Tuesday, November 1, 2011

የጻድቁ ተክለ ሃይማኖት፣የንጉሥ ጦና፣በአማን ቅዱስ የሆኑ የመናኙ ፓትርያርክ ተክለ ሃይማኖት መፍለቂያ፤ወላይታ


(By Mitiku Abera ) ዳግማዊ ምኒልክ(ሕዝቡ በፍቅር እምዬ ይላቸው ነበር) ኅዳር ፳፯ቀን ፲፰፻፹፰(1888)ዓ.ም. ወላይታ ከጦና ዋና ከተማ ደልቦ ደረሱ፡፡ እዚኽ የመገኘታቸው ምስጢር የወላይታው ንጉሥ ጦና አልገብርም ብሎ በመሸፈቱ እሱን ለማረም ነበር፡፡“…አገር ከጠፋ በኋላ ሲያቀኑት ያስቸግራል፡፡ገንዘብም በግድ ካልሆነ በቀር በፈቃድ የሰጡት አያልቅም፡፡አገርህን አታጥፋ፡፡ግብርህን ይዘኽ ግባ፡፡”ብለው በሽምግልና ቢሞክሩም መልሱ እምቢታ በመሆኑ አጤ ምኒልክ ዳሞት ተራራ ላይ ያሰፈሩትን ጦራቸውን አዘው በአንድ ጊዜ ወላይታን አስጨነቋት፣ንጉሥ ጦናም ቆስለው ተማረኩ፡፡የሚገርመው ግን መፍቀሬ ሰብዕ እና የዲፕሎማሲ ሰው የሆኑት አጤ ምኒልክ “አይ ወንድሜን እንዲያው በከንቱ ሕዝብ አስጨረስክ”ብለው የንጉሥ ጦና ቁስል እንዲታጠብና እንዲታከም ካስደረጉ በኋላ የተማረከው የባላገሩ ከብት እንዲመለስ አድርገው፣ንጉሥ ጦና እስኪያ በእግዚአብሔር ቸርነትና ብርቱ በሆነው ተጋድሎአቸው የረቱት አገግሙ ጠብቀው የወላይታን ሕዝብ ሰብስበው“…እንግዲህ ወዲህ የሚያስተዳድርህ ልጄ ወዳጄ ጦና ነውና ተገዛለት፡፡ አውቆ ሳይሆን ሳያውቅ እኔን የበደለ መስሎት ሰው አስጨረሰ እንጂ ከድሮም ከአያቶቻችን ቂም የለንምና መልሼ እሱን ሾሜልሃለው፡፡…እንግዲህ ወዲህ ብታምጽ በራስህ ዕወቅ፡፡ ግብሬን አግባ፡፡…”የማል አዋጅ አስነግረው የወጉዋቸውን ጦናን ሾመው ጥር ፲፩ቀን አዲስ አበባ ገቡ፡፡(አጤ ምኒልክ መጽሐፍ በጳውሎስ ኞኞ)
ክርስትናን አልቀበልም ለሌላውም እሾህ እሆናለው ያለው የወላይታው ንጉሥ ሞተለሚ ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በእግዚአብሔር ቸርነትና ብርቱ በሆነው ተጋድሎአቸው ሲረቱት ፍስሐ ጽዮን በተባለው ስማቸው ተማርኮ ስማቸውን እስከመለመን ደረሶ ነበር፡፡ አባታችን ተክለ ሃይማኖትም “የመንግሥትህንም እኩሌታ ብትሰጠኝ ስሜን አልሰጥህም፡፡ነገር ግን በፈጣሪዬ ብታምን ያለዋጋ እሰጥሃለው” ስላሉት ቃላቸውን ሰምቶ፣አምኖና ተጠምቆ ክርስተናን ተከብሏል፡፡ታዲያ ይኽን የመሰለ ደጋግ ሥራ የተሠራባት ወላይታ በባዶ እግር ይሔዱ የነበሩትንና በወር ደሞዛቸው የሙት ልጆችን ያሳድጉ የነበሩ ፍጹም ባሕታዊ ጸዋሚና ተኃራሚ የነበሩትን ሁለተኛውን የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ብታስገኝ ምን ይደንቃል? ወለይታ ዛሬም ከተሐድሶ መናፍቃን ጋር አንገት ለአንገት እየተናነቁ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንንና የዳሞትን በረከት የሚያስጠብቁ ብዙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች ሞልተውባታል፡፡ ከነዚህ አንደኛዎቹ ደግሞ የወለይታ ደብረ ገነት ቅዱድ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ናቸው፡፡

ወላይታ የተገኘሁት ጥቅምት ፲፰ እና ፲፱  ፳፻፬ ዓ.ም.ነበር፡፡የተገኘነው እኔ ብቻ ሳልሆን በአጠቃላይ ሁለት መምህር፣ ሁለት ዘማሪና አንድ የሞንታርቦ ቴክኒሻን ነበርን፡፡የመገኘቴ ምክንያት ከላይ የጠቀስኩት ሰ/ት/ቤት የ፳፬ኛ ዓመቱን የምስረታ ዓመታዊ በዓል ለማክበር ባዘጋጀው የዓውደ ምህረት ጉባዔ ተጋባዥ መምህር ሆኜ ነው፡፡ጉባዔው ልዩ ነበር፡፡ያስገረሙኝ በርካታ ነገሮች ቢኖሩም ሰ/ት/ቤቱ ለወላጆች ለብቻ መርሐ ግብር አዘጋችቶ ማስተማር መቻሉና ለበዓሉም ዝማሬ ሲያቀርቡ ማየቴ አስገርሞኛል፡፡

ፈረንጆቹ “ ድመትን በጨለማ ቤት ውስጥ መፈለግ በራሱ አስቸጋሪ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ድመቷ ጥቁር ከሆነች ” ይላሉ፡፡ በአስቸጋሪ ላይ ሌላ አስቸጋሪ ማለት ነው፡፡ በወላይታም እንዲህ አይነት ነገር ይታያል በየሜዳው የሚታየው የፕሮቴስታንቱ ጩኸት አንድ አሰቸጋሪ ሆኖ የውስጥ ባንዳው የተሐድሶው ጉዳይ ደግሞ ሌላው ችግር ነው፡፡ ስለዚህ ወላይታ ላይ ተደራራቢ ችግር አለ፡፡ለዚህም ይመስላል የቅዱስ ጊዮርጊሶቹ ሰ/ት/ቤት ወጣቶች ትጉህና ታታሪ ሆነው ሥራቸውን እያቀላጠፉ የሚገኙት፡፡ ይህንን ጽሑፍ የምታነቡ የተዋሕዶ ልጆች ሆይ እባካችሁ በጸሎት አስቧቸው፣አጋርነታችሁንም በጽሑፍ ግለጡላቸው፡፡

7 comments:

 1. እግዚአብሔር ለዘላለም ከነእርሱጋር እንዲሆን ፈቃዱ ይሁንልን የቅዱሳን ልመናና ፀሎት የእመቤታችን አማላጅነት ከእነርሱጋር ይሁን ቅዱሳን መላዕክት በፈጣን ረድኤታቸው አይለዩአቸው አሜን

  ReplyDelete
 2. እግዚአብሄር በድሎትና በሰላም ዉስጥ ሆነው ከሚያመልኩት ይልቅ በችግርና በሃዘን እንዲሁም በአህዛብ መካከል ሆነው በጭንቅ የሚመልኩትን እንዲሁም ወንጌልን በህይወታቸው የሚሰብኩትን በረከቱን እና ረድኤቱን ያድላቸዋል:: ከማንም በላይ በእምነት መጽናትን ይሰጣቸዋል::
  ይሄንን ለመረዳት አሁን ያለንበትን ሁኔታ ማየት ብቻ በቂ ይመስለኛል:: የአዲስ አበባ ምእመናን ተሃድሶና ምንፍቅና የመነጋገሪያ(መነሻ እንዳላልኩ ልብ ይበሉ) ርእስ የሆነባቸው ጊዜያት ከወላይታ ምእመናን ጋር ብናነጻጽረው ልዩነቱ በጣም ትልቅ ነው:: እንደውም በቂ ሰባኪ ሳይኖራቸው፣ በቂ መማሪያና መንፈሳዊ መጻህፍት ሳያገኙ፣ የተለየ ድጋፍ ሳይደረግላቸው እንዲሁም የምእመናን ብዛታቸው እንኳን ከአህዛቡ ጋር የማይመጣጠን ሆኖ እያለ ቤተክርስቲያንን እስካሁን ጠብቀዋታል አሁንም ከማናችንም በላይ እየተጉ ይገኛሉ::
  እኛን ግን ተመልኩቱን አሁን በተፈጠረው ግርግር እንኳን ስንቱ ግራ ተጋባ? ስንቱ ዴንታ ቢስነቱን አሳየን? ስንቱ ተወሰደ? ስንቱስ ሃይማኖቱን ሰደበ? በዚህች ቤተክርስቲያን ዉስጥ ምንም ቃል ሰምቶ እንደማያውቅ የሆነ ስንቱ ነው? ለዛዉም የወላይታ ምእመናንን ያክል ችግር እና ፈተና ሳያጋጥመን ነው እኮ!የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሄር ሁላችንንም ይርዳን!
  እናንተ የወላይታ ምእመናን ግን በርቱ! እናንተ ግን የተማራችሁት ከማን እንደሆነ ታውቃላችውና ጽኑ!!!
  መ.ዘ ከሽሮሜዳ

  ReplyDelete
 3. I wish God bless their great work.

  ReplyDelete
 4. የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ከመናፍቅ ዱላ ከታሀድሶ በሽታ ይታደጋቸው በእምነት ያጽናልን

  ReplyDelete
 5. በመስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን እግዚአብሔር ሐይማኖታችንን ይጠብቅልን አሜን ቸሩ አምላ ከመናፍቅ ዱላ ከተሃድኦ በሽታ ይጠብቅ ማለት ትልቅ አባባል ነው፡፡

  ከተወረወረ ጦር የሚሰውር ጌታ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን፡፡

  ReplyDelete
 6. የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ከመናፍቅ ዱላ ከታሀድሶ በሽታ ይታደጋቸው በእምነት ያጽናልን

  ReplyDelete
  Replies
  1. yigermachuhal key afer yemibal new yeneberkut ena enien haymanotien endikeyr mesbek jemrew neber lisebkugn yemekoru sewoch balna mist nachew ena abat ena enatachew cristian nachew enesu gin kecirstina hiwot wetitew lelawun siyatefu new yemiwulu EGIZIABER wede bietachew yimelsachew

   Delete