Thursday, March 29, 2012

በዋልድባ ጉዳይ ብአዴን/ኢሕአዴግ የጠራው ስብሰባ ምጥን ዘገባ

  • ስብሰባው የጎንደርን ካህናትና ምእመናን እንደማይወክል ተገለጸ፤
  • ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ” (አቶ አያሌው ጎበዜ፤ የክልሉ ፕሬዚደንት)

(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 20/2004 .)የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትበዋልድባ ገዳም ህልውና እና ክብር ላይ የጋረጠውን አደጋ በተመለከተየሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ካህናትና ምእመናን የሚያነሡትን ሐሳብ ለመስማትየሚል ስብሰባ ትናንት መጋቢት 19 ቀን 2004 . በጎንደር ዩኒቨርስቲ ሳይንስ ዐምባ አዳራሽ ተካሂዷል፡፡



የስብሰባው አዘጋጅ የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሲሆን ለተመረጡ ሰዎች በየስማቸው የተሰራጨው የጥሪ ካርድ ደግሞ በጎንደር ከተማ ከንቲባ /ቤት ሓላፊ የተፈረመበት እና እንደ ሰርግ ካርድየጥሪው ካርድ እንዳይለይዎየሚል ማሳሰቢያም የሰፈረበት ነው፡፡
ጥሪው በአንድ በኩል የሀገረ ስብከቱን የአድባራት አስተዳዳሪዎችን፣ የሰበካ ጉባኤ አባላትን፣ የጉባኤ መመህራንና ሰባክያነ ወንጌልን አለማካተቱ በአንጻሩም በቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸው አቋም አጠራጣሪ የሆኑ ግለሰቦች ከየቀበሌው የተጠሩበት መሆኑ የስብሰባው ዓላማ ከጅምሩ ጥያቄ ውስጥ እንዲገባ ማድረጉ ተዘግቧል፡፡



ስብሰባው የተመራው በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ነው፡፡ ከእርሳቸውም ጋራ የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ግዛት ዐብዩ በመድረኩ የተገኙ ሲሆን ለጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የሞከሩት ዋነኛው ተናጋሪ ደግሞ የስኳር ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ኣባይ ፀሃዬ ናቸው፡፡



ከጠዋቱ 230 እንደሚጀመር ቀጠሮ የተያዘለት ስብሰባ ከረፋዱ 415 የተጀመረ ሲሆን እስከ ቀኑ 800 ድረስ ከዘለቀ በኋላ እንዲህ ባሉት ስብሰባዎች ድራማዊ በሆነ መልክ የሚዘጋጁየጋራ አቋም መግለጫዎችሳይነበቡበት ተጠናቋል፡፡ የዚህም ምክንያቱ ከቤቱ የሚቀርቡ አብዛኞቹ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከመድረክ ከሚሰጡት ምላሾች ጋራ አለመጣጣማቸው የተሳታፊዎችን ስሜት እያካረረው በመሄዱ እንደሆነ ተገልጧል፡፡



የስብሰባውን ሂደት የታዘቡ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት በገለጻ ረጅም ጊዜ የወሰዱት አቶ ኣባይ በአብዛኛው ያተኰሩት በመነኰሳቱም ይሁን በምእመኑ ባልተነሡና ደካማ በሆኑ ነጥቦች ላይ ነው - “ገዳሙ በውኃ አይጥለቀለቅም፤ ሸንኮራ አገዳ አይተከልበትም፤ ሕዝብ አይሰፍርበትምበሚሉ ጉዳዮች፡፡ በመሆኑም ተሳታፊዎቹ አቶ ኣባይ ጥያቄያቸውን እየመለሱ እንዳልሆነ በማስገንዘብየገዳሙ መሬት በመንገድ ሥራ ይሁን በእርሻ ተነክቷል ወይስ አልተነካም፤ የቅዱሳን ዐፅም ተቆፍሮ ወጥቷል ወይስ አልወጣም፤ የሚፈርሱ አብያተ ክርስቲያን አሉ ወይስ የሉም?” ለሚሉት ሦስት ዐበይት ጥያቄዎች ቀጥተኛ ምላሽ እንዲሰጧቸው ጠይቀዋቸዋል፡፡ ሚኒስትሩ ግን አለባብሰው ከማለፍ ውጭ የሰጡት ቀጥተኛ ምላሽ አልነበረም፡፡



ከአቶ ኣባይ ቀደም ሲል የሀገረ ስብከቱን /ቤት ጨምሮ ከደባርቅ፣ ወገራ፣ ጃናሞራ እና ከመሳሰሉት አጎራባች ወረዳዎች የተውጣጣ ልኡካን ቡድን ወደ ፕሮጀክቱ ስፍራ በመሄድ ያደረገውን ቆይታ የሚያሳይ ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ ታይቷል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባላት ከተሳታፊዎች ለተነሡ ጥያቄዎችም ምላሽ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡



ከእነርሱም መካከል የጩጌ ማርያም ገዳም አበምኔት አባ ወልደ ገብርኤል እና የኮሶዬ /ወገራ/ በኣታ ለማርያሙ ካህን የሰጡት ምስክርነት ከሌሎቹ ለየት ያለ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ የኮሶዬ /ወገራ/ በኣታ ለማርያሙ ካህንምቤተ ክርስቲያን እንደሚፈርስ ተነግሮናል፤ በሚፈርሱት አብያተ ክርስቲያን ቁጥር ለእያንዳንዳቸው አንድ ሚልዮን ብር ካሳ እንሰጣችኋለን ሲሉ ሰምቻለሁማለታቸው ተዘግቧል። ከሁለቱ የልኡካን ቡድኑ አባላት በተፃራሪ የጎንደር በኣታ እና የአዘዞ ሚካኤል አስተዳዳሪው አባ ብርሃነ መስቀል በዘጋቢ ፊልሙ ላይየእሳት ጎረቤት እንጂ የውኃ ጎረቤት አይጎዳችሁምእያሉ መነኰሳቱን ሲያግባቡ ታይተዋል፡፡ ለዚህ አነጋገራቸው ከቤቱጃፓንን የጎዳት የውኃ ሱናሚ አይደለም ወይ? እንዴት የውኃ ጎረቤት አይጎዳም ትላለህ?” የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ታውቋል፡፡ 
አርእስተ ጉዳይ፡-
  • · በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረበውየሀገረ ስብከቱ ልኡካን ቡድንዘገባ ከእውነታው ፈጽሞ የተለየ ስለ መሆኑ በስብሰባው ላይ ተጋልጧል፡፡ የልኡካን ቡድኑ አባል የነበሩ አንድ አባት በተለያዩ አካባቢዎች 500 ሜትር እስከ ሦስት ሰዓት መንገድ የሚሆን የገዳሙ መሬት ታርሶ መመልከታቸውን መስክረዋል፡፡
  • · የሀ/ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ከቀድሞ የተለየና ያልተጠበቀ አቋም ማሳየታቸው ብዙዎችን አስከፍቷል። ከቤተ ክህነቱና ከመንግሥት ሓላፊዎች በተደረገባቸው ጫና ሳይደረግባቸው አልቀረም ተብሏል።
  • · የመንግሥት ባለሥልጣናት በማይ ፀብሪ፣ በማይ ገባ፣ በዓዲ አርቃይ የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ዘቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳት ላይ የሚፈጽሙትን ልዩ ጫናና ማስፈራሪያ እንዲያቆሙ ተጠይቋል፡፡ የቤተ ሚናስ ማኅበረ መነኰሳቱ በልማቱ ላይ እንደተወያዩ በኢ.ቴቪ የተላለፈውን ዘገባ ተቃውመዋል፤ወደ ቦታው ሄጃለሁ፤ አይቻለሁ፤ ያየሁትን እናገራለሁ፤ ፊልሙ ተቆራርጦ ነው የቀረበው፡፡ ገዳማችንን ደፍራችሁታል፡፡ እዚያ መነኰሳቱን ስንጠይቃቸው ለእኛ የነገሩንገዳማችንን ደፍራችሁታል፤ ምነው በእኛ ዘመን ይህን አመጣብን ብለን እያዘንን፤ እየጸለይን፤ እያለቀስን ነው ያለነው፡፡ ጥያቄያችንን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ልከን መልስ እየጠበቅን ነው፡፡ ልማቱን ስለመደገፍ ሲጠየቁም እኛ የልማት ፀሮች አይደለንም ነው ያሉት፡፡ ነገር ግን በዓዲ አርቃይ፣ በማይ ፀብሪ፣ በማይ ገባ የቤተ ሚናስ መነኮሳትን ስታስጨንቋቸው፣ ስታስፈሯሯቸው፣ ስትጫኗቸው አይቻለሁ፡፡ የቴሌቪዥኑ ጋዜጠኛ ከቆመበት በላይ ወደ ገዳሙ እስከ 500 ሜትር ታርሶ አይቻለሁ፡፡ አባ ነፃ በሚባለው የአትክልት (ሙዝ) ስፍራ እስከ ሦስት ሰዓት የእግር መንገድ የሚሰድ ርቀት ታርሶ አይቼአለሁ፡፡
  • · “በአባቶቻችን አፍረናልበማለት የተናገሩ የስብሰባው ተሳታፊዎች የቡድኑን አባላት እነርሱ እንዳልመረጧቸው፣ ሊወክሏቸውም እንደማይችሉ ገልጸዋል፡፡
  • · “በፕሮጀክቱ 50,000 ሰው የሥራ ዕድል ያገኛል፤ 5000 መኖርያ ቤቶች ይሠራሉ ብላችኋል፡፡ መነኰሳቱኮ ዋልድባ ድረስ የሄዱት ዓለምን ጥለው ጥሞናን ሽተው ነው፡፡ ታዲያ እናንተ የገዳሙን ክልል ከተማ ማድረጋችኹ አግባብ ነው ወይ?” /ከተነሡት ጥያቄዎች አንዱ/
  • · ለተሳታፊዎች ጥያቄ ምላሽ ያልሰጡት አቶ ኣባይ ፀሃዬ አበው መነኰሳቱንፖሊቲከኞችገዳሙንምየፖሊቲከኞች መሸሸጊያበሚል መናገራቸው በኢሕአዴግ አገዛዝ የቀጠለው ቤተ ክርስቲያንን የመናቅና የመዳፈር አስተሳሰብና ተግባር አካል መሆኑ በተሰብሳቢዎቹ ተነግሯቸዋል።
  • · አቶ ኣባይ የዋልድባ መሬትለአፈር ምርመራበሚል መታረሱንና ዐፅሞችም መነሣታቸውን ያመኑ ሲሆን በገዳሙ ክልል ውስጥና ውጭከሕዝቡ ጋራ በመነጋገርየሚፈርሱ አብያተ ክርስቲያን እንዳሉ አስታውቀዋል፡፡
  • · የጠ//ክህነቱ ///አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ውብሸት እና የሰሜን ምዕራብ ትግራይ ሽሬ እንዳሥላሴ /ስብከት ሥራ አስኪያጅ ንቡረ እድ ተስፋይ ተወልደ ወደ አዲስ አበባ ተልከው የሄዱ መነኰሳትንመዋቅር ያልጠበቁ ሕገ ወጦች ናቸውበማለት ዘልፈዋቸዋል፡፡
  • · አቶ ኣባይንና አወያዩን አቶ አያሌው ጎበዜን ሳይቀር ደስ ያላሰኘው የአቶ ተስፋዬውዳሴ ኢሕአዴግበተሰብሳቢው ተቃውሞ ተቋርጧል፡፡
  • · በዕለቱ በስብሰባ አመራራቸው የተወያዮቹ መጽናኛ የሆኑት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት አቶ አያሌው ጎበዜዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም፤ እኛም እንደ ክልል እነ ኣባይ ፀሃዬ ጉዳዩን የት እንዳደረሱት እንከታተላለን፤ ሁላችሁም ሄዳችኹ አይታችኹ እውነታውን ማረጋገጥ ትችላላችኹ፤በማለት ተሳታፊዎች ያነሷቸውስጋቶችበምክክር እና ውይይት መፈታት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
  • · ቅዱስ ሲኖዶስ የራሱን አጣሪ ቡድን ልኰ የገዳሙን ህልውና የሚያስጠብቅ አቋም እንዲወስድ፤ መንፈሳውያን ማኅበራት ትክክለኛውን መረጃ ይዘው ገዳሙን የማስጠበቅ እንቀስቃሴ እንዲያካሂዱ፣ መንግሥትም ቀስ በቀስ በይፋ እያመነ የመጣቸውን መረጃዎች በተሟላ ይዘታቸው (እውነታቸው) ለሕዝቡ ግልጽ በማድረግ ተነጋግሮ የማስማሚያ ነጥብ እንዲያቀርብ ተጠይቋል፡፡

በተያያዘ ጉዳይ፦

  • · ማኅበረ ቅዱሳን ወደ ዋልድባ ገዳም አምርቶ የፕሮጀክቱን ተጽዕኖ በመገምገም ይፋዊ ሪፖርት የሚያቀርብ የባለሞያዎች ቡድን ለመላክ መዘጋጀቱ እየተነገረ ነው፡፡
  • · መጋቢት 27 ቀን በዋልድባ አብረንታንት መድኃኔዓለም ክብረ በዓል (በዓለ ንግሥ) ነው፡፡ በርካታ የጎንደር ከተማ ምእመን በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከነገ መጋቢት 21 ቀን 2004 . ጀምሮ ወደ ስፍራው መጓዝ ይጀምራል - አንድም ለአክብሮ በዓል በሌላም በኩል ለገዳሙ ያለውን አለኝታ ለመግለጽ፡፡ ጉዞው ከጎንደር እስከ ዓዲ አርቃይ በተሽከርካሪ ከዚያ በኋላ 18 ሰዓታት የእግር መንገድ ነው፡፡
  • · “ዋልድባ ዓለም አቀፍ ገዳማችን ነው፤ የትግሬው ወይም የአማራው ብቻ አይደለም !!” (ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አንድ የዞኑ የደኅንነት መኰንን ዋልድባ በትግራይ ክልል የሚገኝ በመሆኑ በልማቱ ላይ ጥያቄ ማንሣት እንደማይችሉ ለተናገራቸው ቃል የመለሱለት)

የአርእስተ ጉዳዮቹ ዝርዝር እንደረሰልን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን፡፡

16 comments:

  1. አደራ በምድር አደራ በሰማይ፣ማኅበረ ቅዱሳን ወደ ዋልድባ ገዳም አምርቶ የሚያቀርበው ሪፖርት እውነታውን እንጅ በማንም ተፅዕኖ መሆን የለበትም ፡፡ ስጋት አለኝ መንግስት ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያሳድርበት ይችላል ወይንም በማህበሩ ስም የመንግስት ጥቅመኞች ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ ታላቁ የማህበሩ የፈተና ሰአት ይመስለኛል፣በፀሎት እናስባቸው፣ አሁንም አደራ እውነትን ባትክዳትም እንዳትሸረሽሩአት፣ ይህን ከምታደርጉ ባትሄዱ ይሻላል፡፡ ከመሄዳችሁ በፊት እግዚአብሄር ሊፈትናችሁ እንደሆነ እወቁ፡፡እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡አደራ በምድር አደራ በሰማይ፣ማኅበረ ቅዱሳን ወደ ዋልድባ ገዳም አምርቶ የሚያቀርበው ሪፖርት እውነታውን እንጅ በማንም ተፅዕኖ መሆን የለበትም ፡፡ ስጋት አለኝ መንግስት ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያሳድርበት ይችላል ወይንም በማህበሩ ስም የመንግስት ጥቅመኞች ሊሄዱ ይችላሉ፡፡ ታላቁ የማህበሩ የፈተና ሰአት ይመስለኛል፣በፀሎት እናስባቸው፣ አሁንም አደራ እውነትን ባትክዳትም እንዳትሸረሽሩአት፣ ይህን ከምታደርጉ ባትሄዱ ይሻላል፡፡ ከመሄዳችሁ በፊት እግዚአብሄር ሊፈትናችሁ እንደሆነ እወቁ፡፡እግዚአብሄር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡

    ReplyDelete
    Replies
    1. Mahberun lifetinut yemichlut degmo ahun new. Aba Sereke siqayun siyabezubet mekerawun siyasayut keremu ahun degimo Aba Paulos ena Mengist wetrew yeyazut yimeslal hulachinim eski beyalenibet bota honen "Abune Ze Besemayat" enadirsilet. Ye Kidusan Amlak Ahun Firedilin. Mahibere Kidusaninim kekebebew fetena yawtaw. "Betekebebe ketema yemiyasdenik mihiretun ke'ene yalarake Egzeabher yimesgen." endinil Emebrehan tirdan. Amen

      Delete
    2. ene bebekule mehedachew gudat enji tikim yelewum bay negn mikiniyatum, hedew ewnetun biyawetum enkuan yih seytanawi mengist kesiraw yemiyagidew neger yelem yilikunim ande yekerenin tenkara mahiber yafersubinal, fertew kedebabekut demo kehizbu gar yitalalu; silezih bayhedu emertalehu. egna yemiyasfeligen metseley bicha new.(yemiserut neger eneza yesudan tenkuayoch le w/ro azeb yeminegiruatin neger new, yeminimeraw eko besudan tenkuwayoch new. lezi demo EGZIABHER bizegeyim mels alew. tseliyu, sigedu, tsumu. amen)

      Delete
  2. we need the brief impact of the project on THE MONASTERY by Mahibere Kidusan.MK is the only representative of our EOTC in this days.Others are living for their belly.We pray for MK peace.We wish God to be with MK.

    NB:- MK as far as u are living only for truth,we need true report.I hope u will not be hesitate to report ur findings as others were hesitated to tell us the truth of Waldiba project.

    ReplyDelete
  3. “ዋልድባ ዓለም አቀፍ ገዳማችን ነው፤ የትግሬው ወይም የአማራው ብቻ አይደለም !!” (ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ አንድ የዞኑ የደኅንነት መኰንን ዋልድባ በትግራይ ክልል የሚገኝ በመሆኑ በልማቱ ላይ ጥያቄ ማንሣት እንደማይችሉ ለተናገራቸው ቃል የመለሱለት)።

    ReplyDelete
  4. የብፁአን አባቶቻችን አቐም ግን በጣም እያስፈራኝ ነው፡፡ ማነው ለቤተ ክርስቲያን ቀድሞ መቆም (መሞት)ያለበት ተራው ምዕምን ብቻ እንዲታገል ለምን ያደርጋሉ ከዚህም አልፈው የተወሰኑት እራሳቸውን ነፃ ለማውጣት የሚሞክሩ አሉ (አቡነ ጼጥሮስን የሚያስታውሰን አባት እንፈልጋለብ ፣ ታግሎ የሚያታግል)የብፁአን አባቶቻችን አቐም ግን በጣም እያስፈራኝ ነው፡፡ ማነው ለቤተ ክርስቲያን ቀድሞ መቆም (መሞት)ያለበት ተራው ምዕምን ብቻ እንዲታገል ለምን ያደርጋሉ ከዚህም አልፈው የተወሰኑት እራሳቸውን ነፃ ለማውጣት የሚሞክሩ አሉ (አቡነ ጼጥሮስን የሚያስታውሰን አባት እንፈልጋለብ ፣ ስጋዊ ፈተናን ያሸነፈ እና በማንኛውም ሰአት ለቤተክርስቲያኑ ሲል መስዋህትነትንም የማይፈራ)

    ReplyDelete
  5. "ዋልድባ ቅዱስ ገዳማችን ነው፤ እንዲነካ አንፈልግም" endih kalu lemin yemibalutin ayisemum. "Doron siyataliluat bemechagna taluat" aye zemen, gize setachewina yetekedesewin enkuan eske medfer deresu. yesemay Amlak ante temelketilin. Atitewen, Atinakenim yeselam Amlak hoy teradan.
    Aba Paulos ye'ejiwotin yistwot.

    ReplyDelete
  6. ewunetna neget ayedel yemibale gena wodefit bzu ewunet yewthel

    ReplyDelete
  7. አንድ አድርገን ነገሩን እየተከታተላችሁ ለሕዝበ ክርስቲያኑ ማቅረባችሁ የሚያስመሰግናችሁ ነው፡፡ የማኅበሩን ሪፖርት እንጠብቃለን፤ የክልሉ መንግስት ፕሬዚደንት ጥሩ ሠው ናቸውና ለመልካም ሥራቸው እግዚአብሔር ያበርታቸው እስከ መጨረሻው ከቤተ ክርስቲያን ጎን እንደሚሆኑ እናምናለን፡፡ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስን እንኳን ብዙም ደስ አልሰኝባቼውም፡፡ ይልቅ በፊት የነበሩት አቡነ እንድሪያስ ቢኖሩ ኑሮ ነገሩ ከዚህም ባልደረሰ ነበር፡፡ ለማንኛዉም ያባቶቻችን ፀሎት ለክፉ እንዳይሠጠን አምናለሁ፡፡

    ReplyDelete
  8. Engidih...min yibalal...ETV yemisetewin megilecha yebetekiristian lijoch lifetishut yigebal...betekiristian: gazetegna/journalist;mehandis/engineer;ye ersha balmuya/agricultural professional;ye meret tinat balemuya/geologist;sayintist/scientist;hakim/medical professionals/doctors;ye economy balemuya/economist;ye poletica mihur/poleticians...etc...leloch bizu muyawoch yalwachew lijoch aluwat...silezih ETV yemisetewin megilecha betimona maten yinoribetal....Hadera..yetaric ena yenefis sihitet endansera

    ReplyDelete
  9. በውጭ በስደት በአገር ቤት በባለቤትነት እና ራሱን ገለልተኛ እያለ የሚጠራው የቤተ ክርስቲያኒቱ የካህናት ስብስብ ቤተ ክርስቲያንን ከተለያየ አቅጣጫ የማፍረስ ስራውን ቀጥሏል:: የአገር ቤቶቹ ራሳቸውን የፖለቲካው አራማጆች አድርገው ከዋናወቹ ፖለቲከኞች በባሰ እና ፖለቲከኞቹ ከሚፈልጉት በላይ የፖለቲካውን ድጋፍ ቀጥለውበታል:: ለዚህ እኩይ ስራቸው ደግሞ በፖለቲካው አካላት ድጋፍ በቤተ ክርስቲያናችን ሙስናን አሳድገው (አስጠምቀው) ማለት ይቀላል የሕዝበ ክርስቲያኑን ንብረት፣ ገንዘብ ቅርስ እና ሃብት እየዘረፉ እያስዘረፉ ይገኛሉ:: የአዲስአበባው አስተዳደር ከዚህም በከፋ ቤተ ክርስቲያኒቱ የአንድ ብሔረሰብ እስክትመስል ድረስ በአንድ ጎሳ አባላት አብዛሃኛውን በተለይም ብዙ የሃብት ክምችት ያለባቸውን አጥቢያዎች አስይዘዋል:: ይህ በፖለቲካው ዘንድ የታወቀ በመሆኑ ጠያቂም የለም:: የኔ አስተያየት አንድን ጎሳ ለምን ተጠቀመ አይደለም ነገርግን ብዙ ብሔር ብሔረሰቦች በበዙባት አገር የአንድ ብሔረሰብ በአንድ ተቋም መብዛቱ ትክክል አይደለም ለማለት ነው:: ሌላው የአድስአባው አስተዳደር ሕዝበ ክርስቲያኑን በትናንሽ ችግሮች በመጥመድ የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ያለምንም ተመልካች ማካሄድ ነው:: ይቅር ባይና መሃሪ ለመምሰል ከአሁን በፊት ከሃይማኖታችን አይደለም ከባህላችን ውጭ በሆነ በጥፋት ላይያተኮረ ያልሆነን በሕዝብ የተሳደበን አካል ጋ የጀመሩት ፍቅር ማህበረሰቡን ስለአስተዳደሩ ያለውን መልካምነት አግዝፎ ለማሳየት የተተወነ ትያትር እንደነበር መገንዘብ የቻልነው ምንያህላችን እንደሆንን አለውቅም::
    አስተዳደሩ ግን ከመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያንን ማጥፋት እንደሆነ ያወቁ ጥቂት አባቶች በጮሁ ጊዜ ስንቶቻችን በጩኸታቸው እንደቀለድን ሳስብ ጥፋተኝነት ያንገበግበኛል:: የተማረ የማይወዱ፣ ከፖለቲከኞቹ ጋ ወገናዊ ስለሆኑ ነው ምናምን እያልን ያወቁ አባቶቻችንን ጩኸት ውሃ የቸለስንበት እኛው ነበርን::
    እውነተኛ የአስተዳደሩ ባሕሪ ግን ዘረፊነት፣ ከሃዲነት፣ እና በአጠቃላይ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት አገሪቱን የሚመራው አውራ ድርጅት ከበረሃ ሆኖ የቀረጸውን ጸረ ቤተ ክርስቲያን ፖሊሲ ማስፈጸም ነው:: ለዚህም ብዙ ምሳሌ ማቅረብ ይቻላል:: በቅርቡ እንኳን ዝርፊያን የተቋቋሙትን የአዲስአባ ሃገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ እንደት እንዳነሷቸው ልብ ይሏል:: በሪሞት ኮንትሮል የሚከፈት ቤት ያላቸው፣ የቅንጦት መኪና የሚያሽከረክሩ፣ ብዙ ሃብትና ንብረትን ከሙዳየ ምጽዋት ገልብጠው ያፈሩ ብዙ በጣም ብዙ እጅግ በጣም ብዙ ሠዎችን መጥቀሱ ራሱ በቂ ነው::
    በስደት ያለው አስተዳደርም ከአገር ቤቱ ባልተናነሰ የሃይማኖታችንን ድንበሮች በማፍረስ ቀኖና ዶግማ የተለያየ ነው ቀኖና ይሻሻላል በመሆኑም ከአሁን በፊት የማይደረጉትን ማድረግ ይቻላል እያሉ ሰባኪና ቄስ በየአጥቢያቸው ቀኖና ሲጥሱ እያዩ ዝም በማለት እና ከአሁን በፊት በቤተ ክርስቲያን ላይ የክህደት መርዛቸውን ረጭተው ካዛም ለይቶላቸው ሌላ የሃይማኖት ተቋማትን የተቀላቀሉትን ሳይቀር ካህን እያደረጉ በሕዝቡ ውስጥ ሰግስገው በክህደት ትምህርት አስደበደቡት አሁንም እያስደበደቡት ነው:: በውጭ አገር ያለውን ሕዝብ የመንግሥት ተቃዋሚነታቸውን እያሳዩ አጋር ካደረጉ በኋላ እየተቃወሙ ያለው መንግስትን ሳይሆን ሃይማኖትን ነው:: ይህንንስ ተቃዋሚዎቹ ገብቷቸው ይሆን? ታዲያ ከአሁን በፊት የቤተ ክርስቲያኒቱ አመራር የነበሩት አባቶች ይህን አይነቱን የሃይማኖት ጉድለት እያዩ ማለፋቸው አብረው ቢኖሩበት ወይንስ ብዞዎች እንደሚሉት ዘር ከልጓም ይስባል ሁኖባቸው:: ያሳለፍነው ጊዜ እኮ አንድ ወጣት አግብቶ ልጅ ወልዶ ልጁን ለዲቁና አብቅቶ ከዛም ዲያቆኑ ልጁ ወልዶ ሦስት ትውልድ የሚኮንበት ነው:: ታዲያ ይህን በሚያህልዘመን ለሃይማኖታቸው ያልቆሙ፣ ያልመሰከሩ መቼ ሊቆቆሙላት፣ ሊመሰክሩላት ነው ወይንስ በስልጣን እንደነበሩበት ጊዜ ሊመክሩና ሊገስጹዋቸው ነው:: መቼ?? ከአሁን በኋላስ ስንት የሚሆን ጊዜ እንጠብቅ:: እንደኔ ግን ለቤተ ክርስቲያን ወገኗ ፣ ነገዷ እንዳልሆኑ አሳይተውናል ከዚህ በላይ አስረጅ አያስፈልገንም::
    ሌሎቹ ራሳቸውን ገለልተኛ ያደረጉት ደግሞ የሁለቱንም አስተዳደር እና አካሄድ እየኮነኑ ሕዝቡን ሰብስበው ቤተ ክርስቲያኑን ከጠላት እንዳያስመልስ ተው አሁን ነገሮ ችሊቀየሩ ነው አንድነት ሊመጣ ነው እያሉ ሕዝቡን በውሸት እልል እያስባሉ ይኸው አሉ::
    ውድ የተዋሕዶ ልጆች ሆይ የቤተ ክርስቲያናችን ነገር እንደ እግርእሳት የሚያቃጥላቸው ሕመሟን የታመሙ ችግሯን የተቸገሩ ሕይዎ ታቸውን እንኩዋንለሷ ለመስጠ የቆ ረጡ እውነተኛ አባቶች ኧሉዋት ነገር ግን ከሃዲ በሰለጠነበት ካድሬ ሃላፊ በሆነበትና ለገንዘብና ለጥቅም በቆሙ ምንደኞች በጣም በበዙባት በዚች ቤተ ክርስቲያን እነዛ ቆራጦች አናሳዎች (minority) በመሆናቸው ብዙም አናያቸውም እናም ትግላችን ቤተ ክርስቲያናችንን ከነጠቁን ከከሃዲዎቹ፣ ከፖለቲከኞቹ እና ከምንደኞቹ መልሰን ማግነትና ለነዛ ለእውነተኞቹ ልጆቻቸን በትነው ለማይሄዱት ለኑፋቄ ትምህርት አሳልፈው ለማይሰጡትና ጥሪቱ ለማያዘርፉት አባቶች እንደ አዲስ አደራ መስጠት ያስፈልጋል::
    አባት ማለት ልጆቹን የሚያሳድግ፣ ቀን ከሃሩሩ ሌሊት ከቁሩ ታግሎ ልጆቹን የሚመግብ ከአደጋ የሚጠብቅ እንጅ ጅብ ሲጮህ ልጁን ቀድሞ ወደ መጠለያው የሚገባ ልጁን ሳያበላ ቀድሞ የሚበላ የሚያደርግ አይደለም ያማ መውለድማ እ____ም ይወልዳል አይነት ነው::
    እንበርታ ዘረኝነትንአጥብቀን እንቃወመው ወደራ ሳችን እንዳይመጣ አትብቀን እንቃወመው::

    ReplyDelete
    Replies
    1. የክልሉ መንግስት ፕሬዚደንት ጥሩ ሠው ናቸውና ለመልካም ሥራቸው እግዚአብሔር ያበርታቸው እስከ መጨረሻው ከቤተ ክርስቲያን ጎን እንደሚሆኑ እናምናለን.tiru mesrat besewm be fetarim yasmesegnal tiru biseru new yemishalew zare bebetekirstian lay endih biwegnubatim nege befetari siteyeku manachewm yemimelsut neger yelem andebetachew dida yhonal yzegeyal enj amlak mefredun ayresam mot degmo aykerm bayhon bezih yamnu yhonal le negeru baleken silehonu ayamnum ewnetun ykidalu andi hager yemtbeletsigew gedam bemafres sayhon bemesrat new China gedam afrsa new habtam yehonesh? Egziabher lib ystachew

      Delete
  10. bzemenachen yetekesete aryosawi tegebare .Yehye newe ewenet Ethiopia kalenezih abatoch selote yemetenore yemeselachuhal ?ferdune ena yezich hageren mecheresh lemayet gyezewe yetekarebe yemeselejal .......

    ReplyDelete
  11. MK lemilkachew sewoch ejig tinqaqie yadrg, papasatna menekosat, bemengistm qulf bota lay yalachihu, bewuchim behager wustim yalachihu, endihum melaw ye'Bie/kn lijoch hulu "Ende'Abatochachihu ewunetin bicha yemitnageru hunu...!" - 'Abune Shinoda'. Be'Bie/k'nm Betarikm tewoqashoch endanihon adera! Yekidusan Amilak Egziabher yirdan. Amen !!!

    ReplyDelete
  12. IN my opinion this time is a challenging time for our church.in addition, some gov't authority have negative attitude for the association.so just lets leave the decision for GOD himself.mk shouldn't involve in any case except praying to GOD.

    ReplyDelete