አቡነ ጳውሎስ ከሌሎች ስድስት ሊቃለ ጳጳሳት (ብፁእ አቡነ እዝቅኤል ፤ አቡነ ገሪማ ፤ አቡነ ቆውስጦስ ፤ አቡነ ጎርጎርዮስ ፤ ብፁእ አቡነ ያዕቆብ) ጋር በመሆን በተማረ እና በአግባቡ በተደራጀ የሰው ሃይል የምትመራው የኮፕት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብተክርስትያ አባት በሆኑት ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ 40ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ላይ ለመገኝት ባለፈው ቅዳሜ ከቀትር በኋላ ወደ ግብፅ ካይሮ አምርተው ነበር፡፡ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስ ጉዞውን እንዲቀላቀሉ በፓትርያርኩ ቢጋበዙም ግብዣውን እንዳልተቀበሉት ታቋል፡፡ ለጉዞ ክብር ከ200,000 ብር በላይ ወጪ መደረጉን የታወቀ ሲሆን አቡነ ጳውሎስ በዚህ ዓመት ሐምሌ ወር ላይ የሚከበረው 20ኛ በዓለ ሲመታቸው ላይ እንዲገኙ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳን ይጋብዛሉ ተብሎ ይጠበቃለል፡፡
እኔ እግዚአብሔር ፈቅዶ ብዙ የገጠር አብያተክርስትያኖችን ለማየት ችያለሁ ፤ ሁሉም ጋር ስመለከት ስር የሰደደ ችግር እንዳለባቸው ጧፍ ፤ እጣን ማግኝት አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ መድረሳቸውን ለመገንዘብ ችያለሁ ፡፡ ቤተክህነቱም ለእነዚህ ቤተክርስትያናት ምንም አይነት እርዳታ ለመስጠት ፍቃደኝነት ይጎለዋል ፤ ነገር ግን ይህው በሆነው ባልሆነው ነገር የቤታችን ብር እየተመዠረጠ ይገኛል፡፡ ምንም ማለት አልፈልግም ‹‹ለሁሉም ግን ልብ ይስጣቸው›› ብያለሁ፡፡
የዛሬ 15 ቀን የተጠናቀቀው የአባቶች ጳጳሳት ጉባኤ ላይ 600,000 ብር ያህል እንደወጣበት ለማወቅ ተችሏል፡፡ እሺ ይህን ይሁን ብለን ስናልፍ ለቤተክርስትያናችን ብዙ ስራ የሰሩ ሰዎችን አቡነ ጳውሎስ የሚከፈላቸው የደሞዝ ችግር ስላለ ፤ ደሞዛቸውን መክፈል ስለማንችል ብለው 3ቱን የቤተክርስትያናችንን ትልልቅ ሰዎች ፤ ቁልፍ ቦታ ላይ የሚገኙትን ገፍትረው ለማባረር ትንሽ ደቂቃ ማሰብ ብቻ ነበር ያስፈለጋቸው፡፡ ምን እየሰሩ እንደሆነ አምላክ ይወቀው፡፡
አቡነ ሺኖዳን እና አቡነ ጳውሎን ምንና ምን ናቸው ? ሁለቱን አንዳቸውን ከአንዳቸው ለማወዳደር እና ልዩነታቸውን ለአንባቢ ለመፃፍ ብዬ የማወዳድርበት ነጥብ ግን ላገኝ አልቻልኩም ፡፡ መመዘኛ መስፈርትም ለማውጣት አዳገተኝ ፤ ለምን ቢባል ምንም አንድ የሚያደርጋቸው ነገር በማጣቴ ነበር፡፡ ሲጀምር አቡነ ሺኖዳ በአባቶች ፀሎት እና በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ የዛሬ 40 ዓመት በማርቆስ ወንበር ላይ ሊቀመጡ ችለዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ደግሞ በመፈንቅለ ፓትርያርክ ጊዜን ክፍተት ተጠቅመው 4ኛ ፓትርያርክ የነበሩትን አባት ወደ ውጭ እንዲሸሹ ተንኮል ተሸርቦ ፤ንስሀ ልጅ ነኝ ባለ የደህንነት ሰው አማካኝነት እሳቸውን አቡነ ተክለሀይማኖት ወንበር ላይ እንዲቀመጡ አስችለዋቸዋል፡፡ መጀመሪያቸው ይህ ነው፡፡ መጨረሻቸውን እሱ ያሳምርላቸው፡፡
ለአቡነ ሺኖዳ ሌላ 40 የአገልግሎት ዘመን ተመኝተንላችዋል ፤ ለአቡነ ጳውሎስ በዚህ ስራቸው ሌላ 20 ዓመት መመኝት ‹‹ጌታ ሆይ የቤተክርስትያን መከራዋን አብዛው›› ብሎ ከመፀለይ አይተናነስም ፡፡ ለአባታችን ለብፅ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ደግሞ ቤተክርስትያንን እና ምዕመኑን የሚያስተዳድሩበትን ጥበብ እግዚአብሔር ያድላቸው ፤ ማስተዋልና ልቦና ያድላቸው ፤ንስሀ የሚገቡበትን እድሜ ጌታ እንዲሰጣቸው እንለምናለን፡፡
ሰላም ሁኑ
...can someone tell me in this 21st centuary how many churches and monastories are going through a hard time because of lack of just a one birr tuaf and shama? I am sure there are many specially yegeter churchs.And here our beloved father spent this much thousand dollars to celebrate.....Abetu yikir belen...
ReplyDelete