Monday, March 26, 2012

ገና እንጮሀለን


(አንድ አድርገን መጋቢት 16 2004 .):- የዋልድባ ገዳም ጉዳይ መልስ እስከሚያገኝ ድረስ እንጮሀለን ሰሚ ባናገኝም እንደገና እንጮሀለን ባለስልጣኖቻችንም ባይሰሙን ጆሮም ባይሰጡን እንጮሀለን ከሰው ዘንድ መልስ ባናገኝ ወደ ላይ እንጮሀለን እግዚአብሔር መልስ እንደሚሰጠን አንጠራጠርም ባለፈው ቅዳሜ 14/07/2004 . ማታ 3 ሰዓት የአሜሪካ ድምጽ ላይ ስለ ገዳሙ አባቶችን አነጋግሮ ነበር። በፊት የመንግስት መልስ «ቦታው ላይ አልደረስኩም አላረስኩም» የሚል ነበር አባቶችም «እንዴት እንደዚህ ትላላችሁ ያረሳችሁትን ቦታ እና እናሳያችሁ» ቢሏቸው አይናችንን ግንባር ያድርገው አላረስንም አሉ  

ቀጥሎም በስኳር ሚኒስቴር ሀላፊው አማካኝነት የሚነሱ መቃብሮች እንዳሉ በራሳቸው አንደበት አመኑ የተነሱትንም መቃብሮች በማን አለብኝነት አንስተው የትም ጥለው ካበቁ በኋላ «በአባቶች ተባርኮ ሌላ ቦታ ላይ አርፈዋል ከአሁን በኋላም የሚነሱት መቃብሮች ቦታ ተለዋጭ ቦታ እንደሚሰጣቸው እና ቦታ ቀይሮ እንደሚያሳርፋቸው ተናገሩ» እዚህ ላይ ደግሞ ‹‹ የተነሳው አጽም የቅዱሳን አባቶች አይደለም» አሉ የሚያርሰው ዶዘር እኮ የእግዜር ጣት አይደለም እየለየ የሚፈነቅለው እሳቸው እንዲህ ሲሉ የቤተክህነቱ ሰው ደግሞ «ልማቱ ከገዳሙ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም ከገዳሙ እና ከፕሮጀክቱ መካከል የስድስት ሰዓት መንገድ አለ» ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ጋዜጣዊ መግለጫ ለኢቲቪ እና መሰል ልማታዊ ሚዲያዎች ሲናገር ሰማን በሐሙሱ መግለጫም «ምን ያህል ቤተክርስትያናት እንደሚፈርሱ አይታወቅም» በማለት ሪፖርተር ጋዜጣ የቤተክህነቱን የመግለጫ ቃል መሰረት በማድረግ ያለውን እውነታ አወጣ የወልቃይት አስተዳዳሪም 8 ቀበሌዎች ይነሳሉ 8,000 አባወራ በጠቅላላ 20 የሚደርሱ ሰዎች ከቦታ ይነሳሉ የሚነሳው ቤተክርስትያን የዋልድባ ገዳም አይደለም ብለውናል 27 መቃብሮችን ማንሳታቸውንም ጨምረው አምነዋል ቤተክርስትያናቱን ለማፍረስ ከሲኖዶስ ተነጋግረው ቀጣይ የሚሆን ነገር ነው እንጂ አሁን ምንም የተነሳ የለም ብለዋል ከእነዚህ አባወራዎች ጋር ጤና ተቋማትና ትምህርት ቤቶች ይነሳሉ ከእነርሱ ጋር ቤተክርስትያንም ሊነሳ ይችላሉ ብለው በቪኦኤ በግልጽ ተናግረዋል የአካባቢው ባለስልጣናት 8 ቀበሌዎች ውስጥ ያሉትን እንደሚያነሱ ቢናገሩም ሪፖርተር ጋዜጣ ግን ‹‹እስከ 11 ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት ውስጥ የሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት ሊፈርሱ ይችላሉ›› ሲልም ጽፏል 

እኛም ቤተክርስትያን እስከ አሁን ፈረሰ አላንም ነገር ግን ይህን ስኳር ልማት ተከትሎ ቤተክርስያናት ሊፈርሱ ይችላሉ የሚል አይኑን አፍጥጦ የሚመጣ ስጋት አለን ፤ የቤተክህነት ሰዎች ‹‹ምን ያህል ቤተክርስትያን እንደሚፈርሱ አናውቅም» ማለት ምን ማለት ነው? ቀድሞውንም ቢሆን አብያተ ክርስትያናት እንደሚፈርሱ አውቀው እና ተስማምተው ነው ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት ማለት ነው? ሪፖርተር ጋዜጣ እንደጻፈው ከሆነ 18 ቤተክርስትያኖች ዙሪያ የሚገኙት ነዋሪዎች ለመነሳት ተስማምተዋል የስኳር ልማቱም 76 ኪሎ ሜትር ቦታን እንደሚያካልል ገልጿል በዚያ ዙሪያ ያሉት ቤተክርስትያኖች እጣቸው መፍረስ እና ተለዋጭ ቦታ እንደሚሰጣቸውም ጠቆም አድርጎ አልፏል ይህንም የቤተክነት ሰዎች ተስማምተውበት «ምን ያህል ቤተክርስትያናት እንደሚፈርሱ አይታወቅም » የሚል በደፈናው ነገን የሚጠቁም ነገር ተናግረዋል። 76 ኪሎሜትር ውስጥ 18 ቤተክርስትያናት እንዳሉ ለማወቅ ችለናል በመቃብር ያሉትን የማንሳት ስራ እየሰሩ መሆኑን ሰምተናል ቀጣይ ደግሞ የነዋሪዎቹ እጣ ይሆናል ቀጥሎ ደግሞ ነዋሪ በቦታው ላይ ሳይኖር ቄስና ዲያቆን የቤተክርስትያን አገልጋዮች ምን ትሰራላችሁ ብለው ቤተክርስትያናትን ማፍረስ ይጀምራሉ። 

አሁን ደግሞ ቆይተን ስንሰማ በፊት ጉዳዩን ይዘው አዲስ አበባ ቤተመንግስት እና ጠቅላይ ቤተክህነት ድረስ የመጡት አባት «ገዳሙ አልወከላቸውም እንዲያው ከመርካቶ ቆብ ገዝተው ያደረጉ ናቸው » አሉን ጉዳዩን ማንም ያምጣው ማን አሁን ግን እየተደረገ ያለ ነገር ስለሆነ አምጭው እኛን አይገደንም ይህ ደግሞ ምዕመኑን ነገሩን ለማስረሳት እና ሌላ አጀንዳ ለመክፈት ሆን ተብሎ የተሰራ ስራ ነው እሳቸውም ለዚህ መልስ ሲሰጡ «እኔ መነኩሴ ነኝ እኔን ያመነኮሱኝ አበመኔት በዋልድባ ይገኛሉ መጥታችሁ ማረጋገጥ ትችላላችሁ» ብለዋቸዋል ይህ ነገርም በሌላ የገዳሙ ትልቅ አባት ተመስክሮላቸዋል «ገዳሙ ውክልና ባይሰጠኝም እንደ አንድ የቤተክርስትያን ልጅ ጉዳዩ ይመለከተኛል ያገባኛል» ብለው አፋቸውን አስይዘዋቸዋል።

የቤተክርስትያን ጉዳይና ገዳማችን ላይ እየተከሰተ ያለው ነገር የመነኮሳት ብቻ አድርጎ ያሰበው ማነው ? ይህ ገዳም እኮ የህዝበ ክርስትያን ሁሉ ነው ለሚጠየቁት ጥያቄ መልስ መስጠት ሲሳናቸው ነገሮች መንገዳቸውን ለመቀየር የሚያደርጉትን ነገር ፈጽመን እንቃወማለን፡፡ እኛ እያወራን ያለነው ስለ ዳግማዊ እየሩሳሌም ዋልድባ ገዳም ሲሆን እነሱ እያወሩን ያሉት ደግሞ ስለ ውክልና በጣም ይገርማል። አካሄዳቸው ገብቶናል «አንድ ሰው በገዳሙ ተወክሎ የውክልና ወረቀት እስካልያዘ ድረስ ከፍተኛ የመንግስት አካላት ጋር ሄዶ ጥያቄም ሆነ አቤቱታ ማቅረብ አይችልም» ለማለት ነው እኛ ይህን እናውቃለን ፍርድ ቤት ይህን ነገር ብቻ መሰረት አድረገው ቢከሷቸው የተቀመጠው ህግ እንደማይረዳቸውም እናውቃለን አንድ መነኩሴ ከገዳሙ ቢወከልም ባይወከልም ገዳሙ እየፈረሰ ተመልክቶ ስላልተወከልኩኝ አያገባኝም የሚል አይመስለንም  
አሁን እያደረጉ ያሉት ነገር ደግሞ አቅጣጫ ማስቀየር ላይ አተኩረዋል ስለ ገዳሙ ህልውና ስናወራ እነሱ ደግሞ ስለ አባቶች ውክልና ያወሩልናል ዋልድባ ገዳም ውስጥ ያሉትን አንደርስባቸውም ይሉናል እነርሱ የፈለጉት የጉዳዩንም አቅጣጫ ለማዞር ነው ይህ ጉዳይ ፖለቲካ አይደለም ይህ ጉዳይ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋርም የሚያያዝ አይደለም በዚህ ጉዳይ ማንም የፖለቲካ ጥቅም ለማግኝት የሚንቀሳቀስ አካልም የለም ማንም የተቃዋሚ አባል ዋልድባ ገዳም ገባ ሲባል ሰምተን አናውቅም ከዋልድባ ሊነሳ የሚችለው የእምነት ጥያቄ እንጂ የፖለቲካ ጥያቄ አይደለም መመንኮስ ማለት መሞት ማለት ነው ታዲያ ትርጓሜው እንዲህ ከሆነ የፖለቲካ ስልጣን አባቶቻችን ለምናቸው ነው የሚፈልጉት? ዓለምን ንቀው ነው ገዳም የገቡት ይህ ስለ አንዲት ቤተክርስትያን እና ስለ አንዲት እምነታችን ብለን የማናነሳው ጥያቄ ነው ሙስሊም ወንድሞቻችንን «መጅሊስ ይወገድ» የሚል ጥያቄ መጠየቃቸው ጉዳዩንም በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር አማካኝት ጥያቄያቸው ተደምጦ የካቲት 26/2004 . በአግባቡ መልስ የተሰጠበት ሁኔታ አለ፣ መንግስት የኛንም ጥያቄ በአግባቡ ያድምጠን ህመማችንን ይረዳን መፍትሄም ይስጠን እንላለን ሰሚ ባናገኝ ግን በጉዳዩ ዙሪያ እንጮሀለን እውነት ላለው ሰው ጊዜ ፈራጅ ስለሆነ በተቃውሞ መፍትሄ እስክናገኝ እንጮሀለን በአንድ ምላስ ስድስት የሚጋጭ ነገር እየሰማን ነው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በአማርኛ እና በትግርኛ ፕሮግራም ላይ የተላለፈውን ዜናና ፕሮግራም አይተናል አስተውለንም ተመልክተናል አስተያየት የሰጡት ሰዎች እኛን አይወክሉም ከመንገድ ላይ ጉዳዩን የማያውቅ ቆብ ያደረገ ሰው እየፈለጋችሁ ቃለ መጠይቅ አታድርጉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ብላችሁም ለዜናችሁ ግብአት አታድርጉ ይህ የጋዜጠኝነት የሙያ ስነምግባር አይፈቅደውም ቆብ ያደረገ ሰው ሁሉ መነኩሴ አይደለም እነሱ ከየት እንዳገኛችዋቸው እኛ አናውቅም የምትሰሩት ስራ መሰረቱ ውሸት ስለሆነ ተቃርኖን የሚፈጥር ነገር እየሰማን እያየንም ጭምር ነው ይህንም አይተን ዝም አንልም ያላዩት እንዲያዩት እናደርጋለን አባቶች የተናገሯቸውን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የዘገበውን ጋዜጦች የጻፉትን የአሜሪካ ድምጽን ቃለ መጠይቆች እኛም የምናውቀውን መረጃ በማመሳጠር ምዕመኑ ጊዜያዊ መረጃ እንዲኖረው እናደርጋለን ይህ ደግሞ ስለ ቤታችን ገዶን የምናደርገው እንጂ ሌላ አላማ ኖሮን አይደለም ምዕመኑ የመፍትሄ አካል እንዲሆንም እንሰራለን ቤተክህነቱ መጋፈጥ አቅቶት ወደ ኋላ ቢልም ስለ ሰጠው መግለጫ ጭምር እየተቃወምን መፍትሄ አስከምናገኝ ድረስ እንጮሀለን ቤተክህነቱ ለዚህ ጉዳይ የመፍትሄ አካል ይሆናል ብለን አናስብም ይህ ለስጋውያን ከባድ ነው በገዳሙ የሚገኙ አባቶችን ያህል ነገሩ ይጠዘጥዘዋል ይሰማዋል የሚል እምነትም ሆነ አመለካከትም የለንም ችግሩ ያለው ዋልድባ ነው መፍትሄውም የሚመጣው በቦታው ላይ ባሉ አባቶች ያማከለ ስራ ሲሰራ ብቻ ነው እኛ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ሆነን መፍትሄ እንደምናመጣ አንጠራጠርም። ዛሬ እንጮሀለንነገም እንጮሀለንመፍትሄ እስክናገኝ እንጮሀል እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው

11 comments:

  1. ዛሬ እንጮሀለን … ነገም እንጮሀለን… መፍትሄ እስክናገኝ እንጮሀል ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ።

    ReplyDelete
  2. The crisis is catalyzed by some individuals who have ant-Ethiopia mission with in our leadership.
    So HE Ato Melese has to do something.

    ReplyDelete
  3. እግዚአብሔር ይስማን ይህ ታሪክ የቤተክርስተያን ታረክ የሚያጠፋ ነው አባቶች ሥር በልተው ለትውልድ ያቆዩትን እንዴት በዲሞክራሲ ሀገር ኃይማኖት የለውም ቤተክርስቲያንን ያጠፋል ሲባል የነበረው ደርግ ያላደረገውን እንዴት በኢህአዲግ ዘመን ዲሞክራሲ በሰፈነበት ማንም ቢሆን የእምነት መብቱ በተጠበቀበት ሃገር እንዴት እንዲህ ይደረጋል እርግጠኛ ነኝ ይህንነ ነገር ጠቅላይ ሚኒስትራችን እሚያውቁት አይመስለኝም

    ReplyDelete
    Replies
    1. Yewah!! Who has planned the project if not Meles. He know even the place very well b/c he was there being a fighter before 20yrs. The source of everything for EPRDF is Ato Meles, the otherts are tubes to transfer what he says. Democracy,kkkkkkk!!are you here in Ethiopia, you should be in USA and simply leason what EPRDF talks through ETV.

      Delete
    2. ይቅርታ ዲሞክራሲ በሰፈነበት ላልከው ዲሞክራሲ ቢሰፍንማ ኖሮ ይህ ሁሉ ባልተፈጠረ ነበር....እንደው ዲሞክራሲ በወረቀት ላይ እንጂ በተግባርማ መች አለና ስለዚህ ወንድሜ አይንህን ገልጠህ መመልክት ጀምር...እኛ ግን የምትሰሩት ስራ መሰረቱ ውሸት ስለሆነ ተቃርኖን የሚፈጥር ነገር እየሰማን እያየንም ጭምር ነው ፤ ይህንም አይተን ዝም አንልም ፣ ያላዩት እንዲያዩት እናደርጋለን::እኛ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ሆነን መፍትሄ እንደምናመጣ አንጠራጠርም። ዛሬ እንጮሀለን … ነገም እንጮሀለን… መፍትሄ እስክናገኝ እንጮሀል ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው::

      Delete
  4. ቤተክህነቱ መጋፈጥ አቅቶት ወደ ኋላ ቢልም ስለ ሰጠው መግለጫ ጭምር እየተቃወምን መፍትሄ አስከምናገኝ ድረስ እንጮሀለን ፣ ቤተክህነቱ ለዚህ ጉዳይ የመፍትሄ አካል ይሆናል ብለን አናስብም ፣ ይህ ለስጋውያን ከባድ ነው ፤ በገዳሙ የሚገኙ አባቶችን ያህል ነገሩ ይጠዘጥዘዋል ፣ ይሰማዋል የሚል እምነትም ሆነ አመለካከትም የለንም ፣ ችግሩ ያለው ዋልድባ ነው ፣ መፍትሄውም የሚመጣው በቦታው ላይ ባሉ አባቶች ያማከለ ስራ ሲሰራ ብቻ ነው፡፡
    ለአባቶች፡ጽናቱን፡ይስጥልን

    ReplyDelete
  5. amlalye amlakye netsreni
    welemint hadeggeni

    ReplyDelete
  6. Awo enchohalen, gen Megfate yemaycheluten bayetagelu yeshalal!

    ReplyDelete
  7. ውጊያቸው ከቤተክርስቲያንና ከእግዚአብሔር ጋር ስለሆነ የዘሩትን ያጭዳሉ የተዋህዶ ልጆች የሆንን ሁሉ ግን ጩሀታችንን ወደ ላይ ወደ አምላካችን እግዚአብሔር እያሰማን እንጸናለን ምንም ምን አንረበሽም ክርስትና የተጋድሎና የጽናት ሃይማኖት እንጅ የፍርሀትና የሥጋዊ ጥቅም ማስከበሪያ አይደለምና!!!

    ReplyDelete
  8. egezeahbher selbetekehenet sayehon selebetuena selemenanaeyan selegedamatochu abatochena denagelaweyanoch sil ferdun yeset chuhetachewenem yesemachew lehayemanotu yekomem chuhetachewen semeto chich ayebel esum yedenegeil wedaj kehone atebko yechuh egezeabher yeredan teyakeyachen yemeleselen

    ReplyDelete
  9. የቤተክህነቱ ሰው ደግሞ «ልማቱ ከገዳሙ ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር የለም ፣ ከገዳሙ እና ከፕሮጀክቱ መካከል የስድስት ሰዓት መንገድ አለ» ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ጋዜጣዊ መግለጫ ለኢቲቪ እና መሰል ልማታዊ ሚዲያዎች ሲናገር ሰማን ፣

    I am interested to see every body worrying about our beloved church.
    but
    Are you sure that the information about the distance of the project is wrong.
    Do you have concrete info?
    because what I am hearing from most interviewee Monks at this moment is not the same to what they were scared of before and you are saying now.
    God bless our beloved Tewahedo church.

    ReplyDelete