(አንድ አድርገን የካቲት 28 ፤ 2004)፡- ከወራት በፊት ደብረ ዘይት በባቦጋያ አካባቢ የሚገኘው የመድሀኒአለም ቤተክርስትያን ታቦት ማደሪያ ቦታን ለባለሀብት መሸጡን አስመልክተን መጻፋችን ይታወቃል ፡፡በአካባቢው የሚገኙ ምዕመናን ጉዳዩን ለእግዚአብሔር ከእንባ ጋር ኣሳልፈው ከመስጠት ውጪ ምንም ማድረግ አልቻሉም ነበር ፤ ቦታው ከ10 ሺህ ካሬ በላይ ይገመታል ፤ ይህ ቦታ ቤተክርስትያኗም ሆነች በህገወጥ መንገድ የገዛው ባለሀብት ሁለቱም ለቦታው ካርታ ያቀረቡ ሲሆን ጉዳዩን በመንግስት ጣልቃ ገብነት ለመፍታት በሂደት ላይ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፡፡ ይህ እንዲህ እያለ የውስጥ ምንጭ እንደጠቆሙት ቦታውን ላለመመለስ ከፍተኛ አድልዎ ከላይ በሚመጡ አካላት እየተፈጸመ ነው ተብሏል ፤ ሰዎችንም የማስፈራራት ነገር ይታይበታል ፤ በተለያዩ ጊዜያትም ዛቻዎች እየደረሱ ይገኛሉ ፤ በዚህ ጉዳይ ያለፈው ሰኞ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ተመልክቶት ነበር ምን እንደተባለ መረጃው ለጊዜው አልደረሰንም ፡፡ ማክሰኞ በ27/06/2004 ዓ.ም በመድሀኒአለም ቀን ባቦጋያ የሚገኝው የቀድሞ ሪዞርት የከፍተኛ ባለሀብቶችና ባለስልጣናት መዝናኛ እና ማረፊያ ቤት በእሳት መቃጠሉን ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል ፡፡ እሳቱ በተነሳበት ሰዓት እሳቱን ለማጥፋት ባደረጉት አንቅስቃሴ ተጨማሪ ጥቂት ሰዎች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ይህ የማንቂ ደውል ሆኗችሁ የቤተክርስትያኗን ቦታ ብትመልሱ መልካም ነው እንላለን ፤ የምትጋፉትን የምትገዳደሩትን በመጀመሪያ እወቁት
፤ የመድሀኒዓለምን ቦታ ለተጨማሪ የሪዞርት መዝናኛ ለማዋል የሚደረገውን ጥረት እንቃወማለን ፤ ለነገይቱ ቤተክርስትያን የማይቆረቆሩ ጥቂት ሰዎች አማካኝነትና በመንግስት ባለስልጣናት ጋር ባለ የተለየ ግንኙነትን ይህ ህገወጥ ስራ ቢሰራም የመድሀኒአለምን የታቦት ማደሪያ ቦታ ወስዶ ሰላም ማግኝት አይታሰብም ፤ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የዚህ ሪዞርት VIP MEMBER መሆናቸውን ጠቅሶ የዛሬ ሁለት ዓመት በአሁኑ ሰዓት በመንግስት ተፅህኖ ፈጣሪነት ከገበያ ውጪ የሆነው ‹‹አዲስ ነገር›› ጋዜጣ ፀሀፊ መጻፉን እናስታውሳለን ፤ ይህን ጽሁፍ በተፃፈ በሳምንቱ ፀሀፊው ላይ ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት 22 አካባቢ የሚገኝው ቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል ለቀናት መተኛቱም ትውታችን ነው ፤ የሰማይ አምላክ ይወቀው እንጂ እኛ በዚህ ላይ ምንም መረጃ የለንም ፡፡ እኛ አቅሙ ኖሮን ተጋፍተን እና ተጋፍጠን ቦታውን ማስመለስ ባንችል እንኳ እሱ በተዓምሩ እየቀጣ ቦታውን እንደሚያስመል አንጠራጠርም ፤ ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ጉዳት በቦታው ላይ ደርሶ እንደማያውቅ ለማወቅ ችለናል ፤ አሁን በቦታው አማካኝነት እሰጣ ገባ ውስጥ ከገቡ በወራት እድሜ ውስጥ ይህ የእሳት ቃጠሎ አደጋ በሪዞርቱ ላይ ሊከሰት ችሏል ፤ ከወራት በፊት የአርሴማ ቅድስትን ቤተክርስተያን ያፈረሱ ሰዎች አንዱ ራሱን ሲያጠፋ አንዱ ደግሞ በድንገተኛ አደጋ ራሱን አጥቷል ፡፡ በአሁኑ ሰዓት መንግስት የዋልድባል ገዳም በሸንኮራ ልማት ሰበብ የገዳሙን ህልውና በሚጋፋ መልኩ ስራ እየሰራ ይገኛል ፤ ‹‹ቄሱም ዝም መጽሀፉም ዝም›› እንደሚባለው ፤ ቤተክህቱም ዝም ብሏል ፤ ምዕመኑም ዝም ብሏል ፤ እኛ ሀገሪቱ ውስጥ የምንኖር ምእመናን ከመነኮሳቱ ጎን ሳንፈራ እግዚአብሔርን መከታ አድርገን የምንቆመው መቼ ነው ? ከወደ አሜሪካ ያሉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በአሜሪካ የሚገኝው የኢትዮጵያ ኢምባሲ በራፍ ላይ በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ የደረሰን መረጃ ያመለክታል ፡፡
‹‹መድሀኒዓለም ቤቱን ይጠብቅ››
ከመድኃኒዓለም ጋር እንደሚጋፉ ይወቁት! በሆሳዕና አካባቢ በሶሮ ወረዳ በበዕናራ ቀበሌ መድኃኒዓለም ድንበሩን እራሱ በእሳት እንዳስከበረ ንገሩዋቸው፡፡ ማንም ይሁን ማን ህይወታቸው ሳይጠፋ መድኃኒዓለምን መጋፋት ቢያቆሙ ይሻላቸዋል፡፡
ReplyDeleteአብነት ከሆሳዕና
Antewu lebetih tamgn neh geta hoy kebetihm kelijochih gar yemitalu hulu yejachewun yikebalalu Bewunat E/r kin amlak neh kutah yizegayal inji aykerim yerahelin enba yabesk amlak yegnanim enbachinin abislin amen!!!
ReplyDeletefered kegziabeher new serawenem eyesera new
ReplyDeleteስለ ዋልድባ ስላሳወቃችሁን እግዚአብሔ ይስጥልን፡፡ እኛ ኃይላችን እግዚአብሔር ነው ከቤታችን ወጥተን ገድለን ወይም በጉልበታችን ተመክተን ሳይሆን በደማችን እንዋጋለን እግዚአብሔር ይኽን ቦታ ይጠብቀዋል እንታመናለን!! ቤታችን ቁጭ ብለን ዝም ብለን አናይም ይኽን የሰሙ ህፃናት እንኳን ምን እደተሰማቸው መንግሥት የሚያይበት ጊዜ ቢኖረው መልካም ነበር እንኳን ስለ ዋልድባ ስለ ቤተክርስቲያኖቻችን ለሰከንድ አናርፍም አምላካችን እንደ ዓይን ብሌን እንደሚጠብቀን እናስተውላለን ክብር ምስጋና ይግባው እኛን እንደ ሐጢያታችን ቸል ያላለን፡፡
ReplyDeleteBETOLO MERETON BETEW YESHALAL BMEGEBA YKETACHEWAL.
ReplyDelete