በጣም አሳዛኝ ዜና!!
አንድ አድርገን መጋቢት 7 ፤ 2004ዓ.ም)፡- ለ4 ዐሠርት ዓመታት የግብጽ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንና ሁላችንንም በትጋትና በጽንዕት ያገለገሉት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ በ88 ዓመታቸው እንዳረፉ ቢቢሲ ዘገበ፡፡ ቅዱስነታቸው ከ5ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ የቲዎሎጂ ሴሚናሪ ዲን የሆኑ የመጀመሪያው ፓትርያርክ ሲሆኑ በአገልግሎት ዘመናቸው ከ3 የአሜሪካን እንዲሁም ከ1 የጀርመን ዩኒቨርስቲ የክብር ዶክትሬት ተቀብለዋል፡፡ቅዱስነታቸው ሕይወታቸው የትምሕርምት፣ የጸሎትና የአገልግሎት እንደነበር የሕይወት ታሪካቸውን የሚዘግቡ ድርሳናት የሚገልጹ ሲሆን ባለፉት 20 ዓመታት የዓለምን ሕዝብ ያስተማሩባቸው ከ100 በላይ መጻሕፍትን ደራሲና የቤተ ክርስቲያኗ ኦፊሴላዊ መጽሔት ኤል-ኬራዛ ዋና አዘጋጅ ነበሩ፡፡
በግብፅ ርዕሰ ብሔር አንዋር ሳዳት ጊዜ አክራሪ ሙስሊሞች በክርስቲያኖች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመርና መፋፋም ያሳሰባቸው ቅዱስነታቸው በመንግሥቱ ላይ ባነሱት ተቃውሞ፣ ለ40 ወራት ከመንጋዎቻቸው ተለይተው ወደ ቅዱስ ቢሶይ ገዳም ተግዘው የአባቶቻቸውን በረከት ተካፍለው እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን በኋለኛው መሪ ሆስኒ ሙባረክ ዘመን ወደ መንበራቸው ተመለሰው እስከ ዛሬ ድረስ ጠቦቶችን ሲጠብቁ፣ ግልገሎችና በጎችን ሲያሰማሩ ቆይተው ዐርፈዋል፡፡ ለእርሳቸው ወደ ክርስቶስ መሄድ የሚናፍቁት ቢሆንም ለእኛ በሕይወተ ሥጋ ላለን ግን አጽናኝን አባት ማጣት ነው፡፡
ወዮ… ወዮ
ፊል 1፣21 “… ልሂድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፤ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፡፡ ”
- ወዮ… ወዮ የ21ኛው መ/ክ/ዘ ታላቁን አባት ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ 3ኛ አረፉ፡፡
- ወዮ…ወዮ የተሰጣቸው መክሊት እጥፍ አድርገው ያተረፉ፤ በጎቻቸውን በፍቅር፣በትህትና እና በትጋት ያገለገሉ መልካሙ እረኛ ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ አረፉ፡፡
- ወዮ….ወዮ የመናፍቃንን አንገት ያስደፉ፣ የዓለማችን ፈላስፋዎች በቃለ እግዚአብሔር አፍ ያስያዙ፣በትምህርታቸው የብዙ ሰዎች ነፍሳትን ያለመለሙ፣ቅዱሳን ሐዋርያትን የመሰሉ ታላቁ አባት ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ አረፉ፡፡
- ወዮ…ወዮ ከመቶ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የጻፉ፣ በዓለም ዙሪያ በርካታአብያተክርስቲያናትን ያሳነጹ፣በመቶዎች የሚቆጠሩ ዲያቆናት፣ቀሳውስትንና ኤጲስ ቆጶሳትን የሾሙ ታላቁ አባት ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ አረፉ፡፡
- ወዮ…ወዮ በካህናት ፣ በምእመናንና በኢአማንያን ዘንድ ከልብ የሚወደዱ፤ ንጹሁ፣ድንግል፣ካህን፣ባህታዊ፣ትህርምተኛ፣ወንጌላዊ፣ደራሲ፣ተርጓሚና ገጣሚ የሆኑት ታላቁ አባት ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ አረፉ፡፡
- ትልቅ አባት በእውነት አጣን ፣ ሥራቸው ግን ለዘላለም ይኖራል ፣ በገነትም በሰላም ከቅዱሳኑ ጋር ያኑራቸው። የአገልግሎት ጊዚያቸውን በመልካም እረኝነት አሳልፈዋል:: መክሊታቸውንም አትርፈውበታል:: ሞት ለማንም አይቀርምና እርሳቸውም አርፈዋል:: እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይቀበላቸው ፤ ከቅዱሳን ጋርም ያኑርልን::
- አቤቱ የቅዱሳን አምላክ ሆይ፣ በነቢዩ ኤልያስ የነበረውን ቅዱስ መንፈስ እጥፍ አድርገህ በነቢዩ ኤልሳ ላይ እንዳወረድክ፣ እንዲሁም በአባታችን በብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ የነበረውን ቅዱስ መንፈስ በቅዱስ ማርቆስ መንበር ላይ ለሚተካ አባት እጥፍ አድርገህ ታወርድለት ዘንድ ፍቃድህ ይሁን፤ አሜን፡፡
- ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ መልካሙን ገድል ተጋድለዋል፣ ሩጫዎቶን ጨርሰዋል፣ ሃይማኖቶን ጠብቀው አስጠብቀዋል፣ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶሎታል፣ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያን ቀን ለእርሶ ያስረክባል፡፡
- ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ ሆይ ለዚህ ታላቅ ክብር ያደረሶት ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፣ በዚያን ጊዜ ቅዱስነትዎ እኛም ከእርሶ ጋር በክብር ትንሳኤ እንድንገልጥ በጸሎቶ ያስቡን፡፡
- ወዮ… ወዮ የ21ኛው መ/ክ/ዘ ታላቁን አባት ብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ 3ኛ አረፉ፡፡
በጣም አዝነናል በዚህ ጊዜ አቡነ ሺኖዳን በማጣታችን ፤ ይህ የኮፕቶች ሀዘን ብቻ አይደለም ፤ የእኛም የእህት አብያተክርስያናት ጭምር ነው ፤ በጣም በጣም አዝነናል ፤
አምላክ ነፍሳቸውን በገነት ያሳርፍልን
ታላቁን አባታችንን ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳንን ማጣት ምን ያህል ይከብዳል!!!....
አምላክ ሆይ እኛን ባሪያዎችህን እባክህ ያለ እረኛ አታስቀረን ፡፡
የአቡነ ሺኖዳ ሞት ለእኔ ‹‹ትልቅ ዋርካ የወደቀ ያህል ነው የተሰማኝ››
ለእምነታቸዉና ለሐይማኖታቸዉ የኖሩ ሰዉ መሆናቸዉን ያወቁ እዉነተኛ አባት ፤ አስተማሪ መካሪ ታላቅ የሀይማኖት ሰው ማጣት በጣም ከባድ ነው።የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን፤ ይደርብን፤ ለግብጽ ቤተ ክርስቲያንም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳን ዐይነት አባት ይተካላቸው፤ ይስጣቸው። አሜን
እኔ ጨርሻለው ልምጣ ወደ ቤቴ
ሰላምህ ይብዛልኝ ውሰዳት ህይወቴ
አራት ሰው ሞተ
አራት ሰው ሞተ ደረሰ እና ጥሪ
ደራሲ፣ ሰባኪ፣ ጳጳስ እና መሪ
እንግዲህ መቃብር ደኅና አርገህ እፈስ
መጽሐፍ ተሸክሞ መጣልህ ጳጳስ
በግብጽ በካይሮ ጩኸት በረከተ
የዓለሙን አናውቅም አንድ የእግዜር ሰው ሞተ
ሞተዋል እንዳይሉ ጽፈው አገኟቸው
አልሞቱም እንዳይሉ ተኝተው አዩዋቸው
ምናሉ ቅብጦቹ ሰው ሲጠይቃቸው
ለወሬ አልተመቸም በችግር ላይ ናቸው
የአቡነ ሺኖዳ ሞት ለእኔ ‹‹ትልቅ ዋርካ የወደቀ ያህል ነው የተሰማኝ››
ለእምነታቸዉና ለሐይማኖታቸዉ የኖሩ ሰዉ መሆናቸዉን ያወቁ እዉነተኛ አባት ፤ አስተማሪ መካሪ ታላቅ የሀይማኖት ሰው ማጣት በጣም ከባድ ነው።የቅዱስነታቸው በረከት አይለየን፤ ይደርብን፤ ለግብጽ ቤተ ክርስቲያንም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳን ዐይነት አባት ይተካላቸው፤ ይስጣቸው። አሜን
ቀና ወደ ሰማይ!!!
ይቺን ቤተክርስቲያን አምላኬ ጠብቃት
ፍሬን የሚያፈራ ተተኪ ተካላትይቺን ቤተክርስቲያን አምላኬ ጠብቃት
እኔ ጨርሻለው ልምጣ ወደ ቤቴ
ሰላምህ ይብዛልኝ ውሰዳት ህይወቴ
አራት ሰው ሞተ
አራት ሰው ሞተ ደረሰ እና ጥሪ
ደራሲ፣ ሰባኪ፣ ጳጳስ እና መሪ
እንግዲህ መቃብር ደኅና አርገህ እፈስ
መጽሐፍ ተሸክሞ መጣልህ ጳጳስ
በግብጽ በካይሮ ጩኸት በረከተ
የዓለሙን አናውቅም አንድ የእግዜር ሰው ሞተ
ሞተዋል እንዳይሉ ጽፈው አገኟቸው
አልሞቱም እንዳይሉ ተኝተው አዩዋቸው
ምናሉ ቅብጦቹ ሰው ሲጠይቃቸው
ለወሬ አልተመቸም በችግር ላይ ናቸው
(ዲ/ን ዳንኤል ክብረት)
በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስትያናችን ላይ እየደረሰ ያለውን ነገር ሳስተውል ፤ የአቡነ ሺኖዳን ሞት ስመለከት ፤ ውስጤ በጣም ፈራ
Egziabher ye abatachenen nebse yemarelen betekerestiyan telek abat new yatachew.
ReplyDeleteoh no no no noooooooo nooooooo please wushet new belugne pleaseeee wushet yihun! abatey lemin? lemin?? be akal alawqwotm gin metshaftwon degagmey anbibealew hiwot honewgnal hulem eyedegagemku anebachewalew fetsimo yemiyaregagu yemiyatenekru nachew , fiqerwon abatnetwon lemayet ejig silemnafeq ctv coptic channel etebqwotalew getsiwo yimarkal,yaregagalm,ababa lemin lemin tilewn hadu? gena eko yasfelgunal, eeeee enbayen maqom alchalkum yemenfes abateyn ataw....amlake hoy ebakhn nefsachewn be qegnih anur..bereketachewn asadrben!! baba behiwot salew fetsimo fetsimo alresawotm,be akal bayawqugnim bemenfes yeeledugne lijwo negne tselotwo yitebqegne,bereketwo yiderbegne erswos yegenet mushira newot uuuuhhhhhhh hazenen min biye labkaw yihon amlake.................
ReplyDeleteende abat yemitebekbachewin sertew yalefu bemehonachew le'ersachew kedikam maref new. anuanuarachewinima endet endet endeneber enawkewalen michot, dilot sayfeligu lemiemenan ewnetegna eregna neberu yesachewin metsehafit yalanebebe sew yelem biye asibalehu endih new krstian kerasu alfo lelelaw yemiyabera.
ReplyDeleteየቅዱስነታቸው በረከት ይደርብን
በጣምና በጣም አሳዛኝ መርዶ ነው!!!! አምላካችን ሆይ ያለ እረኛ አትተወን!
ReplyDeleteበጣም አዝነናል። አባታችንን የሚተካ አባት ያድለን።
ReplyDeleteየአባታችን ነፍስ በገነት ያኑርልን፤ ነፍስ ይማር፡፡
ReplyDeleteNefisachewun yimarlin!
ReplyDeleteየጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን። ሥራ 21፤14
ReplyDeleteየዘመናችን ጳውሎስና አትናቴዎስ ከኛ መለየት የማያሳዝነው እውነተኛ ክርስቲያን ያለ አይመስለኝም፡፡
ሥራዎቻቸው ግን እንደ ሌሎቹ ቅዱሳን ሥራዎች ህያዋን ሆነው ሰዎችን ወደ ህይወት መንገድ ሲመሩ ይኖራሉ፡፡
አቤቱ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ በርቀት ያጽናኑንና ያበረቱን አባታችንን እንዲያርፉ ፈቃድህ ከሆነ ፤
የሳቸው እግር የሚከተሉትን አብዝተህ ትሰጠን ዘንድ ቅዱስ ፈቃድህ ይሁን፡፡
አሜን
ገብረሚካኤል ዘ እንዳሚቺአል
help help help
ReplyDeleteZiquala monastrey forest is under fire
the fire is hard to control b/c of wind with monks alone.
for more information call 0115545452 or 0920675349
Berketachew Yederben, Melekam Ergana
ReplyDeletenafes yemar nafesachwen begnat yanurelne
ReplyDeletenefisachewun be gent yanerln
ReplyDeleteersachewen teto yegnawen lemen aywesedelenem?
ReplyDeleteye abbatechin nefse Egziabiher amlakachin begenet yanurilin !! bereketachew be igna be lijochu yidaribin!!amen
ReplyDeleteEgziabiher Nefsachwen Begenet Yanurilin.....Telek Abate Bematatachen Ejege betam Aznenale...
ReplyDeleteK
Egziabiher Nefsachewen Begenet yanurilin....Legna le Orthodoxawian talake astaraki astemari meri abate atetenale. Bezi fetagne gize esachewen yemiakele talake talake abate matate ejege betam yasazenale....Bereketachew be egnal laye yiderriben ...Amen!!!
ReplyDeleteእንደእርስዎ ያለ አባት
ReplyDeleteበሚያስፈልግ ሰአት
ሁሉ አላምር በሎዎት
ሄዱ ወይ ወደሞት
እንግዲህ ምን ይባላል በቀኙ ያኑርዎት
EGZIO SELAME HABA LAGERKE LETSDKENI BET KIRSTIYAN:
ReplyDeleteAGRER TSERHA TAHIT EGERIHA EQEB HIZBA WE HAYMANOTA LE HAGERITNE ETHIOPIA:
orthodoxawiyan ebakacehun ke enkilfashehu niku!!!!!!!! are be emeberhan yesew yaleh!!!! gedamatochahen siqatelu zime blo be esatu yemimoke tiwled
‹‹…ዝም ብለን የእግዚአብሔርን ማዳን እንጠብቃለን… ፡፡››
ReplyDeleteእንደእርስዎ ያለ አባት
በሚያስፈልግ ሰአት
ሁሉ አላምር በሎዎት
ሄዱ ወይ ወደሞት
እንግዲህ ምን ይባላል በቀኙ ያኑርዎት
በጣም አዝነናል። አባታችንን የሚተካ አባት ያድለን።
Tadiya min enilalen?.....yefeterkawun yematitewu nigus liul Egziabiher hoy le kristiyanoch abat siten!....gin lemin?....Yelelawu sayihon Ye Ethiopianis ferawu...bicha Egziabiher yawukal!!!!!tselotachewu,bereketachewu ayileyan!
ReplyDeleteatefra lekereseteyanoch abat feter malet new
ReplyDeleteYE ABTACHIN BITSU WEKIDUS ABUNE SHINODA MOT BATAM YASAZNAL. EGZIABHER NEFSACHOWN BEGENET YASARF ! AMEN !!!
ReplyDeleteBEREKETACHEW AYLEYEN
ReplyDeleteንጋት /ወለተ ጊyorgis/
ReplyDeleteየብጹዕ ወቅዱስ አብነ ሺኖዳ ሞት አሳዛኝ ነው ::በመጻሕፍቶቻቸው የክርስትናን ብርሀን በውስጤ ያበሩ እረኛ አባት ነበሩ:: እርሳቸውስ ወደ ፊትም የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶላቸዋል:: እኛ ስለ ወደ ፊት እናልቅስ እርሳቸውን የሚተካ እረኛ አባት እግዚአብሔር እንዲሰጠን::
በአሁኑ ሰዓት ቤተክርስትያናችን ላይ እየደረሰ ያለውን ነገር ሳስበውና ፤ የአቡነ ሺኖዳን ሞት ስመለከት ፤ ውስጤ በጣም ፈራ ፈራ ፈራ ፈራ ...::
እንደእርስዎ ያለ አባት
በሚያስፈልግ ሰአት
ሁሉ አላምር በሎዎት
ሄዱ ወይ ወደሞት
እንግዲህ ምን ይባላል በቀኙ ያኑርዎ
የቅዱስነታቸው በረከት ይደርብን