- ‹‹ማኅበሩን የማዳከምና የማፍረስ ፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ተልእኮ ነው›› አባላትና ደጋፊዎች
(አዲስ አድማስ
መጋቢት 13 2006 ዓ.ም)፡- ማኅበረ
ቅዱሳን የተዘጋጀውን የአስተዳደር መዋቅር ተቆጣጥሮ ለፖለቲካ ጥቅም ሊያውል ይፈልጋል በማለት የሚቃወሙ የአዲስ አበባ
የደብር አስተዳዳሪዎች ዛሬ ስብሰባ የሚያካሂዱ ሲሆን፤ የማህበረ ቅዱሳን አባላት በበኩላቸው ዘመቻ
ተከፍቶብናል ይላሉ፡፡ የአዲስ አበባ አድባራት አስተዳዳሪዎች ማኅበሩ ሀብቱንና ንብረቱን እንዲያስረክብ ሊያስገድዱት ተዘጋጅተዋል ይላሉ
የማህበሩ አባላት፡፡
ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን
መዋቅር በመጣስ እንደሚንቀሳቀስ
የሚጠቅሱት አስተዳዳሪዎቹ በበኩላቸው፤ ገንዘቡንና ንብረቱን የሚያንቀሳቅሰው
ከጠቅላይ ቤተ
ክህነት አሰራር ውጭ ስለሆነ የሀብቱና ንብረቱ መጠን አይታወቅም ይላሉ፡፡
‹‹ማኅበሩ አቅጣጫውን የሳተ የኦርቶዶክስ ሰለፊ ነው›› በማለት ማኅበረ ቅዱሳንን የሚፈርጁ አስተዳዳሪዎች እንዳሉ የሚናገሩት የማህበሩ አባላት፤ ዘመቻ እንደተከፈተባቸው የሚገልፁ ሲሆን፤ የአድባራት አስተዳዳሪዎች በበኩላቸው ማህበሩ በቤተክርስቲያን ላይ ዘመቻ ከፍቷል ይላሉ፡፡ ማኅበሩ ለሀገረ ስብከቱ የሠራው የመዋቅር፣ የአደረጃጀትና የአሠራር ጥናት፣ ማኅበሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር በመቆጣጠርና በፖለቲካ ከቤተ መንግሥቱ አጣምሮ በመያዝ ዓላማውን ለማራመድ ያዘጋጀው ነው ሲሉ የሚቃወሙ አስተዳዳሪዎች እንዳሉ ታውቋል፡፡
‹‹ሕግ የሌለውና ለሕግ የማይታዘዘው ማኅበረ ቅዱሳን ለእኛ ሕግ ሊያወጣልን አይችልም›› የሚሉት አስተዳዳሪዎቹ፤ ከየአድባራቱ አምስት አምስት ሠራተኞች ይገኙበታል በተባለው በዛሬው ስብሰባቸው፤ ማኅበሩ ሕግ ወጥቶለት ወደ መዋቅር እንዲገባ በመግለጫቸው እንደሚጠይቁ የማኅበሩ አባላት በበኩላቸው፣ ማኅበሩ የሚመራው በ1994 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ለሦስተኛ ጊዜ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ ነው በማለት ‹‹ሕግ የሌለው ሕገ ወጥ ነው›› መባሉን ተቃውመዋል፡፡
ማኅበሩ በየዓመቱ ፈቃድ ባለውና ብቃቱ በተመሰከረለት የውጭ ኦዲተር፣ የፋይናንስ እንቅስቃሴውን እያስመረመረ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ሪፖርት እንደሚያቀርብ አባላቱ ተናግረዋል፡፡
< Yedebir Astedadari > tbeyewoch, bertu bertu !!!!!! hayalu egziabher betekrstianin yetegafuatin beandei bmot siwsede lechefrochachew (le enante ) milikit yibekachu neber. Yekefa kitat tikebelalachu bertu !!!! Weladit Amlak Dingil Mariam Ylijochuan Enba tabisalech. Beteley bezih amete.
ReplyDeleteBertitachu rutu, tederaju, yitekemenal kalachut gar hunu. The church will never be failed. Ever and ever.
EPRDF think 10 times before cutting once. If decided, do what ever u like. The response is from above. be ready to take it in. No way out.