Wednesday, March 7, 2012

የዋልድባ ገዳም ህልውናና የገጠመው ፈተና የVOA ዘገባ




‹‹እናንተ ደፋሮች ይህን ጉዳይ ብላችሁ የአንድን ሀገር መሪ ልታናግሩ መጣችሁ ›› ለዋልድባ ገዳም መነኮሳት 4ኪሎ ቤተመንግስት የተሰጠ ምላሽ ፤ እዚህኛው ቃለ ምልልስ ላይ ያገኙታል ያድምጡት ፡፡ እኔ በበኩሌ በዚህ ጉዳይ በጣም ተናድጃለሁ የእርስዎን አላውቅም ፤ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ግራ አጋብተው ነው የላኳቸው ፤ ይህን ከጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ይመለሳል ብለን አንጠብቅም ፤ ብቻ የቢተክርስትያ ጠባቂ አይተኛም ፤ እርሱ አያንቀላፋም ፤ 

2 comments:

  1. ቤተክርስቲያን ስለሁሉ ሰላም ስለፀለየች ክፉወች በእርሷ ላይ ተነሳሱባት ፤ ክብሯን ሲገፉባት ፡ አጥሯን ሲወዘውዙባት ፡ ክዳኗን ሲያነሱባት ክርስቶስ ይናገር ዘንድ እሷ ዝም ማለቷን ቢያዩ ይበልጥ ተበረታቱባት ፤ ስለክርስቶስ ሁሉን በማክበሯ ፡ ክፉ መሪ ደግ መሪ ሳትል ፡ መልካም ሰው ክፉ ሰው ሳትል ስለሁሉ በመፀለየዋ ፡ ስለሁሉ ምህረትን በማድረጓ ፡ ክፉወች ይቅር ባይነቷን ፡ ትእግስቷን መጠቀሚያ አደረጉት ፡ ሁሉ ተነሳሱባት ፡ የወላድ መካን እንደሆነች ፡ ጥቃቷን የሚመክትላት ልጅ እንደሌላት ሁሉ በሷ ላይ ተነሱ ፤ ልጆቿ ሁሉ አድር ባዮች መሰሉ ፡ ለሆዳቸው የሚጋደሉ ፡ ለስጋቸው የሚጨነቁ የመንፈስ ባይተዋሮች መሰሉ ፡ ስለዚህም ክፉወች ፡ የምድር ፈራጆች ፡ ጠላቶች የድፍረት እጃቸውን አነሱባት ፤ ይበልጥም በገዳም ያሉ አባቶቻችን ረሃብ ጥሙን ቻሉ ፡ የስጋ ስሜትን ቻሉ ፡ የአራዊትን ክፋት ቻሉ ፡ ሙቀት ቁሩን ቻሉ ፡ የሰይጣንን ተንኮል ቻሉ ፡ ሁሉን ቻሉ ፡ ሁሉን ስለክርስቶስ በክርስቶስ ቻሉ ፡ የቤተክርስቲያንን ነገር ግን እንደምን ይችላሉ? ስለክርስቶስ ሲሉ በዱር በገደል አለም እንዳልተገባቸው ተቅበዘበዙ ፡ አብዝቶ ስለመፆም ፡ ሳያቁርጡ ስለመፀለይ ፡ ለምስጋና ስለመቆም ፡ ደክመው ከስተው ባዩአቸው ጊዜ ገፍተው ይጥሏቸው ዘንድ ተነሳሱ ፤ መንፈሳውያን ናቸውና ጋሻና ጦር ፡ ወጥመድና ቀስት እንደሌላቸው ባዩ ጊዜ ክብራቸውን ያሳጧቸው ዘንድ ተበረታቱባቸው፡፡ ገዳማውያን አባቶቻችን ግን ምን አድረጉ ዘወትር ስለኢትዮጵያ ስለፀለዩ? ስለሃገር መሪው ፡ ስለወታደሩ ፡ ስለሁሉ ቀን ሳያስታጉሉ በባዶ ሆዳቸው ስለለመኑ? ደመወዝ ክፈሉን አላሉ ፡ ግለጡን ስበኩን አስተዋውቁን አላሉ ፡ ቤታችሁ ወስዳችሁ መግቡን አላሉ ፡ ምን አደረጉና ይናቁ? ምን አደረጉና ከቤታቸው ይባረሩ? ምን አደረጉና ትምክህታቸው ትፍረስ? ምን አድረጉና የአባቶቻቸው ክብር ይነካ? ጌታችን መድሃኒታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በሁሉ መገፋታችንን አስብ፡፡ ክርስቶስ ሆይ አባቶቻችን እንዳስተማሩን አንተ ትናገር ዘንድ እኛ ዝም ብለናልና ትእግስታችንን አፅናልን ፡ የቤተክርስቲያንንም ለቅሶ ሰምተህ ቸል አትበል፡፡ አሜን፡፡

    ReplyDelete
  2. i am unable to get any voice, can you help me?

    ReplyDelete