Sunday, March 18, 2012

በዝቋላ የእሳት ቃጠሎ

For more information call 
0115545452 or 0920675349 

አንስዕ ኃይለከ ወንአ አድኅነነ
አምላከ እስራኤል ተራድአነ

ኃይልን አንሳ መጥተህ አድነን
የእስራኤል አምላክ እርዳን


ተኝተሃል አሉ
ደልቶሃል ይባላል ተኝተሃል አሉ
እሳት እየበላው ሳር ቅጠሉ ሁሉ
እሳት እየበላው የቅዱሳን ቤት
ተኝተሃል አሉ ቀንና ለሊት
ላስታውስህ ወዳጄ ይህን ዘንግተሃል
ዳሩ ነዶ ሲያልቅ መሃል ዳር ይሆናል፡፡

(አንድ አድርገን መጋቢት 10 ፤ 2004ዓ.ም)፡ የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የተነሣው የእሳት ቃጠሎ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ማምሻውን በቁጥጥር ስር መዋል ቢችልም ዛሬ ቀትር 6 ሰዓት ላይ ተመልሶ መቃጠል ጀምሯል፡፡ በአከባቢው ከሰው ሐይል በስተቀር ሌላ እሳት ማጥፊያ መሳሪያ የለም ፡፡በመሆኑም የአየር ሀይል እሳት አደጋ በፍጥነት ሊድርስ ባለመቻሉ ተጨማሪ ጉዳት እያስከተለ ነው ፡፡ የመንግስት አካላት እርዳታ እንዲያደርጉ ከቦታው ያሉ ክርስቲያኖች ጥሪያቸውን እያስተላለፉ ይገኛሉ፡፡ ይህንን ታሪካዊ ገዳም ከእሳት በማዳን ክርስቲያናዊ ግዴታችንን እንወጣ፡፡ በእያለንበት መረጃውን በማስተላለፍ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ በማድረግ ደኑን በእሳት ከመጥፋት እናድነው፡፡ 


(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 9/2004 .ም፤ ማርች 18/2012 
  • ቃጠሎው የገዳሙን ዙሪያ ገባ እያካለለው ነው። 
  • የቃጠሎው መንሥኤ ከሰል አክሳዮች ናቸው መባሉ አጠራጥሯል። 
  • ትናንት ምሽቱን ነው ዳግመኛ የተቀሰቀሰው፤ የተጠበቀው የአየር እገዛ አልተደረገልንም፤ እሳቱ ዙሪያውን ይዞታል፤ በእሳቱ እየተከበብን፣ በጭሱ እየታፈንን ቢሆንም ባፈር በቅጠሉ እየታገልን ነው፤ ወደ ጠበሉ ከገባ ግን አለን ለማለት አይቻልም፤ . . . ገብረ መንፈስ ቅዱስ መቶ ዓመት ለጸለዩባት፣ ለደከሙባት ቅድስት ቦታ ምላሹ ይህ ነውን? እንዲያው ወሬ ብቻ ነን!!” /የገዳሙ መነኰስ/
  • ዳሩ እሳት - መሀሉ እሳት!! በምሥራቅ እሳት - በመሀል እሳት - በሰሜን እሳት!!  
(ደጀ ሰላም፤ መጋቢት 9/2004 .)  በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ቀበሌ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ በሚገኘውና የመንግሥት ይዞታ በሆነው ደን ምሥራቃዊ ገጽ ትናንት ቀትር ላይ ተነሥቶ ማምሻውን በቁጥጥር ሥር መዋሉ የተገለጸው ቃጠሎ ሌሊቱን አገርሽቶ ዙሪያ ገባውን ከፍተኛ ጥፋት እያደረሰ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ሌሊቱን ዳግመኛ ማገርሸቱ የተነገረው ቃጠሎ የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በሚገኝበትና ትናንት እሳቱ ከተነሣበት አዱላላ ከሚባለው ምሥራቃዊ ቦታ በምዕራብ አቅጣጫ የሴቶች ገዳም ወደሚገኝበት የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያንና ወደ መሀል የገዳሙ ክልል እየተዛመተ ነው፡፡
ከስፍራው በደረሰን መረጃ መሠረት÷ በአሁኑ ወቅት የቃጠሎው ጭስ እሳቱን ለማጥፋት የሚካሄደውን ጥረት በእጅጉ አዳጋች አድርጎታል፡፡ በቦታው በርከት ብሎ የሚታየው አስታ የተባለው አጭር ዛፍ፣ የደረቀው ሣርና በበጋው ሙቀት የከቸረው መሬት/ አፈር እሳቱን በከፍተኛ ደረጃ በማቀጣጠል÷ በምሥራቅ አቅጣጫ በከባዱ ከሚነፍሰው ነፋስ ጋራ ተደማምሮ ለእሳቱ በአጭር ጊዜ መዛመት አስተዋፅኦ ማድረጉን የገዳሙ መነኰሳት ተናግረዋል፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ ቃጠሎው ከገዳሙና ከአካባቢው ማኅበረሰብ አቅም በላይ ለመሆኑ ርግጥ ቢሆንም በትናንትናው ዕለት በአየር ኀይሉ ሄሊኮፕተር ወይም የእሳት አደጋ መከላከል መኪኖች ይደረጋል ተብሎ የተጠበቀው እገዛ እንዳልደረሰላቸው አንድ የገዳሙ መነኮስ መግለጻቸው ተዘግቧል፡፡ እኚህ አባት እንዳስረዱት ቃጠሎው ከቁጥጥር ውጭ ሆኖ ጠበል እየተባለ ወደሚጠራው ጫካ ከደረሰ የገዳሙን ጠቅላላ ህልውና አጠያያቂ ያደርገዋል፡፡

መነኮሱ አያይዘው የሰጡት ገለጻ ቃጠሎውበከሰል አክሳዮች ነው የተነሣውየሚባለውን የሚያስተባብል ነው - የትናንቱ ጠፍቷል ስንል ይኸው ሳይጠፋ አደረና በመድኃኔዓለም፣ በኪዳነ ምሕረት፣ በሴቶች ገዳም በኩል እያስጨነቀን ነው፤ መሬቱ፣ ሣሩ፣ ቅጠሉ በጣም ደረቅ ነው፤ ይነዳል፤ ነፋስ አለ፤ ጭሱም ያፍናል፤ በዕድሜ የገፉ አባቶች ሳይቀሩ በእሳት ተከበውም ቢሆን ባፈር በቅጠሉ ቢታገሉም ከአቅም በላይ ሆኗል፡፡
ምንም ዐይነት እገዛ ባለመደረጉ በእጅጉ ያዘኑት ሌላዋ እናትም ጣድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መቶ ዓመት ለጸለዩባት፣ ለደከሙባት ቅድስት ቦታ ምላሹ ይህ ነውን? እንዲያው ወሬ ብቻ ነን!!” ሲሉ የተሰማቸውን ብሶት ገልጸዋል፡፡

የዜና ዘገባው እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ በሀገረ ስብከቱ ደረጃ ይኹን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ /ቤትና የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ምን ጥረት እየተደረገ እንዳለ በጎላ በተረዳ የተሰማ ነገር የለም፡፡
የዝቋላ ገዳም ዐፄ ገብረ መስቀል እና ቅዱስ ያሬድ ከነበሩበት አምስተኛው // ጀምሮ የሚነገር ታሪክ ቢኖረውም በታወቀ መነሻ የቀናው ገድላቸውን በግብጽ ጀምረው በኢትዮጵያ በፈጸሙት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አማካይነት 1168 . እንደሆነ ይታመናል፡፡ ጻድቁ ሁለት . ርዝመት እና 60 ሜትር ጥልቀት ባለው የዝቋላ ሐይቅ ውስጥ የቁልቁሊት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያና ለዓለም ሁሉ 100 ዓመታት እንደ ጸለዩ፣ በርእሰ ደብር ዝቋላም 262 ዓመታት እንደኖሩ፣ በዚህም ወቅት ልዩ ልዩ የአጋንንትን ፈተና ድል መንሣታቸውንና ከጌታችን ዘንድ ቃል ኪዳን መቀበላቸውን በገድላቸው ሰፍሮ ይገኛል፡፡ 15ኛው // የነበረው ንጉሥ እንድርያስ (ሕዝበ ናኝ) በርእሰ ደብር ዝቋላና በዙሪያው በመድኃኔዓለም፣ በእመቤታችን፣ በቅዱስ ገብርኤል፣ በቅዱስ ሚካኤል እና በጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም አብያተ ክርስቲያን አሳንጧል፡፡ እኒህ አብያተ ክርስቲያን በግራኝ ወረራ ወቅት ጠፍተው ገዳሙ ጠፍ ሆኖ እስከ ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ እና ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ከቆየ በኋላ መተዳደሪያ መሬት (ጉልት) አገልጋዮች ተሰጥተውታል፤ አብያተ ክርስቲያኑም ዳግመኛ ታንፀዋል፡፡ በእሳተ ጎሞራ የተፈጠረ ሐይቅ (Crater Lake) ተግኖ የሚገኝ ጥንታዊው የዝቋላ ገዳም በአምስቱ ዓመት የጠላት ወረራ ዘመን ከየካቲት 12 1928 . ጭፍጨፋ በኋላ (ፋሽስት ኢጣልያ በደብረ ሊባኖስ ገዳም ላይ እንደፈጸመው ሁሉ) የአርበኞች መደራጃ ማእከል ነው በሚል ከባድ ጥፋት ቢያደርስበትም ፋሽስቱ በአየር ይሰንዝር የነበረውን የቦምብ ድብደባ አንጥሮ የሚመልስ ታላላቅ ገቢረ ተኣምራት እንደተፈጸሙበት ይነገራል፡፡ 1989 . አንሥቶ ከርዳታ ጋራ በተያያዘ ወደ አካባቢው በገቡት ሉተራውያን ምክንያት ገዳሙ ከሚደርስበት ሰው ሠራሽ ችግር በተጨማሪ በበጋ የውኃ እጥረት፣ በክረምት ደግሞ ከባድ ቁርና የመንገዱ አስቸጋሪነት ተግዳሮቶቹ ናቸው፡፡

ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

10 comments:

  1. እግዚኦ ማህረነ ክርስቶስ ፣ ልብ ያለው ልብ ይበል ይሄ ሁሉ የግዘር ቁጣ ነው
    አቤቱ ይክር በለን

    ReplyDelete
  2. Please we need update...what's happening now @ zequala??
    Is the fire under control??

    ReplyDelete
  3. Fetenaw eyayele new wegen betselot eniberta.

    ReplyDelete
  4. abetu getahoy maren yeqer balen

    ReplyDelete
  5. weyne betekrstyanie akm yelengm eko mnlbl?

    ReplyDelete
  6. ke kirb ametat wedih yih esat tedegageme!!!! lib yalew lib yibel??...Abune Paulos ena Meles...min eyeseru yihon??

    ReplyDelete
  7. ahun mn lay derese betam yemiyasazn new egziabher cher were yaseman hulachnm betselot enberta

    ReplyDelete
  8. አምላካችን ሆይ ዝም አትበለን እባክህን ጩህታችንን ስማን!!!የ አብርሃም የይሳቅ የያይቆብ አምላክ ሆይ
    ለነሱ እንደተለመንክ ለኛም ተለመነን

    ReplyDelete
  9. አምላካችን ሆይ ዝም አትበለን እባክህን ጩህታችንን ስማን!!!የ አብርሃም የይሳቅ የያይቆብ አምላክ ሆይ
    ለነሱ እንደተለመንክ ለኛም ተለመነን

    ReplyDelete