ከ2 ወር በፊት ለሃይማኖት ሰባኪያን ፈቃድ ሊሰጥ ነው በማለት መዘገባችን ይታወቃል ፡፡ በደረሰን መረጃ መሰረት በቅርብ ቀናት ውስጥ ፈቃዱን የመስጠት ሂደቱ እንደሚከናወን ለማወቅ ችለናል፡፡ የበፊት ዜናውን ለማንበብ
መስከረም 9 እና 10 የተለያዩ የእምነት የተቋማት አባቶች በሂልተን ሆቴል ተገናኝተው ስለ ሰባኪዎቻቸው በምን አይነት መንገድ የራሳቸውን እምነት ማራመድ እንደሚችሉና ፤ በመካከላቸው ያለውን ክፍተት እንዴት ወደ ወንድማማችነት መቀየር እንዳለባቸው፤ ያለውን ልዩነት ማጥበብ የሚችሉበትን መንገድ መንግስት ባዘጋጀው ሴሚናር ላይ ተወያይተው ውሳኔ ያሳለፉበት አንዱ ነጥብ ለሰባኪዎቻቸው ከመንግስት ጋር በመተባበር የሰባኪነት ፍቃድ እንደሚሰጧቸውና ይህን የፍቃድ መታወቂያ ያልያዘ ሰባኪ እምነቱን ወክሎ በየትኛውም አውደ ምህረት ላይ እንዳይሰብክ የመግባቢያ ሀሳብ ላይ ደርሰው ነበር፡፡
ይህን ወደ ተግባራዊነት ለመቀየር በአሁኑ ሰዓት አንዳንድ ነገሮች እየተካሄዱ ሲሆን በቅርቡ ወደ ስራ በመግባት ለየእምነቶች ሰባኪያን የመታወቂያ ካርድ በመስጠት ሁሉም በተሰጠው መታወቂያ የወከለውን እምነት ድርጅት በአግባብ ያገለግላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህን ጉዳይ ወደ ስራ ሲገባ በርካታ ችግሮች እና ጥሩ ጎኖች ይመጣሉ ብለን እናስባለን ፡፡ ዛሬ ችግሮቹንና ጥሩ ጎኖቹን ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡
ይህን ወደ ተግባራዊነት ለመቀየር በአሁኑ ሰዓት አንዳንድ ነገሮች እየተካሄዱ ሲሆን በቅርቡ ወደ ስራ በመግባት ለየእምነቶች ሰባኪያን የመታወቂያ ካርድ በመስጠት ሁሉም በተሰጠው መታወቂያ የወከለውን እምነት ድርጅት በአግባብ ያገለግላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ይህን ጉዳይ ወደ ስራ ሲገባ በርካታ ችግሮች እና ጥሩ ጎኖች ይመጣሉ ብለን እናስባለን ፡፡ ዛሬ ችግሮቹንና ጥሩ ጎኖቹን ለመዳሰስ እንሞክራለን፡፡
ጥሩ ጎኖች
- በአሁኑ ሰዓት ለቤተክርስትያን እና ለህዝበ ክርስትያኑ የጭካ ውስጥ እሾህ ፤ የጭን ውስጥ እሳት ሆነው በቤተክርስትያን ስውር አላማ ይዘው በመንቀሳቀስ ላይ ለሚገኙትን ቡድኖች ይህ ጥሩ ዜና አይሆንላቸውም ፡፡ በከተማ እና በገጠር በሚገኙ አብያተክርስትያናት ላይ እነርሱ እንደፈለጉትና ደጋፊዎቻቸው እንዳዘጋጁላቸው የእግዚአብሔርን አውደ ምህረት ላይ በማን አለብኝነት በመውጣትና በመውረድ በጎርናና ድምፃቸው ማይኩን ፤ህዝበ ክርስትያኑ ሲያስጨንቁት ከርመዋል ፤ በተጨማሪ ምንፍቅናቸውን በደንብ አድርገው ዘርተዋል፡፡ ከአሁን በኋላ ግን ይህን የሚያደርጉበት ምንም አግባብ ስለማይኖራቸው ከተግባራቸው የሚገቱበት ህግ ነው ብለን እንገምታለን፡፡
- የእግዚሐብሔር አውደ ምህረት ከማንም መፈንጪያ ፤ አጉራ ዘለል ሰባኪ መቆሚያ ከመሆን ይታደገዋል፡፡
- በቤተክህነት እና የየደብሮቹ ሰበካ ጉባኤዎች በተጋባዥ ምህራን ምክንያት የሚመጣውን ችግር ፤ክርክር ይቀንስላችዋል ብለን እናምናለን፡፡
- ቤተክርስትያናችን እኔን ይወክሉኛል ፤ ወንጌልን ማስተማር ይችላሉ ብላ በየአመቱ ከሙዳ ምፅዋት በተሰበሰበ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠር ብር ተማሪዎችን አስተማራና ፤ አስመርቃ ፤ ወደ አገልግሎት የምትልክ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በአግባቡ የተማሩትን እና ወንጌልን በዓለም ለመስበክ ብቃት ያላቸውን መምህራንን በአግባቡ በህግ የሚመራ የወንጌል ስርዓት ይዘረጋል ብለን እናምናለን ፤ የእግዚሀብሔርን ቃል ለተጠሙ ምዕመናን የወከለቻቸው አስተማሪዎቿ ትክክለኛ እምነቷንና ስርዓቷን ለማስተላለፍ አመቺ ሁኔታ ይፈጠራል ብለን እናምናለን፡፡
- በየቤተክርስትያን አውደ ምህረት ላይ የሚቆሙ መምህራን ህጋዊ የመስበኪያ መታወቂያ ሳይኖራቸው አገልገሎት ቢሰጡ ደብሩንና ፤ የሰበካ ጉባኤውን በህግ አግባብ የሚጠየቅበት አካሄድ ይፈጠራል ብለን እናምናለን፡፡
- ቤተክርስትያንን የማይወክሉ ነገር ግን በየበዓላት ላይ በመገኝት ከቤተክርስትያን አካባቢ ቆዳ የለበሱ ፤ ፀጉራቸውን ያሳደጉ ፤ በባዶ እግራቸው ሚሄዱ መነኩሴ የሚመስሉ ነገር ግን ሰውን ሽብር በመንዛት ከየዋህን ምዕመን ብር የሚሰበስቡ መነኩሴ መሳዮች ነገር ግን መነኩሴ ያልሆኑ ፤ አባት መሳዮች ነገር ግን አጭበርባሪ ሰዎችን የማየት እድላችን ይቀንሳል ብለን እንገምታለን፡፡
- አሁን ለጀመርነው የተሀድሶ እንቅስቃሴን ለማስወገድ ፤ ጥላውን በዘመናችን እንዳያጠላ ለማስቻል ለምናካሂደው ትግል አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለን እናምናለን፡፡
- ከዚህ በፊት የነበሩ ሰባኪያን በአውደ ምህረታችን ላይ ቆመው መናፍቁን ፤ ሙስሊሙንም የመሳደብ እና እነሱ በተናገሩት ነገር ቤተክርስትያናችን የምትጠየቅበት ሁኔታን ያሳለፍን ሲሆን አሁን ግን እንዲህ አይነቱ ህገወጥ አካሄድ በተጠያቂነት ላይ ያመዘነ የመቻቻል እና የራስን እምነት በአግባቡ የማራመድ ሂደታችንን በተሻለ ሁኔታ ያሻሽለዋል ብለን እናምናለን፡፡
ፍራቻ
- እነዚህን መምህራን የሚመርጠው ክፍል ከፍተኛ ጥንቃቄ እስካላደረገ ድረስ መምህራን ነን ብለው በህጋዊ መንገድ የሚሰጧቸው መታወቂያ ተመሳስለው ገብተው አሁን ካለንበት ሁኔታን ከድጡ ወደማጡ እንዳይወሰወዱን ፍራቻ አለን፡፡
- የአባ ጳውሎስ እጅ ከዚህ ስርአት ላይ ማረፍ ከቻለ ፤ የራሳቸውን ሰዎች መሾም ከቻሉ ፤ በእሳቸው ስር እንዲሆን እና የሳቸውን ቀጭን ትዕዛዝ በማተላለፍ ስራውን የሚያሰሩ ፤ የሚከታተሉ ፤ መታወቂያ የሚሰጡ ፤ እና መታወቂያ የሚቀሙ ከሆነ በጣም አደገኛ እና እምነታችንን የማናጋት አቅም ያለው አካሄድ ስለሆነ የእሳቸውን ረዣዥም እጆችን እንፈራለን፡፡
- መምራኖችን የሚመርጠው ክፍል ፤ እምነቷን ይወክላሉ ማስተማር ይችላሉ የሚለው አካል ወይም ስብስብ ምን መምሰል እንዳለበት በቅዱስ ሲኖዶስ ካልተጤነ ፤ የሚመጥኑ ሰዎች ካልተመደቡ ፤ እንደ አባ ሰረቀ አይነት መዥገር ፤ እንደ ፋንታሁን ሙጬ አይነት እስስት ፤ እንደ አቡነ ፋኑኤል አይነት ጉዳይ አስፈፃሚ ሰዎች ገብተው ነገሩ ከመሰረቱ እንዳይናጋ ፍራቻ አለን፡፡
- ለቀሳውስት ፤ ለመነኮሳት ፤ በተለያዩ መዓረግ ላይ የሚገኙ ቤተክርስትያኗን የሚያገለግሉ አባቶች ጉዳይ ምን ሊሆን ይችላል? የእነሱ ጉዳይ የሚታይበት መልክ ምን ሊሆን እንደሚችል ስናስበው ለሀሰተኞች ሰባኪያን በር የሚከፍት ሁኔታ እንዳይፈጠር እንፈራለን፡፡
- ይህ ህግ የሚሰራው ለቴዎሎጂ ተመራቂዎች ታስቦ ሲሆን በየደብሩ የሚገኙት ቀሳውስት ፤ መነኮሳት እና አበው ሊቃውንት የማስተማር ፍቃድ ካልተሰጣቸው አገልግሎቱ ላይ ከፍተኛ ክፍተት የሚፈጥር በመሆኑ አገልግሎቱን በአግባቡ እንዳይካሄድ እንቅፋት ይሆናል የሚል ስጋት አለን፡፡
- በየገጠሩ የሚገኙ ምዕመናኖች ቤተክርስትያን አስተምራ እና መታወቂያ ሰጥታ ማስተማር ይችላሉ ያለቻቸው መምህራን ካለው ምዕመንና የቤተክርስትያኖች ብዛት የተነሳ በአግባቡ ማዳረስ ስለማይቻል ያለመምህራን የሚቀሩ ምዕመኖች እና አብያተክርስትያናት ቁጥር ይጨምራል ስለዚህም ወንጌልን በማሰራጨት ላይ ሌላ እንቅፋት እንዳይሆን ስጋት አለን፡፡
- መቼስ በህገመንግስቱ ላይ ሀይማኖት እና መንግስት የተለያዩ መሆናቸውን ይነግረናል፡፡ በተግባር ግን ሲለያዩ ለማየት አልቻልንም፡፡ የመንግስት እጆች ከእዚህ አሰራር ላይ እስካለ ድረስ የፈለገውን የመስጠት ፤ ያልፈለገውን የመከልከል ስርዓት ዘርግቶ ነገሩን ፍትሃዊነቱ ላይ ጥቁር ጥላሸት እንዳያጠላ ህዝቡን ከመንግስት ፤ አባቶችን ከመምህራን የሚያኳርፍ ጉዳይ እንዳፈጠር እንሰጋለን፡፡
- ይህን መታወቂያ ያልተሰጣቸው መምህራን በብር አማካኝነት ይህን መታወቂያ ማግኝት የሚችሉ ከሆነ ሌላ አደጋ ነው ብለን እናምናለን፡፡
- ይህን መታወቂያ ያላገኙ አጉራ ዘለል ሰባኪያን እና መዘምራን የምዕመኑን ቀልብ ለመሳብ በሲዲ ፤ በቪሲዲ ፤ በካሴት ምንፍቅናቸውን ከዚህ በፊት አብረዋቸው ከሚሰሩት ፤ በዓላማ ትስስር ካላቸው መሰል የመናፍቃን ድርጅቶች ጋር በመሆን ‹‹አለን አልሞትንም›› በማለት ሰውን ግራ የሚያጋቡት ይመስለናል፡፡
- ለጊዜው የታየንን ነገርናችሁ እናንተ ደግሞ የሚታያችሁን በአስተያየት ግለፁልን፡፡ ሁሉንም ነገር ሲደርስ እናየዋለን
አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ስራ መሰራት ያለበት መምህራንን መረጣ ላይ ፤ ዲያቆናት እና ቀሳውስት ሹመት ላይ ፤ ጳጳሳት እና ኤጲስ ቆጶሳትን ማጨት እና መሾም ላይ መሆን አለበት፡፡ እንደ አባ ፋኑኤል አይነት ጳጳስ ያለ ሀገረ ስብከቱ ለዲያቆናት እና ቀሳውስት ሹመት የሚሰጥ ፤ እንደ አባ ሰረቀ አይነት መነኩሴ እንዳይሾም ጠንክረን መስራ አለብን እንጂ ይህ ሁለተኛና ተከታይ ነገር ስለሆነ የመጀመሪያው ላይ ትኩረት ሰጥተን ብንሰራ የተሻለ ለውጥ እናመጣለን ብለን እንገምታለን፡፡ ሁሉም ነገር በስርአተ ቤተክርስትያን ብቻ ይከናወን ዘንድ እኛም የበኩላችንን አስተዋፅኦ መወጣት ይጠበቅብናል ፤ ፓትርያርኩም ቢሆኑ ስህተት ሲሰሩ ስርዓት ሲጥሱ ትክክል አይደሉም ያስተካክሉ ብለን መናገር መልመድ አለብን ፡፡ በተረፈ እኛ የሀላፊነታችንን እንወጣ የተቀረውን ደግሞ ለቤቱ ጠባቂ ፤ ለበጎች እረኛ ለጌታችን ለመድሀኒታችን ለእየሲስ ክርስቶስ እንተው፡፡
ሰላም ሁኑ
Yegnan tiret ayto Amlak yeredanal,Amlak hoy kenden aberta enebel.
ReplyDeleteLebetu esu yawkebetal.
selebegochu ena sele betu Enetseley!
This comment has been removed by a blog administrator.
ReplyDeletewud Tsehafi sile Tsehufu KHY gin ebakotin ayisadebu! esisit ... ????
ReplyDeleteI wonder your view and critics further more God bless us because we have no power.
ReplyDeleteምን ይውጠዋል ማለት ማ/qedusanene sayhone yetehadeso gurbochen new ma.qedusanema yebete kerstiyane mahetote,meqrez,fana wegi mehonun atersa yene qelamaje eshi? lehulum melkam astedader lebete kerstiyan yeset zenede elshaday ede honew metsiley new
ReplyDeleteit is nice view
ReplyDeleteቤ/ክ አሁን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ሳየው ከጥቅሙ ጉዳቱ ይበልጣል:: አመንም አላምንም በፓትርያሪካችን እጅ መውደቁ አይቀሬ ነው:: ባይወድቅ እንኳ አሁን በሌሎች ጉዳዮች እንደሚያደርጉት በአምባገነንነት እንደሚያዙበት ቅንጣት አለጠራጠርም:: ስለዚህ ቤ/ክንን እሳቸውና መሰሎቻቸው ( መንግስትን ይጨምራል) ወደሚፈልጉት አቅጣጫ ለመዘወር ይመቻቸዋል:: መታወቂያ ወረቀት የተሰጣቸውን መህራንን ደግሞ ቤ/ክንን የማይወክል ትምህርት ቢያስተምሩ እንኳ አሁን ምዕመኑ እንደሚያደርገው ከአውደ ምህረት ማውረድ ከባድ ነው የሚሆነው:: ይህ ደግሞ ፓትርያሪኩ ዓላማዎቻቸውንና ደጋፊዮቻቸውን ብቻ በአውደምህረት ላይ ለማቆየት ህጋዊ ሽፋን በመስጠት እጅግ ይጠቅማቸዋል::
ReplyDeleteይህ መታወቂያ ሳይኖር እንኳ የአዋሳ ምዕመናን እንዴት እንደተቸገሩ ልብይሏል::
እንደ ኔ እንደ ኔ የቅ. ሲኖዶስን ውሳኔዎችን የሚያስፈጽም ጠንካራ አስፈጻሚ እስኪመጣ ቢዘገይ መርጣለሁ::
አወአ- ዘኦሮማ
ዝም በሉ ወሬኛ ሁሉ እናንተ ምንም ቦታ የላችሁም መናፍቅ ሲፈነጭባት ሲሰድባት ሲዋርዳት ተባባሪ ነበራችሁ መቼታያችሁ በመድረኩ መልስ መቼ ሰጣችሁ ፣ታቦታችን አህዛብ በሄዱበት መንግድ ኤሄድም ብለው መንገድ በኦሞ ሲጥቡ የነበሩትን ትላንት ከጫት፣ከመጠጥ ከአልባሌ ቦታ የተሰበሰበውን ወጣት የትም ለመበተን ከፊት ለፊቱ አጥር ሆናችሁ ቆማችሁ የወንጌል ሳይሆን የተንኮል ቅንቅን በላችሁ ለምን ዞር አትሉም ከመንገዱ ቤተክርሰቲያን የራስዋን ስራ ትስራበት ሀላፊነታቸውን የሚወጡ ህዝቡን ወደ ጽድቅ መንገድ የሚመሩ ሰዎች ትምረጥና ታስቀምጥ ህዝቡን ግራ አታግቡት ያለችው ይቺ ቤተክርስቲያን ናት የጭንቀት የመከራ አጋር፡፡ እግዚያብሄር መልካሙን ሁሉ ያድርግ ጥላቻን ሳሆን ፍቅርን የሚሰብኩ አገልጋይ ስጠን ከፋፋዮችን አስታግስልን ቤተክርስቲንን ጠብቅ የድንግል አማላጂነት የቅዱሳን ተራዳይነት አይለን አሜን፡፡
ReplyDeleteእናንተ መናፍቅ የምትሉአቸውን ሰዎች እኮ እግዚአብሔር እራሱ ነው ያስነሳቸው፡፡ ጳውሎስ እራሱ መናፍቅ እንደተባለ አስታውሱ፡፡ በእግዚአብሔር እይታ ደግሞ መናፍቁ ማን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ ከተሐድሶ ጋር መጣላት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ማለት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት ማለት ደግሞ መድቀቅ ማለት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የሚጣሉ ይደቃሉና ይላል ቃሉ፡፡
ReplyDeletethis is anice commentto all.we should help our fathers in providing spritual
ReplyDeleteviewes and suggetions.