Wednesday, March 21, 2012

መንግሥት በዋልድባ ገዳም የስኳር ልማት አላካሄድኩም አለ


(ሪፖርተር ጋዜጣ)
- ገዳሙን በከበበው ዛሬማ ወንዝ ላይ ልማት እየተካሄደ ነው
በጥንታዊውና በአገሪቱ ካሉ ቅዱሳን መካናት በቀደምትነቱ የሚታወቀው የዋልድባ ገዳም ውስጥ ምንም ዓይነት የስኳር ልማት ፕሮጀክት አለማካሄዱንና የማካሄድ ዕቅድ እንደሌለው ያስተባበለው የኢትዮጵያ የስኳር ልማት ኮርፖሬሽን፣ በበርካታ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችም ሆነ በገዳሙ መነኮሳት የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ያጣጣለው ‹‹ሌላ አጀንዳ ባላቸው ሰዎች የተነሳ ጥያቄ ነው፤›› በማለት ነው፡፡ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ ከሌሎች ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር በመሆን በወልቃይት፣ በአክሱምና በመቀሌ ያደረጉትን ስብሰባ አጠናቀው ትናንት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ በገዳሙ የቀረበውን ተቃውሞ አግባብ ባለው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር መሠረት ያልቀረበ፣ ይልቁንም የገዳሙ አንዳንድ መነኮሳት ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ያሰሙት አቤቱታ ትርጉም የሌለውና ተገቢ ያልሆነ በማለት ኮርፖሬሽኑ አጣጥሎታል፡፡ 
ነገር ግን የኮርፖሬሽኑ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የዋልድባን ገዳም ከከበቡት ወንዞች አንዱ በሆነው የዛሬማ ወንዝ ላይ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክት እየተካሄደ ይገኛል፡፡ 
በትግራይ ክልል በሚገኘው ወልቃይት ወረዳ ላይ የሚካሄደው የስኳር ፕሮጀክት 25 ሺሕ ሔክታር መሬት የሸንኮራ አገዳ የሚለማበት ሲሆን፣ በቀን 10 ሺሕ ቶን አገዳ የሚፈጭ ፋብሪካ የሚገነባበት ነው፡፡
ፕሮጀክቱ የሚካሄድባቸው ቦታዎች ዛሬማ፣ ዱቁቆና ተከዜ ሸለቆ ሲሆኑ በተለይ የዛሬማ ወንዝ ለገዳሙ በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ ቢሆንም፣ ሪፖርተር ከኮርፖሬሽኑ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘው መረጃ ግን ያንን የሚያስተባብል ነው፡፡ 
ወንዙን በመገደብ 3.8 ቢሊዮን ሜትር ኩብ ውኃ በመያዝ ለአገዳ ልማት እንደሚጠቀምበት ያስታወቀው ኮርፖሬሽኑ፣ ከስኳር ፋብሪካው በዓመት 284 ሺሕ ቶን ስኳር እንዲሁም 26.8 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል ለማምረት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
ከዚህም ባሻገር በአካባቢው 3,442 መኖርያ ቤቶች እንዲሁም 120 የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እንደሚገነቡ ሲጠበቅ፣ ሥራውን የሚያካሂድበትን ጽሕፈት ቤት በማይገባ ከተማ እንደከፈተ ታውቋል፡፡ እስካሁንም የግድብ ግንባታው ቁፋሮና እርሻውን፣ ፋብሪካውንና የመኖርያ መንደሮችን የሚያገናኙ መንገዶችም እተገነቡ ይገኛሉ፡፡
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በትናንትናው የዜና እወጃ ምሽት ላይ ስቱዲዮ ተገኝተው በገዳሙ ላይ ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ የሰጡት ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ዓባይ ፀሐዬ፣ በገዳሙና በስኳር ፕሮጀክቱ መካከል የስድስት ሰዓት ያህል ርቀት የሚገኝ ከመሆኑም በላይ በቅዱስነቱ ሳይነካ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ሆኖም ግን በታህሳስ ወር ላይ ገዳሙ በስኳር ፕሮጀክት ግንባታ ሳቢያ እየታረሰ፣ የቅዱሳን አባቶች አጽም እየፈለሰ፣ መቃብራቸው እየተደፈረና የጥርጊያ መንገድ እየወጣበት እንዲሁም ደግሞ ለፓርክነት እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ከገዳሙ ውስጥ ከሚገኙ ልዩ ልዩ ገዳማት መፍትሔ እንዲሰጧቸው  በጹሑፍ መጠየቃቸው የሚታወስ ቢሆንም፣ አቶ ዓባይ ግን በመነኮሳቱ ያልቀረበ ጥያቄ በማለት ውድቅ ከማደረጋቸውም በላይ፣ ለገዳሙና ለሃይማኖት በመቆርቆር ሳይሆን በሰበቡ ተጠቅመው ተቃውሞ ለማስነሳት የፈለጉ ሰዎች ያነሱት ጥያቄ ነው ብለውታል፡፡
ጥያቄውን ያቀረቡት ግን የየገዳማቱ ተጠሪዎች እንደሆኑ ቢነገርም፣ የቤተ ክህነት አጣሪ ኮሚቴ በቦታው ተገኝቶ ማጣራቱንና ምንም ዓይነት ጉዳት በገዳሙ ላይ አይደርስም ማለቱ  ተነግሯል፡፡ ያም ሆኖ አቶ ዓባይ የሰዎች አጽም በክብር እየተነሳ እንደሚገኝ፣ በፕሮጀክቱ አካባቢ ተነሺ ለሆኑ ሰዎች ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲዛወሩ ከሕዝብ ጋር ውይይት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡


16 comments:

  1. ውድ አንድ አድርገኖች………..ስለምታደርጉት ልዩ የሆነ ጥረት መድሀኒዓለም ይክፈላችሁ…….አንድ ሀሳብ አለኝ…..በአሁን ሰዓት በአ/አ አድባራት በፒቲሽን አማካኝነት ምዕመኑ ሁሉ የመነኮሳቱን ድምፅ የሚደገፍበትን ሁኔታ እየተፈለገ ነው….እና እባካችሁ በዚህ ሰዓት ያለን ትልቁ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ይህ ብቻ ነውና በሁሉም ቦታ ይህ ተደርጎ በአስቸኳይ መከናወን እንዲችል ከአስፈላጊው የቤ/ያን ሁኔታ ከሚገዳቸው ሰዎች ጋር ተነጋግራችሁ መረጃ ብታደርሱን እላለሁ………..በዋልድባ ከመጡብን ነገ በሌሎች የማይመጡበት ሁኔታ የለምን በቶሎ እናስብበት…አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ይሁን….

    ReplyDelete
    Replies
    1. Selam all, can you please post the website to sign the petition. I couldn't find it and all my friends don't know where to find it. Please post it, that is the least we can do. thanks

      Delete
  2. ውድ አንድ አድርገኖች………..ስለምታደርጉት ልዩ የሆነ ጥረት መድሀኒዓለም ይክፈላችሁ…….አንድ ሀሳብ አለኝ…..በአሁን ሰዓት በአ/አ አድባራት በፒቲሽን አማካኝነት ምዕመኑ ሁሉ የመነኮሳቱን ድምፅ የሚደገፍበትን ሁኔታ እየተፈለገ ነው….እና እባካችሁ በዚህ ሰዓት ያለን ትልቁ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ይህ ብቻ ነውና በሁሉም ቦታ ይህ ተደርጎ በአስቸኳይ መከናወን እንዲችል ከአስፈላጊው የቤ/ያን ሁኔታ ከሚገዳቸው ሰዎች ጋር ተነጋግራችሁ መረጃ ብታደርሱን እላለሁ………..በዋልድባ ከመጡብን ነገ በሌሎች የማይመጡበት ሁኔታ የለምን በቶሎ እናስብበት…አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ይሁን….

    ReplyDelete
  3. What surprises me is that EPRDF tries to give some targa for those who tries to tell the truth. Are they planed to make everybody againest them? otherwise they couldn't say question of poletics with few individuals knowing that it is a question of all Oethodox christians except those like Aboy thehaye. I think it realy irritates people who are true chirstains and hate EPRDF but also those who are true chirstains and supporters of EPRDF b/c it is not issue of poletics rather issue of religion. He says "tsere selamoch and tsere limat" with out hestation. This shows that he is totaly authocratic talking democracy. Aboy thehaye don't start to attack the church today, he started attacked by interfirng to synods decision before 3 or 4 years. He was called "abune Thehaye" by some individuals due to his act on Synod. I think his mind is deteriorated like his hair.

    ReplyDelete
  4. anyone who can give me the right information?thanks

    ReplyDelete
  5. አባቶቻችን የዚህ አለም ኮተት ስልጣን ሱስ የለባቸውም አሳዛኝ የሚያደርገው ያ ሣይሆን የመንግስት ፍረጃ ነው ይሁን ግዜ የሰጠው ቅል… እኛም እንጮሃለን መንግስትም የሰለቸንን ውሸት ይዋሽ የናቁት የቅዱሳን አምላክ ይፈርዳል ፡፡

    ReplyDelete
  6. ውድ አንድ አድርገኖች………..ስለምታደርጉት ልዩ የሆነ ጥረት መድሀኒዓለም ይክፈላችሁ…….አንድ ሀሳብ አለኝ…..በአሁን ሰዓት በአ/አ አድባራት በፒቲሽን አማካኝነት ምዕመኑ ሁሉ የመነኮሳቱን ድምፅ የሚደገፍበትን ሁኔታ እየተፈለገ ነው….እና እባካችሁ በዚህ ሰዓት ያለን ትልቁ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ይህ ብቻ ነውና በሁሉም ቦታ ይህ ተደርጎ በአስቸኳይ መከናወን እንዲችል ከአስፈላጊው የቤ/ያን ሁኔታ ከሚገዳቸው ሰዎች ጋር ተነጋግራችሁ መረጃ ብታደርሱን እላለሁ………..በዋልድባ ከመጡብን ነገ በሌሎች የማይመጡበት ሁኔታ የለምን በቶሎ እናስብበት…አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ይሁን….

    ReplyDelete
  7. What always surprise me politicians they feel all things will be resolved just by " fabricated news and press release". Let me tell you the truth you will see results ... time will tell

    ReplyDelete
  8. ውድ አንድ አድርገኖች………..ስለምታደርጉት ልዩ የሆነ ጥረት መድሀኒዓለም ይክፈላችሁ…….አንድ ሀሳብ አለኝ…..በአሁን ሰዓት በአ/አ አድባራት በፒቲሽን አማካኝነት ምዕመኑ ሁሉ የመነኮሳቱን ድምፅ የሚደገፍበትን ሁኔታ እየተፈለገ ነው….እና እባካችሁ በዚህ ሰዓት ያለን ትልቁ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ይህ ብቻ ነውና በሁሉም ቦታ ይህ ተደርጎ በአስቸኳይ መከናወን እንዲችል ከአስፈላጊው የቤ/ያን ሁኔታ ከሚገዳቸው ሰዎች ጋር ተነጋግራችሁ መረጃ ብታደርሱን እላለሁ………..በዋልድባ ከመጡብን ነገ በሌሎች የማይመጡበት ሁኔታ የለምን በቶሎ እናስብበት…አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ይሁን….


    try to collect petition through the website or any other possible means

    ReplyDelete
  9. መፍትሄው በመቀናጀት እስከ መጨረሻው ይህን መንግሥት ያለን የሐይማኖት አጀንዳ መሆኑን ማሥረዳት ነው:: ዜጎች የመደመጥ መብት ሊኖረን ይገባል:: ማንም እየተኮሰ ሊገለን አይገባም:: ሰው በተሰበሰበ ቁጥር ከመሸበር ይልቅ መልካም ነገር መስራት ይሻል ነበር::ለደረሰብን በደል ሁሉ የቤተክህነቱም እጅ አለበት::

    ReplyDelete
  10. +++
    Always truth will be the winner eventhough burned, perscuted, or ------
    I don't think anyone against the construction has any other agenda but ptotect our Holy Monastery. We are against any activity close to our holy Monastery!
    I just wanted to ask concerned associations to propose to the EPRDF, Ethiopian Government to send an independent group of experts and journalists to the site and to let us know what is going on there! Otherwise what the government is doing is the same tactic of terrorizing those who speak up!

    ReplyDelete
  11. Aquwamachin And mehon Alebet Gedamu Akrabiya (Gedamun bayineka enkuwan) yaskuwar fabrika ayihonem! slezi hulachinm abiren enchuh.

    ReplyDelete
  12. I should also ask the same question, I never been confused by information before, this one is really confusing " anyone who can give me the right information?thanks"

    ReplyDelete
  13. ye'aboy Tsehaye eju endefetefete sayamrbet ezih derese ere lemehonu mot yemibal neger minew alasfera alachew? Mot hoy minew 4 Killo akababi yeteterakemutin hawltoch alnekachew alk? Patriarch tebiyew esu emerawalehu bilo yemiyasibew eminet be'esat sichenek yesew kebir liyademk hedo tegolete. ahunis endet astelachihugn meselachihu enante yemist lijoch.

    ReplyDelete
  14. egzeha ethiopan yetabek

    ReplyDelete
  15. I was the supporter of the government being a member paying my own part but now it becomes real that the government is lead by real mafias. I have never feel like this till now. I was thinking +vely. Currently I feeel sorry for what I did till now. I could struggle this bozene leaders. Diros kwonbedie min yitebekal. Derg was better for us (this is my current feeling). Lie, lie, lie always lie. It it shem to lie throughout ones life. I realize today that what the prime minister talks was lie and the opposers critisises is realy correct.

    Pleas Ato Meles think and do some good things in life. You did evel till last 50th otherwise no dought the people will through you out.

    ReplyDelete