(by Wubishet Tekle) ቢመሻሽም ጻድቁ አባታችን ተክለሀይማኖትን ተሳልሜ ልምጣ ብዬ ወደ ደብረ አሚንተክለሀይማኖት ቤተክርስቲያን ሄድኩኝ፤ ወርሃዊ በዓላቸው እንደመሆኑ መጠን መግቢያው በር ላይ ግርግር አለ፤ አንዲት ተሽከርካሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብላ ጧፍ የምትሸጥ ነጋዴ ጋር አንዲት ነጠላ የተከናነበች ወጣት ጧፍ ለመግዛት ቆማለች፤ እኔም አጠገባቸው ነኝ “ወንድም ይቅርታ አለችኝ’’ ወጣቷ፤ “አቤት” አልኳት “እኔ ስለማልገባ ነው ይህንን ጧፍ ስጥልኝ” አለችኝ፤ “እኔም ተሳልሜ ነው የምመለሰው ለሚገባ ሰው ስጪው” አልኳት፤ እሺ ለሚገባ ሰው አንተ ስጥልኝ አለችኝ፤
እኛ ስንነጋገር ተሽከርካሪ ወንበሩ ላይ ያለችው ጧፍ ነጋዴ ጧፉን እንደያዘች እጇን ዘርግታለች፤ እሺ ችግር የለውም እሰጥልሻለሁ ግን ለምን አንቺ አትሰጪም አልኳት፤ እኔ ሴተኛ አዳሪ ነኝ እንዴት በእጄ እነካዋለሁ ፤ ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ሲቀደስ የሚበራ አይደለም ? አረክሰዋለሁ ብዬ ነው አለቺኝ፤ ደነገጥኩኝ ፤ አንዳች የሆነ ፍርሃት ሰውነቴን ወረረኝ፤ከዚህ በኃላ መልስ አልሰጠዋትም፡፡ እሺ ብቻ ብዬ ጧፉን ከጧፍ ነጋዴዋ ተቀበልኩላት፤ ብሩን ስትከፍላት እግዚያብሔር ይስጥልኝ ብላ ስትመርቀኝ አስታውሳለሁ፤ አንገቴን አቀረቀርኩኝ እኔ ግን ንጹህ ሆኜ ነው ? ይህንን ጧፍ የያዝኩት እንዴት ያለሁ ደፋር ነኝ ፤ ለምን እኔም ካንቺ የባስኩኝ ኃጢያተኛ ነኝ ፤ እኔም አልነካውም አላልኳትም? ስል ራሴን ሞገትኩት፤ ‹‹አንተ ውሸታም ጧፍ አይደለም ከታቦቱ ጋር ስትጋፋ አላውቅህም›› ሲል ጭንቅላቴ ወቀሰኝ፤ እኔ ዞርም ብዬ አላየዋትም ምናልባት እሷ ግን እየተመለከተችኝ ከሆነ ብዬ ወትሮ አድርጌው የማላውቀውን ወደ ቤተክርስቲያኑ ቅጥር ስገባ ተንበርክኬ መሬቱን ሳምኩኝ ፤ አረማመዴንም አስተካከልኩኝ ፤ ምናልባት ንጽህናዬን ካረጋገጠሊኝ ብዬ፤ ወይ አምላኬ በስንቱ ታስተምረኛለህ? አቤት ይህን ጊዜ ዮሐንስ ሐጺር በኖረ ስል ተመኘሁ፤‹‹የጥበብ መጀመሪያ እግዚያብሔርን መፍራት ነው›› የሚባለው ትርጉሙ ለካስ ይህ ነው፤ በወንጌል ላይ ያለው ቀራጭ ትዝ አለኝ ፤ ጌታ ያመሰገነው፤ከዛ ቀራጭ ግን ይህቺ ሴት ትበልጣለች ፤ እርሱስ ወደ ምኩራብ ገብቶ ነው፤ ይህች ሴት ግን ደጀ ሰላሙ ጋር እንኳን አለቀረበችም፤ እንዲህ ያለ ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው፤ እንደዚህስ ያለ እግዚያብሔርን መፍራት እንደምን ያለ ፍርሃት ነው፤ በዚህ ዘመን አይቼውም ሰምቼውም የማላውቀው፤ወይ ግሩም።
እኛስ ከእህታችን ምን እንማራለን ?
ብዙ ማለት ቢቻልም እግዚአብሔር የቅዱሳን አምላካቸው እኛንም ልቦናችንን አቃንቶ ለንስሃ ያብቃን፤ ፅሁፉን ላካፈላችሁን ቃለ ህይወት ያሰማልን፡፡
ReplyDeletewow! be'ewnet yalechiwun kanebebiku behuala keriwun belikso new yecherskut. Enes manegn???????
ReplyDeleteGen.naz.
abetu egnanis besintu tasitemirenaleh geta hoy
ReplyDeleteesiki anten mefirat asitemiren.
It is touching!! Ye Neseha lib yadlen.
ReplyDeleteTazabiw
እኔስ ምንልበል ማንነቴን የሸፈንክልኝ ገበናየን የከደንክልኝ አሁንከርሱዋ እምኑዋጋር እደርሳለሁ በዚህዘመን እንዲህያለትህትና እንዲህያለ ግልጽነት ያልሆነውን ሆነን ለመታየት ቀሚሳችን መሬት እየጠረገ ንጹህለመምሰል በቤቱ ስለተመላለስን ብቻ ያለኛ ሰውየለም ያለኛ ቆራቢየለም እስክንል የደረሰን ስንቶቻችን እንሆን ? በውነቱ እህታችን አስተምራናለች የሊድያን ልብየከፈተ አምላካችን የኛንም ይክፈትልን በፍጹምልባችን እርሱን መፍራትን ያሳድርብን አሜን
ReplyDeleteእንዲህ ያለ ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው
ReplyDeleteሁላችንም በኃጢያትችን ውስጥ ተነክረን እያለን እንደ እህታችን ግን ተሳቅቆ እግዚያብሔርን መፍራትና ማክበር መታደል ነው
ReplyDeleteእንዲህ ያለትህትና ይኖራል ብዩ አላምንም ነበር ሁላችንንም እግዚአብሄር ይርዳን
ReplyDeleteአኔስ ምን ልበል! እግዚአብሔር ማስተዋን ይስጠን የዝችን እህት ፍጹም ትህትና ያድለን፡፡ ለእናንተም እግዚአብሔር ይስጥልን፡፡
ReplyDeletebewnetu ende ehtachin yemesele tehtna yalat hiwot yadlen!!! sentochu gin le sew entayi emilu meslo sayigegu lemasmesel lemetayet bicha emifelgu bemekdesu bedfret eminoru alu beewnetu yewnet amlak yifred!!!
ReplyDeleteይህም አለ ለካ ቅድስና ስራ መታየት በቀረበት ዘመን ጆሮ ጭው የሚያረግ ነገር ብቻ በሚሰማበት ጊዜ እንዲህ ያለ ትህትና መስማት ድንቅ ነው አቤቱ እንዲህ አይነት ትህናና እግዚአብሄርን መፍራት አድለን!!!
ReplyDeleteBeyetignawum medrek kemiset sibket yebelete timihirt new yesetechin.Kale hiwot yasemalin-ehitachininim tsehafiwunim!!Amen.
ReplyDeleteeeeeeeeeeeeeeeee ndih yale tehtena leben nekaw weyew lene!!! EMBAYE WERDE!!!sAHLE
ReplyDeletelbona yisten!
ReplyDelete