zemetah eseke meche new?lebachen qosele bemenesemawe hulu feteneh tadegen
ReplyDeletewe have to be one & fight this no
ReplyDeleten sense government wisely!!!
Yehatiatachin bizat betkirstianachinin lemekera daregat ena gobez lehatiatachin masteseria yihoniln endehon ahun enkua lewelad mekanua enat betkirstian alehulsh enbelat enbawan enabsilat
ReplyDeleteበአንድ ወገን እሳት ይለቁባታል ፡፡ በሌላው ደግሞ ውስጥ ያሉትን ልጆቿን እየከፋፈሉ ሞት ቀረሽ ትግል ውስጥ አስገብተዋቸዋል ፡፡ ስድስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በተለያየ ሥፍራ ፣ የሰማይ ቁጣ እስኪመስል ድረስ በተደጋጋሚ ቤተ ክርስቲያናትና ገዳማት ተቃጥለዋል ፤ ሁሉም ነገር የሉተራን ልጆችን ለማስደሰት የሚሰራ ሥራ ነው ፡፡ በጐጥ የተሞከረው አሁን በሃይማኖት ሲሆን የረዳቸው ስለመሰለ በተለያየ መልክ ለማጋጋም እየታገሉ ነው ፡፡ የህዝቡን ማናወጫ ቁልፍ ያገኙት ይመስላል ፡፡ እስላሙንም ብትመለከቱት ከክርስቲያን ወገኑ ባልተናነሰ መልኩ እንዲሁ ይታመሳል ፡፡ ይኸ የሚያሳየው መልስና እልባት ከመስጠት ይልቅ ፣ ከጀርባ ሆነው የሚሰሩት ታላቅ የቤት ሥራ እንዳለ ነው ፤ በበኩሌ ከመንግሥት ብዙ አልጠብቅም ፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔር ለነሱም ማብረጃውን ፣ ለልጆቹም የሚሆነውን መልስ ራሱ ይስጥ ፡፡
"Abatu dagna liju kemagna" Bete Kihinetu ena bete mengistu tilik yeteleko sira lay tetemdewal genzeb yemayseraw sira yelem. endihum Ethiopiawinet le'enesu minachewim silalihone hizibu bichoh minim ayametam eyalun new. Awo "እግዚአብሔር ለነሱም ማብረጃውን ፣ ለልጆቹም የሚሆነውን መልስ ራሱ ይስጥ ፡፡"
DeleteAlfo Ayichew
እኛ ከአባቶቻችን የተረከብነውን የቤተክርስትያ ቅዱሳት ቦታዎችን በገንዘብ እና በሌላ ተለዋጭ ቦታ አንለውጥም››እንደ ናቡቴ ያባቶቻችንን እረስት አንለቅም እንበል ለምን በተለዋጭነት ሊሰጥ የተፈለገዉን ቦት ለራሱ ልማት የማያደርገው ከእግዚአብሔር ጋር ተዋግቶ ያሸነፍ ማእንዳለ መንግስታችን በእርሱ ይጀመር እንድሆን እስኪ ይሞክርዉ እኛም አምላክን በአምልኮታቸዉ ደስ በማሰኝታችዉ ጸጋ የተሰጣችዉን የአባቶቻችንን ተርፍ አጽማችዉን በማንሳት ወደአምላካችን ስንጩሕ እርሱ ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ አልዉና ይህን የመሰለዉን መአት ያሰማን ደግሞ ነጌ ታሪክን እንዴት እንደሚለዉጥ ያሳየናል እኛ ብቻ ወደአምላካችን እንጩህ እርሱ ለጥያቄዎች ሁሉ መልስ አለዉና "ባለ ስልጣን በወንበሩ ላይ ሲቆይ አምላክ የሆነ ይመስለዋል" ድንገት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እግዚአብሔር ሊያስተላልፍ የፈለገዉ መልክት የኖራል እንጂ መቼስ ካሁን ቀደም ያሉት ባለ ስልጣናት ቤት እግዚአብሔርን በድለዉ ምን እንደደርሰባችዉ ታሪክ አገላብጠዉ ሳያነቡ አልቀርም አማርኛ ማንበብ ባይችሉም እንኳ በአስትርጓሚ ይሰማሉ ብለን እናስባለን!::
ReplyDeleteአምላካችን ኢትዮጲያን ከክፉ መሪ ይሰዉራት
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ መአቱን በምሕርት ሐዘኑን በድስታ ለዉጠክ አሳየን አሜን!!!
Amlake Kidusan hailun yemigeltibet seat dersoalina wogene betselot berta. Melsachin Kelay new.
ReplyDeleteyekedusan ena yabatoche tselote melashe mene yehone amelake hoye kezhe belaye bebethe mene yemytale ena new kehulete mekefelachen sysazenene yebase meta ebakhene lebethe kante belaye asabe yelemena ande belene .
ReplyDeleteyemuselymochen heberte yadelene .
ጌታ ቢዘገይም የሚቀድመው የለም "እኛ ጋር ያለው ከነሱ ይበልጣል" ስለሁሉም አንተ ታውቃለክ፡፡
ReplyDeleteአባቶች ወገንተኛ አትሁኑ ይቅር ተባባሉ ለህዝባችሁ ይቅርታን አስተምሩ !!!!!የቤተክርስቲያን ልጆች እርስ በእርሳችሁ ይቅር ተባባሉ ክፍፍል ዋጋ ስክፍላል ድንግል ሆይ የህችን ሀገርና ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ጠብቂልን ጠብ ፤ክርክር፤አድመኝነት ሰፍኖዋል የቅር ብሎ ይቅር የሚያስብል የለምና ክልጅሽ አማልጂን!!!!!!
ReplyDeleteዋልድባ lay industry indisera yefekedew woyim lisera yefelegew sew woyim akal
ReplyDeleteእግዚአብሔር yikir yibelih/yibelachihu,gin yihin kemasebachihu befit bizu asibu,asibu,asibu..............begna betekiristian lay yetenesut hulum yetim alideresum......asibu.....
‹‹እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ ሰራተኞች በከንቱ ይደክማሉ እግዚአብሔር ከተማ ካልጠበቀ ጠባቂ በከንቱ ይተጋል›› መዝሙረ ዳዊት 127 ፤ 1
ReplyDeleteEne gin zim biye sasibew ABUNE PAULOS besew eji yemitefu new yemimesilegn.
Deletegeta hoy tigesth eskemin deres new?
ReplyDeletepeople people ethio people please stand up 4 fight the gov't.everything is come next to ortodox.
ReplyDelete