የአባቶቼን ርስት እሰጥህ ዘንድ እግዚአብሔር ያርቅልኝ 1ኛ ነገስት 20፤3)
በዋልድባ ገዳም ገዳማውያኑ እና የአካባቢው ምእመናን በጋራ የሚጠቀሙባቸው አራት አብያተክርስቲያናት - ማየ ሕርገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን (የሴቶች ገዳም)
- ዕጣኖ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን (የገዳሙ እህል ቤት)
- ደላስ ቆቃ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን እና
- ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን
ይህንን የገዳማቱ አባቶች አቤቱታ የሰሙ ቅናተ ቤተ ክርስቲያን ያደረባቸው/የበላቸው ወንድሞች የአቤቱታ ሰላማዊ ሰልፍ በተለያዩ የዓለማችን ከተሞች ለማድረግ እቅድ ይዘዋል:: የመጀመርያው ሰላማዊ ሰልፍ የአሜሪካ መንግስት መቀመጫ በሆነችው በዋሽንግተን ዲሲ ማርች 26፣2012 ወይም መጋቢት 17፣2004 ከጠዋቱ 3 ሰዓት፤ ይደረጋል:: ሰልፉ ላይ ሁሉንም የቤተ ክርስቲያን አማኝ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ልዩነት ሳይገታቸው በአንድነት ድምጻቸውን እንዲያሰሙ አዘጋጆቹ የአደራ ጥሪ አስተላልፈዋል::
አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት ስድባችንንም እይ።
ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።
የልባችን ደስታ ቀርቶአል፤ ዘፈናችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል።
አክሊል ከራሳችን ወድቆአል፤ ኃጢአት ሠርተናልና ወዮልን!
ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፤ ስለዚህም ነገር ዓይናችን ፈዝዞአል፤
ስለ ጽዮን ተራራ፥ ባድማ ሆናለችና፥ ቀበሮችም ተመላልሰውባታልና።
አቤቱ፥ አንተ ለዘላለም ትኖራለህ፤ ዙፋንህ ከትውልድ እስከ ትውልድ ነው።
ስለ ምን ለዘላለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?
አቤቱ፥ ወደ አንተ መልሰን እኛም እንመለሳለን፤ ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድስ።
ነገር ግን ፈጽመህ ጥለኸናል፤ እጅግ ተቈጥተኸናል።
ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።
we must stand together to this.other wise we will be historyless generations. so, we must start now strageling. because it is preferable that our diammage must come before our religion and our blessed places. GOD is always with us.
ReplyDeleteooooooooooo i'm so crying.God please look to us.
ReplyDelete