Thursday, March 1, 2012

የአሰቦት ገዳም እሳት


(አንድ አድርገን የካቲት 22 ፤ 2004ዓ.ም)፡-በአሰቦት ገዳም የተነሳው እሳት ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል ፤ በገዳሙ ላይ ምንም አይነት ጉዳት(ከደን ቃጠሎ ውጪ) እንዳላደረሰ ለማወቅ ችለናል ፤ ባለፉት ሁለት ቀናት በከፍተኛ ሁኔታ ለመቆጣጠር ያስቸገረ ቢሆንም ከአሰበ ተፈሪ ድረስ ህዝበ ክርስትያን በመረባረብ  በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ፤ ቦታው ላይ ያለን ሰው በስልክ ደውለን ማነጋገር የቻልን ሲሆን እሳቱ ወደ ገዳሙ እንዳይመጣ ሰዎች የማጥፋት ጥረቱን እያከናወኑ ይገኛል ፤ ይህ ሊሆን የቻለው ከወደታች አካባቢ ደርቀው የወደቁ ብዙ ዛፎች መኖራቸው እንደምክንያት ተቀምጧል ፤ እንደ ዋና ምክንያት ግን በአካባቢው ላይ ገዳሙን ከበውት የሚገኙ ሙስሊም ማህበረሰቦች ናቸው የሚል ግምት አለ፡፡ ለማንኛውም እግዚአብሔር ይመስገን ለክፉ የሚሰጥ አደጋ አለመሆኑን ለማወቅ ችለናል ፤ የተሻለ መረጃ ተከታትለን እናቀርብሎታለን ፤

5 comments:

  1. አቤቱ ምህረትህ የበዛ ቁጣህ የዘገየ ቸርና ኃያል ንጉስ እግዚአብሔር ሆይ እንደ እኛ ኃጢያት ሳይሆን ስለ ቅዱሳን አባቶቻችን ብለህ በዱር በበረሀ ላንተ ብለው ስለወደቁት ብለህ፣ ለስምህ ስለተፈጩት ስለተደቆሱት ብለህ ይህችን የተቀደሰች የተመረጠች ኃይማኖታችንን ጠብቃት አሜን እኛንም ከሁሉ ነገር ጠብቀን አሜን አሜን

    ReplyDelete
  2. chere zena yaseman

    ReplyDelete
  3. amen melkamun yaseman

    ReplyDelete