የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለሀገራችን
ስልጣኔ በር ከፋች
ሆና የኖረች
ከመሆንዋም በላይ ዛሬ
ላለው የዘመናዊ
ስልጣኔም መሠረት የጣለች
ባለውለታ ናት፡፡ ቀደምት
የቤተ ክርስቲያን አበው ደከመን
ሰለቸን ሳይሉ ዕረፍተ
ዘመን እስከገታቸው ድረስ ሲያገለግሉ ኖረው ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ከምትገኝበት የዕድገት ደረጃ አድርሰዋታል፡፡
በዚህ ዘመንም
የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱ ልጆች
ሁሉ ይህን
አስበው የተማሩትን ሃይማኖትና
ሥርዓት ጠብቀውና አስጠብቀው
ለሚመጣው ትውልድ ለማቆየት
ኃላፊነት ያለባቸው መሆኑ
ግልጽ ነው፡፡
በእርግጥ ይህንን ሥርዓተ
ቤተ ክርስቲያን የማስጠበቅ ሂደት
በውስጥም ሆነ በውጭ
ሆነው ለማደናቀፍ
ሌት ተቀን
የሚዳክሩ ጠላቶች መኖራቸው
እሙን ነው፡፡
እነዚህ በውስጥና
በውጭ የሚገኙ
የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ቤተ ክርስቲያን
ላይ በየዘመኑ
በሚነሳው ፈተና እየተጠቀሙና
በምክንያት እየተሳቡ ለቤተ ክርስቲያን
ወዳጅ መስለው
እየቀረቡና እያስቀረቡ የቤተ ክርስቲያን
አገልጋዮች በቀናነት ያደራጁትን
ማኀበረ ቅዱሳንን ለማፍረስ
በገንዘብ በቁሳቁስ የሚያስታጥቋቸው
መናፍቃን ሴራና ዓላማ
እንዳይጋለጥ እና በቤተ ክርስቲያኒቱ
ላይ እንደፈለጋቸው
እንዲሆኑ ማኀበሩ አገልግሎቱ
ተገድቦ እንዲቀር ለማስደረግና
ለማድረግ የጥፋት ዘመቻቸውን
በመክፈት ላይ ናቸው፡፡
እነዚህ አካላት በማኀበረ
ቅዱሳን ላይ ጊዜ
በሰጣቸው ጊዜ ሁሉ
በመጠቀም ማኀበሩን ለማሳጣትና
ለማጥላላት የሚጠቀሙባቸው ስልቶች
በርካቶች ናቸው፡፡
ማኀበረ ቅዱሳን
ግን ባለፉት
ዓመታት እነዚህ የውስጥና
የውጭ የቤተክርስቲያን
ጠላቶች በየጊዜው የሚያናፍሱትን
ወሬ ችላ
በማለት ከወሬ ሥራ
ይቅደም
በማለት ከቅዱስ ሲኖዶስ
የተቀበለውን ዓላማ በዓይን
የሚታየ በእጅ በሚዳሰስ
መልኩ ሲሰራ
ቆይቷል፡፡
ማኀበረ ቅዱሳን
ለዓመታት የመናፍቃኑንና ቤተ ክርስቲያንን
እናድሳለን ብለው የተነሱትን
የመናፍቃን ተላላኪ ቡድኖችን
ሴራና እንቅስቃሴ
በመረጃ አስደግፎ በማጋለጡ
ከክፉ ትምህርታቸው
መመለስ ያልፈለጉ የተሐድሶ
ቡድን አባላት
በቅዱስ ሲኖዶስ ከቤተ ክርስቲያን
እንዲወጡ ስለተወሰነባቸውና ሌሎችንም
የቤተክርስቲያን ችግሮች እየተከታተለ
ለዕድገቷና ለብልጽግናዋ በመስራቱ
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቤተ ክርስቲያን
ወዳጆች አፍርቷል፡፡
ከዚህ በተቃራኒ የተሰለፉት ወገኖች ደግሞ ወጣቱን እንደጠፍ ከብት ወደማያውቀው የመናፍቃን አዳራሽ የመንዳት ልምዳቸው በመቋረጡና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በመግባት የሚያደርጉት ሥርዓትዋን የማፋለስ እንቅስቃሴ እንዲሁም አገልጋዮችዋንና ምእመናኖችዋን የማስኮብለሉ አካሄድ ማኀበሩ በክትትል በተለያዩ መረጃዎች ስለገለጠባቸው ማኀበረ ቅዱሳንን በጠላትነት በማየት ማኀበሩ እንዲፈርስ የማይቧጥጡት ዳገት የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡
እነዚህ የቤተ ክርስቲያን
የውስጥ ጠላቶች ለጥቂት
ጊዜ ጋብ
ብለው የነበሩ
ቢሆንም አሁን ባገኙት
አጋጣሚ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ
እንጀራዋን እየበሉ የሚኖሩ
ወዳጆቻቸውን በማጠናከርና በማስፋፋት
በሚሊዮን የሚቆጠር በጀት
ከወዳጆቻቸው ተመድቦላቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን
ሥርዓት ለማዛባትና በጎችዋን
ለመበታተን ሌት ተቀን
እየሰሩ ነው፡፡
ይኼ ዕቅዳቸው
የሚሳካው እንደ ማኀበረ
ቅዱሳን ያሉ ለቤተ ክርስቲያኒቱ
እምነትና ሥርዓት መጠበቅ
የሚቆረቆሩ ማኀበራትን ባገኙት
አጋጣሚ ሁሉ አጀንዳ
በማድረግና እንዲበተኑ ክፉ
ሥራ በመስራት
ነው፡፡ እነዚህ የቤተ ክርስቲያን
ጠላቶች ይሔንን ከንቱ
ቅዠታቸውን እውን ለማድረግም
በቤተ ክርስቲያኒቱ የሚገኙትን ግለሰቦች
የዓላማቸው አስፈጻሚዎች ሁሉ
እየተጠቀሙ እንደሚገኙም ይታወቃል፡፡
ከዚህም ሌላ ድብቅ
ዓላማቸው እንዲሳካ ተላላኪዎቻቸው
በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚሆን
ነገር ግን
ስውር ዓላማ
ያለው ማኀበር
እንዲመሰርቱና ከዚህ በፊት
ከንቱ ተግባራቸው
ታውቆ በቤተ ክርስቲያኒቱ
ታግደው የነበሩ ማኀበራት
ሁሉ ከሞቱበት
እንዲቀሰቀሱ እየሰሩም ይገኛሉ፡፡
የማኀበር ቅዱሳን
አባላት በገንዘባቸው በዕውቀታቸው
በጉልበታቸውና በመላ ሕይወታቸው
ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ ናቸው፡፡
ማንኛውም አካል
እንዲያውቅልን የምንፈልገው ሐቅ
ማኀበረ ቅዱሳን ቅዱስ
ሲኖዶስ ለሰጠው ሓላፊነትና
አባላቱም ለገቡለት ቃል
ኪዳን ሐይማኖታቸው
የሚፈቅደውን መስዋዕትነት ለቤተክርስቲያን
ልዕልናና ክብር ለመክፈል
የተዘጋጁ እንጂ በተዛባ
አመለካከት ወደ ኋላ
የሚያፈገፍጉ አለመሆኑን ነው፡፡
ማኀበረ ቅዱሳን
አገልግሎቱ የሚታይ አሰራሩም
ግልጽ ነው፡፡
ስለዚህም የመናፍቃኑን ተላላኪዎች
መሠረተ ቢስ ውንጀላ
ከአገልግሎታችን አንዲት ጋት
ወደ ኋላ
እንደማይመልሰን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፡፡
ርእይና ተልእኮአችንን ለማሳካት
ዛሬም ነገም
እንሰራለን ትናንትን ያሻገረን
እግዚአብሔር ዛሬንም ያሳልፈናልና፡፡
ኀበረ ቅዱሳን ለዓመታት የመናፍቃኑንና ቤተ ክርስቲያንን እናድሳለን ብለው የተነሱትን የመናፍቃን ተላላኪ ቡድኖችን ሴራና እንቅስቃሴ በመረጃ አስደግፎ በማጋለጡ ከክፉ ትምህርታቸው መመለስ ያልፈለጉ የተሐድሶ ቡድን አባላት በቅዱስ ሲኖዶስ ከቤተ ክርስቲያን እንዲወጡ ስለተወሰነባቸውና ሌሎችንም የቤተክርስቲያን ችግሮች እየተከታተለ ለዕድገቷና ለብልጽግናዋ በመስራቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች አፍርቷል፡፡
ReplyDeleteEGZIABHERE EMNETACHENE BEBETU EYAGELEGELU YEMIGNU MAHBERATNE YETEBEKELEN
ReplyDeletemahberun amlake esrael yetebekelen yasefalen.... bertu ayzuachu serachu lebetekerstiyanena lelem hulu new
ReplyDeletewe always with you mahebere kidusan i know God is with u
ReplyDeleteችግራችሁን እንደሌሎቹ የቤተክርስቲያኒቱ አካላት በውስጥ ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ በየጋዜጣው፣በየመጽሄቱ፣በየብሎጉ፣በየፌስቡኩ ስትለቁ ትከርሙና ጥይቱ ወደራሳችሁ ሲባርቅ አሁን-አሁን እውነተኛውን ክስ ከሐሰተኛ ውንጀላ ለመለየት እስኪያዳግት ድረስ የመጫወቻ ካርድ ያስመሰላችሁትን “ተሐድሶ” እየመዘዛችሁ ከመስመር የወጣ ትርፍ ነገር ትናገራላችሁ፡፡ስለራስ በመመስከር ማን እንደናንተ!!
ReplyDeleteቤተክርስቲያን ትናንትን ስትሻገር ማኅበሩ አልነበረም፡፡ዛሬ በመኖሩ ግን ደስ ይለናል፡፡ኑሩ፡፡
የሚከፋን ትክክለኛውን ቅሬታ ከሀሰተኛው ሳትለዩ “እኛን የአካሄድ ችግር አለባችሁ የሚል ሁሉ ተሐድሶ ነው” የሚል ትምክህታዊና በአባላት ብዛት የታወረ የቲፎዞ አካሄዳችሁን ስናይ ነው፡፡አትመኩ፡፡ነጠላ የሸፈነውን ትምክህትና በዲግሪ የታጠረን ድንቁርና የሚያይ አምላክ አለ፡፡በኤቢሲዲ እየተመካችሁ አባቶችን አታቃሉ፡፡ከአባቶች ተግሳጽን፣ከቤተክሕነት መመሪያን፣ከካሕናት አስተያየትን ለመቀበል ያላችሁ ዝግጁነት እጅግ ደካማ ነው፡፡ትምክሕት፡፡
እዚህ ያሰፈራችሁት ያቋም መግለጫችሁ ጥሩ ነው፡፡ብቻ እላዩ ላይ በአባላት ብዛት መመካትን ሳይሆን ቅንነትን እና ገንቢ ሂስ ለመቀበል መዘጋጀትን ጣል አድርጉበት፡፡ “ለእኛ ያላጨበጨበ ሁሉ የማርያም ጠላት ነው” አትበሉ፡፡የአባላት ብዛት የአካሄድን ትክክለኛነት መመዘኛ ቢሆን ኖሮ ሃይማኖተ አበው ከቤተክርስቲያን ተቆርጦ አይጣልም ነበር፡፡እነ ባሕታዊ ገብረመስቀል እና እነ አባ አምኃኢየሱስም በሺህ የሚቆጠር ሰው አስከትለዋል፡፡ኢህአፓም ምሁሩን አሰልፎት ነበር፡፡
ሌባ ሌባ ነህ ሲባል ይደነግጣል ምነው ሌባው ተሐድሶ ነህ እንዴ?!
Deleteጻድቁ “ከአባቶች ተግሳጽን፣ከቤተክሕነት መመሪያን፣ከካሕናት አስተያየትን ለመቀበል ያላችሁ ዝግጁነት እጅግ ደካማ ነው፡፡ትምክሕት፡፡” የምትለዋንም አንብባት፡፡
Deleteበካሕናትና በማዕከላዊ ተቋም የሚመራ ተሐድሶ እንደሌለ ስታውቅ ማኅበር ተጠልለህ ስድብ ትዘራለህሳ!!መጻጉዕ!መጻጉዐ-አእምሮ!!
መናፍቃኑ ኢየሱስ በሚለው ስም ተጠልለው ቅዱሳንን ለማራከስ እንደሚተጉት ሁሉ እንዳንተ አይነት ጥቃቅን ሰዎችም ማኅበሩን ተጠልለው መሳደብን እንደቡራኬ ቆጥረውት በየሚዲያው ያደነቁሩናል፡፡ድንቅው!!ጽምው!!
EMEBETACHIN MARIAM MAHIBERACHININ TEBKLIN BEMILIJASH.
ReplyDeleteማኀበረ ቅዱሳን አገልግሎቱ የሚታይ አሰራሩም ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህም የመናፍቃኑን ተላላኪዎች መሠረተ ቢስ ውንጀላ ከአገልግሎታችን አንዲት ጋት ወደ ኋላ እንደማይመልሰን እንዲታወቅልን እንፈልጋለን፡፡ ርእይና ተልእኮአችንን ለማሳካት ዛሬም ነገም እንሰራለን ትናንትን ያሻገረን እግዚአብሔር ዛሬንም ያሳልፈናልና፡፡
ReplyDeleteLet our almighty God protect our church from all evils
ReplyDeleteAs a Sunday school members I will contribute my share. Please keep it up, We are with you brothers and sisters
ReplyDeleteyabatochachin amlak zarem yitadegenal
ReplyDeleteYekidusan amlak yatsnachihu yabertachihu yabzachihu deablos yifer bezih tifat bebezabet zemen letewahdona lelijochwa betam tasfelegunalachhu tsegawn yabzalachhu.
ReplyDeleteርእይና ተልእኮአችንን ለማሳካት ዛሬም ነገም እንሰራለን ትናንትን ያሻገረን እግዚአብሔር ዛሬንም ያሳልፈናልና፡፡ ይህ ተልዕኮ የማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የክርስቲያኖች ስለሆነ ከጎናችሁ ሆነን እናንተ የምትከፍሉትን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፡፡ የማህበሩ ልጆች ከቀና የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን እንዲሁም ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ጋር በትጋት አገልግሉ፡፡አገልግሎታችን በመናፍቃን ሁከትና ጩኸት አይደናቀፍም፡፡ የገሃነም ደጆች አይችሏትምና፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን አሜን፡፡
ReplyDeleteጥላሁን ጉግሳ ተሳደበ... እከሌ ተሃድሶ መናፍቅ ሆነ .....ተደረገ.... ወሬ ብቻ
ReplyDeleteመፍትሄው ማለቃቀስ አይደለም፣ እንደአባቶቻችን የሚገባውን ገድል በመፈጸምና ቤተክርስቲያንን ከጥፋት ሃገሪቱንም ከውርደትና ከጥፋት ማዳን ነው፡፡ በቃ ተዋህዶ ዋናው ጦሯ እየሱስ ክርስቶስ ቢሆንም እርሱ የሚልካቸውና የሚዋጉ ሰራዊቶች ያሥፈልጓታል፡፡ ጠላትን አንገቱን የሚቀነጥሱ ተሃድሶ ፕሮቴስታንቶችን አንገታቸው የሚያርዱ ......በቃ....በቃ....... እያንዳንዳችን ይመለከተናል የምንል ሁሉ ከዚህ በኋላ ማሰብ ያለብን ስለዚህ ጉዳይ ነው፡፡
god bless mk
Deleteርእይና ተልእኮአችንን ለማሳካት ዛሬም ነገም እንሰራለን ትናንትን ያሻገረን እግዚአብሔር ዛሬንም ያሳልፈናልና፡፡ ይህ ተልዕኮ የማኅበረ ቅዱሳን ብቻ ሳይሆን የሁላችንም የክርስቲያኖች ስለሆነ ከጎናችሁ ሆነን እናንተ የምትከፍሉትን መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፡፡ የማህበሩ ልጆች ከቀና የቤተ ክርስቲያን አባቶችና ምዕመናን እንዲሁም ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ጋር በትጋት አገልግሉ፡፡አገልግሎታችን በመናፍቃን ሁከትና ጩኸት አይደናቀፍም፡፡ የገሃነም ደጆች አይችሏትምና፡፡ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን አሜን፡፡ማንም ቢያወራ እርባና የለውም፡፡
ReplyDeleteእግዚአብሔርን ይዞ ያፈረ የለም።እንኩዋን ከተራ አሉባልታ ከአናብስት አፍና ከእሳት ነበልባል የሚያድንን አምላክ አናምናለንና።
ReplyDelete