ከዕንቁ መፅሄት 4ተኛ ዓመት ቁጥር 54 ላይ ያገኝነውን እናካፍላችሁ
- ምዕመኑ ለሚቀጥለው ትውልድና ስለነገይቱ ቤተክርስትያን ህልውና ሲጨነቅ አንዳንዶች የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ዛሬ ሊያገኙት ስለሚጓጉት ተጨማሪ ሹመት ፤ ቤት ፤መኪና ፤ እንቅልፍ አጥተው ይጨነቃሉ ፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰብአዊ ገፃቸው ወደ ማህበራዊ ትህምክተኝነት እንዲዘቅጡ አድርጓችዋል ፡፡ ምጣኔ ሀብታዊ ቅርምት ውስጥም ከቷችዋል፡፡
- በቅዱስ ሲኖዶስ መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ልዕልና ቀጣይነትና ተከታታይነት ባጣበት ፤ አይናችንን አበው ረሀብ በሚሰቃይበት በዚህ ዘመን ሁሉ አቀፍ ታሪኮች ያስፈልጉናል፡፡ አለበለዚያ ግን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሰብአዊ ገፅ እያየለ ሄዶ ሲኖዶሳዊ ይዘቱን እና ቅርፁን እንዳያሳጣን እንሰጋለን ፡፡ አሁን እየሆነ ያለው ይህው ነው፡፡ በዚህ ዘመንም ቤተክርስትያኒቱ የሚሞቱላትን ብፁአን አበው አጥታ እንደማታቅ ሁሉ የሚያዋርዱአትንም ተቸግራ አታውቅም ፡፡
No comments:
Post a Comment