Saturday, July 12, 2014

የላሊበላን አብያተ-ክርስቲያናትና የፋሲል ቤተመንግስትን በናኖ ቴክኖሎጂ ለማደስ ታቅዷል

From Addis Admass 
            ጥንታውያኑ የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትና የጎንደር ፋሲለደስ አብያተ መንግስታት ህንፃዎች ለዘመናት ሳይፈራርሱ እንዲቆዩ ለማድረግ ያስችላል በተባለው ናኖ ቴክኖሎጂ ለማደስ ታቅዷል፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰለሞን መስፍን፤ ቴክኖሎጂው በዓለም ላይ እየተስፋፋ እንደሆነ ጠቁመው፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲም የናኖ ቴክኖሎጂ ማዕከል አቋቁሞ በቅድሚያ በአብያተ ክርስቲያናቱና ቤተመንግስቱ ህንፃዎች ላይ ቴክኖሎጂውን ቻመተግበር እቅድ መያዙን፤ በቀጣይ ዓመትም ፕሮጀክቱ እንደሚጀመር ተናግረዋል፡፡ 
የፊዚክስ የፈጠራ ውጤት የሆነው ናኖ ቴክኖሎጂ ከሞሎኪዮሎች (ቅንጣቶች) የተፈጠረ ሲሆን ከሲሚንቶ ጋር በመቀላቀል ለህንፃ ግንባታዎችና እድሳቶች ከዋለ፣ ለህንፃው ጥንካሬና እድሜ ይሰጠዋል ተብሏል፡፡ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ናኖ ቴክኖሎጂን በሃገራችን ለማስተዋወቅ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ጠቁመው፤ናኖ ግሎባልከሚባል ድርጅት ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት መፈረሙን ገልፀዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲው የቴክኖሎጂው ማዕከል የተቋቋመ ሲሆን የቴክኖሎጂው ሊህቃን ከውጭ ሀገር መጥተው የላሊበላና ጎንደር አብያተ ክርስቲናትና ቤተመንግስታት እንዴት ይቀቡ በሚለው ላይ የምርምር ስራዎችን ያከናውናሉ ብለዋል፤ አቶ ሰለሞን፡፡ 
ቴክኖሎጂው በምግብ ሳይንስ፣ በኤሌክትሮኒክስ ቁሶች፣ በኢነርጂ፣ በህክምና፣ በህንፃዎች ወዘተ ላይ እየተሰራበት ሲሆን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚከፈተው ማዕከል ለወደፊት አቅሙ ሲጠናከር የመኪና አካላትንም በቴክኖሎጂው ለመቀባት እቅድ መያዙ ተጠቁሟል፡፡ 


1 comment:

  1. Good to think about re reservation of our beloved heritages. But i am suspicious of the project. How such new technologies be tested in such great church like lalibela before we are sure in any other small rock buildings. Indeed i am so much concerned and please clarify further.

    ReplyDelete