Wednesday, March 28, 2012

ሌላ ቀውስ

(አንድ አድርገን መጋቢት 20 2004ዓ.ም)፡- በተለያዩ ጊዜያት በመንግስት አማካኝነት በሰፈራ ፕሮግራም በተለያዩ ቦታዎች ተነስተው ወደ ተለያዩ ክልሎች በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በ1993 ፤ 1995 እና በ1997 ዓ.ም መስፈራቸው ይታወቃል ፤ ዛሬ ጠዋት በቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ከ3 መኪና ያላነሱ ሰዎች ከነ ሙሉ ቤተሰቦቻቸው የሚዛን ተፈሪ ፤ቤንች ማጂ እና ሸካ ዞኖች አካባቢ የሚገኙ ባለስልጣናት ተባረው ለመንግስት አቤት ለማለት መሬት ላይ ወድቀው ይገኛሉ ፤ በጣም ህጻናት ፤ ወጣቶች ፤ አሮጊቶች ሽማግሌዎች ይገኙበታል ፤ አካባቢው ላይ የሰፈሩት  ዜጎች አብዛኞቹ ከአማራ ክልል የመጡ እና ቦታው ላይ መሬት ተሰቷቸው ኑሯቸውን በግብርና ላይ የሚመሩ መሆኑን ለማወቅ ችለናል፤ አቤቱታቸውን ለመንግስት ለማሰማት መንገድ ያደሩ 4 መኪና አውቶቡሶች እዳሉም ለማወቅ ችለናል ፤ እነዚህ ሰዎች በአሁኑ ሰዓት ማደሪያም ሆነ መጠለያ ሳይኖራቸው በሜዳ ላይ 4 ኪሎ ስላሴ በር ላይ ተበትነው ይገኛሉ ፤ ጥያቄያቸውንም በተወካዮቻቸው አማካኝነት  ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡   ሰው በሀገሩ እንደ ዜጋ ተከብሮ መኖር ካቃተው ሌላ ምን ተስፋ ሊኖረው ይችላል? እኛ እንደ ክርስትያን እንደ ወገን እነዚህን ሰዎች ምግብ ብናቀርብላቸው ምን ይመስላችኋል? ከመንግስት መልስ ካላገኙ እነዚህ ዜጎች አቅራቢያ የሚገኝው ስላስ ቤተክርስትያን ነው የምንገባው ብለዋል ፤ ከቤተክርስትያን ውጪ መሸሻ የት ሊገኝ ?



(4፡00 ሰዓት )በአሁኑ ሰዓት ከቦታው እንደደረሰን የአይን እማኞች መረጃ መሰረት መንግስት መኪና አቅርቦ ሁሉንም የመጡትን ሰዎች ከቦታው ላይ አንስቷቸዋል ፤ ወደ የት ይሂዱ አላወቅንም ፤ የመገናኛ ብዙሀን በዚህ ዙሪያ ምን እንደሚሉ ወደፊት የምንሰማው ይሆናል ፤ ስላሴ ቤተክርስትያን ደጃፍ አሁን ቢመጡ ምንም ያልተፈጠረ ያህል ረጭ ብሏል፤ 

በቀኑ ቤተክርስትያኒቱን ለማረፊያነት ጠይቀው ቢሆንም አስተዳደሩ ግን ሊፈቅድላቸው አልወደደም

15 comments:

  1. yigermal gudna jirat kewodehala new

    ReplyDelete
  2. በአሁኑ ወቅት እየተካሄደ ያለው ነገር ግራ የሚያጋባ ነው፣ለጊዜው እነዚህን ወገኖቻችንን ከጎናችሁ ነን እንበላቸው፡፡ እኔኮ ግራ የሚገባኝ ብዙ የሀገራችን ዜጎች በሌሎች ሀገሮች የሀገሮቹን ህግ እስካከበሩ ድርስ እየኖሩ ነው፣ ኢትዮጵያዊ ባይሆኑ እንካ ግብር ከከፈሉ እና የሀገሪቱን ህግ ካከበሩ በሰባዊነታቸው መኖር አለባቸው ብየነው የማስበው፡፡ ምናልባት መጣራት ያለበት ጉዳይ አነዚህ ተፈናቃዮች ሰው መሆናቸውን ማረጋገጥ አለብን ምክንያቱም ለሰው ልጅ ሊሰጥ የሚገባው ነገር ለነሱ ብቻ ሊከለከል አይችልም፡፡

    ReplyDelete
  3. sewchun barefubet bota migib ena lilochinim asfelagi negerochin enamoalalchew:: keresitinachin lifeten meselegn

    ReplyDelete
  4. እኛ እንደ ክርስትያን እንደ ወገን እነዚህን ሰዎች ምግብ ብናቀርብላቸው ምን ይመስላችኋል? ክርስቲያን ስለሆኑ ሳይሆን የሰው ልጅ በመሆናቸው ብቻ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡

    ReplyDelete
  5. what about yesterday's assembly in gonder???

    ReplyDelete
  6. እኛ እንደ ክርስትያን እንደ ወገን እነዚህን ሰዎች ምግብ ብናቀርብላቸው ምን ይመስላችኋል? ክርስቲያን ስለሆኑ ሳይሆን የሰው ልጅ በመሆናቸው ብቻ ልናደርግላቸው ይገባል፡፡

    ReplyDelete
  7. we need information about them

    ReplyDelete
  8. The contribution should be in kind not in money...otherwise, the famous corruption,,,,

    ReplyDelete
  9. ተዘከረኒ እግዚኦ አምላክ አበዊነ!!!አቤቱ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ አንተ አስበን፣በሀገሪቱ ምን እየሆነ እንዳለ ማሰብ ራሱ እያስጨነቀኝ ነው። እባካችሁ አንድ አድርገኖች የደረሱበትን ማወቅ ከቻላችሁ በአቅማችን እንርዳቸው ጠቁሙን...አምላክ አገልግሎታችሁን ይባርክ!

    ReplyDelete
  10. 1. ተቃዋሚዎችም መንግስታትም፤
    የሚሰብኩልኝ ሁለቱም፤
    የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰማህ፤
    ዕያየህ ነው ባይንህ፤
    ሲረጋገጥ መብትህ፡፡
    2.የዘመኑ ግዳይ ግራ ቢያጋባችሁ፤
    አንዳችሁ ካንዳችሁ አድማ እገባችሁ፤
    ያን የጥንት ዘመን እያማረራችሁ፤
    ላማረ አላማረ ምን አበሳጫችሁ፡፡

    ReplyDelete
  11. Thanks Andadirgen for nice updates. Be wise and try to always get Video footages for evidence if possible, ask every Orthodox to be brave and at least keep some footages of the event by Mobile phones or what ever they have. Later people can upload it to some safe websites. It is always about evidence.

    I remember a recent incident at Asebot. A child (only 7) was killed there and he was buried quickly. I don't know if we have a footage or a photograph of this kid. It could have been good evidence.

    Amilak menakachinin asib.

    ReplyDelete
  12. ay and adrgenoch???
    a little truth, many doubt on u????

    ReplyDelete
  13. Hagerachin yeminlew meche yihon???

    ReplyDelete
  14. Hagerachin yemnilew meche yihon???

    ReplyDelete