ከመቅረዝ ዘተዋሕዶ መንፈሳዊት ድረ ገጽ የተወሰደ
በመቅረዝ ዘተዋሕዶ መንፈሳዊት ድረ ገጽ አድራሻ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እምነት ፣ ሥርዓት ፤ ትውፊትና ታሪክ መሠረት
ያደረጉ ትምህርታዊ የሆኑ ጽሑፎች የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመጠቀም በአራት
በተለያዩ ቋንቋዎች(በአማርኛ
፤ በትግርኛ ፤ በኦሮምኛ እና በእንግሊዝኛ) ላለፉት
፬ ዓመታት ወጥተዋል፡፡ እነዚህ ትምህርቶች ጸሐፊው በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጪ የኢንተርኔት አቅርቦት ላላቸው ምዕመናኖች በተቻለ መጠን ለማድረስ
ሞክሯል፡፡ ነገር ግን እነዚኽን መንፈሳውያን ጽሑፎች በዓቅም ማነስ ምክንያት ቴክኖሎጂውን መጠቀም ላልቻሉ ምእመናን ሊዳረሱ አልቻሉም፡፡
ኢንተርኔት ተጠቅመው ጽሑፎቹን ማንበብ ላልቻሉ ወገኖች ጽሑፎቹን በመጽሐፍ
መልክ ለማዘጋጀት ያስችለው ዘንድ ከሳምንታት በፊት መልዕክት ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ ይህን መልዕክቱን ያነበቡ ምዕመናን
ከልጁ ጎን በመሆን የመጀመሪያው መጽሐፍ ለህትመት እንዲበቃ ክርስቲያናዊ ግዴታቸውን በመወጣት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርገው መጽሐፏን
ለህትመት አብቅተዋታል፡፡
‹‹መቅረዝ ዘተዋሕዶ - የውዳሴ ማርያም ማብራርያ›› ከዚኽ
በፊት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጁት የትርጓሜ መጽሐፍ ተንተርሳ የተዘጋጀች መጽሐፍ ስትኾን የምትለየውም በሚከተሉት ዋና
ዋና ነጥቦች ነው፡-
፩ኛ) የጥንቱን ለዛ ሳይለቅ ቀለል ባለ አቀራረብና ይዘት በእያንዳንዱ ምዕመን እጅ እንዲደርስ በማሰብ መዘጋጀቷ፤
፪ኛ) “እንዲል፣ እንዳለ፣ እንዲሉ” የሚለውን ጥንታዊ አቀማመጥ ጸሐፊውንና ደራሲውን መለየቷ፤
፫ኛ) አንዳንድ ተጨማሪ ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸውን ምንባባት ከተለያዩ ድርሳናት ተጨማሪ ማብራሪያ መያዟ፤
፬ኛ) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች ላይ ጥቅሱን በማስቀመጥ ምዕመናን እንዲያመሳክሩት መንገድ መክፈቷ፡
በመኾኑም ላለፉት ዐራት
ዓመታት በድረ
ገጽ መልክ
ስታገለግላችኁ የነበረችውን መቅረዝ ዘተዋሕዶ መንፈሳዊት ድረ ገጽ አኹን ደግሞ ለኹሉም ምዕመናን ትዳረስ ዘንድ በመጽሐፍ መልክ
መምጣቷን ስታበሥር ከታላቅ ደስታ ጋር ነው፡፡ ርስዎም ይኽችን መጽሐፍ በመግዛት ይጠቀሙ ዘንድ ግብዣችን ነው፡፡
በዚኹ አጋጣሚ የማሳተሚያ ወጪዋን ሙሉ ለሙሉ በመሸፈን ከጐኔ ላልተለያችኁኝ የመቅረዝ ዘተዋሕዶ ወዳጆች እናንተን የማመሰግንበት ምንም ቃላት የለኝም፡፡ ኹሉን ማድረግ የማይሳነው እግዚአብሔር ዋጋቸኁን በሰማያት ያቈይላችኁ፡፡
በጸሐፊው
በአዲስ ዓመት በገበያ ላይ የሚውሉ መጻሕፍት
- ምክር ወተግሳጽ ዘቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - ክፍል ፩
- የትንቢተ ዮናስ ትርጓሜ
- የዮሐንስ ወንጌል ማብራሪያ ክፍል ፩
መጽሐፏን ማከፋፈል ወይም ማግኘት የምትፈልጉ፡-
በስልክ 09 12 07 45 75
በፖ.ሳ.ቁ. 8665 አ.አ.
በእ-ጦማር gebregzabher@gmail.com
በስልክ 09 12 07 45 75
በፖ.ሳ.ቁ. 8665 አ.አ.
በእ-ጦማር gebregzabher@gmail.com
የተሻለ አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን
ያደርጉ ዘንድ እውቀቱ እና አቅሙ ያላቸውን አገልጋይ ምዕመናን እናበረታታ፡፡
No comments:
Post a Comment