Friday, September 21, 2012

ቀይ መብራት



  • ·        አንደኛ ……….. ጠቅላይ ሚኒስትር …….   ONLY JESUS (የሐዋርያ እምነት ተከታይ)
  • ·        ሁለተኛ ……….ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ….. MUSLIM
  • ·        ሶስተኛው …. ጠቅላይ ሚኒስር ለመሆን የታጩት ሰው ….. MUSLIM
(አንድ አድርገን መስከረም 10 2005 ዓ/ም)፡- አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ እና የቀድሞ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ፤ አቶ ደመቀ መኮንን የትምህርት ሚኒስትር ፤ አቶ ሶፊያን አህመድ የገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስትር ፤ እነዚህ  በስም የተዘረዘሩት ሶስት ከፍተኛ የሀገሪቱ ቱባ ባለስልጣናት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ከዚህ ዓለም በህይወት በተለዩበት ወቅት የኢህአዴግ ፓርቲ ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ቦታ ለውድድር ያቀረባቸው ሰዎች  ናቸው ፡፡ ፓርቲው ባደረገው ምርጫ መሰረት አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝን ሊቀመንበር ፤አቶ ደመቀ መኮንን ደግሞ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር አድርጎ መሾሙ የሚታወቅ ነው ፤ በቂ ድምጽ ያላገኙት በወ/ሮ አዜብ መስፍን የተጠቆሙት አቶ ሶፍያን አህመድ በሶስተኝነት ወደ ኃላ ቀርተዋል ፤ ነገ 11/01/2005 ዓ.ም ፓርላማው ምርጫውን በ99.6 በመቶ ድምጽ ያጸድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል ፤ አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ የOnly Jesus እምነት ተከታይ ናቸው ፤ ምክትላቸው አቶ ደመቀ መኮንንና አቶ ሶፍያ አህመድ ደግሞ የእስልምና እምነት ተከታይ ናቸው ፤ በመሰረቱ ደመቀ መኮንን ብሎ የእስልምና እምነት ተከታይ ይኖራል ብለው ሰዎች ላያስቡ ይችላሉ ፤  አቶ ደመቀም ከወደ ወሎ መሆናቸው ሰዎች ይናገራሉ ፤ አሁን እኛን ያሳሰበን ነገር የኢህአዴግ የፓርቲ ምርጫ አይደለም ፤ የነዚህ ሰዎች ሹመትም አይደለም ፡፡

የዛሬ 10 ዓመት ገደማ አቶ አሊ አብዶ በስልጣን በነበሩበት ጊዜ በጣም ቁልፍ የሆኑ አሁን ድረስ አከራካሪ የሆኑ ቦታዎችን በበታች ባለስልጣኖችና በእሳቸው ከለላ አማካኝነት በርካታ ቦታዎችን በሊዝና ከሊዝ ውጪ ሰጥተዋል ፤  አቶ አሊ አብዶ የአዲስ አበባ መስተዳድር በነበሩበት ጊዜ በቀጥተኛም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ከእሳቸው ትዕዛዝ በማውረድ በጥቂጥ ዓመታት ውስጥ 98 ያህል መስኪዶችን በአዲስ አበባ ማሰራት ችለው ነበር ፤ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙትን 132 አብያተክርስትያናት ለመስራት በ1826 ዓ.ም የታነጸው የቀራንዮ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ጀምሮ አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ለመድረስ የ170 ዓመት ጊዜያትን ወስደዋል ፤ ባሳለፍነው ጥቂት ዓመታት ብቻ በአዲስ አበባ የመስኪዶች ቁጥር በ40 ልቀው ተገኝተዋል ፤ በአሁኑ ሰዓት በየአብያተክርስቲያናቱ በጥቂት መቶ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙት መስኪዶች የአቶ አሊ አብዶ ለቀጣይ ትውልድ ያስቀመጡላቸው ትሩፋቶቻቸው ናቸው ፤ ለገሀር ባቡር ጣቢያ ውስጥ ከባቡር ጣቢያው መሬት  በኪራይ በመውሰድ ህገ ወጥ መስኪድ የተሰራው የዚያን ጊዜ ሰሞን ነው ፤ በአዲስ አበባ በየዓመቱ የቦታ ኪራይ እየተከፈለበት የቆመ መስኪድ ቢኖር የለገሀሩ መስኪድ አንዱ ነው(ዓመታዊ ኪራይ የተከፈለበትን ሰነድ በእጃችን አለ) ፤ ወደፊት መንግስት መሬቱን እፈልገዋለሁ እና ልቀቁ ቢል እንኳን ሊነሳ የሚችለውን ችግር መገመት አያዳግትም ፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም በለገሀር ባቡር ጣቢያ ግቢ ውስጥ በህገወጥ የተያዙትን ቦታዎች በ”አይናችን” ፕሮግራም ላይ ሲያቀርብ የመስኪዱን ነገር ማንሳት ግን አልፈለገም  ፤ ይህ ጥያቄ ቢነሳ ቦታው በኪራይ ከባቡር ጣቢያው እንደተከራዩ የሚያውቁት ጥቂት ሰዎች በመሆናቸው ችግር ይፈጠራል የሚል ስጋት አለ ፤ ሙስሊሞች በመንግስትና በአማኙ መካከል ባሉት ሰዎች አማካኝነት ይህን የመስኪድ ጥያቄ መፍታት የሚችሉ ባለስልጣናት በየቦታው አሏቸው  ፤ ይህ ጉዳይ በጥቂት በመንግስት ስልጣን ላይ በተቀመጡ የእምነቱ ተከታዮች አማካኝነት በቀላሉ ሊከናወን ችሏል ፡፡
የኢትዮጵያ ታሪክ ከተነሳ ቀድማ ስሟ የሚነሳው የኢትዮጵየ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ናት ፤ ኢትዮጵያ ትልቁ ታሪኳ ቤተክርስትያናችን ላይ ያጋደለ ሆኖ ያገኙታል ፤ ከዘመናት በፊት በአማርኛ እና በግዕዝ ቋንቋዎች በብራና ላይ ተጽፈው የሚገኙ ተዓምረ ማርያም ፤ የአራቱ ወንጌላውያን መጽሀፍቶች ፤ ገድሎች እና ድርሳናት የሚገኙት በኢትዮጵያ ባህልና ቱሪዝም ውስጥ ነው ፤ ከነዚህ ዘመን ከማይሽራቸው መረጃዎች በተጨማሪ በርካታ ንዋየ ቅዱሳት በተለያዩ የሀገሪቱ ሙዝየም ውስጥ ይገኛሉ ፤ ነገር ግን ባለፉት 15 ዓመታት የእነዚህ የበላይ ጠባቂ ሚኒስትር ማነው ? ብለው ቢጠይቁ መልሱን የተገላቢጦሽ ሆነው ያገኙታል ፤ ይህን የቤተክርስትያኒቱን ቅርስ የያዘ ተቋም መንግስት ባለፉት 10 ዓመታት አስተዳዳሪ አድርጎ የሾመው አቶ መሀመድ ድሪልን ነበር ፤  አቶ መሀመድ ድሪል ለ10 ዓመት ያስተዳደሩትን ሚኒስትር መስሪያ ቤት እሳቸው የኢትዮጵያ ኢምባሲ የግብጽ አምባሳደር ተደርገው በተሾሙበት ወቅት በእሳቸው ቀጥታ ጠቋሚነት ቀጥሎ የተሾመው ሰው የእስልምና እምነት ተከታይ ነው ፡፡ እንዴት ነው ነገሩ ? የሚያስብ ጉዳይ መሆኑን ብዙዎች ሲናገሩ ይሰማል፡፡ የዛሬ ዓመት ገደማ ሙስሊም ማህበረሰብ በሚሊኒየም አዳራሽ ትልቅ አውደ ርዕይ አዘጋጅተው ነበር ፤ በጊዜው ከመቶ ክፍለ ዘመኖች በፊት ተጻፈ የተባለ ብራና ተመልክተን እጅጉን ገረመን ፤ የገረመን ነገር በአዲስ ብራና 50 ዓመት እንዳስቆጠረ እንኳን በCarbon dating ያልተረጋገጠን ቁርዓን ከዘመናት በፊት ተብሎ መቅረቡ ነው ፤ ይህ ቁልፍ ቦታ ላይ የተቀመጡት ሰዎች አስተዋጽኦ ይኖርበት ይሆን? ብለን እንድናስብ አስገደደን  (እንዲህ አይነት ነገሮችን ወደፊት…እንመለስበታለን)
የዛሬ 2 ዓመት ገደማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የባህልና ቱሪዝም ቋሚ ኮሚቴ ሃላፊ የነበሩት የእስልምና እምነት ተከታይ ነበሩ ፤ የዛሬ ሶስት ወር ግድም በቴሌቪዥን የተመለከትናቸው የባህልና ቱሪዝም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሃላፊ ደግሞ ሌላ በቀድሞ ሃላፊ የተተኩ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ ሰውን ነው ፤ በመንግስት መሾሙ ብቻ ሳይሆን ቀጣይ ዱላ ተቀባይን አሳቢ ያደረገ ስራ እንደሆነ ያመላክታል ፤ በዚህ አይነት ውስጥ ለውስጥ ያለው ትስስር የጠበቀ ከመሆኑ የተነሳ ወደፊት የሚመጡትና በዚህ ቦታ ላይ የሚቀመጡ ሰዎች እምነታቸው ከዚህ ይወጣል የሚል እምነት የለንም ፤ ለዚህ ቦታ የሚመጥኑ በርካቶች እያሉ ለ15 ዓመታት የተለያዩ የስልጣን ተዋረድ ላይ ያሉን ሰዎች በአንድ እምነት የበላይነት ማስቀጠሉ ወደፊት ጥያቄ የሚያስነሳ ጉዳይ መስሎ ይታየናል፡፡
መሪ ስትራቴጂ
በእስልምና እምነት ውስጥ ያሉ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና ከበታች ያሉት ከፍተኛ ሃላፊዎች በተቻላቸው መጠን የመንግስትን ህግ ሳያፋልሱ እምነታቸው ሲያድሩ ተስተውሏል ፤ ከ4 ወር በፊት በፍርድ ቤት አካባቢ የሚገኙ 13 መንግስት የሾማቸው ዳኞችና አቃቢ ህጎች በጠቅላይ ፍርድ ቤት አንድ ቢሮ ውስጥ በእለተ ቅዳሜ ከስራ ሰዓት ውጪ ተሰብስበው ወቅታዊ ጉዳያቸውን መነጋገራቸው ፤ የወደፊት አካሄድ ማስቀመጣቸው ተደርሶበት ከመንግስት ቀጭን ትዕዛዝ መተላለፉን ገልጸን መጻፋችን ይታወቃል ፤ ይህ የመንግስትን እና የህዝብን ሃላፊነት ወደ ኋላ በማለት የሚደረግ ሴራ በአንድም ይሁን በሌሎች ቦታዎች ሲከናወን ማየትና አቤቱታ መስማት እየተለመደ መጥቷል ፤ ይህ ነገር ሀገሪቱን ወዴት እንደሚወስዳት አመላካች መስሎ ይታየናል ፤ በአሁኑ ሰዓት የእስልምና እና ሌሎች የእምነት ተከታዮች ያስቀመጡት ስትራቴጂ ቢኖር የመተካካት መንገድ አንዱ ነው ፤ ነገሩ  ኢህአዴግ እንደሚለው ዱላ ቅብብል መሆኑ የገባቸው ይመስላሉ ፤  እነዚህ ሰዎች በስልጣን ላይ ሳሉ በርካቶችን በእምነት የሚመስሏቸውን የማስጠጋት ስራ ሲሰሩ ይታያሉ ፤ ቀድሞ የነበረው ኃላፊ ሲነሳ በአካባቢያቸው የሰበሰቧቸውን ሰዎች ለኃላፊነት በማጨት እንዲሾሙ ያደርጋሉ ፤ የእነዚህ ሰዎች የእርስ በርስ ቁርኝት ከሚታሰበው በላይ መሆኑን የተመለከተ ሰው  አንዳች ጥርጣሬ ውስጡ መጫሩ አይቀሬ ነው፡፡
በሀረር ውስጥ የሚገኝውን ጀጎል ግምብ በማለት የሚጠራው በድንጋይ የታጠረ አካባቢ በእስልምና ከካ ቀጥሎ ሁለተኛ ቅዱስ ቦታ ለማድረግ ውስጥ ውስጡን ስራ እየሰሩ መሆኑን ነገሩን የሚያውቁ ከውስጥ ሰዎች መረጃው ደርሶናል ፤ ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመረው ይህ ስራ በውስጡ የሚገኙትን የክርስትና እምነት ተከታዮች ከፍተኛ ብር በመክፈል ቀስ በቀስ እንዲለቁ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል ፤ ከሀረር ዋናው በር እስከ መድኃኒዓለም ቤተክርስትያን የሚገኑት በግራና በቀኝ ያሉት የተለያዩ ከእስልምና ውጪ እምነት ያላቸው ሰዎች ሲሰሩበት የነበረው ቦታ በዚህ ዓይነት መንገድ እያስለቀቋቸው ይገኛል ፤ ይህን መረጃ ለማረጋገጥ ከጀጎል ውስጥ ባለፉት ሁለት ዓመታት ምን ያህል ሰው ለቆ እንደወጣ የተካሄዱትን ሽያጮች  ቢመለከቱ መልሱን ያገኙታል ፤ ሀረር ጀጎል ውስጥ ከ88 በላይ መስኪዶች ይገኛሉ ፤ ጀጎል እምብርቷ ላይ ደግሞ የመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ይገኛል ፤ ቤተክርስትያኑ ፊት ለፊት የጨለንቆ ሰማዕታት ሃውልት ቆሞ ይመለከታሉ ፤ የሰማዕታት በዓላቸውን በሚከብሩበት ጊዜ የመድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን በቪዲዮ ቀረጻ ወቅት እንዲገባ አይፈለግም ፤ ለምን ? ብለው ቢጠይቁ …….. !!!  ???  ፤ ቢቻል ቤተክርስቲያኑን በአንድ ቀን ሜዳ ሆኖ ቢያገኙት ደስታቸው ወደር የለውም ፤ “ሐረር የመቻቻል ከተማ” የሚለው ብሂል ውስጣቸው ገብተው ሲኖሩ ግራ ይገባዎታል…፡፡ 
የክልሉ ባለስልጣናት ከሞላ ጎደል ሁሉም በሚያስብል ሁኔታ ሙስሊም ስለሆኑ በተለያዩ ጊዜያት መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ላይ የሚደርሱት በደል ይህ ነው ብሎ መጥቀስ አይቻልም ፤ የመድኃኒዓለም የዓመት ክብረ በዓል ጊዜ ውሃ እና መብራት እስከማቋረጥ ይደርሳል ፤ ሬንቦ የሚባለው የሐረር ሙዚየም ቢገቡ እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ  ከሆኑ የማይነገርዎት ነገሮች አሉ ፤ ሙስሊም ከሆኑ ግን ውስጥዎ በክርስትያኖች ላይ ጥያቄ እንዲጭር በርካታ ነገሮች ይዘረዘርሎታል ፤ ከዓመታት በፊት አንድ ጊዜ ለጥምቀት የመድኃኒዓለም ታቦት ጥር 10 ወጥቶ ጥር 11 ቀን ወደ መንበሩ ለመመለስ በሰንበት ተማሪዎች ፤ በካህናትና በበርካታ ምዕመናን እየተመለሰ ሳለ ዋናውን በር ሜንጫ (የአካባቢው ጎራዴ መሳይ መሳሪያ) በያዙ በርካታ ሙስሊም ወጣቶች  በመያዝ አናስገባም አሉ ፤ ከደቂቃዎች በኋላ ግን ከሰማይ መብረቅ ወርዶ ካሉት 88 መስኪዶች ውስጥ የትልቁን መስኪድ ጨረቃና እና ኮከቧን ሲያነሳት የተመለከቱት ሰዎች በሩን መልቀቃቸው  ራሳቸው የሚናገሩት ተዓምር ነው ፤ 
ከዛሬ ሁለት ዓመት በእነዚህው ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖቻቸው አማካኝነት  የአልነጃሺን መስኪድ ከአክሱምና ከላሊበላ እኩል በአለም አቀፍ ደረጃ የማስመዝገብ ስራ መጀመራቸው ይታወቃል ፤ በጊዜው ትልቅ ተቃውሞ ያስነሳው “በኢትዮጵያ የእስልምና ሃይማኖትን የተቀበለ ንጉስ አለ” ፤ “በዓለም እስልምናን የተቀበለ የመጀመሪያው  ንጉስ የሃበሻው ንጉስ አስማን (ነጃሺ) ነው ይላሉ” ፤ “በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ የርቀት ሰላት(ሰላት አል ገይብ) የተሰገደበት ንጉስ የሃበሻው ንጉስ ነጃሺ ነው” የሚሉ ነጥቦች ናቸው ፤   የተሳሳተ የታሪክ መዛባትን የሚፈጥር መሆኑን የተገነዘቡ አይመስልም ፤ መጻህፍት ሙስሊም ንጉስ ኢትዮጵያ ላይ እንደነገሰ በጽሁፍ ተጽፎ አልተመለከትንም ፤ ታሪክን በመበረዝ የሚገኝ አንዳች አላማን ለማሳካት የሚደረግ አካሄድ እንቃወማለን ፤ ባይሆን አሁን በእኛ ዘመን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስሩ እና በምርጫው ላይ ተሳትፈው በሶስተኛ ደረጃ የተቀመጡት አቶ ሶፊያን አህመድን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት የቀረቡ ሰዎችን ተመልክተናል ፤ የወደፊቱን አናውቅም ፤ እዚች ሀገር ላይ የሚኖር ሁሉም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር የመሆን እድሉ ፤ በከፍተኛ የመንግስት ስልጣን ላይ ተቀምጦ ህዝብን የማስተዳደር መብቱን አንቃወምም ፤ ነገር ግን ይህን ከለላ በማድረግ የሚሰሩ ስራዎችን እንቃወማለን ፤  መተካካት የሚባለው ስትራቴጂ እምነትም መሰረት ባደረገ ሁኔታ እንዳይከናወን መንግስት የራሱን ስራ መስራት ይገባዋል፡፡ 
ይህ ክፍተት ይሞላ
በአሁኑ ሰዓት ሙስሊም ማህበረሰብ በእምነቱ ላይ ያለውን ጥያቄ ማንሳቱ ይታወቃል ፤ ህዝቡ ወክሎናል ያሉ 17 አባላቶቹን መምረጡም ይታወቃል ፤ መንግስት ለጥያቄያችሁ በቀበሌ ምርጫ ማካሄድ ትችላላችሁ የሚል መልስ መስጠቱን በመቃወም ሽብር ሲያነሱ አግኝቻቸዋለሁ ፤ ሲያስተባብሩ እና ነገር ሲጠነስሱ ነበር ያላቸውን 17ቱን ተወካዮች እስር ቤት ካስገባቸው ሳምንታት ተቆጥረዋል ፤ እነዚህ ሰዎች ፍርድ ቤት ሲቀርቡ በርካታ የአላማቸው ተጋሪ ሰዎች ፍርድ ቤት አካባቢ እየተሰበሰቡ ሁኔታውን እንደሚከታተሉ እየተመለከትን እንገኛለን ፤ አሁን ይህን ጉዳይ ከመንግስት ፤ ከሃይማኖት አባቶች እና በእስር ከሚገኙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጋር በመሆን ታሳሪዎች በመንግስት ስልጣን ላይ የተቀመጡ የእስልምና እምነት ተከታዮች መጅሊሱን ይቅርታ እንዲሉ እና ጉዳዩን በሰላማዊ መልክ እንዲፈታ ከፍተኛ ስራ ጀምረዋል ፤ በቅርቡም የታሰሩት ይቅርታ ጠይቀው እንደሚወጡ ምንጮች ይጠቁማሉ ፤ ይህ ሊሆን የቻለው በአሁኑ ወቅት የራሳቸው ሰዎች በመንግስት ከፍተኛ ስልጣን ላይ ስለሚገኙ ነው ፤ አሁን ወደ እኛ ስንመጣ ዋልድባ ገዳም ላይ የስኳር ልማት ሊሰራ አይገባም ካልን ወራቶች ተቆጠሩ ፤ ከመንግስት እና ከገዳሙ መነኮሳት መሃል በመሆን ነገሩን የሚያረግብ ስምምነት ላይ የሚያደርስ ባለስልጣን ግን መመልከት አልቻልንም ፤ ሁላችንም በቪኦኤ ላይ የገዳሙ አባቶች የሚናገሩትን እየሰማን ከመናደድ በቀር ምንም ያመጣነው ነገር የለም ፤ መፍትሄ ባንሻም ከድረ-ገጾች የሚጻፉትን ከማየትም አልቦዘንም ፤ የመንግስት ስልጣን ላይ ያሉ ስለ ቤተክርስቲያን ግድ የሚላቸውን ሰዎችን ማፍራት አልቻልንም ፤ በዚህ አካሄዳችን ወደ ፊት ሌሎች ስለኛ ካልመሰከሩ በቀር እኛ ስለ ራሳችን የምንናገርበት ሙግት የምንገጥምበት ጊዜ ይናፍቀናል ፤  የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሞት ሲለዩ ኢህአዴግ ሆኖ ለቦታው የሚመጥ ሰው ማየትም አልቻልንም ፤ ከላይ ካልተጠጉ ደግሞ ለትልቅ የኃላፊነት ቦታ መታጨት የማይታሰብ ነው ፤ ታዲያ እስከ መቼ ድረስ ሆድና ጀርባ ሆነን እንቀጥላለን ? ታዲያ ስለ ዋልድባ ማን ይናገር ? ፖለቲከኛ መሆን ሀጥያት ነው እንዴ ? ሙስሊሞች ለመንግስት እምነታቸውን በሚመለከት ጥያቄ ሲያነሱ  መንግስትና ጥያቄውን ያነሱት ሰዎች መካከል የራሳቸው ሰዎች ነበሯቸው ፤ እኛ ግን ለመንግስት ዋልድባን መሰረት አድርገን ጥያቄ ስናነሳ የጥያቄውን አግባብነት የሚያስረዳልን አንድም ሰው ከእኛና ከመንግስት መካከል የለንም ፤ ይህ ክፍተት ካተሞላ በቀር ወደፊት ለብዙ ችግሮቻችን መፍትሄ እንደማናመጣ እሙን ነው ፤ ወደፊትም  ይህ ክፍተት የሚሞሉ ሰዎች በቅርብ ርቀት አይታዩንም ፤ 
የወደፊት  ጫና 
አቶ ኃ/ማሪያም ደሳለኝ ደቡብ ክልል በነበሩበት ጊዜ የራሳቸውን የብሔረሰብ አካላት ወደ ስልጣን የመሰብሰብ ስራ ሲሰሩ ከሲዳማ ማህበረሰብ በኩል ለምን እኛስ ? የሚል ጥያቄ መነሳቱን የቅርብ ምንጮች ይጠቁማሉ ፤ አቶ ኃ/ማርያም ለዚሀ የሰጡት መልስ “ከእናንተ የተማረ ማህበረሰብ ስለሌለ ነው ካቢኔውን በተማረ ማህበረሰብ ያዋቀርኩት” የሚል መልስ ነበር ፤ ወደፊትም ከእኛ የሚመጥን ለሚንስትርነት ደረጃ የሚበቃ ሰው መኖር አለመኖሩን ጊዜው ሲደርስ የምናየው ነገር ይሆናል ፤ ይህ ማለት በየትኛው የስልጣን ተዋረድ ላይ የሚገኙ የተለያዩ ባለስልጣናት በእምነትም ሆነ በዘር አምሳያቸውን የማፈላለጋቸው ሁኔታ የማይቀር መሆኑን ነው ፤ እነዚህ ሰዎች እምነትን ወይም ብሔርን መሰረት በማድረግ ሰዎች በዙሪያቸው የሚሰበሰቡ ከሆነ አደጋው ሊከፉ ይችላል ፤ እነርሱን የሚሉ ሰዎች ጉዳዮቻቸው  በባለስልጣኖቻቸው ተጽህኖ የተነሳ በቀላሉ ሊፈቱ ይችላሉ ፤ እነዚህን ሰዎች በመተማመን ተጨማሪ የእምነት ተቋማት በሚያስፈልግም በማያስፈልጉም ቦታዎች ሊገነቡ ይችላሉ ፤ የመምረጥና የመመረጥ የመተካካት ሂደቱ እንደዚህ ባለህ የውስጥ ሴራ የሚቀጥ ከሆነ …… ቀይ መብራት ይታየናል፡፡በአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ቦታ እና የምክትሉን ቦታ የሚገኙ ሶስት ሰዎች ሲወዳደሩ አንድም የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ አለመኖሩ ነገን በሌላ አይን እንድናይ ያስገድደናል ፤ ካለን መረጃ ጥቂቶቹን እናንተው ዘንድ አድርሰናል ፡፡
ታቹን ስንርመጠመጥ (ለማይጠቅም ነገር ስንቦዝን) ላዩን መዘንጋት የለብንም ፤ ወደድንም ጠላንም የመንግስትን የተለያዩ  የስልጣን ተዋረዶች ላይ የተቀመጡ ሰዎች ቤተክርስትያኒቱ የምታነሳቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ቀጥተኛም ሆነ ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ ተጽህኖ ሊያሳርፉ እንደሚችሉ መዘንጋት የለብንም ፤  የማንኛውም እምነት ተከታይ ከፍተኛ ባለስልጣን ሆኖ ቢሾም ተቃውሞ የለንም እኛ የምንቃወመው ከጀርባ ያለውን ስራ ብቻ ነው ፤ ይህ ህዝብና መንግስት ያሸከማቸውን ኃላፊነት ሳይዘነጉ እምነታቸውን ሳያስቀድሙ በአግባቡ የሚሰሩ ሰዎች አይመለከትም ፡፡
በመጨረሻም
ስድስት ኪሎ አፍንጮ በር ጋር ተሰርቶ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኝው ግዙፍ መስኪድ እንዴት ቦታው ሊሰጣቸው ቻለ ? ማን ጠየቀ ? ማንስ ቦታውን ፈቀደ ? የነበረውን ውጣ ውረድ እንዴት አለፉት ? ስንት ካሬ ነው ? ስንት ተከፈለበት ? ሌሎች መረጃዎች ጠቃሚ ከሆኑ ወደፊት እናቀርባለን ፤ ወደ እኛ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ደግሞ  ቤተክህነቱ ውስጥ ጥቂት ለጥቅማቸው የቆሙ አቶ ጌታቸው ዶኒን የመሰሉ ሰዎች የባቦጋያ መድኃኒዓለምን 10 ሺህ ካሬ ታቦት ማደሪያ  ቦታ አሳልፈው ሲሸጡ እያየን ዝም ፤ በወይራ ቤተል አካባቢ የሚገኝውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የነበረውን የቦታ ይዞታ በቆርቆሮ አጥር ማጠር አቅቶን ከመንግስት ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ በመግባት የሰው ህይወት ሲያልፍ ብዙዎች ሲታሰሩ እያየን ዝም ፤ በተለያዩ በአዲስ አበባ ዳር አካባቢ የሚገኙ የቤተክርስቲያናችንን የጸበል ቦታ በፖሊስ ግብረ ኃይል መጥተው ሲያፈርሱብን ዝም ፤ዋልድባ ሲታረስ ዝም  ፤ አባቶች ሲሰደዱ ዝም ፤ ቤተክህነቱም ይሁን መንግስት በተሳሳተ ጎዳና ላይ ሲቆሙ ዝም ፤  “ዝም አይነቅዝ” የሚል የአማርኛ ብሂል የተስማማን ይመስለናል  !!!!!  ????  …… እነርሱ ደግሞ እንዴት ቦታ እንደሚገዙ ፤ እንዴት መስኪዳቸውን እንደሚተክሉ ፤ እነርሱ ሲሰሩ የባለስልጣኖቻቸው ጡንቻ ፤ እኛ ስንሰራ የባለስልጣኖቻችን ጉሸማ በንጽጽር ወደፊት እናቀርባለን  ፤ ዘምዘም ስለሚባለው በምስረታ ላይ ስለነበረ የሙስሊሞች ባንክስ ያውቃሉ ? እነማን ነበሩ አክሲዮኑን የገዙት? የትኞቹ ባለስልጣናት እና ባለሀብቶች ምን ያህል አክሲዮኖች ነበራቸው ? ለምን ተቋቋመ?  ለምንስ ፈረሰ ? ወደ ስራ ቢገባ የሚያሳድረው ተጽህኖ ምነ ነበር? (አስፈላጊ ከሆነ ብዙ አናዳጅ ነገሮች ቢኖሩም ከላይ ያነሳናቸውን ነጥቦች ወደ ፊት ከመረጃ ጋር  እናቀርባለን……)፡፡ 
ቸር ሰንብቱ…

24 comments:

  1. Ahunim metseley alebin.ledoro chachitoch rasua dorowa tasibalech enji amora atsiblachewm. silezih kegna yliq amlakachin fetariachin medhanitachin eyesus kirstos ysiblnal.ena benitsuh libona entsely.

    ReplyDelete
  2. edime lezih leneqeze menifesawi negn bayi tiwulid. tiwulidu bemenifesawi kaba teshefino yemenigist silitanin eyerake yigegnal. ayi tiwulid. ayimenifesawinet. yerasin tikim askedimo menifesawinet yemibal neger yelem.

    ReplyDelete
  3. ብላቴናዋ ከጀርመንSeptember 20, 2012 at 3:58 AM

    ሰላም አንድአድርገኖች እንደምን ከረማችሁ እንኩዋን ለሜቤታችን በአል አደረሳችሁ ላደረሰችሁን መረጃ እግዚአብሄር ይስጥልን በጣም እናመሰግናለን በትክክልም ቀይመብራት ከፊታችን እያበራብንነው በትክክልም የቤተክርስተያን አባቶች አሁንእንኩዋን ትንሽ ፋታና የማርያም መንገድ አግኝተዉ እንኩዋን ስለወልድባ ጉዳይ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር ያደረጉት ውይይትም ሆነ ያቀወረቡት የይግባኝ ጥያቄ የለም አሁንደግሞ ማንን እንደፈሩ አናውቅም ስለዚ አንድአድርገኖች መረጃ እንደሰጣችሁን የመፍትሄሀሳብም ጨምሩበትና አወያዩንና ባለን አቅምም ማድረግ የምንችለውንና ቤተክርስቲያናችንን መርዳት በምንችለው አቅማችን እንድንረዳ እድሉን ጠቁሙን በተረፈግን ገዳማውያንን በጸሎት ጻድቃንና ሰማዕታት በምልጃ እሜበታችንን ይዘው ቤተክርስቲያናችንን በረድኤቱ ይጠብቅልን ዘንድ ቸሩ መድሀኒአለምን ያሳስቡልን ዘንድ ጩሀንከልባችን እንጥራቸው እላለሁኝ ጼደንያማርያም አስራትሀገርዋን ታስባት አሜን.

    ReplyDelete
  4. It is good to have the information about Demeke. I was asking people since I have never heard of him any where if he has been in a church. So he is a Muslim. Most of us have been blaming the TPLF dictators and they left but still they give us to non believers. From Dictators to non orthodoxes.

    As to me these guys are political leaders not of religious leaders. Even though some people like Ali Abdu think that they can misuse their power to favor for their religion, that is illegal and should be stopped.We are the people who shall make this to stop. We shall follow each and every issue and forward to the anti corruption office if we see this.

    In the long run we should participate in politics. As EPDRF has bad politics it doesn't attract young, intellectual orthodox Christians to participate and grow up in it. However in any case we shall be part of it.

    We know most of the diaspora politicians are educated and have attachment to church but this doesn't help. The diaspora politicians cannot easily come and get power.


    ReplyDelete
  5. ejig betam enamesginalen bezihu bertu

    ReplyDelete
  6. Ene gin leyet yale astesaseb alegne mikniyatum kalefew 21 amet min temarin? Meles new weyis Aba Paulos betachinin yakeberew sim becha min yadergal endewim enzih yishalalu tekawemo endayimetabachew hayimanotachinim yakeberalu....beseme orthodox min agegnen endewim techekonin tebedelin afachihun yazu tebalin ahun gin yishalal abet endet malet yemichal yimeslegnal.....lehulum hulun yaderege amelak le zich betekerstiyan alelat.

    ReplyDelete
  7. አንድ አድርገኖች በጣም እናመሰግናለን!
    ችግሩ በጣም አሳሳቢ ነው:: ከዘመኑ ባለስልጣናት አንዱ የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ ሰሞኑን ገዛ ተጋሩ በተባለ ፖል ቶክ ላይ የሰጡትን መግለጫ ላልሰሙት ማሰማት ይገባል:: አቶ ስብሐት እንዲህ አሉ "ሥልጣንን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይና ከአማራ መንጭቀን ወስደናል ስንታገል የኖርነው ለዚህ ነውና" ይህ ንግግር አያሳዝንም??????!!!!! ስለዚህ ወደድንም ጠላንም እውነቱ አሁን ሃገሪቱን እየገዛ ያለው መንግሰት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለማጥፋት ከመጀመሪያው እቅድ እንደነበረው አሁንም ያንን በማሳካቱ መደሰቱን ከመስራቾቹ አንዱ በሆኑት ሰው አንደበት መስማታችን በእውነት ቀይ መብራት ነው:: ወደፖለቲካ ሥልጣን የሚጠጋ ሰው ኦርቶዶክስ እንዳይሆን የተፈለገበት አቢይ ምክንያት ሃይማኖትዋ ክነጭራሹ እንድትጠፋ መንግሰት ባለው ጽኑ ፍላጎት መሆኑን መረዳት ይገባል:: የሕወሀት ማኒፌስቶ(ሲመሰረት የተጻፈ የአባላት ስምምነት) ኦርቶዶክስ ተዋህዶን በተመለከተ የጻፈውን ስናነብ ደግሞ የተደገሰልን ጥፋት በደንብ ይገባናል:: እናም ሰማዕትነት ከፍሎ ተዋህዶን ማዳን ጊዜ ሊሰጠው አይገባምና እንመካከር! ዋጋ እንክፈል! ቤተክርስቲያናችንን እናድን አደራ አደራ አደራ በልዑል እግዚአብሔር ሥም!

    ReplyDelete
    Replies
    1. Orthodox Tewahdo Church is the symbol of Unity and Ethiopianism. The church is store house of Ethiopian history and independence. Those who want to disintegrate Ethiopia to small powerless ethnic based states are fighting Tewahdo to implement their plan of disintegrating Ethiopia. Be aware that unless we stand together we will end up in a disintegrated Ethiopia with no more history and Tewahdo. Lets Pray, pray, pray and do something together please?

      Delete
  8. If Hilemariam and Demeke are spentig a time to attack Orthodox Church, we don't be quiet any more. We don't stop praying and also we protest with spritual brave.

    ReplyDelete
  9. please, let us come together for our church members unities. we hate each others, no respects for each others. some gave bad names to our church members like tehadesso. I don't think not good ideas for our future church history.and unities, that why we loosing so many opportunity to our church and members. we need to ask our self regarding what is my faith ? really, do you love each others according Holy Bibles.? instead of blaming somebody, ask your self. which one is right and wrong way. unity is very important for all of us...in the future we gonna loose a lot of things. Be smart.........

    ReplyDelete
  10. ብዙ ከማውራት ብዙ ብንጸልይ ጥሩ ነው አስተያየቱ ሁሉም ጥሩ ነው እኛም በዚህ በጀርመን የምንገኝ ሕዝበ ክርስቲያን በጣም የተሰቃየንበት ጉዳይ የምንፍቅና ካባ አርገው ወደ መቅደስ የገቡትን ትኩላዎች ማውጣት ነው። እግዚአብሔር መልስ አለው አሁንም አምናለሁ የሙኒክ ገብርኤል ቤ/ክ መልስ ያየ ሁሉ ሊረዳ ይገባል ቅዱስ ገብርኤል ሆይ ና ወደኛም ወደ ፍራንክፈት ማርያም እንዲሁም ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ አሜን.
    ማሳሰብ የምፈልገው ግን የአስራት ሀገር ናት እያልን ተኝተን በኋላ ጉድ እንዳንሆን እናስብበት እላለሁ ጸሎት፤ አንድነት ፤ እንዲሁም ሥራ ያስፈልገናል በመላው ዓለም ለምንገኝ የኦርቶዶክስ ልጆች ።
    የጀርመን ነዋሪ ኢትዮጵያዊ!!!

    ReplyDelete
  11. Selam Andadrigen editors,
    The Article is so awesome based on facts and it makes us to rise from our night mare. As u suggested us the way forward we have responsibility to defend and protect our faith. Specially,the youth of TEWAHIDO ought take the very responsibility in its shoulder.
    By the way 10 years back I heard the prophecy of an hermit who said that 'ETHIOPIA WILL GOVERN BY MUSLIM LEADER SOON". Now I think we are in the verge of this process. More to the point, Mahibere Kidusan is often warn us about the threats of Muslim expansion in governmental administration and building of mosques nearest of us.
    Hence, ALL TEWAHIDO BELIEVERS WE MUST WAKE UP!!!

    ReplyDelete
  12. Eski ante tawikaleh amlakachin endecherinetih new enji ende bedelachin ayihun min yishalal ere medhaniyalem ebakih mela aleh echin betekristiyan mela belat egna eko akim yelenim akim eko yalew ante gar new negerin eko bedekika ante tilewitaleh ebakih lewitilin ebakachu wid ye ortodox lijoch beyetignawim ager yalachu atibikachu tseliyu. amlakachin tareken bedekika melewet yichilalina tarikin endilewitilin entseliy egziyabher yirdan.

    ReplyDelete
  13. አንድ አድርገኖች በጣም እናመሰግናለን!
    ችግሩ በጣም አሳሳቢ ነው:: ከዘመኑ ባለስልጣናት አንዱ የሆኑት አቶ ስብሐት ነጋ ሰሞኑን ገዛ ተጋሩ በተባለ ፖል ቶክ ላይ የሰጡትን መግለጫ ላልሰሙት ማሰማት ይገባል:: አቶ ስብሐት እንዲህ አሉ "ሥልጣንን ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታይና ከአማራ መንጭቀን ወስደናል ስንታገል የኖርነው ለዚህ ነውና" ይህ ንግግር አያሳዝንም??????!!!!! ስለዚህ ወደድንም ጠላንም እውነቱ አሁን ሃገሪቱን እየገዛ ያለው መንግሰት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ለማጥፋት ከመጀመሪያው እቅድ እንደነበረው አሁንም ያንን በማሳካቱ መደሰቱን ከመስራቾቹ አንዱ በሆኑት ሰው አንደበት መስማታችን በእውነት ቀይ መብራት ነው:: ወደፖለቲካ ሥልጣን የሚጠጋ ሰው ኦርቶዶክስ እንዳይሆን የተፈለገበት አቢይ ምክንያት ሃይማኖትዋ ክነጭራሹ እንድትጠፋ መንግሰት ባለው ጽኑ ፍላጎት መሆኑን መረዳት ይገባል:: የሕወሀት ማኒፌስቶ(ሲመሰረት የተጻፈ የአባላት ስምምነት) ኦርቶዶክስ ተዋህዶን በተመለከተ የጻፈውን ስናነብ ደግሞ የተደገሰልን ጥፋት በደንብ ይገባናል:: እናም ሰማዕትነት ከፍሎ ተዋህዶን ማዳን ጊዜ ሊሰጠው አይገባምና እንመካከር! ዋጋ እንክፈል! ቤተክርስቲያናችንን እናድን አደራ አደራ አደራ በልዑል እግዚአብሔር ሥም!

    ReplyDelete
  14. Chegeru ekoo egna emenetachen beafachen lay hono new mekeraw yebezabin ena serachen kemgibarachen yeteleyaye honoal ke Germen yalkew ewy egnam Germen yaleew sewoch minadergewen senmegebar chegir enastekakel egziabher yiredanal

    ReplyDelete
  15. Dear Andadrgen
    Thanks alot for the great information, what exactly the government is taking steps as they try to destroy but (can not)Ethiopian Orthodox Tewahedo church.
    GOD will punish them the punishments of punishment. We keep praying we will see soon the result as we saw and heard with the two previous situations.

    MAY GOD DEFEND OUR TEWAHEDO.

    Pls read the following article

    የኢሕአዴግ ቤተ ክርስቲያንን የተመለከተው “ፖለቲካዊ ትንታኔ” ገና ከትግሉ ዘመን ጀምሮ ፈር በያዘ መልክ የተጠናና አቋም የተያዘበት እንደሆነ የህወሐት መሥራች አረጋዊ በርሄ ለዶክትሬት ዲግሪ ማሟያ ባደረጉት የምርምር ሥራቸው (A Political History of the Tigray People’s Liberation Front (1975-1991): Revolt, Ideology and Mobilisation in Ethiopia/ Amsterdam 2008) ላይ ጽፈውልናል። የፓርቲው ሃይማኖትን በተመለከተ የያዘው ይህ አቋም በተለይም ነባሮቹን የኢትዮጵያ ቤተ እምነቶች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እና እስልምናን የተመለከተ መሆኑን፣ ኮሚኒስታዊ ፓርቲዎች ሁሉ ባላቸው “የጨቋኝ - ተጨቋኝ” ትንታኔ መሠረትም እነዚህ ሁለቱ ቤተ እምነቶች በተለያየ ጎራ እንዲቀመጡ መደረጋቸውን፣ ክርስትና ጨቋኝ፣ እስልምናም ተጨቋኝ ተብሎ መፈረጁን አንብበናል።

    ዶ/ር አረጋዊ ባብራሩት የኢሕአዴግ ትንታኔ መሠረት “ቤተ ክርስቲያን ከቀድሞቹ መንግሥታት ጋር “በነበራት ቁርኝት” ከገዢው መደብ ጋር የተሰናሰለ የጥቅም እና የጨቋኝነት ግንኙነት ነበራት። በነዚህ ረዥም የጭቆና ዓመታት ከተጨቆኑት መካከል ደግሞ ሙስሊሞች” ይገኙበታል፤ ስለዚህም ኢሕአዴግ ይኼንን የጭቆና ቀንበር “ለመስበር” እና እኩልነትን ለማስፈን የተከተለው ፖሊሲ፣ “ቤተ ክርስቲያንን ማምከን/ፍሬ ቢስ ማድረግ” እና “ሙስሊሞችን ማንቀሳቀስ” ("neutralizing the Church and Mobilizing Muslims) ነው። (ገጽ. 300)

    እንደ ዶ/ር አረጋዊ ገለጻ ከሆነ “በኢህአዴግ እና በቤተ ክርስቲያን መካከል የነበረው ግንኙነት ከመጀመሪያው ጀምሮም ችግር ያልተለየው” ነበር። የትግሉ ማዕከል ከነበረው ከትግራይ ስንነሣ በሕዝቡ መካከል የሚደረገው ማንኛውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኒቱ እና በአገልጋይ ካህናቷ ቁጥጥር ሥር የወደቀ ነው። ሰርጉ፣ ክርስትናው (የሕጻናት ጥምቀቱ)፣ ቀብሩ እና በጎረቤቶች አለመግባባት ወቅት ያለው ሽምግልናውና እርቁ በሙሉ የሚፈጸመው በቤተ ክርስቲያን በኩል ነው። ያንንም ለማከናወን ደግሞ በቂ ካህናት አሉ። በተጨማሪም እያንዳንዱ ቤተሰብ ሕይወቱን የሚከታተሉ አባቶች (የነፍስ አባቶች) በነፍስ ወከፍ አለው። ስለዚህም በያንዳንዱ አካባቢ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሕዝቡ ሕይወት ጋር ከፍተኛ ቁርኝት አላት።

    በሁለተኛ ደረጃ ቤተ ክርስቲያን በሕዝቡ እና በመንግሥታት መካከል ድልድይ ሆና ትሠራለች። ዶ/ር አረጋዊ እንዳሉት “ቤተ ክርስቲያኒቱ ሁልጊዜም ካለፉት ነገሥታት ጋር አብራ ቆማለች፤ መንግሥታቱም ቤተ ክርስቲያኒቱ እንድትኖር፣ እንድትስፋፋ እና አንድነቷ እንዲጠበቅ” ረድተዋታል። ቤተ ክርስቲያን ከቤተሰብ ጀምሮ እስከ አገር አቀፍ ድረስ ተቋሟን ከመዘርጋቷም በላይ በመንግሥትና በተቀናቃኞች መካከል ለሚፈጠር ቅራኔ በአስታራቂነት እስከመግባት ትደርሳለች። ምእመናኗም ለመንግሥታቸው እንዲገዙ ታስተምራለች፣ አገራዊ ብሔርተኝነት እንዲዳብርም በማዕከልነት አገልግላለች። ባንዲራን የመሳሰሉ አገራዊ ምልክቶችን በበዓላቷ ሳይቀር ከፍ አድርጋ በማውለብለብ ብሔራዊ ማንነትን (national consciousness) ገንብታለች። የቤተ ክርስቲያን በዓላት ካለ ሰንደቅ ዓላማ በጭራሽ አለመከበራቸውን ልብ ይሏል።

    ReplyDelete
  16. በሦስተኛ ደረጃ በየዘመኑ የነገሡ ነገሥታት በቤተ ክርስቲያን እስካልተቀቡ ድረስ ንግሥናቸው ተቀባይነት አልነበረውም። ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን የነገሥታቱ ሥልጣን አረጋጋጭ እና ወሳኝ ሆና አገልግላለች። በአኩሱም ጽዮን ለሚፈጸመው ለዚህ ቅብዓ መንግሥት ነገሥታቱ በበኩላቸው ርስት እና ጉልት በመሥጠት ቤተ ክርስቲያኒቱን ጠቅመዋል። አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ሳይቀሩ መተዳደሪያ እንዲኖራቸው፣ የአጥቢያው ምእመንም እንዲንከባበከባቸው፣ አገልጋይ ካህናቱም የሚያስፈልጋቸውን ነገር እንዲያገኙ የአጼዎቹ አስተዳደር ጠቅሟቸዋል።

    “አጼያዊው አስተዳደር ከወደቀና ቤተ ክርስቲያን ርስት ጉልቷን ሁሉ ካጣች በኋላ በወታደራዊው መንግሥት እና በሰሜን በሚዋጉ ተቃዋሚዎች መካከል አጣብቂኝ ውስጥ ገባች” ይላሉ አረጋዊ በርኸ። “ኢ.ዲ.ዩን በመሳሰሉ ፓርቲዎች ላይ ተስፋ አሳድራ ብትቆይም ሳይሳካ” ቀርቷል።

    እንደ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ገለጻ ከአብዮቱ በኋላ የትግራይ ሕዝቦች ነጻ አውጪ ግንባር (ሕወሐት) ቤተ ክርስቲያን በሕዝቡ መካከል ያላትን ሚና እና አብዮቱን ከሚቃወሙ ኃይሎች ጋር ሊኖራት የሚችለውን ግንኙነት ተረዳ። ግንባሩ በሚያደርገው ትግል ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ከመንገዱ ላይ እንደተደነቀረች እና በጥንቃቄ ሊይዛት እንደሚገባ አወቀ። ቤተ ክርስቲያኒቱን የትግሉ አካል እና ደጋፊ ማድረግ እንደሚገባው ተገነዘበ። ስለዚህም ሊያዳክሟትና እና ለዓላማው መሳካት እንድትቆም ሊያደርጉ የሚችሉ ተከታታይ ሥራዎችን ሠራ - ይላሉ።

    ግንባሩ በመጀመሪያ የወሰደው ርምጃ ወታደራዊው መንግሥት ያወጀውን “የመሬት ላራሹ” አዋጅ ባለመቀልበስ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብቷ፣ ንብረቷ፣ መሬቷ እንዳይመለስላት ማድረግ፣ በዚህም ጉልበቷን ማዳከም እና ለሺዎች ዓመታት የነበራትን አቅም በመስበር ከአማኞቿ ጋር አዲስ ውል እና ቃል ኪዳን እንድትገባ ማስገደድ (በምእመናን ምጽዋት ላይ እንድትደገፍ ማድረግ)፣ ልትረዳቸው የምትችላቸውን የተቃውሞ ኃይሎች እንዳትረዳ ደካማ ማድረግ ነው። ቤተ ክርስቲያን የነበራትን መሬት ራሱ ፓርቲው በመውረስ ለሕዝቡ ለማከፋፈል ከመሞከሩም በላይ የቤተ ክርስቲያንን መሬት ለመጠቀምና ለማከፋፈል ፍላጎት በሌለባቸው አካባቢዎችም ፓርቲው ራሱ በመቆጣጠር ተሰሚነቱን ከፍ ለማድረጊያነት ተጠቀመበት።

    የቤተ ክርስቲያኒቱን ተጽዕኖ በማዳከሙ በኩል ፓርቲው በሁለተኛ ደረጃ የወሰደው ርምጃ በማንኛውም የዕለት ተዕለት ግንኙነቱ ማለትም (ሰርጉ፣ ክርስትናው (የሕጻናት ጥምቀቱ)፣ ቀብሩ እና በጎረቤቶች አለመግባባት ወቅት ያለው ሽምግልናውና እርቁ) ሕዝቡ ዓይኑን ከቤተ ክርስቲያን ላይ እንዲያነሣ እና ፓርቲው በሚያቋቁማቸው ተቋማት ላይ እንዲያደርግ በዚህም ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊነቷ ዝቅ እንዲል ማድረግ ነው። እንደታሰበውም ቤተ ክርስቲያን የሸምጋይነት ተግባሯን እንዲሁም ቦታዋን አጣች።


    በሦስተኛ ደረጃ ፓርቲው ያደረገው ነገር ተከታታይ ሴሚናሮችን ለተመረጡ ካህናት ማካሔድ ነበር። ይህ እ.ኤ.አ በ1979 የተካሔደው ሴሚናር ዓላማ በትግራይ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ከመላው አገሪቱ ካለው መዋቅራዊ አሠራር በመለየት እና በመነጠል፣ የትግራይ ብሔርተኝነትን በማጠናከር ፓርቲው ለተነሣለት ዓላማ እንዲጠቅሙ ማድረግ ነው። የቤተ ክርስቲያኒቱን ተጽዕኖ ለመቋቋም ትግራዋይነትን እና የትግራይ ብሔርተኝነትን መቀስቀሱና ማራገቡ ትልቅ አስተዋጽዖ ሊያደርግ ቻለ። በወረዳ ደረጃ የነበረው የትግራይ ካህናት ተከታታይ ሴሚናር የተከናወነው “በአንደበተ ርቱዑ የቲዮሎጂ ምሩቅ በገብረ ኪዳን ደስታ” ሲሆን የውይይቱ ርዕሰ ጉዳይም የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን አስተዳደርን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ድርጅትን ዓላማ በተቀበሉ እና “ትግራዋይነትን እና የትግራይ ግዛትን በሚያስፋፉ ካህናት” መተካት ነበር።

    (ማስታወሻ፦ የነዚህ ሴሚናሮች እና ቀረጻዎች ውጤቶች የሆኑ አያሌ ካህናት፣ መነኮሳት እና ጥቁር ራሶች ዛሬ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተለያዩ መዋቅሮች ላይ ተቀምጠዋል። ብዙዎቹም ቤተ ክርስቲያን የምትፈልግባቸውን በማድረግ እና ፓርቲያቸውን በመታዘዝ መካከል ተወጥረው የሚኖሩ ሆነዋል። የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎትም በፓርቲ መነጽር ብቻ የሚመለከቱ ናቸው።)

    ይህ እንቅስቃሴ “የአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ካህናትን እና ተርታ ምእመናንን በማንቀሳቀስ እና በማነቃቃት” የተከናወነ ሲሆን ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስተዳደር በመነጠል እና በመገንጠል፣ ዋናዋን እናት ቤተ ክርስቲያን በማዳከም ላይ ያተኮረ ነበር። በአቶ ስብሐት ነጋ የሚመራ የስለላ መዋቅር የተደራጀ ሲሆን የፓርቲውን ሰላዮች በመነኮሳት እና በካህናት ስም ደብረ ዳሞን በመሳሰሉ ዋና ዋና ገዳማት በማስገባት እና ቤተ ክርስቲያኒቱን በመቆጣጠር ላይ ሥራ ተሠርቷል። እ.አ.አ በ1979 የተጀመረው የካህናት ተከታታይ ሴሚናር አድጎ በ1987 እና በ1989 ክልላዊ እና አገር አቀፋዊ የካህናት ጉባኤዎች ‘ነጻ በወጡ መሬቶች ላይ” ሊካሔዱ ችለዋል። ዓላማውም የቲ.ፒ.ኤል.ኤፍን ዓላማ የተቀበለች ቤተ ክርስቲያን በትግራይ መመሥረት ነበር። በውጤቱም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት ልትከፈል ችላለች፣ አንደኛው በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር፤ ሌላኛውና ሁለተኛው ደግሞ በፓርቲው ሥር ያለ አስተዳደር። ሁለቱም አስተዳደሮች ፓርቲው መቐለን እስከተቆጣጠረበት እስከ 1990 ድረስ በትግራይ ውስጥ በትይዩ ሲሠሩ ቆዩ። መቐለ “ነጻ ሲወጣ” አንደኛው አስተዳደር አበቃለት፣ በፓርቲው አስተዳደር ተተካ ሲሉ ያትታሉ።

    ReplyDelete
  17. Freedom of Religious

    After PM Hailemariam Desalegn sworn, he stated that, different religions that approved by the rule of government have to have freedom and equality. Inaddition, religions have to conform their faith without interfrence and biased. These seems to me a good idea, but we will see how they change it into practical. God bless Ethiopians and Orthodox Church.

    ReplyDelete
  18. poletikawin inante ina dejeselam selayochu gibubeta tadya. hulum endechilotaw new!!!!!

    ReplyDelete
  19. wegenoch, qininetin yemesele neger yelem. yenegerochin bego gesita memelket berasu talaqinet new:protestantim honu muslimoch wede siltan bimetu yemingemegimacew le ethiopia hizb lehageracew bemiyadergut tegbar enj behaymanotacew mehon eyelebetim. minalbat ke ortodox wuch yale wegen siltan meyaz yelebetim yemil amelekaket yalew sew kale siltan yemisetim hone yeminesa fetari aenj enante aydelachihum.bemeles yederese beaba pawlos yedere timihirt lihone betegeba neber enesu siltan muchch bilu fetari beqachihu bilo wesedacew.ahunim tigist yasfelgal teb achari athunu.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Yih yemogn asteyayet new. Ethiopia yeEgziabher ager nat. protestantoch ena muslimoch siltan yemifelgubet wana alama lakiwochachew endetelemut Tewahdon lematfat new. Ahun laygebah yichlal behuala Tewahdon kadeqequat behuala yigebahal. Endih aynet kentu asteyayet lemetsaf kemenesatih befit ye Ethiopian tarik mermir.

      Delete
  20. minew melkam melkamu bitayachu ESATv honachubin lib yalew chrstianima ahizabochun or whatever wede andit imnet melisilin bilachu betseleyachulachew??! man yawqal enezi sewoch nege biqeyeru??????

    ReplyDelete
  21. Who said that the only religion in Ethiopian is orthodox? Everyone has the right to have its religion and the Government has to treat all of them equally and fairly. Why don't you first solve your own problem inside your church rather than to criticize others.

    ReplyDelete