እረ. . ." የቤተ ክርስቲያን አምላክ ወደኛ ተመልከት"
ለአሜሪካ የሀገረ ስብከት የሥራ አስኪያጅነት የተጠቆሙ ሰዎች ሥምም አብሮ ደርሶናል
- አባ ሰረቀ በሥራ አስኪያጅነት
- ሊቀ ካኅናት ኃይለሥላሴ (ዴንቨር ) በጸሀፊነት
- አቶ በጋሻው ደሳለኝ በስብከት ወንጌል ኀላፊነት (ከፓትሪያሪኩ የትብብር ደብዳቤ ለአሜሪካን ኤምባሲ እንዲጻፍላቸው በአባ ፋኑኤል ተጠይቀው ፈቃደኝነታቸውን ገልጸዋል) ደብዳቤው በዛሬው እለት ተዘጋጅቶ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ እንደሚፈርሙበት ዛሬ ይጠበቃል)
- የመከፋፈል ሥራቸውን 02/21/2004 ጀምረው በሳሪስ በሚገኘው መኖሪያ ቪላቸው ውስጥ ስብሰባ አድርገዋል(እስከ ምሽቱ ፮ ሰዓት ድረስ በአባ ፋኑኤል ቤት ሲዶልቱ አምሽተዋል)
- “እኔ አሜሪካዊ ነኝ ምንም አይጎድልብኝም ይብላኝ ለእናንተ”አቡነ ፋኑኤል ከሐዋሳ ሲነሱ የተናገሩት
". . .ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት. . ." የያዕቆብ መልእክት ፩ ፥ ፪ - ፫
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ በሚሆን አሜን
ሰሞኑን ከቅዱስ ሲኖዶስ አካባቢ የመጣው ዜና እጅግ አስደንጋጭ፣ አሳዛኝ፣ ሚዛናዊ ያልሆነ እንደሆነ ለማናችንም ግልጽ ነው፥ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን እስቲ ተጠየቁ እረ ለመሆኑ ከመቼ ጀምሮ ነው
- ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲጥሱ እና ሲያስጥሱ፣
- ለፕሮቴስታንታዊያን ተሀድሶ ቡድኖች እውቅና በመስጠት የነበሩ፣
- ሕገ ወጥ ሰባኪያንን እና ዘማሪያንን (ኑ በእኔ ሀገረ ስብከት ማንም ሊከለክላችሁ አይችልም) በማለት ሲያበረታቱ እና ሲያዋቅዱ የነበሩ፣
- የግል ንብረትን እና ሃብትን ብቻ ማጋበስ የለመዱ፣
- ከዋሺንግተን ዲሲ ደብረ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን $ 150,000.00 ገንዘብ የዘረፉ፣
- በዋሺንግተን ዲሲ ላይ የውጪ ግንኙነት የተባለውን ጽ/ቤት (አሁን ቅዱስ ሲኖዶስ የዘጋውን) ያዋቀረ እና የመሰረቱት
እነዚህን ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሱት በደልን ሳይመለከቱ እና ሚዛናዊነት በጎደለው ወይም የበቀለኝነት ስሜትን በሚያሳይ መልኩ አባ ፋኑኤል በምን መመዘኛ ነው የካሊፎርኒያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስንከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ለመሥራት የተመደቡት፣ እውነት እንነጋገር ከተባለ እኮ እኝህ ሰው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሊያዳክሙ እና መልካም የሆነውን ጅምር እንዲያጠፉ ካልሆነ በስተቀር እንደእውነቱ ሥራ ሰርተው ያሠራሉ የሚል እምነት የለንም።
የሆነ ሆኖ ወደ አሜሪካ ሄዱ እንበል፣ በገለልተኛ አስተዳደር ስር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት በምንም መልኩ ሊቀበሏቸው እንደማይችሉ የታወቀ ነው፣ ምክንያት እያደረጉ ያለውም የአቡነ ጳውሎስ ፕትርክና ህጋዊ አይደለም፣ ፓትሪያሪክም አይሰደድም ስለዚህ በሀገር ውስጥ ያለውም ሆነ በውጪ ያለው ሲኖዶስ በገለልተኛ አስተዳረስ ስር ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ተቀባይነት የሌላቸው እንደሆነ የታወቀ ነው። ታዲያ እኚህ ከፋፋይ የመናፍቃን ጠበቃ የሆኑ አባት እውን አሁን መጥተው በገለልተኛ አስተዳደር ስር ያሉትን አብያተ ክርስቲያናት አሰባስበው ሥራ ሊሠሩ ቀርቶ ያለውን ልዩነት እንዳያጠቡት ያስፈራናል።
ሌላው ደግሞ በካሊፎርኒያ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ስር ግምቱ ወደ ፲፱ የሚሆኑ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ያሉ አጥቢያች እንዲሁም በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ደግሞ እንዲሁ ግምቱ ወደ ፲፮ የሚሆኑ አጥቢያዎች እንዲሁ በእናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚገኙት፣ አሁንም እኚህን አባት ሥራቸውን እያየ በአዋሳ ሕዝበ ክርስቲያን ላይ ያደረሱትን በደል እና ግፊት ሲመለከት የነበረ ምዕመን ሁሉ ዛሬ እንዴት ብሎ ነው የቅዱስ ሲኖዶስን ትዕዛዝን ለማክበር እንደዛ የቤተ ክርስቲያንን ልጆች ሊያሳድዱ የነበሩን አባት ዛሬ እንዴት አባታችን ብሎ ሊቀበል ይችላል? ይህ ደግሞ በፍፁም እንደማይሆን የታወቀ ነው።
ታዲያ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እኚህን ከፋፋይ አባት በምን መመዘኛ እንደሆነ ባልታወቀ መልኩ እነዚህን ሁለት ሀገረ ስብከቶች አጠቃለው እንዲሰሩ ትዕዛዝ ተሰጥቷቸዋል ነው የሚባለው፣ ትልቁ እና አስቸጋሪው የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት ትልቅ አደጋ ላይ እንደሚወድቅ የታወቀ ቢሆንም የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ያለምንም ማመላከት ይሁን ብለው ተቀብለዋል።
ዘግይቶ የደረሰን ዜና እንደሚያስረዳን፣ እኚህ ከፋፋይ አባት የመከፋፈል ሥራቸውን ከዛሬው ጀምረው በትላንትናው እለት በሳሪስ በሚገኘው መኖሪያ ቪላቸው ውስጥ ስብሰባ አድርገው እንደነበር እና ይንን ሥራቸውን ከአሁኑ መጀመራቸውን ዘጋቢያችን ከሳሪስ ገልጸውልናል በስብሰባው ላይ
፩ኛ/ ወ/ሮ እጅጋየሁ በየነ (እማትሪያሪክ)
፪ኛ/ አቶ በጋሻው ደሳለኝ
፫ኛ/ አቶ ያሬድ አደመ
፬ኛ/ አራተኛው ሰው በትክክል ማንነቱ ያልተረጋገጠ ሰው
ቤተክርስትያንን ለእነዚህ ጥቅመኞች ላለማስረከብ ሁላችን እንትጋ
አሁንም ወደ እዚህ ሀገረ ስብከት ሲሄዱ የመጀመሪያ ሥራቸው የሚሆነው በሀገረ ስብከቱ ሥር ያሉትን አጥቢያዎች በምክንያት በመበተን እና የራሳቸው የሆነ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንደሚያዋቅሩ ከወዲሁ ተገምቷል። በዚህም መሰረት ለመጪው የሀገረ ስብከት የሥራ አስኪያጅነት የተጠቆሙ ሰዎች ሥምም አብሮ ደርሶናል
አባ ሰረቀ በሥራ አስኪያጅነት
ሊቀ ካኅናት ኃይለሥላሴ (ዴንቨር ) በጸሀፊነት
አቶ በጋሻው ደሳለኝ በስብከት ወንጌል ኀላፊነት (ከፓትሪያሪኩ የትብብር ደብዳቤ ለአሪካን ኤምባሲ እንዲጻፍላቸው በአባ ፋኑኤል ተጠይቀው ፈቃደኝነታቸውን ገልጸዋል) ደብዳቤው በዛሬው እለት ተዘጋጅቶ ፓትሪያሪክ ጳውሎስ እንደሚፈርሙበት ዛሬ ይጠበቃል)
በእጩነት ተጠቁመው ሊሰራባቸው እንደሚገባ ከወዲሁ የሥራ ትዕዛዝ ለአባ ፋኑኤል እንደተሰጣቸው ይገመታል፣ ከዚህ በተጨማሪ በዋሺንግተን ዲሲ የሚመገኘው የደብረ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን መንበረ ጵጵስና አድርገው ሥራቸውን ከእዚው እንደሚጀምሩ ከወዲሁ ተገምቷል
በአጠቃላይ የተዋኅዶ ቤተሰቦች፣ ይኅንን የማፍረስ ዓላማቸውን ከወዲሁ አውቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ከመናፍቃን እና ሰርጎ ገቦች ልንጠብቅ ይገባናል፣ ዛሬ በቤተ ክርስቲያን ላይ የመጡት ኅይሎች እንደ በፊቱ ጠላት ሆነው አይደለም፣ ጠላት በጠላትነት ሲመጣና ወዳጅ መስሎ ሲመጣ በጣም ልዩ ስለሆነ እነዚህ ኃይሎች እኛን መስለው የበግ ለምድ ለብሰው (በቅርቡ ለምዳቸውን አውልቀው ተኲላነታቸውን እስኪያሳውቁን) እኛኑ ሊያጠቁን የመጡትን ልንከላከል እና ይህችን ርትዕይት ቤተ ክርስቲያን ለትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት የሁላችንም ነው ብለን እናምናለን።
ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎች:
ይሁን ብለን ተቀብለን አብረን ብንሠራ ሊመጡ የሚችሉ ፈተናዎች የሚከተሉት ናቸው
፩/ የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ጉዳይ ትልቅ አደጋ ላይ መውደቅ
፪/ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የማጥፋት፣ የማበላሸት አደጋ
፫/ በብዙ ድካም እና ልፋት የተቋቋሙት የምዕራብ እና ካሊፎርኒያ እንዲሁም የዋሺንግተን እና አካባቢዋ ሀገረ ስብከት መፈራረስ
፬/ ዋሺንግተን ዲሲ የሥርዓት አልበኞች እና የመናፍቃን መደበቂያ እና መናኧሪያ መሆኗ
፭/ በቅን አገልጋዮች አባቶች ላይ የሚደርሰው የማሳደድ ዘመቻ
፮/ የካሊፎርኒያ እና የዋሺንግተን አካባቢዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ መገዛቱ ቀርቶ በቀጥታ ለፓትሪያሪክ ጳውሎስ ብቻ ተጠሪ የማድረግ ትግል
፯/ የቤተ ክርስቲያኒቱ ንብረቶች እና ሃብቶች በግል ጥቅም አሳዳጆች መመዝበራቸው
፰/ ወደፊት ከነ አባ ፋኑኤል በኃላ ለሚመጣ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን አካል ከባድ ፈተና እንደሚሆን
እነዚህን የመሳሰሉ ከባድ ፈተናዎች ሊደርሱ በዓይናችን ላይ ተጋርጠዋል ወቅቱ አሁን ነው ትክክለኛ የሆነ አባቶች ለነዚህ ሀገረ ስብከቶች ተልከው የነበረውን መንጋ ሳይበትኑ የራቀውንም ሊያቀራርቡ የሚችሉ ችሎታና ብቃት ያላቸው የቤተ ክርስቲያን አባቶች እንዲላኩ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ወይም የቋሚው ሲኖዶስ አባላት ሊያሳስቡልን ይገባል፣ ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ደግሞ ከወዲሁ ተረድቶ መከላከል የናንተ ኅላፊነት እንደሆነ ቅዱስ መንፈስ የሰጣችሁ ኅላፊነታችሁን በትክክል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በምታዘው መልኩ ልትሰሩበት ይገባል ብለን ልንጠቁም እንወዳለን። ያ መሆን ካልቻለ ግን ጌታ በወንጌሉ እንደተናገረው
". . . የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። . . ." የሐዋሪያት ሥራ ፳ ፥ ፳፰ ላይ ያለው ሀይለ ቃል ለናንተ ስለሆነ፣ አበው የሰሩልን ሥርዓት ሳይጓደል፣ ሳይበረዝ፣ ሳይደለዝ እንዳለ ከነ ሙሉ መንፈሳዊ ትጥቁ ለትውልድ ማስተላለፍ ካልቻልን እናንተንም በታሪክም፣ በፈጣሪ ፊትም ከተጠያቂነት የምታመልጡ አይመስለንም::
‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ››
If this happens , that will be the end of the beginning...
ReplyDeleteEgzio!!!!!!!! Abetu Adinen enji zim Atbel.
ReplyDeleteአድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር፤ ወውሀደ ሃይማኖት እምዕጓለ እመሕያው፡፡ ከንቶ ይትናገሩ አሐዱ ምስለ ካልኡ፤ በከናፍረ ጉሕሉት ልበ ወበልብ ይትናገሩ፡፡ ይሤርዎን እግዚአብሔር ለከናፍረ ጉሕሉት፤ ወለልሳን እንተ ተዐቢ ነቢበ፡፡ መዝ. ፲፩፥፩—፫
An evil envy have come from evils that is you!
ReplyDeleteአድኅነኒ እግዚኦ እስመ ኀልቀ ኄር፤ ወውሀደ ሃይማኖት እምዕጓለ እመሕያው፡፡ ከንቶ ይትናገሩ አሐዱ ምስለ ካልኡ፤ በከናፍረ ጉሕሉት ልበ ወበልብ ይትናገሩ፡፡ ይሤርዎን እግዚአብሔር ለከናፍረ ጉሕሉት፤ ወለልሳን እንተ ተዐቢ ነቢበ፡፡ መዝ. ፲፩፥፩—፫
ReplyDeleteAmelak hoy yichin kidist betechirisitiyan silemin zim alikat ''abetu kinidihin atitef ejochihinim zeriga ayinochihim egnan kememeliket ayibozinu fetineh na atizegiyibin''
ReplyDeleteይድረስ ለአሜሪካ የሀገረ ስብከት ምዕመናንና ካህናት በሃይማኖት የምትመስሉኝ ሁላችሁ አባቶቼ እናቶቼ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንዲሁም ህፃናት የኢትዮጰያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች በሙሉ ቤተክርሰቲያን አንድነቷ ተጠብቆ ታሪኳ ለትውልድ እንዲተላለፍ ሁላችሁም የበኩላችሁን አስተዋፆ እንድትወጡ የጀመራችሁትን ተጋድሎ በመተጋገዝ በመተባበር በመጠናከር ልታጎለብቱት ይገባችኋል እኔ የሚሰማኝ ለቅዱስ ሲኖዶስ የፃፋችሁት ደብዳቤ ጥሩ ነው ቅዱስ ሲኖዶስ የፃፋችሁትን ነገር ባይሰማ መልሱንም እንደምትፈልጉት ባይሆን ግን እራሳችሁ ተጠናከሩ እንጂ ቤተክርስቲያንን ሊከፋፍሏት ለተነሱት ጠላቶች አሳልፋችሁ አትስጡ እያንዳንዱ ምዕመን በአንድ ልብና በአንድ ሀሳብ ሆኖ ለቤተክርስቲያን ከቆመ ጥቂት ሰዎችን ጉልበት እንዳይኖራቸው ማድረግ ይችላል እነሱ ስልጣናቸውንና ገንዘባቸውን አምነው ቢነሱ ምዕመኑ ደግሞ እግዚአብሔርን ይዞ ያሸንፋልና አትደናገጡ ህብረታችሁንም አጠንክሩት እንጂ አትዳከሙ ሁልጊዜ ጥሩ ሥራ ከሰራችሁ እግዚአብሔር ይዋጋላችኋል አታስቡ እዚህ ያሉት ጳጳሳትም እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች የሆኑትን እንዳናጣቸው ያሰጋኛል አንዳንዴ ውሳኔው የሚያስደነግጥ ቢሆንም በጫናም ሊሆን ስለሚችል መፍረድ ከባድ ነው እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች በህይወት ቢኖሩ ደግሞ ወደፊት ሊያስተካክሉት ስለሚችሉ ለህሊናቸውና ለፈጣሪያቸው ታማኝ ከሆኑ ማለቴ ነው ምክንያቱም አሁን የተጠቀሙበት ዘዴ እኔ እንደሚመስለኝ አንዱን ሰጥቶ አንዱን መቀበል አንድ ለፓትሪያርኩ አንድ ለእውነተኛ የተዋህዶ ጳጳሳት አባ ሰረቀን ከማደራጃ መምሪያው ማንሳት አቡነ ፋኑኤልን አሜሪካ ላይ መሾም እኔ የሚያሰጋኝ ወደፊት ተሃድሶ ፕሮቴሰታንቱ ጉልበት አግኝቶ ቤተክርስቲያንን እንዳይከፍል ምእመኑ ከፍተኛ ተጋድሎ ማድረግና ነቅቶ መጠበቅ ያለበት ይመስለኛል ምዕመኑ እኮ ከተጠናከረ መሪዎቹን ማስተካከል አያቅተውም ምክንያቱም የገንዘቡ ምንጭ ምእመኑ ነው እንጂ ጳጳሳቱ እኮ አይደሉም እግዚአብሔርን ማስደሰት የሚቻለው በአግባቡና በሥርኣት ሲሰሩ ነው
ReplyDeleteyebase atameta yilal yagere sew. yezenderow degmo betam beza....
ReplyDeleteAheyawen ferto dawelawen!!!
ReplyDeleteGize yansaw qile dengay yesebral!!!
menafiqun teto haqegnawen meqtate!!!
abune fanuel menfiq degafiwen teto Abune Abrahamin ena Abune kewestasiosen ye EOTC ewenetegna Papasat mansat!!!!
Geleltegnawen degifo haqegna Eotc yehonewen mawared!!!!
Haseten aqfo ewneten metal!!!
yesereqewen teto yalsereqewn mawgez!!!!!
Yemayetazezewen teto yemitazezewen menaqe!!!!
Ere lemehonu min yaladeregachihut neger ale? Ere Egziabeher and belachew.
Egziabeher hoy
endaleh enawqalen
yehe hulu siderg zim alken
yelehim maletem anechilemna
ere freden mehreten lakelen.
Abune Poulosen tureta bet lakelein
Abune fanuelen abirelen
Aba sereke en menafikan gebre aberochachewn ezaw yazelen yezeh ye esart erat adergilen
Bete kirstianachinin tebekelen
Yemiafersuaten aferselen
yemindegfwaten barkilen
miskin Ethiopianochin degifilen
Hagerachinin tebiqelen kerehab kechenefer kekifu agezaz awtalen
bewnet tselotachinin endemiteseman enamnalen
Mechem yehin hulu biadergunem egna endenesu anehonemena gehanem esat gin atagbachew.
Amen
It is better to re organize in the name of Renaissance that the old and traditional way of orthodox religion. other ways our unity is not possible with out those like Begashaw.......WHO is called menafkan.
ReplyDeletelezih hulu TPLF new teteyakiw. be haymanot talka bayigeba ena aba poulos papas bayhonu endik ayihonm neber. ER 1 ken yiferdal, legenzeb yemiyadergutin flimiyam kene birachew yizoachew yihedal. Ebakih amilakachin bedikamachin mikniyat yazorkewun fitikin azurilin, Amen!!!
ReplyDeleteDiasporawun attention maskeyesha new EPRDF leteliko yemilkachew, lehulum meftihe TPLF'N matifat new, aremoch silehonu!!!
ReplyDeleteGIZYW YE EGZIABHYR NEW MAHBERE KIDUSAN YE AWASSAW SAYANSISH ZARYM BYTEKRSTIYANIN LEMAWEK ABATOCHIN LEMASADED ADMA ATCHYIM AMLAK ZIM BILO AYAYISHIM YILKUN ADMAWIN TITESH ERASHIN BE NISEHA LEWCHY ABATOCHIN BEMASADED TSIDK YELEM BE HASET MENGSTE SEMAYAT AYIGEBAM YILKUN MINIM YEMAYAWKUTIN ABALATOCHISHIN ADMA KIFAT KEMITASTEMRI WENGYL ASTEMRI.
ReplyDelete