ተጨማሪ ፎቶዎች
(የአንድ ሰው አስተያየት)
እናንተ የተዋህዶ የቁርጥ ቀን ልጆች...ፎቶአችሁን በፍቅርና በስስት ሀዘን በሰበረው ልቤ...እንባን በተሞሉ አይኖቼ ደግሜ ደጋግሜ ቅድምም አሁንም ቆይቼም ደግሞ እንደ አዲስ አያቸዋለሁ:: የሆነብን ሁሉ ልብን የሚያደማ ቢሆንም ግን ደግሞ ያደረጋችሁት ጊዜ የማይሽረውና ትውልድ የማይዘነጋው በመልከሙ ተጋድሎአችሁ ኮራሁ ለካስ ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋ ተወልደው አልቀሩም...ለካስ አድገውላታል....ለካስ እንደ ቀደሙት አበው ስለ እርስዋ ዛሬም ለእሳት የተዘጋጁ ልጆች አሉዋት!!!...ብዬ...ኩራቴና ትምክህቴ ትክክል ሆኖ አገኜሁትና....ልቤና አይኔ በሲቃ አብረው አነቡ...ፍቅራችሁ ማረከኝ....በሩቅም ሁኜ ናፈቅሁዋችሁ...ኩራታችን...መጽናኛወቻችን ናችሁና ኑሩሉን...እናንተም የኔ እኔም የእናንተ በመሆኔ...በወገኔ ምንኛ...ኮራሁ!!!....ግን ደግሞ ቀናሁባችሁ...አምላክ ከክፉ ይጠብቃችሁ...ተባረኩ...ሌላማ ምን ይባላል...?...!!!...ተመስገን...!!!
ቤተ ክርስቲያን የወላድ መካን አለመሆኗን ያረጋገጥንበት ወንድሞችና እህቶች በሁሉ የስራ ሁኔታና ደረጃ ያሉ ማህበረ ምዕመናን ወምዕመናት በእውነት ያኮራል፡፡ ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ፤ እነዚህን ብታደርጉ ከቶ አትሰናከሉምና። እንዲሁ ወደ ዘላለሙ ወደ ጌታችንና መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት መግባት በሙላት ይሰጣችኋልና። ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም። ሁልጊዜም በዚህ ማደሪያ ሳለሁ በማሳሰቤ ላነቃችሁ የሚገባኝ ይመስለኛል። 2ጴጥ.1፡10-13
የገዳማውያኑ አባቶች ምስጋና
‹‹ለቦታው ተቆርቋሪ ከሆነው ወገን የቀረ ሰው የለም፡፡ የዩኒቨርስቲ ተማሪው፣ የከተማው ወጣት፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ ፖሊሱ፣ መከላከያው በአጠቃላይ ሕዝበ ክርስቲያኑ እዚሁ ነው ያለው፡፡ በተለይ ወጣቱ ለቦታው ታላቅ ባለውለታ ነው፡፡ ሃይላንዳቸውን ብቻ ይዘው ተራራውን ወጥተው ከዚህ መድረሳቸው ብቻ ለእኛ አለኝታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሐሳባቸውን ያስፈጽምላቸው፡፡ ውለታቸው በሰው ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ቦታውን ታድገውታል፡፡››
እኛ እንሙት በደጅሽ
ላዩ ታቹ ተናዶ
የቆመውም ተንጋዶ
እሳት በእሳት ሲደራረብ
በነፋሱ ሲርገበገብ
ያንች ልጆች አርበኞቹ
የቁርጥ ቀን ደራሾቹ
ተመሙልሽ ከያሉበት
ጠላትሽን ለመመከት
ተዋሕዶ
ክፉውሽን ከሚያሳየን
ለመከራሽ ከሚያቆየን
እኛ እንሙት በደጅሽ
ያሳደግሽን ልጆችሽ
ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን
/መታሰቢያነቱ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት ገዳም እሳት በማጥፋት ተግባር ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች/
እግዚአብሔር ይባርካችሁ በጣም ታኮራላችሁ
ReplyDeleteአምላክ ያክብርልን
ReplyDeleteአምላክ ያክብርልን
ReplyDeleteEgziabhere Yibarkachu!
ReplyDeleteThanks for updating us always.
ReplyDeleteEgziabher Dikamachihun yikuterlachihu
ReplyDeleteሀገራችንን እግዚአብሄር ለዘላለም ይባርክ፡፡ እግዚያብሄር ይባርካችሁ
ReplyDeleteThis comment has been removed by the author.
ReplyDeleteWud yekurt ken lijoch
ReplyDeleteAbet and mehon endet des yilal. Hagerachin yan hulu mekera yalefechiw lijochua and honew yemetawin hulu silemeketut new. Mengist bekuankua ena bezer yekefafele bimeslewim endih yale chigir, hazen, simeta wede andinet yimelesal lenegeru kegize hehuala yemetabin tata silehone gena wustachinim altewahadenim. Yekidusan Amlak bezihch eminetachin ena hagerachin lay and yadirgen.
እግዚአብሔር ይባርካችሁ በጣም ታኮራላችሁ::አቡዬ ለችግራችሁ ይድረሱላችሁ
ReplyDeleteእግዚያብሒር ፍጻሚያችውን ያሳምርልን ጉልነታችውን ይባርክ
ReplyDeleteEgziabher kekfu hulu yitebkachu. ke tsadiku bereket yikfelachu! behayimanot yatsnalin! photowachun bayehuna basebkuwachu kutr befikr bedsta aleksalehu.
ReplyDeleteበመጀመሪያ እግዚአብሔር ክብሩ ይስፋ ይህንን ትልቅ የእምነትና የታሪክ ቦታ ስለጠበቀልን፡፡ በመቀጠል እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነው ቦታ ገብተው ለመታደግ የታገሉትን ወጣቶች እድሜ፣ ጤና ፍቅር ይስጥልን፡፡
Deleteበመጀመሪያ እግዚአብሔር ክብሩ ይስፋ ይህንን ትልቅ የእምነትና የታሪክ ቦታ ስለጠበቀልን፡፡ በመቀጠል እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነው ቦታ ገብተው ለመታደግ የታገሉትን ወጣቶች እድሜ፣ ጤና ፍቅር ይስጥልን፡፡
DeleteAmlake Kidusan wagachihun yikfelachihu YEBETEKIRISTIAN YEKURT KEN LIJOCH.
ReplyDeletegeta hoy silekidusan bileh yikir belen. igziabher yibarkachihu
ReplyDeletemelkam sira keminim Yibeltal, bertu
ReplyDeleteበታም የሚያኮራ ግደል ነው የሰራቸሁት ፃድቁ አቡዬ በዘመናቹ ሁሉ የልባችሁን መሻት ይፈፅሙላችሁ! ! !!.
ReplyDelete