· አበምኔቱ መምህር ገብረ ጊዮርጊስ ገብረ አረጋዊ ያሉበት አልታወቀም።
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡
· የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ልኡካን ጠንካራ ተቃውሞ እየገጠማቸው ነው።
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 8/2004 ዓ.ም፤ ማርች 17/2012)፦ በዋልድባ ገዳማት ህልውና እና ክብር ላይ ከተፈጠረው ችግር ጋራ በተያያዘ ወደ ስፍራው ያመሩት ሁለት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች በዓዲ አርቃይ ስብሰባ ማድረጋቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ እና የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ ሓላፊው አቶ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ በዓዲ አርቃይ ከገዳሙ ማኅበር ተወካዮች ጋራ ያደረጉት ውይይት የገዳሙን ተወካዮች በጫና ውስጥ በሚያስገባ አኳኋን በመንግሥት የተወጠነውን ዕቅድ አሳምኖ ‹ልማቱን በማስቀጠል› ላይ ብቻ ያተኰረ እንደ ነበር ተጠቁሟል፡፡

ይኹንና በውይይቱ “የታሰበው ሳይሳካ ቀርቷል” ያሉት ምንጮቹ ከስብሰባው በኋላ በውይይቱ ላይ ያልነበሩት የገዳሙ አበምኔት ቤት በፌዴራል ፖሊስ እና ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቀዳሚ ውይይት ከተካሄደበት ማይ ፀብሪ በመጡ ባለሥልጣናት ፍተሻ እንደተካሄደበት ተዘግቧል፡፡ የመረጃው ምንጮች አበምኔቱ መምህር ገብረ ጊዮርጊስ ገብረ አረጋዊ ያሉበት ትክክለኛ ቦታ ለጊዜ እንደማይታወቅ ለደጀ ሰላም ገልጸዋል፡፡
ዋልድባ እንዲህ ባለ ችግር ላይ ባለበት በአሁኑ ወቅት ቅዱስ ሲኖዶስ እና ፓትርያርኩ ምን እያደረጉ ነው የሚለው ጥያቄ ከፍ ብሎ መሰማት ጀምሯል። አንዳንዶችም “አባ ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያኒቱን እያጠፏት ነው” የሚለውን ወደማመኑ እየደረሱ ነው። ከ16 ዓመት በፊት የዋልድባ አብረንታንት ገዳምን የጎበኙት አቡነ ጳውሎስ “ሴቶችና ወንዶች በአንድነት የሚቆርቡበት ቤተ ክርስቲያን ይሠራ” በሚል የሰጡት መመሪያ ከፍተኛ ተቃውሞ ቀስቅሶ ነበር፡፡ መመሪያው በገዳማውያኑ ጸሎት እና ለፓትርያሪኩ በቀጥታ በተጻፈላቸው የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ተፈጻሚነት አለማግኘቱ ቢገለጽም አሁን የሚታየው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዳተኝነት የዚህ ክትያ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
በወቅቱ (በ1989 ዓ.ም) አበምኔቱ በገዳሙ ክልል ውስጥ በሚካሄደው የከብት ስምሪት እና በየዓመቱ በሚያጋጥመው ሰደድ እሳት ሳቢያ ቅዱሳኑ እየተረበሹ፣ የዱር እንስሳቱም እየተሰደዱ የመሆኑን ችግር ለፓትርያርኩ አመልክተው ነበር፡፡
በ1989 ዓ.ም በከፍተኛ የጥበቃ አጀብ በገዳሙ ተገኝተው የነበሩት አቡነ ጳውሎስ እንደ አንድ ድርጎኛ ተቆንነዋል፤ በአብያተ ምርፋቁ ቋርፍ ተመግበዋል፣ ጭልቃ ጠጥተዋል፤ ሕጽበተ እግር ተደርጎላቸው ማየ ዮርዳኖስን ቀምሰዋል፤ ከገዳሙ ሥምረት ገብተው መቁጠሪያተቀብለዋል፡፡ ለመናንያኑና አገልጋይ መነኰሳቱ የረዱት 50,000 ብር ግን “ኀምሳ ሺሕ ጣጣ ያመጣብናል” በሚል “ይቅርብን” አሰኝቶ ነበር፡፡
ስለ ዋልድባ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃዎችን እንደ ደረሰን እናቀርባለን፡፡
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡
Please also update us about the fire @ ዝቋላ
ReplyDeleteቸር ወሬ ያሰማን
ReplyDeleteአምላክ ሆይ ስማን!
ReplyDeletecher were yaseman
ReplyDeleteEgziabher hoy atetewen sewu seten!
ReplyDeleteአሁንስ በዛ መንግስት እራሱ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለማጥፋት ከፍተኛ የሆነ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ስለዚህ እባካቸሁ ህዝበ ክርስቲያኑ መሮታል የሚቻላችሁን ሁሉ አድረጉ፡፡ለምን ሰልፍ አንወጣም; እኛ ዝም ስላልን እኮ ነው ይሄ ሁሉ ስራ የሚሰራብን፡፡ አንዲ ነገር ልንገራችሁ አቡነ ፓውሎስ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን አይጠቅማትም፡ እሳቸው የፖለቲካ ስው ናቸው፡፡የኢህአደግን አላማ እንጂ፡ የቅድስት ቤተክርስቲያንን አላማ አያራምዱም፡፡ብቻ……………………………………………….እግዚአብሔር ይርዳን፡፡
ReplyDelete