(አንድ አድረገን መጋቢት 12 2004ዓ.ም)፡- ትላንትና ከጠዋት ጀምሮ ሰዎች ወደ ዝቋላ እሳቱን ለማጥፋት እንዲሄዱ የበኩላችንን የቻልነውን ያህል መረጃ በመስጠት ስራ ስንሰራ ነበር ፤ ጠዋት ላይ ከመንፈሳዊ ማህበራት አንዱ ‹‹ደጆችሽ አይዘጉ›› መንፈሳዊ ማህበር ፍቃደኛ የሆኑ ሰዎች አብረዋቸው እንዲሄዱ ሰዎችን እድናነሳሳ መረጃ ደርሶን ነበር ፤ እኛም መስቀል አደባባይ ተገኝተን ሰዎች በምን አይነት ሁኔታ ግንኙነት ፈጥረው መሄድ እንደሚችሉ መረጃ አግኝተን ነበር ፤ መኪና የሚሄድ እደተዘጋጀ ሰዎች እስከ 8፡00 ሰዓት አብረው መሄድ እንደሚችሉ ፤ ለበለጠ መረጃ ደግሞ ለግንኙነት የ3 አባላትን ስልክ አግኝተን ነበር፡፡ በጊዜው ዳቦ በዝቋላ ላሉ ሰዎች ዳቦ መግዣ ይሆን ዘንድ ሰዎች በአካል በመገኝት ብር እና ዳቦ ሲሰጧቸው ተመልክተናል፡፡ በጣም በርቀት የሚገኙ ሰዎች ለዚች ቀን ብቻ ብር መላክ ከፈለጉ ብለን የማህበሩን የባንክ አካውንት አስቀምጠናል ፤ ይህ ማህበር ደግሞ ወፍ ዘራሽ አይደለም ፤ ለቤተክርስትያን የሚሰራ መንፈሳዊ ማህበር መሆኑን ሰዎች የሚያውቁ ይመስለናል ፤ ይህ ማለት ጊዜያዊ መፍትሄ ለመሻት እንጂ ቋሚ ዝቋላ ገዳሙ ያቋቋመው አይደለም ፤ እሳቱን ለማጥፋት በማህበር መልክ ሲንቀሳቀሱ ተመለከትን ፤ መልካም መሆኑን ተገንዝበን ከእነሱ ጋር ግንኙነት ፈጥረን ሰውን ማንቀሳቀስ ችለናል ፡፡ አሁን ግን ያለው ሁኔታ ጥሩ ስለሆነ ሰዎች በአካውንቶቹ እንዳይጠቀሙ እናሳስባለን፡፡ ዝቋላ ገዳሙ ኦፊሺያል የሆነ ይህን የጠፋውን ደን መልሶ ለማልማት ኮሚቴ ካቋቋመ ከእነሱ ጋር ግንኙነት በመፍጠር ምዕመኑ ሀላፊነቱን እንዲወጣ መልዕክት እናስተላልፋለን፡፡
የዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን ገዳም ለዘለቄታው በእሳት በማይጠቃበት መልኩ ማቋቋም ይገባናል፡፡ ገዳሙ በመከላከሉ ሥራ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እና የአካባቢ ጉዳት ደርሶበታል፡፡ እነሆ ገዳሙን መርዳት የምትፈልጉ ምእመናን የገዳሙ የባንክ አድራሻ የሚከተለው ነው፡፡
ለዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ደብረ ዘይት ቅርንጫፍ
የባንክ ቁጥር 19789
ደብረ ዘይት
What ever the reason to protect the Church and its suroundings, Your effort is very appreciable. You took the assignment of the government to protect the natural resources and ensure enviromental protection activities. I do appreciate you irrispective to my relegious background. I can't say more than this but I have to express my gratitude for those coordinators. May God Bless You!
ReplyDeleteTebareku ande adergenoch!!!! I have been looking for a legit bank account to send money to be used only for this disaster... keep the good work going!!!!
ReplyDelete