Wednesday, September 26, 2012

ዋልድባ ገዳምን ለማፍረስ የተነሳ ሥራው ብቻ ሳይሆን እሱም ይፈርሳል





  • በዋልድባ ዛሬማ ወንዝ ላይ የተሰራውን ድልድይ በመብረቅ ተመ
  • በአቲካ ወንዝ ላይ የተሰራው የሸንኮራ ማልማያ ግድብ  በዚሁ ቀን ፈራርሷል
  • የገዳማውያኑ እንግልት እንደቀጠለ ነው
እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፦ ወደ ፈርዖን ግባ እንዲህም በለው። እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ። ለመልቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ እኔ አገርህን ሁሉ በጓጕንቸሮች እመታለሁ ፤ ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል፥ ወጥተውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህም፥ ወደ ባሪያዎችህም ቤት፥ በሕዝብህም ላይ፥ ወደ ምድጆችህም፥ ወደ ቡሃቃዎችህም ይገባሉ ፤ ጓጕንቸሮችም በአንተ በሕዝብህም በባሪያዎችም ሁሉ ላይ ይወጣሉ። ኦሪት ዘጸአት 8  ፤ 1-4 አሁንም እግዚአብሔር በዋልድባ ጉዳይ እየተናገረ ይገኛል ፤ ከወራት በፊት በዋልድባ ላይ የተከሰተውን ነገር ሰምቶ ያላዘነ ሰው የለም ፤ በቦታው የሚገኙ መነኮሳትም ከአቅማቸው በላይ ሲሆን “ይግባኝ ለክርስቶስ” ብለው አሳልፈው ሰጥተዋል ፤ መንግስትና በአቋሙ በመጽናቱ እግዚአብሔር ባሳለፍነው ወር አጋማሽ ላይ በሚናገርበት መንገድ ተናግሯል እየተናገረም ይገኛል ፤ አሁንም  በተደረገው ነገር ከመማር ይልቅ እልህ የመጋባት ነገር እየተመለከትን እንገኛለን ፤ ይህ ለማንም አይጠቅምም፡፡

“ፈርዖንም ጸጥታ እንደሆነ ባየ ጊዜ ልቡን አደነደነ እግዚአብሔርም እንደተናገረ አልሰማቸውም። እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ አሮንን፦ በትርህን ዘርጋ፥ በግብፅም አገር ሁሉ ቅማል እንዲሆን የምድሩን ትቢያ ምታ በለው። እንዲሁም አደረጉ አሮንም እጁን ዘረጋ፥ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታው፥ በሰውና በእንስሳም ላይ ቅማል ሆነ በግብፅ አገር ሁሉ የምድር ትቢያ ሁሉ ቅማል ሆነ። ጠንቋዮችም በአስማታቸው ያወጡ ዘንድ እንዲሁ አደረጉ፥ ነገር ግን አልቻሉም ቅማሉም በሰውና በእንስሳ ላይ ነበረ።ጠንቋዮችም ፈርዖንን፦ ይህስ የእግዚአብሔር ጣት ነው አሉት የፈርዖን ልብ ግን ጸና፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ አልሰማቸውም።  ኦሪት ዘጸአት 8  ፤ 15-19 ፈርዖን በእግዚአብሔር ላይ ልቡን አደነደነ ፤ እግዚአብሔር እንደተናገረም አልሰማቸውም ፤ እግዚአብሔር ስተዋለ በፍጥረቱ ሁሉ ይናገራል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመሞታቸው ከ4 ቀናት በፊት ግዙፍ የሆነ ዋርካ በቤተመንግስት ወድቋል ፤ ይህን ብዙ ሰው እንደፈለገው ትርጓሜ ሰጥቶታል ፤ ፈርኦር እግዚአብሔር ያደረገውን ነገር በመገዳደር ልቡን አደንድኗል ፤ የሆነውንም ነገር በስልጣኑ በመመከት ለመገዳደር ሞክሯል ፤  “የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር” መጽሐፈ ነገሥት ካልዕ 19፤ 31 እንደተናገረም ማንም አላስተዋለም ፤ “እግዚአብሔርም ምድሩን በትቢያ መታው ፤ ጠንቋዮችም እጁን መቋቋም አልቻሉን እነርሱም ይህ የእግዚአብሔር እጅ ነው አሉት ፤ ፈርኦን ሊሰማ አልወደደም”

 ፈርኦን ወደፊት የሚነሱ አሁንም ያሉ የብዙ ነገስታት ምሳሌ ነው ፤ የእግዚአብሔርን ኃይል የሚፈታተኑ የብዙዎች ተምሳሌት ነው ፤ አሁንም በዋልድባ ገዳም የሚደረገውን የስኳር ልማት በመቃወም ብዙዎች መነኮሳት ተቃውሟቸውን በአደባባይ አሰምተዋል ፤ ፈርኦናውያን ግን በጉልበታቸው ተማምነው ሊሰሟቸው አልወደዱም ፤ ጉልበትም የእግዚአብሔር መሆኑን አላወቁም ፤ አባቶችን ቤተመንግስቱ “እናንተ ደፋሮች” ብሎ ቀልባቸውን ነሳቸው ፤ ቤተክህነቱ በዝምታ አለፋቸው ፤ እነዚህ አባቶች በፍልሰታ አንባቸውን ወደ አምላክ አፈሰሱ ፤ “መልስ ካልሰጠህን ይህን ዳዊት እና ይህን መቋሚያ ተመልሰን አናነሳም” ብለው አምርረው ጥለው ወደ በዓታቸው አመሩ ፤ የንጹዓን  አባቶችን እንባ መሬት እንዳትወድቅ የማይፈቅድ አምላክ ……………….ስራውን እያከናወነ ይገኛል ፤ አያንቀላፋም የተባለውን ማን አስተዋለ፡፡


አሁንም በዋልድባ ገዳም ላይ የሚደረግን የመነኮሳት አባቶችን ማንገላታት ከዚህ በላይ ጉዳት እንደማያመጣ እርግጠኞች ሆነን መናገር አንችልም ፤ የላመ እና የጣመን በመተው እርሱን ብለው እድሜ ዘመናቸውን በዱር በገደል ያሳለፉ አባቶቻችንን አምላክ ጸሎታቸውን ዝም አይላቸውም ፤ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው ያሉትን አባቶች እንዳሉ እንወቅ ፤ ላስተዋለ የሆነው እና የተደረገው ነገር በቂ ነው ፤ ላላስተዋለ ግን የዚህን አስር እጥፍ ቢደረግ ያው ነው ፤ 21 ዓመታት በስልጣን ሳላችሁ ከዚህ የከፋ ጊዜ አይታችኋል ብለን አናስብም ፤ እጃችሁን ከገዳማትና ከአብያተክርስትያናት ላይ ካላነሳችሁ ግን ከዚህ የባሰ ነገር ሊመጣ ይችላል ፤ እርሱ ሁሉን ማድረግ ሁሉን ማከናወን ይችላል ፤ እንባችሁ ጎርፍ ከመሆኑ በፊት የቆማችሁበትን ቦታ አስተውሉ “ማንም የቆመ ቢመስው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ” 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10፤12 ቃሉ እንዲህ ይላል ፤ የአባቱ የዳዊትን እና የልጁን የሰለሞንን ስርወ መንግስትን የመሰረተው ጊዜው ሲደርስም ያሳለፈ እርሱ እግዚአብሔር ነው ፤ አሁንም እናንተን እዚህ ወንበር ላይ ያስቀመጣችሁ የሚያወርዳችሁም እርሱ ነው ፤ ዘመናችሁ እንዲረዝም የምትፈልጉ ከሆነ እጃችሁን ከገዳማትና ከአብያተ-ክርስትያናት ላይ አንሱ ፤ እርሱን ታግሎ ያሸነፈ በዘመናችን የለም ፤ ወደፊትም አይኖርም ፡፡


ከ savewaldba.wordpress.com የተገኝ
ባለፉት ጥቂት ሳምትታት ውስጥ በዋልድባ ገዳም አካባቢ በሚሰራው የወልቃይት ስኳር ፋብሪካ የቻይናው ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሥራውን ቀን ከሌሊት በመስራት ላይ እንደነበረ ከአካባቢው በደረሱን መረጃዎች ለመገንዘብ ችለናል። እንደሚታወቀው ከጥቂት ወራት በፊት በዋልድባ ገዳም አካባቢ ሊሰራ የታሰበውን ፕሮጀክት ሙሉ ለሙሉ ሃላፊነቱን ወስዶ ሥራዎቹን ጀምሮ የነበረው የሱር ኮንስትራክሽን በተለያየ ጊዜ በአካባቢው በደረሰው ተአምራት ስራውን ማከናወን አልቻለም ነበር ፤ የዲዛይን ኢንጂነሩ በአጋጣሚ በመሞቱ፣ ጥቂት ሰራተኞች በአውሬ በመበላታቸው፣ የግድቡ ሥራ በጣም አዳጋች በሆነ መልኩ መስራት ባለመቻላቸው ለግድብ ሥራ ጉድጓድ ቆፍረው በነጋታው ሲመለሱ ውሃ ሞልቶት ወይንም አፈር ተንዶ በመሞላቱ እና ተደጋጋሚ ክስተቶች በመፈጸማቸው የሱር ኮንስትራክሽን ኮንትራቱን አፍርሶ መውጣቱ ይታወሳል። ኮንትራት አፍርሶ መውጣት (breach of contract) በብዙ ሚሊዮን ብር ቅጣት የሚያስቀጣ ቢሆንም ሱር ኮንስትራክሽን ባለቤቶቹም ኢትዮጵያውያን በመሆናቸው የእግዚአብሔርን ተአምራት በዓይናቸው በማየታቸው ቅጣቱን ተቀጥተው ትተው ወጥተው ነበር።

ሱር ኮንስትራክሽን ጥሎ እንደወጣ -አማናውናኑን ጣዖት አምላኪዎቹን የቻይና ኮንስትራክሽን ካምፖኒዎችን በማስመጣት ሥራዎቹን እንዲቀጥሉ ማድረግ ተችሎ ነበር፤ በመጀመሪያው አካባቢ የአካባቢው ሰው በማንኛውም የቀን ሥራ ተቀጥሮ ለመስራት ፈቃደኛ ሆኖ ባለመገኘቱ፣ የአካባቢውም ነዋሪዎች በገዳሙ ላይ እንዲህ አይነት ሥራዎችን ሲሰሩ ከማየት ሞታችንን እንመርጣለን በማለት ከመንግሥት ወታደሮች ጋር ፍጥጫ መፈጠሩ የሚታወስ ነው፤ የመንግሥትም አካላት ምንም ዓይነት ግብግብ ከአካባቢው ነዋሪ ጋር እንዲፈጠር ባለመፈለግ ሊመጣ የሚችለውን የከፋ አደጋ አስቀድሞ በመገመት በወቅቱ ሥራው ትንሽ ጋብ ለማድረግ ችለው  ነበር። የአካባቢው ገበሬ መኅበራት ሥራቸውን እና ቤታቸውን በዚህ ምክንያ ጥለው ወጥተው ነበር

 በአሁኑ ሰዓት በዛሬማ ወንዝ ላይ ትልቅ ድልድይ ወደ ገዳሙ ውስጥ logistics ሊያስገቡበት የሚችሉበት ድልድይ መሰበሩ ታውቋል ፤ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በአቲካ ወንዝ አካባቢ መጠነኛ ግድብ ገድበው ለሸንኮራ ልማት ችግኝ ማፍያ የሚሆን ግድብ ተገድቦ ነበር ፤  ባለፈው በጳጉሜ ቀን ፳፻፬ . . መብረቅ ቀላቅሎ የወረደው ዝናብ በዋልድባ ገዳም በቻይና ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ላለፉት ወራት ሲገነቡ የነበሩ ግንባታዎች በሙሉ ምንም ሳይቀር በመብረቅና የዝናም መዓት ተመተው ድራሻቸው መጥፋታቸው ለአምላከ ቅዱሳን መድኅኒዓለም ክርስቶስ ምን ይሳንሃል ያሰኘ ክስተት ነበር፤

ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ እንደተናገረው ” . . እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፥ ለትሑታን ግን ጸጋን የሰጣል ይላል . . .” ስለዚህ ዛሬም እግዚአብሔር ለተገፉት፣ ለተገረፉት፣ ለተደበደቡት ገዳማውያን አባቶቻችን ሃይሉን ሰጥቷቸው በጸሎታቸው ሃይል እንካሁም በአምላካችን ቸርነት በዛሬማ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ በመብረቅ ለወሬ እንዳያመች ሆኖ በጥፋቱ በአቲካ ወንዝ ለሸንኮራ ማፍያ የተገደበው ግድብ እንዲሁ በጎርፍ ሙላት ሙሉ ለሙሉ ከነሸንኮራ ችግኝ ማፍሊያ እና የተለያዩ ከባድ እና ቀላል machinery በአንድነት በአንድ ጀምበር ድምጥማቱ መጥፋቱ ማወቅ ተችሏል፤ ከዚህም ጊዜ ጀምሮ በምንም መልኩ የቻይናው  ኮንስትራክሽን ካምፓኒ ሊያንሰራራ ባለመቻሉ እስከ አሁኗ ቀን ድረስ ሥራው ሊጀመር አልቻለም

ተግዳሮቱ ከፈጣሪ ጋር በመሆኑ ፤ የፈርዖንን ልብ የያዘ ደግሞ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችል በዓይናችን የምናየውን ማየት ከተሳነን ምከረው ምከረው፤ አልመለስ ካለ መከራ ይምከረው የሚለውን የአባቶቻችንን አባባል እኛም ለመድገም እንገደዳለን።

ከዚሁ ዜና ጋር በተያያዘ በዚሁ በዋልድባ ገዳም አካባቢ እግዚአብሔር መዓቱን አውርዶ እነዚህ ግድብ እና ድልድይ ከፈረሱ በኃላ የአካባቢው ጸጥታ ሰዎች በገዳሙ ውስጥ በመግባት አባቶችን ማወክ እና መደብደብ ጀምረውየእናንተ መተት ነውበማለት ሲያውኩ አንድ ስማቸው ክንፈ ገብርኤል የተባሉ መናኝ የግድቡ እና የድልድዩ አይግረማችሁ፣ ይህንን ገዳም ለማፍረስ የተነሳ ሥራው ብቻ ሳይሆን ራሱም ይፈርሳል በማለት በኃለ ቃል ለታጣቂዎቹ በመናገራቸው  ታጣቂዎቹም በአጸፋው መናኙን አባት  ክፉኛ ደብድበዋቸው ክፉኛ በመቁሰላቸው ማይገባ በሚባል ከገዳሙ የሰባት ሰዓት መንገድ የሆነ ጤና ጣቢያ ተወስደው በህክምና ሲረዱ መቆየታቸውን እና በአሁን ሰዓት በማገገም ላይ እንደሚገኙ ከምንጮቻችን ለመረዳት ችለናል።

ዋልድባ ገዳም በመድኅኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የድንጋይ ቆብ ቀርጾ ባመነኮሳቸው መነኮሳት የተገደመ ገዳም እንደመሆኑ መጠን ችግሩ ምን ቢጸና፣ ምን ያህል አባቶቻችን መነኮሳት እና እናቶቻችን መነኮሳይት ቢንገላቱ እና ቢሰደዱ፣ በገዳሙ ውስጥ የሰው ዘር እንኳ ቢጠፋ በፍጹም ልንገነዘበው የሚገባን የገዳሙ መስራች እና የቤተክርስቲያናችን ጉልላቷ ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፍጹም ሊተዋት አይችልም መንግሥታት፣ ጎበዛዝት፣ ሃይለኞች በለጊዜዎች እና ባለመሣሪዎች በሙሉ ሰማይና ምድርም ሳይቀሩ ያልፋሉ ነገር ግን ቤተክርስቲያን እና የፈጣሪያችን ቃሉ ለዘላለም ህያው ሆነው እስከ ዓርያም ይኖራሉ። ዋልድባም ከነሙሉ ክብሩ በመድኅኒታችን ጠባቂነት እና ረደኤት ከትውልድ ትውልድ ይተላለፋል።

መድኅኒዓለም ክርስቶስ ዘወትር በተዓምራቱ እና በቸርነቱ ያልተለየን የአባቶቻችን አምላክ ስሙ የተመሰገነ ይሁን

ቸር ሰንብቱ


14 comments:

  1. It is amazing story! Yigbagn le chrestose yemilew neger liben nektotal. Zim bilo ye-egzabherin tamir malyet new. Ejachihun ke gedamachin lay ansu bilenal...mikerew mikerew ayi kal mekera yimkerew...

    ReplyDelete
  2. Amen. Libona yistachew

    ReplyDelete
  3. AMLAK HOY SIRAH GIRUM DINK NEW.AHUNIM AMLAKE KIDUSAN MASTEWALUN YISTACHEW.

    ReplyDelete
  4. zebo ezin semi'a leyisima.

    ReplyDelete
  5. Waldiba ena China 1 lay yitsaf?! Woy Gize!!! True... this church will never fall, for it is formed on the blood of Christ. Waldiba FOREVER!!!!

    ReplyDelete
  6. Labatochachen bertatun yestelen
    yehegiza alfo yegedamachen keber yemitebkebetn giza yamtalen
    lehulum lebona yestachew
    Amen!

    ReplyDelete
  7. Misgana Le Cheru Medhanealem Yihun! Ke Igziabher Gar Yemitalu Yidekalu!

    ReplyDelete
  8. AMEN AMEN ye E/rn bet ye miyafers E/r ersun yaferswale

    ReplyDelete
  9. AMEN AMEN ye E/rn bet ye miyafers E/r ersun yaferswale

    ReplyDelete
  10. Temesgen Medihanialem!
    MinYisanihal Ante.

    ReplyDelete
  11. Temesgen Medihanialem!
    MinYisanihal Ante.

    ReplyDelete
  12. sew zem belo yegziabhern meheret bitebek melkam new

    ReplyDelete