Tuesday, November 29, 2011

ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ የግብረ ሰዶማውያንን ጉባኤ ልታዘጋጅ ነው

 • ‹‹The African Men for Sexual Health and Rights (AMSHeR)›› ብሎ የሚጠራ የዚህ ቡድን/ድርጅት ዓላማ በአፍሪካ የሚገኙ ግብረሰዶማዊ ወንዶች የተሻለ ሕይወትና ተቀባይነት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡ 
 • የውይይቱ መሪ ቃል ‹‹የራስ ማድረግ፣ ማሳደግና ቀጣይነት›  (Claim, Scale-Up and Sustain) በሚል መሪ ቃል ኅዳር 23 ቀን 2004 .ከጧቱ 2 ሰዓት ተኩል እስከ 11 ሰዓት ተኩል ድረስ በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሔዳል
 • በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ግብረሰዶማዊነት ወንጀል ነው
 • ግብረሰዶማዊው የኬንያው ተቋም ኢሽታር ካነገበው ዓለማዎች መካከል በግብረሰዶም ዙርያ የአቻ ለአቻ ትምህርት የኬንያን አምሳያ በኢትዮጵያ ማዳረስ እንደሆነ አመልክቷል
 • ስብሰባው 15 አገሮች ላይ በጤናና በግብረሰዶማዊያን መብቶች ዙርያ የተዘጋጁ ተሞክሮዎች ይቀርብበታል
መሰይጠን ወይስ መሰልጠን

(አንድ አድርገን ህዳር 20  2004 ዓ.ም ):በመጪው ቅዳሜ እንደሚጀመር የሚጠበቀው እና ከ10ሺህ በላይ ተሳታፊዎች የሚገኙበት ICASA (International Conference on AIDS and Sexuallity Transmitted infection) የተለያዩ ሀገራ መሪዎች ቀዳማይ እመቤቶች ፤ ምሁራን ፤ ለጋሾችና ተማሪዎች 5 ቀን የሚቆይ ጉባኤ ያካሂዳሉ ተብሎ ይጠበቃ፡፡ መንግስትም ለዚህ ጉባኤ መሳካት ያላሰለሰ ጥረት በሆቴሎች ላይ፤ በመሰብሰቢያ አዳራሾች ፤ በፀጥታ እና ጥበቃ ላይ እየሰራ እንደሚገኝ በመገናኛ ብዙሀን አማካኝነት አሳውቋል፡፡ ይህ እንዲህ እንዳለ ሆኑ ከ15 ሀገራት የተወጣተጡ 200 የሚጠጉ ግብረሰዶማውያን በጉባኤው ላይ እንደሚገኙ እና ከስብሰባው በፊት በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ‹‹ ግብረሰዶምን እንዴት ህጋዊ ማድረግ እደሚቻል እና በየሀገሩ ያሉትን ጥሩ ተመኮሮዎች ላይ ውይይት በማድረግ በተለያዩ አፍሪካ ሀገሮች ውስጥ ተቀባይነት እንዲያገኝ ፤ በህገመንግስታቸው ውስጥ እንዲያስገቡትና የሰዎችን ዲሞክራሲያዊ መብቶች በዚህም አኳያ እንዲያከብሩ›› በሚል መንፈስ እንደሚወያይ ለማወቅ ችለናል››

አባቶች ጋዜጣዊ መግለጫ ሊሰጡ በተሰበሰቡበት ወቅት

ይህን የሰሙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ፤ የእስልምና ፤ የካቶሊክ እና የመካነ ኢየሱስ የሀይማኖት አባቶች ተወካዮቻቸውን በመላክ ጉባኤውን ለመቃወም ‹‹ይህ አይነቱ ድርጊት በዕምነትም ሆነ በስነምግባር በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት የሌለው ምግባር ነው›› ለማለት ትላንት 19/03/2004 ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት ጋዜጠኞችን የጠሩ ሲሆን መግለጫው ሊጀመር ጥቂት ደቂቃዎች ሲቀሩት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ወደ አዳራሹ በመግባት የእምነት አባቶችን ረዘም ላለ ደቂቃ በዝግ ክፍል ያነጋገሯቸው ሲሆን ከጥቂት ቆይታ በኋላ የተቃውሞ መግለጫው አሁን መሰጠት እንደሌለበት ከስምምነት ላይ እንደደረሱ በተወካያቸው አማካኝነት ማሳወቅ ችለዋል፡፡ ለዓለም አቀፍና የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን ሊሰጡ የነበረው መግለጫ፤ እንዲሁም ለህዝቡ ሊያቀርቡት የነበረው ጥሪ ከጤና ጥበቃ ሚንስትሩ ጋር ከመከሩ በኋላ፣ ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ገልጸዋል። በዚህ ዙሪያ ላይ የመንግስት አቋም ህዝቡንም ሆነ ተሰብሳቢዎችን ላለማስቀየም ስብሰባው በሰላም ያለ ምንም ተቃውሞ ተጀምሮ እዲያልቅ ነው፡፡

አስተያየት ሰጪዎችም በበኩላቸው «ድርጊቱ መታሰቡ፤ በራሱ፤ አስጸያፊ ነው» ማለታቸው ተደምጧል።የሃይማኖት አባቶች፣ ይህንን ጉዳይ፣ ጸያፍ፤ ከሥነ-ምግብር ውጭና ባህላችንን የሚያቆሽሽ አጀንዳ ነው ብለዋለል፡፡


ዝርዝር መረጃ ከሪፖርተር ጋዜጣ ላይ 
በኢትዮጵያ የአራቱም ሃይማኖቶች መሪዎች በአዲስ አበባ በቅርቡ በሚካሄደው 16ኛው የአይካሳ ጉባዔን አስታክኮ በአገሪቱ ጸያፍ፣ ከሥነ ምግባር ውጭና ባህልን የሚያንቋሽሽ አጀንዳ ለማስፈጸም ተነሣሥቷል ያሉትን የአንድ ቡድን እንቅስቃሴን በመቃወም ትናንት ሊሰጡት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ላልተወሰነ ጊዜ ተላለፈ፡፡ የሪፖርተር ፎቶግራፍ ጋዜጠኛ መሪዎቹ መግለጫ ለመስጠት እንደተዘጋጁ ያነሳውም ፎቶግራፎች እንዲጠፉ ተደረገ፡፡

መሪዎቹን በመወከል መግለጫው ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ያስታወቁት ከኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ቄስ ኢተፋ ጎበና ሲሆኑ፣ የጋዜጠኛው ፎቶ ግራፎች እንዲጠፉ ያደረገውም በሥፍራው የነበረ አንድ የደኅንነት አባል ነው፡፡

መግለጫው የሚሰጥበት ትክክለኛው ቀን መቼ ነው ተብሎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ከጉባዔው በፊትም ሆነ በኋላ ሊሆን ይቻላል፡፡ ከዚህ ውጭ ትክክለኛው ቀን ይህ ነው ብዬ ለመናገር ያስቸግረኛል፤›› ሲሉ ቄስ ኢተፋ መልሰዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ መሪዎች በተወካያቸው አማካይነት መግለጫው ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ያስታወቁት፣ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ዶክተር ቴዎድሮስ አጽሃኖም በተገኙበት የዝግ ስብሰባ አድርገው በጉዳዩ ላይ ለአንድ ሰዓት ያህል ከተወያዩ በኋላ ነው፡፡ 

በኢትዮጵያ የአራቱም ሃይማኖቶች መሪዎች ኅዳር 19 ቀን 2004 .. 4 ሰዓት ሊሰጡ ያቀዱትን መግለጫ ለመዘገብ ይጠባበቁ ለነበሩ ጋዜጠኞች ‹‹ብርቱ ማሳሰቢያ›› በሚል ርእስ ከታደለው ጽሑፍ ለመረዳት እንደተቻለው፣ ራሱን አፍሪካን ሜን ፎር ሴክሿል ሄልዝ ኤንድ ራይትስ (አምሸር) ‹‹The African Men for Sexual Health and Rights (AMSHeR)›› ብሎ የሚጠራ የዚህ ቡድን/ድርጅት ዓላማ በአፍሪካ የሚገኙ ግብረሰዶማዊ ወንዶች የተሻለ ሕይወትና ተቀባይነት የሚያገኙበትን መንገድ ማመቻቸት ነው፡፡ 

ድርጅቱ 13 አፍሪካ አገሮች መቀመጫቸውን ያደረጉ 15 ግብረሰዶማዊነት እንደ በጎ ምግባር የሚያንጸባርቁ ድርጅቶች ያዋቀሩት የጋራ ድርጅት መሆኑን ጽሑፉ አስረድቷል፡፡ 

አምሸር ከአይካስ ጉባዔ ጋር አስታኮ ‹‹ቅድመ ኮንፈረንስ›› በሚል ርእስ ቅዳሜ ኅዳር 23 ቀን 2004 .. በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል 25 አገሮች ለተውጣጡ 200 ታዳሚዎች ኤምኤስኤም ኤንድ ኤችአይቪ (Men who have sex with men and HIV) በሚል  አጀንዳ ላይ ውይይት ለማካሄድ አቅዷል፡፡

የውይይቱ መሪ ቃል ‹‹የራስ ማድረግ፣ ማሳደግና ቀጣይነትየሚል መሆኑን ጽሑፉ ጠቁሞ፣ አምሸር በዕለቱ አይካስ ከሚያነሳቸው የውይይት ነጥቦች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው፣ ነገር ግን ግብረሰዶማዊነትና ግብረሰዶማዊ የመሆን መብትን በአዎንታዊ መልኩ የሚያንጸባርቁ የውይይትና የልምድ ልውውጥ መድረኮችን ለማካሔድ ማቀዱን አስረድቷል፡፡

በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ ግብረሰዶማዊነት ወንጀል እንደሆነ በግልጽ ተቀምጦ ሳለና 97 በመቶ በላይ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን እንደ አጸያፊና ኢሞራላዊ አድርገው የሚቆጥሩት መሆኑ እየታወቀ፣ ይህንን ስብሰባ ለማድረግ አምሸር ማቀዱ በኢትዮጵያ ሕግና ለኢትዮጵያውያን ሞራል ቦታ ያልሰጠ መሆኑን ያሳያል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የዚህ ኢሞራላዊ ስብሰባ በቅድመ ጉባዔ ስም 16ኛው አይካሳ ጉባዔ በፊት መደረግ በጉባዔው ላይ አሉታዊ አንድምታ እንዲያጎለበት ያደርጋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡ 

አምሸር በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል የሚያካሒደው የቅድመ አይካሳ ስብሰባ የማነቃቂያ ጉባዔ ዋና ዓላማዎች፣ በአፍሪካ የወንድ ለወንድ ግብረሰዶማዊ ግንኙነቶችን እውን የማስደረግ ጉዳይ ለኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት አስተዋጽኦ ስለሚያደርግ ትኩረት እንዲገኝ ማስቻል፣ ግብረሰዶማዊነት ሕጋዊ እንዲሆን ከማስቻል አኳያ አፍሪካዊ ምላሽና ነጸብራቅ ማሳየት፣ ኤችአይቪን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንጻር ግብረ ሶዶማዊነትን ሕጋዊ ማድረግ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ በመለየት ለተግባራዊነቱ አቅጣጫን መቀየስ ነው፡፡

ይህንን ስብሰባ የተሳካ ለማድረግ የዕለቱ ተጋባዥ ተናጋሪዎችም ሚሼል ሲዲቤ የተባበሩት መንግሥታት የኤችአይቪ ዋና ዳይሬክተር፣ ዶክተር ደብረ ወርቅ ዘውዴ የግሎባል ፈንድ ፀረ የኤችአይቪ፣ ቲቢ፣ የአባለዘር በሽታዎችና ወባ ፕሮግራም ምክትል ዳይሬክተር፣ አምባሳደር ኤሪክ ጎስቢ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የኤችአይቪ አስተባባሪ፣ የተከበሩ ሬኔ አላፒኒ ጋንሱ የቀድሞ የአፍሪካ ሰብዓዊ መብቶች ሊቀመንበርና የወቅቱ ቫይረሱ በደማቸው የሚገኙ ወገኖችና ይበልጥ ተጋላጭ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሰብዓዊ መብት አስከባሪ ኮሚቴ ሊቀመንበርና የአይካሳ ተወካይ ናቸው፡፡

ስብሰባው 15 አገሮች ላይ በጤናና በግብረሰዶማዊያን መብቶች ዙርያ የተዘጋጁ ተሞክሮዎች ይቀርብበታል፡፡ በዕለቱ ከተለያዩ 25 አገሮች የተውጣጡ 200 ተሳታፊዎች እንደሚታደሙበት የተገመተ ሲሆን፣ ይህ ስብሰባ ለግብረሰዶማውያኑ  አዲስ ትስስር ለመፍጠርና ለመቀናጀት፣ ልምድን ለማዳበር ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋፋትና ለሚቀጥለው ትውልድ ይህንኑ ዘይቤ ለማስተላለፍ ለየት ያለ ዕድል የሚፈጥር መሆኑ ይታመንበታል፡፡

አቶ ሚኪያስ ሲሳይ የአይካሳ የኮሙዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን ሥራ አስኪያጅ ስለዚሁ ጉዳይ በስልክ ተጠይቀው፣ ጽሑፉ እንዳልደረሳቸውና ምንም እንደማያውቁ ገልጸዋል፡፡ 16ኛው የአይካሳ ጉባዔ ላይም እንዲህ ዓይነት ቡድን ወይም ድርጅት ስለመሳተፉ የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ተናግረዋል፡፡

ስብሰባው የሚካሔድበት ጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ሥራ አስኪያጅ / ሮማን ታፈሰወርቅ፣ ‹‹ቅዳሜ የሚካሔድ ስብሰባ የለም፤ ውሸት ነው፤ የወሬው ምንጭ ከየት እንደመጣ አናውቅም፣ በእኛ ስም መጥፎ ወሬ እየተወራብን ነው፤ብለዋል፡፡ 

ሥራ አስኪያጇ ‹‹ዝም ብሎ ወሬ ነው›› ብለው ቢያስተባብሉም፣ አምሸር በድረ ገጹ ‹‹ቅድመ አይካሳ ኮንፈረንስ›› የሚካሔደው ስብሰባ ‹‹የራስ ማድረግ፣ ማሳደግና ቀጣይነት›› (Claim, Scale-Up and Sustain) በሚል መሪ ቃል ኅዳር 23 ቀን 2004 .. ከጧቱ 2 ሰዓት ተኩል እስከ 11 ሰዓት ተኩል ድረስ በጁፒተር ኢንተርናሽናል ሆቴል ይካሔዳል ብሏል፡፡ 

በተያያዘ ዜና መንበሩን በኬንያ ያደረገው ግብረሰዶማዊው ተቋም ኢሽታር ኤምኤስ ኤም፣ ለኢንጄንደር ሔልዝ ስታፍ እና ሬንቦ ኢትዮጵያ ከመስከረም 14 ቀን እስከ መስከረም 20 ቀን 2004 .. ድረስ ስለግብረሰዶም የምክክርና ጥናት መድረክ ማከናወኑ፣ በተለይም በመደገፍና በማስተባበር ሚናውን መወጣቱን የአምሸር ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡ መሠረቱን በኢትዮጵያ ያደረገው ሬንቦ ኢትዮጵያ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የግብረሰዶም አራማጅ ወጣቶች፣ ወንድ አዳሪዎችና ሌሎችም መካከል ኤችአይቪ ኤድስና የአባላዘር በሽታን ለመቀነስ የሚንቀሳቀስ ተቋም ነው፡፡

ግብረሰዶማዊው የኬንያው ተቋም ኢሽታር ካነገበው ዓለማዎች መካከል በግብረሰዶም ዙርያ የአቻ ለአቻ ትምህርት የኬንያን አምሳያ በኢትዮጵያ ማዳረስ እንደሆነ ኅዳር 5 ቀን 2004 .. ‹‹Ishtar MSM Hosts Engender health and Rainbow Ethiopia›› በሚል ርእስ የተሰራጨው ዘገባ አመልክቷል፡፡

በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግ (1996) ክፍል ሁለት ‹‹ለተፈጥሮ ባሕርይ ተቃራኒ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነቶች›› በሚል ርእስ በአንቀጽ 629 ግብረሰዶም እና ለንጽህና ክብር ተቃራኒ የሆኑ ሌሎች ድርጊቶች በሚል ርእስ፣ ‹‹ማንም ሰው ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ጾታ ካለው ከሌላ ሰው ጋር ግብረሰዶም ወይም ለንጽህና ክብር ወይም ለመልካም ጠባይ ተቃራኒ የሆነውን ሌላ ድርጊት የፈጸመ ማንኛውም ሰው ከቀላል እስራት እስከ ከባድ ወንጀል ቅጣት እንደሚጠብቀው ይደነግጋል፡፡ 

በአንቀጽ 631 ደግሞ ‹‹ለአካለ መጠን ባልደረሱ ልጆች ላይ የሚፈጸሙ የግብረሰዶም ጥቃትና ለክብረ ንጽህና ተቃራኒ የሆነ ሌላ ድርጊት›› በሚል ርእስ፣ ንኡስ አንቀጽ 1. ማንም ሰው ከእርሱ ጋር አንድ ዓይነት ጾታ ባለውና ለአካለ መጠን ባልደረሰ ልጅ ላይ የግብረሰዶም ጥቃት የፈጸመ እንደሆነ፤ የተበዳዩ ዕድሜ አሥራ ሦስት ዓመት ሆኖ አሥራ ስምንት ዓመት ያልሞላው ሲሆን፣ ከሦስት ዓመት እስከ አሥራ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡ የተበዳዩ ዕድሜ ከአሥራ ሦስት ዓመት በታች ሲሆን፣ ከአሥራ አምስት ዓመት እስከ ሃያ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት ይቀጣል፡፡ በተጨማሪም አንዲት ሴት ለአካለ መጠን ባልደረሰች ልጅ ላይ የግብረሰዶም ጥቃት የፈጸመች እንደሆነ፣ ከአሥር ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እስራት ትቀጣለች በማለት ደንግጓል፡፡  
ድምፃችን ለምን ፌስ ቡክ ላይ ብቻ ሆነ ? 
ዛሬ አይሆንም ብለን መቃወም ሲያቅተን ነገ ለሚከሰተው ግብረ ሶዶማዊነት ተግባር ተባባሪ መሆናችንን አንዘንጋ ፤ ለምን ? ዛሬ አልተቃወምንምና

28 comments:

 1. Ahunes tesfachin Man new?Egziabeher aydelemen!
  Yekedusan hager Ethiopian selewedajochih beleh Tebekat!!!

  ReplyDelete
 2. liqedim yemigebawin titen eris berisachin sininekakes seytan yerasun sira beadebabay ligelit tenesa yih tiliq subae (EGZIOTA) new yemiyasifeligew ye church tiliq gulibetua tsomina tselot new silezih yefikirina yeyikirita lib yizen Geta Jesus Christ yihin kifu sira endiyaferis enitseliy qalu eko እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቍጣ ከሰማይ ይገለጣልና ፤ እግዚአብሔር ስለ ገለጠላቸው፥ ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና። የማይታየው ባሕርይ እርሱም የዘላለም ኃይሉ ደግሞም አምላክነቱ ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሠሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤ ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቁ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤ ነገር ግን በአሳባቸው ከንቱ ሆኑ የማያስተውለውም ልባቸው ጨለመ። ጥበበኞች ነን ሲሉ ደንቆሮ ሆኑ፥
  የማይጠፋውንም የእግዚአብሔር ክብር በሚጠፋ ሰውና በወፎች አራት እግር ባላቸውም በሚንቀሳቀሱትም መልክ መስለው ለወጡ። ስለዚህ እርስ በርሳቸው ሥጋቸውን ሊያዋርዱ እግዚአብሔር በልባቸው ፍትወት ወደ ርኵስነት አሳልፎ ሰጣቸው ፤ ይህም የእግዚአብሔርን እውነት በውሸት ስለ ለወጡ በፈጣሪም ፈንታ የተፈጠረውን ስላመለኩና ስላገለገሉ ነው፤ እርሱም ለዘላለም የተባረከ ነው፤ አሜን።
  ስለዚህ እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤rome 1:18-28 yilalina betselotim enasibachew God yitebiqen fitunim yabiralin

  ReplyDelete
 3. ወቅታዊ የሆኑ ጉዳዮችን ስለምታሳውቁን በርቱ እንላለን ፤፤ የህን ነገር ስሰማ ውስጤ በጣም ነው የደነገጠው ምነው የትንቢት መፈጸሚያ አደረከን ብያለሁ ፡፡ አሁንም ቢሆን መቃወም መቻል አለብን ፤ ጊዜው ገና ነው የመንግስትም ሀሳብ ሊገባን አልቻለም ፤ ለምን አባቶች አስተያየት እንዳይሰጡ ተከለከሉ ? መንግስት ከግብረሰዶማውያኑ ጋር መተባበሩን ነው ይህ የሚያሳየው ፡፡ ስብሰባ ለሀገሪቱ ጥሩ ሊሆን ይችላል ፡፡ ነገር ግን ይህን አይነት አስነዋሪ ነገር እንዲደረግ መፍቀድ ‹‹ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል›› የሚባለውን ነገር ከግንዛቤ ማገባት መቻል አለብን፡፡ ደግሞ ሁሉም ነገር ይቅርብን ይህን መፍቀድ የለብንም ፤ ነገ ላይ የሀገራችን ግብረ ሰዶማውያን ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ…ጃል አንድ እንበል

  ReplyDelete
 4. Geta hoy!!! yichin kidist hager tebikat ebakih
  ''endecherinetih new enji endebedelachin atikifelen''.
  ahun gena maninetachinin yemineka metabin bewinet zim mebal yelelebet guday new

  ReplyDelete
 5. my God please to give me believe

  ReplyDelete
 6. መንግስት ጋዜጣዊ መግለጫውን የተቃወመው የእንግሊዝ መንግስት የተቃራኒ ፆታን መብት ለማያከብሩ ሀገራት የእርዳታ እጄን አጥፋለሁ ብሎ በማስታወቁ ነው::
  መንግስት ና ሀይማኖት ፖለቲካ ና እምነት ወደ አንድ መሪ እየተጓዙ ነው::

  ReplyDelete
 7. This is not something we ahould protest; WE MUST FIGHT. Is this our historical Ethiopia or Weyane's backyard? I m so mad!

  ReplyDelete
 8. ርብቃ ከጀርመንNovember 30, 2011 at 8:00 AM

  እዚኦ ወዴት እንጩህ ? ካንተ ሌላ ካላንተስ እኛምን አቅም አለን እንዲህያለውን የሞራልዝቅጠትስ በምን አቅማችን እንችለዋለን እባክህን አሳልፈህ አትስጠን ስንቱን እንቻለው:: አልመሸም አሁንም ግዜአለን ወደመንግስትም ወደአምላካችንም ለመጮህ ያቅማችንን ካደረግን ሌላውን ሁሉን በአግባቡ ዉብአድርጎ የፈጠረ አምላክ ያግዘናል የድንግልማርያምልጅ ሀገራችንን ከንዲህያለ ቅሌት ይጠብቅልን!

  ReplyDelete
 9. gin fekaju manew ye Zimbabwe president mugabi endih aynet tiyake siteyek yemelesew melis betam yemiyasidest new be 9 wer weldachu kasayachugn eshi kalhone gin be 24hr ke Zimbabwe enditileku new yalew

  ReplyDelete
 10. don't worry this is nothing but the sign of a beginning 4jujmentday !

  ReplyDelete
 11. ቸሩ፡አምላክ፡ይህን፡ክፉ፡ይንቀልልን፣አገራችንን፡ሃይማኖታችንን፡ሕዝባችንን፡ይጠብቅልን!!!
  እባካችሁ፡ይህንን፡ከጽሁፉ፡በላይ፡ያለውን፡አጸያፊ፡ሥዕል(foto)፡አንሱት፡፡ እንኳን፡ከቅዱሳን፡ሥዕላት፡በታች፡ቀርቶ፡እንዲሁም፡መቀመጥ፡ያለበት፡አይመስለኝም፡፡
  እግዚአብሔር፡ሁላችንንም፡ይጠብቀን!!!
  የእመቤታችን፡አማላጅነት፡አይለየን!
  የቅዱሳን፡መላእክት፡እርዳታ፡አይለየን!

  ReplyDelete
 12. hmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmmm!!!!!, mechereshachn yhe hon??????????? hager egzabhar, b emnt kedmetnet yemntawokew zara b zhe rekash sebseba astnagajent y hagerachn sem b alme media leserach??????? hmmmmmmmmmmmm!!!!!!

  ReplyDelete
 13. ቁመው የሰቀሉት ተቀምጠው ለማውረድ ይከብዳል
  ዛሬ ዛሬ በአገራችን የምንሰማቸው ፤የምናያቸው፤የምናዳምጣቸው የዕድገት ዜናዎች ሁላችን እንደሚያስደስቱን ሁሉ በተቃራኒው ከመሰልጠን/እኔ ግን ከስልጣኔ ጋር ተያይዞ የሚመጣ መሰይጠን ብየዋለሁ/ ጋር ተያይዘው የሚመጡ አጉል ልምዶች፤ትውፊትን እና ባህልን የሚጎዱ ድርጊቶች እጅጉን የሚሰቀጥጡ እየሆኑ በመምጣታቸው ለእድገት እና ለለውጥ የተነሳውን ህዝብ ወኔ እና አልሸነፍ ባይነት ወደ ኋላ እንዳይቀለብሰው ያሰጋል፡፡
  ለኢትዮጲያ ስልጣኔ፤ብልጽግና፤እድገት አድስ ነገር አይደለም፡፡በርካታ አገሮች ምንም ሳይኖራቸው ከባዶ ተነስተው ዛሬ እድገት እና ስልጣኔ ማማ ደርሰዋል ምንም እንኳን ስልጣኔያቸው ለሁከት፤ ከጭንቀት፤ ከሰቆቃ፤ ከዕሮሮ፤ ከመከራ ፤ከዋይታ ፤ከሃዘን፤ ከመከፋት ፤ከባዶነት ስሜት--- እንዲወጡ ባያስችላቸውም፡፡አገራችን ኢትዮጲያ የስልጣኔ ምንጭ ከነበሩት ግሪክ፤ግብጽ፤ባቢሎን የምትመደብ ነች፡፡አግኝቶ ማጣትን፤አጥቶም ማግኘትን የምታውቅ አገር ነች ኢትዮጲያ፡፡የነአክሱም፤የነላሊበላ---ስልጣኔ ጠፍቶ በረሃብ ህዝቦቿ የተጎዱባት፤የውጭው ሚዲያ ሳይቀር የተሳለቀባት፤የረሃብ ምሳሌ ተደርጋ የተጻፈች አገር ኢትዮጲያ በቅርብ እያስመዘገበች ባለቸው እድገት መሰረት ደግሞ አጥቶ ማገኘትን በማጣጣም ላይ ትገኛለች፡፡ይህ አጥቶ በማግኘት ላይ የሚገኝ ህብረተሰብ በድህነት፤በረሃብ፤በችግር፤--በነበረበት ዘመናትም ቢሆን አነሰም በዛም ያጣው ነገር ከጎተራው ምርትን ፤ከሳጥኑ ገንዘብን ፤ከጓሮው አዝመራን--- እንጂ ባህሉን፤ወጉን፤ትውፊቱን፤መቻቻሉን፤መተባበሩን፤መረዳዳቱን አልነበረም፡፡
  በጥንቱ ስልጣኔዋም ሆነ በችግር ዘመናቶቿ ባህሏን እና ወጓን ጠብቃ እንዳላለፈች ሁሉ ዛሬ ዛሬ ኢትዮጲያ የባህል እና ወግ ወረራ እየተደረገባት ትገኛለች ፡፡በሞቴ ምን ያህል ቢደፍሩን ነው ደግሞ ብለው ብለው አገራችን ላይ የግብረ-ሰዶም ስብሰባ ለማካሄድ የተዘጋጁት?ለነገሩ እነርሱ እኮ (የባህል ወረራ ለማድረግ የተዘጋጀ ማንኛውንም የውጭ ዜጋ ያጠቃልላል) አሁን ዝም ከተባሉ ከዚህ የባሰ ፈተና በአገራችን ሊያመጡ እንደሚችሉ በተለያዩ አገራት የፈጸሟቸውን አሉታዊ ስራዎች መዘከር በቂ ነው፡፡
  አገር አገር ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው የራሱ ባህል እና ወግ ተጠብቆለት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ያ ካልሆነ ግን አንድ አገር አገር ነው ስንል ያካለለውን የቆዳ ስፋት ብቻ ይዘን ሳይሆን በውስጡ የሚኖሩትን ህዝቦችንም አካቶ በመሆኑ የእኛ ኢትዮጲያኖች ማንነት ሊጠበቅ የሚችለው ባህላችን ሲጠበቅ ብቻ ነው፡፡ ስለሆነም የግብረ ሰዶም ድርጊት በአገራችን ላይ እውቅና የሚያገኝ ከሆነ፡-
  1) ከ90%/?/በላይ ህዝቧ ሃይማኖተኛ በመሆኑ እና በአገራችን ያሉ ሁሉም ሃይማኖቶች ይህን ፀያፍ ተግባር ስለማይቀበሉ በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረው የተስፋ መቁረጥ ስሜት እጂግ ከፍተኛ ነው የሚሆነው
  2) ተስፋ የቆረጠ ህብረተሰብ ደግሞ ለአንድ አገር እድገት የሚኖረው አስተዋፅኦ አሉታዊ ነው የሚሆነው፡፡ ከዚያም ባለፈ ይህንን ተግባር በሚፈጽሙ ሰዎች ላይ አጸፋ ሊወስድ ይችላል፡፡
  3) በርካታ ህብረተሰብ ላይ የአስገድዶ መደፈር እና በሽታ መስፋፋት መንስኤ ይሆናል
  4) የመንግስትን ህልውና መገዳደሩ አይቀርም ---እናም ሳይቃጠል በቅጠል እንዲሉ
  ሀ.ይህ ሊደረግ የታሰበው ስብሰባ በአስቸኳይ ቢሰረዝ
  ለ.ማንኛውም ኢትዮጲያዊ ይህን ተግባር ለማስተባበር ከሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ጋር አብሮ ባያብር፡፡ለምሳሌ ህትመት ባለማተም፤ቢሮ እና ሆቴል ባለማከራየት፤አብሮ እንዲኖሩ ባለመፍቀድ--
  ሐ.ስብሰባው በአድስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመደረግ በመታቀዱ ከታሪክም ተወቃሽነት ለማምለጥ ይቻል ዘንድ የአድስ አበባ ህዝብ ድርጊቱን በተመለከተ አስቸኳይ ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርግ
  መ.በአሁኑ መንግስታችን ውስጥ ካሉ ሚኒስትሮች አንዱ እና በህዝቡ ተወዳጅ የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም በእርሳቸው የጤና ሚኒስተርነት ይህ ጸያፍ ድርጊት እውቅና እንዳያገኝ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ቢወጡ
  ሠ.መንግስት እንደ መንግስት ይህ ጸያፍ ድርጊት በአገራችን እውቅና የማያገኝበትን ስራ ቢሰራ፡፡ በተለይም በእርዳታ እናቋርጣለን ሰበብ ድርጊቱ ተግባራዊ ሊሆን ይችላል ብለው ትንበያ ለሚተነብዩ ሰዎች የፈረንጆቹ እርዳታ ሳይሆን የህዝባችን የልማት ስሜት ብቻ ነው እዚህ ደረጃ ያደረሰን ብሎ ድርጊቱ እውቅና እንደማይኖረው ለእኛ ለህብረተሰቡ ቢያረጋግጥልን

  ይህ ሳይሆን ቀርቶ ግን ድርጊቱ እውቅና ካገኘ በእኛ ዘመን በአገራችን ላይ እኛው እራሳችን ያወጅነው የእራስን ባህል እና ወግ በራስ የማጥፋት ክስተት ሆኖ ያልፋል፡፡ስለሆነም መንግስትም ሆነ እኛ ህብረተሰቡ ይህ ድርጊት እንዳይፈጸም ቆመን ሳለን አንድ ነገር እንበል እላለሁኝ፡፡

  ውብሸት ነኝ ከባህር ዳር!

  ReplyDelete
 14. Please remove the picture. This is not a right place.

  ReplyDelete
 15. Homosexuality & Sodomy are not simple ethical sins rather are religious sinful practice. It should not be on statistical research or majority openion but for Orthodox christians the HOLY BIBLE is the final authority for both belief and behaviour.
  Here on the first epistle of PAUL THE APOSTLE to the Corinthians(1Cor 6:9-10) "Do you not know the unrighteous will not inherit the kingdom of God? Do not be deceived. Neither fornicatos, nor idolators, nor adulterors, nor HOMOSEXUALS, nor SODOMITES, ..."
  SO, our apostolic, historic and national Tewahido church has to condemns those who excommunicate to our Apostles and ancient holy fathers teaching. Also we have to protect those church oppositions and pretenders rose from every direction.

  >>> GOD BLESS ETIOPIA

  ReplyDelete
 16. Homosexuality & Sodomy are not simple ethical sins rather are religious sinful practice. It should not be on statistical research or majority openion but for Orthodox christians the HOLY BIBLE is the final authority for both belief and behaviour.
  Here on the first epistle of PAUL THE APOSTLE to the Corinthians(1Cor 6:9-10) "Do you not know the unrighteous will not inherit the kingdom of God? Do not be deceived. Neither fornicatos, nor idolators, nor adulterors, nor HOMOSEXUALS, nor SODOMITES, ..."
  SO, our apostolic, historic and national Tewahido church has to condemns those who excommunicate to our Apostles and ancient holy fathers teaching. Also we have to protect those church oppositions and pretenders rose from every direction.

  >>> GOD BLESS ETIOPIA

  ReplyDelete
 17. please remove the picture, it is absolutly wrong to see this picture in this place. are you teaching us religious education or something else ?

  ReplyDelete
 18. thise is very dangerous road!!!

  ReplyDelete
 19. ይህን እኮ የኢህዲግ መንግስት የሚደርገው ለምን እነደሆነ ይታወቃል፤
  1ኛ- ከእነዛ ሀይማኖት እና ስርአት የለሽ ምአራባውያን ገንዘብ ለማግኘት፤
  2ኛ- የኢህዲግ መንግስት የአጉልና የእውሸት ዲሞክራሲ እከተላለሁ ስለሚል ይህን አጸያፊ ተግባር በግልጽ እነዲካሄድ በመፍቀድ ዲሞክራሲዊ መንግስት ነኝ የሚለውን የእውሸት ፕሮፖጋንዳ ለመናዛት፤
  3ኛ- የዚህ አጸያፊ ተግባር ተከታይ የሆኑ ሰወችን የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት ነው;
  ግን እኔን የገረመኝ ……………. ዴሞክራሲያዊነት የሚገለጸው ይህን አጸያፊ ተግባር በዚህች በተቀደሰች ሀገር ህጋዊ እንዲሆን በመፍቀድ ነው ???????????????? ጠነካራ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓረቲ ሲመጣማ አሸባሪ እየተባለ ይፈረጃል!!!
  ኦ…..አምላኬ
  ኦ…… የሰራዊት ጌታ እግዝያብሔር ሆይ ኢትዮጵያን እያት ህዝቦቹዋ እየተራቡ፤ አየታረዙና እየተሰቃዩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 20. ይህን እኮ የኢህዲግ መንግስት የሚደርገው ለምን እነደሆነ ይታወቃል፤
  1ኛ- ከእነዛ ሀይማኖት እና ስርአት የለሽ ምአራባውያን ገንዘብ ለማግኘት፤
  2ኛ- የኢህዲግ መንግስት የአጉልና የእውሸት ዲሞክራሲ እከተላለሁ ስለሚል ይህን አጸያፊ ተግባር በግልጽ እነዲካሄድ በመፍቀድ ዲሞክራሲዊ መንግስት ነኝ የሚለውን የእውሸት ፕሮፖጋንዳ ለመናዛት፤
  3ኛ- የዚህ አጸያፊ ተግባር ተከታይ የሆኑ ሰወችን የፖለቲካ ድጋፍ ለማግኘት ነው;
  ግን እኔን የገረመኝ ……………. ዴሞክራሲያዊነት የሚገለጸው ይህን አጸያፊ ተግባር በዚህች በተቀደሰች ሀገር ህጋዊ እንዲሆን በመፍቀድ ነው ???????????????? ጠነካራ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓረቲ ሲመጣማ አሸባሪ እየተባለ ይፈረጃል!!!
  ኦ…..አምላኬ
  ኦ…… የሰራዊት ጌታ እግዝያብሔር ሆይ ኢትዮጵያን እያት ህዝቦቹዋ እየተራቡ፤ አየታረዙና እየተሰቃዩ ነው፡፡

  ReplyDelete
 21. እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤rome 1:18-28

  ReplyDelete
 22. እግዚአብሔር ለሚያስነውር ምኞት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ሴቶቻቸውም ለባሕርያቸው የሚገባውን ሥራ ለባሕርያቸው በማይገባው ለወጡ ፤ እንዲሁም ወንዶች ደግሞ ለባሕርያቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኘት ትተው እርስ በርሳቸው በፍትወታቸው ተቃጠሉ፤ ወንዶችም በወንዶች ነውር አድርገው በስሕተታቸው የሚገባውን ብድራት በራሳቸው ተቀበሉ። እግዚአብሔርን ለማወቅ ባልወደዱት መጠን እግዚአብሔር የማይገባውን ያደርጉ ዘንድ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤rome 1:18-28

  ReplyDelete
 23. Egziabeher Amelak redton Hgerachen Ethiopianena Weganachenen enaden! yeh yeseytan sera new Egziabeher kegna gar yehun!

  ReplyDelete
 24. no no no,,tebabarima ayidelenim,,hagerachin sitidefer ena bahlachininina siriatachinin lemabelashet yemetutin hulu ,mekawem bicha sayihon ,,le hagerachin ye dem wagam bihon enkefilalen,,,,egzihabher kega gar yihun,,,emebrihan hagerachinin le zelialem titebikilin AMEN,lesimu aterari kibir misgana yigbawu,,AMEN

  ReplyDelete
 25. አሁንስ የት እንድረስ ልጆቻችንን የት እናሳድግ ብለው ብለው ደግሞ ይሄን አመጡብን መንግስት ቢያስብበት ጥሩ ነው ይህ ነው ዘርማጥፋት ወንወጀል ስንቱን እንታገል ኑሮውን ወይስ ደግሞ ስሙን አልጠራውም ስሙ ይጠፋ የዚችን ሀገር ከነህዝቡዋ አምላክ የጠብቅልን ሰዎች እናልቅስና አምላክን እንለምን እሱ አያሳፍረንም ፈጥሮናልል እና በስራአቱ አለሙን ሲፈጥር እኮ እንደ አልማዝና እንቁ ውብ ያድገው እሱ ነውና ከስርአት ውጭ መሆን ደግሞ ሞት የሞት ሞት አለበት ሀገርም ይጠፋል ‹‹ጌታ ሆይ ከሐይለኞችና ጨካኞች ተጽእኖ ጠብቀን መሪዎቻችንን መልካሙን ነገር አመልክታቸው አሜን››

  ReplyDelete
 26. እንደዚህ ዓይነቱ መዓት ሲመጣብን መጸለይና ንሰሐ መግባት
  እግዚያብሔርን መለመን እንጂ ሌላ በምንም አናሸንፈውም
  እግዚያብሔር አገራችንን ይጠብቅ
  የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን

  ReplyDelete
 27. በጣም አሳፋሪ ነገር ነው ለእንደዚህ አይነቱ እራሱ ለእራሱ ጉዳይ ይምጣና ፍሬውና ግርዱ ይለይ አለያም እሳቱን በአጥፊው ላይ ያድርገው በየዘመኑ በቤተክርስትያ ጣራ ውረዱ ልባችሁን ለቅንንነት አዘጋጁ ንስሀ ንስሀ ንስሀ

  ReplyDelete