Sunday, July 20, 2014

ምንፍቅናን በ‹‹ምክር›› ወይስ በ‹‹ንስሐ›› ?

(አንድ አድርገን ሐምሌ 13 2006 ዓ.ም)፡- በደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስያን አስተዳዳሪ “መልአከ ብርሃናት አባ” ማርቆስ ብርሃኑ ከምዕመኑ እና ከማኅበረ ካህናት በተነሳባቸው አስተዳደራዊ እና  ሃይማኖታዊ ህጸጽ ጥያቄ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከትአስፈላጊውን ማጣራት ካደረገ በኋላ በ28/02/06  ዓ.ም አባ ማርቆስን ከአስተዳዳሪነት ሥራቸውን ከደመወዝ ጋር ማገዱ ይታወቃል ፡፡ ጉዳዩም በመንበረ ፓትያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት እንዲታይ መወሰኑ ይታወቃል…


መንበረ ፓትርያርክ ጽ/ቤት የሰጠው ውሳኔ እንደሚቀጥለው አቅርበነዋል

“መልአከ ብርሃናት አባ” ማርቆስ ብርሃኑ ከምዕመኑ እና ከማኅበረ ካህናት የተከሰሱባቸው ዋና ዋና ነጥቦች
  • ‹‹አማላጅነት የጌታ ተግባር ነው፤ ኢየሱስ አማላጃችን ነው እሱ ሁሉን ፈጽሞልናል›› ብለው መስበካቸውን
  • ‹‹ማርያምን ስሰብክላችሁ ደስ ይላችኋል ፤ ስለ ኢየሱስ ግን ይከፋቸዋል ፤ ማርያም እኮ ከእግዲህ ዋጋ የላትም›› ብለው ማስተማራቸውን
  • ተአምረ ማርያም ፤ ድርሳናት ፤ ገድላት በጸበል ቤት እንዳይነበቡ ማገዳቸውን በርካታ ምዕመናንና ሊቃውንተ ቤተክርስቲያና በምስክርነት ቆመው መስክረውባቸዋል፡፡

5 comments:

  1. Egziabher amlak ersu ewunetun yigletsew firdun yist enji ye assa gimatu kechinkilatu endilu kelayi tekemtew ye sinodossun wussane yemiyaslewutu ena yemiyaskeyiru endemesger betekrstiyanachinin tetabtewat yelut sewochi eyalu min tikikilegna firdi yitebekal

    ReplyDelete
  2. ወይ ዘንድሮ! ለምንፍቅና ዕድገትና ሹመት፣ የተሻለ ቦታ ቅያሪ ይሰጣል፤ ለልማት ገንዘብ የለም ይባላል፤ ከራሱ ገንዘብ አውጥቶ የሚሠራ ደግሞ የልማት አደናቃፊ የሚል ስም ይሰጣል። ቤተ ክርስቲያንን የሚንቁ፣ አስተምህሮዋን የሚያንቋሽሹ፣ ስሟን የሚያጠፉ እና ኑፋቄን የሚዘሩ 'እብድ እና ዝናብ' ከተማ ይወዳል እንደተባለው አዲስ አበባ እንዲጠራቀሙ ማድረግ ምን ይሉታል? የጀመሩትን የኑፋቄ ትምህርት ከላይ ሆነው እንዲስተባብሩ ዕድል ለመስጠት ነው ወይንስ ለሌላ ዓላማ...ጆሮ ያለው ይስማ! እግዚአብሔር አምላክ አፅራረ ቤተ ክርስቲያንን ያስታግስልን! በእምነታችን ፀንተን የመንግሥቱ ወራሾች ያድርገን! አሜን!

    ReplyDelete
  3. Are you wishing to take over gov. Power?

    ReplyDelete
  4. ወይ ዘንድሮ! ለምንፍቅና ዕድገትና ሹመት

    ReplyDelete
  5. LEWEDEFETU ENDAYEDEGEM BELO NEGE MEN MALTE NEW EYETDEFERE YALEW HAYEMANOTE AYEDEL ENDE JALLLLLL

    ReplyDelete