- የቤተክርስቲያኒቱ ካህናት በፖሊሶች በጥፊ ሲመቱ ነበር፡፡
- የፈረሰው ንብረት ዋጋ 6 ሚሊየን ብር ይጠጋል ተብሎ ተገምቷል፡፡
(ኢትዮ ምኅዳር ሰኔ 25
2006 ዓ.ም)፡- ንብረትነታቸው የቡልቡላ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን የሆኑ 53 የንግድ ቤቶች የግንባታ ፍቃድ የላቸውም በሚል
ሐሙስ ሰኔ 19 ቀን 2006 ዓ.ም መንግሥት በላካቸው ግብረ ኃይል መፍረሳቸው ተቃውሞ አስነሳ፡፡ የቤተ ክርስቲያኒቷ ካህናት ልብሰ
ተክህኖ ለብሰው ፤ መስቀልና ጥላ ይዘው እንዳይፈርስባቸው ቢጠይቁም በወቅቱ ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተዋል፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አፍራሽ
ግብረ ሃይል የንግድ ቤቶቹ በሚፈርሱበት ሰዓት ፤ ቤተ ክርስቲያኗ ባሰማችው ደውል የተሰበሰቡት ምዕመናን ካህናትና የሱቆቹ ተከራዮች
በቦታው በመገኝት የረዥም ጊዜ ገደብ እንዲሰጣቸው ሲጠይቁ ከፖሊስ
ጋር በመጋጨታቸው አስር የሚጠጉ ካህናትና የተለያዩ ግለሰቦች በዱላ እና በጥፊ እየተደበደቡ ወደ መኪና ሲገቡ የተመለከትን ሲሆን
በወቅቱ በስፍራው ላይ የተገኙት ጋዜጠኞች በመፍረስ ላይ ያሉትን ቤቶች ፎቶ ግራፍ እንዳያነሱ እና ተበዳዮችን እንዳያነጋግርሩ ተደርጓል፡፡
ከግጭቱ በኋላ ያነጋገርናቸው ተበዳዮች እንደገለጹት ቤተ ክርስቲያኗ በይዞታነት በያዘችው እና ካርታ ባገኝችበት ቦታ ላይ የአካባቢውን ማኅበረሰብ በማስተባበር ባገኝችው 6 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በብሎኬት ፤ በላሜራ እና በቆርቆሮ የተገነቡ ንግድ ቤቶች እያንዳንዱ ተከራይ ከ120 እስከ 400 ሺህ ብር የሚያወጣ ንብረት በመያዝ ለአንድ ዓመት ከስድስት ወር ለሚሆን ጊዜ ሲሰሩበት እንደነበር ጠቅሰው ፤ ከወረዳው በሱቆቹ ቁጥር ንግድ ፍቃድ ስናወጣ እና ብድር ጠይቀን ባገኝበው ገንዘብ ሰርተን ቤተሰብ የምናስተዳድርበት መሆኑ እየታወቀ አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት ንብረታችንን ሳንሰበስብ እንዲፈርስ መደረጉ አግባብ አይደለም ብለዋል፡፡
በቤተክርስቲያኗ አስተምህሮ መሰረት
መስቀል ትልቅ ክብር እንዳለው የተናገሩት ቀሲስ በበኩላቸው ፤ በደውል
የተጠራው አገልጋይ ፤ ካህናት ፤ ምዕመናኑ እና የሱቆቹ ተከራዮች በጋራ ሆኖ መስቀል እና ጥላ በመያዝ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቦታ ላይ
የተሰራው የንግድ ቤት እንዳይፈርስ ብንለምንም በስፍራው የተገኙት ፖሊሶች እየሰደቡንና በዱላ እየተማቱ ማሰራቸው እና ማባረራቸው
እጅግ ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡ ስለዚህ የሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያኗ እና የመንግሥት አመራሮች በጉዳዩ ላይ ተወያይተው መፍትሄ
ሊሰጡን ይገባል ብለዋል፡፡
የ‹‹አንድ አድርገን›› አስተያየት
በየጊዜው ቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ይህን መሰል ችግር መፈጠር ከጀመረ ሰነባብቷል ፤ የዛሬ 2 ዓመት ገደማ ቤተ ክርስቲያኒቱ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የአምልኮ ስፍራዎች ከ126 የሚበልጡ የይዞታ ማረጋገጫ ከወቅቱ ከንቲባ ከአቶ ኩማ ደመቅሳ መቀበሏ የሚዘነጋ አይደለም ፤ ነገር ግን ቀድሞ የተመሰረቱትንና በቅርብ ጊዜያት የተመሰረቱት የይዞታ ማረጋገጫ መንግሥት የላቸውም የሚላቸውን ቤተ ክርስቲያናት የሚመለከተው አካል ጉዳዩን ጉዳዬ ብሎ መያዝ ባለመቻሉ ይህን የመሰለ ለሰሚም ሆነ ለተመልች አጅግ የሚያሳዝን ተግባር ሲፈጸም መመልከቱ ያሳዝናል፡፡ አሁንም ቢሆን ከዚህ የባሰ ውድመት ካርታ የላቸውም ወይም ካርታቸው ሕጋዊ አይደለም በሚባሉ ቤተ ክርስቲያናት ፤ ታቦት ማደሪያዎች እና ምዕመኑ ፈውስ እያገኝባቸው የሚገኙ የጸበል ቦታዎች ላይ መንግሥት እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ነገሮች መስመራቸውን የሚይዙበት ፤ ምዕመኑም ያለመሳቀቅ አምልኮተ እግዚአብሔር የሚፈጽበት ሁኔታን መፍጠር የቤተክህነቱ የዛሬ የቤት ስራው መሆን ይገባዋል፡፡
ከደርግ ዘመነ ወያኔ ይሻላል እያላችሁ ብዙ ጊዜ ስትቀላምዱ ተመልክቻለሁ፤ ያው ያፋችሁን ያድርግላችሁ። ቤተክርስትያንም ጳጳስም ሲኖዶስም የሚባል የለም፤እንደው ሁሉም የይስሙላ ነው። የሰይጣን ልጆች መናሃሪያ የሆነችው እስራኤል ተብዬ ሃገር ሹማ የላከችላችሁ ፓትሪያርክም፣ ካለፈው ፀረ ኢትዮጵያና ፀረ አማራ ከሆነው ግለሰብ የባሰ ፀረ ተዎህዶ ምስጥ ነው። መንግስት ተብዬው የዘረኛ ትግሬ ጥርቅምም የውጭ ሀይሎች ጉዳይ አስፈፃሚ ነው እንጂ ስለ እናንተ ጉዳይ የለውም ፤ እንደውም ቤንጤውንና እስላሙን በተጨማሪም
ReplyDeleteሌሎች በኢትዮጵያ መነጫነጭ የሚቀናቸውን ምናምንቴዎች በጉያው ከቶ መጕዙን ነው የሚመርጠው። ቤተክርስትያኒቱን ግን አይሁዶችና ቤንጤዎች በእጅአዙር እየተጫወቱባት ነው ያለው።
የሚገርም ነው። ካህንን በጥፊ መምታት ይቅርና ከቤተክርስቲያኗ አካላት ፍቃድ ሳያገኝ ፖሊስ ወደ ቤተክርስቲያን ቅጽር እንዲገባ የሚፈቅደው የትኛው የሀገሪቷ ሕግ ነው። ይህ ሁሉ ድፍረት ከየት ተገኘ? መንግሥት ሕገ ወጥ ይዞታን የማፍረስ መብት አለው ከተባለ የሚመለከተውን የቤተክርስቲያን አካል አሳውቆ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እርምጃ ለመውሰድ ለምን አልተሞከረም? ብቻ ይህ ሁሉ መደፋፈር የት ያደርሰን ይሆን?
ReplyDeleteወይ መድኃኔዓለም!!!
ReplyDeleteDerg yebetekrstiyan telat bihon beswr aydelem beglts now. Endezih mengst yebetekrstiyan telat yehone alayehum. seraru tkklegna yeseytan aserar slehone. Bemengst yepolitica agenda wst honew b/nyann eyateqo yalut 1/ keortodox haymanot wchi yalu beteley protestantna eslmna haymanot yalachew 2/ betebab yemiyasbu zeregnoch, ortodox yeamara haymanot nech yemil amelekaket yalachew 3/ bewananet EPRDF nachew. Hulum yalfalu b/n guzowan tqetlalech egna gn lebetekrstiyanachn zeb meqom ygebanal.
Deleteየሚገርም ነው። ካህንን በጥፊ መምታት ይቅርና ከቤተክርስቲያኗ አካላት ፍቃድ ሳያገኝ ፖሊስ ወደ ቤተክርስቲያን ቅጽር እንዲገባ የሚፈቅደው የትኛው የሀገሪቷ ሕግ ነው። ይህ ሁሉ ድፍረት ከየት ተገኘ? መንግሥት ሕገ ወጥ ይዞታን የማፍረስ መብት አለው ከተባለ የሚመለከተውን የቤተክርስቲያን አካል አሳውቆ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ እርምጃ ለመውሰድ ለምን አልተሞከረም? ብቻ ይህ ሁሉ መደፋፈር የት ያደርሰን ይሆን?
ReplyDelete