እንኳን ለፆመ ነቢያት በሰላም አደረሳችሁ
(ከአለቃ አያሌው ታምሩ በ1953 ዓ.ም ታትሞ ከወጣ መፅሀፍ የተወሰደ)ሙሉውን በ PDF ያንብቡ
ጾም በብሉይ ኪዳን በተወሰነ ባልተወሰነ ጊዜም ይፈፀም ነበር፡፡ በሀዲስ ኪዳን የዘወትር እና የተወሰነ ፆም አለ፡፡ የፆም መሰረቱ ‹‹ቀድሱ ጾመ ወሰብኩ ምህላ›› ፤ ‹‹ፆም ለዩ ፤ ምህላ ያዙ›› የሚለው ነው ፡፡ ኢዩ 2፤16 ፆም በብዙ ወገን ስለሆነ ክፉ ከማየት ዓይንን ፤ ክፉ ከመስማት ጆሮን ፤ ክፉ ከመስራት እጅን ፤ ወደ ሀጥያት ከመሄድ እግርን ፤ ክፉ ከመናገር ምላስን ፤ ክፉ ከማሰብ ልብን መከልከል ታላቅ ፆም ነው ፡፡ ስራውም ከፍፁምነት በላይ ነው፡፡
ስለዚህ ቅዱስ ጾም መድሀኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ሲያስተምር ‹‹ ልቦናቸውን ከክፉ ሀሳብ ንፁህ ያደረጉ ሰዎች ብፁዓን ናቸው ፤ እነሱ እግዚአብሔርን ያዩታልና ›› ብሉዋል ማቴ 5፤6 ፡፡ አንደበትን ክፉ ከመናገር መከልከል ስለሚገባ ‹‹ ከትዕዛዛት አንዲቱ ታንሳለች ፤ አንዲቱ ትበልጣለች ብሎ ለሌላው የሚያስተምር ፤ ራሱም የሚሰራ ፤ በመንግስተ ሰማያት ታናሽ ይሆናል፤ ከትእዛዛት አንዲቱ ካንዲቱ አታንስም ብሎ ራሱ የሚሰራ ፤ ለሌላ ለሚያስምር በመንግስተ ሰማያት ታላቅ ይሆናል››ማቴ 5፤19
ጾመ ነቢያት ጾመ ድኅነት ይባላል፡፡ ጾመ ነቢያት መባሉ ነቢያት ስለጾሙት፡፡ ጾመ ድኅነት መባሉም መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ ጠፍቶ ድኅነት የተገኘበት ስለሆነ ነው፡፡ በመሆኑም በአጭሩ ነቢያት ስለጌታ ሰው መሆንና ስለሰው መዳን የጾሙትን ፤ የጸለዩትን ፤ በማዘከር ከበዓለ ልደት አስቀድሞ ያሉትን ስድስት ሳምንታት እንጾማለን፡፡ ጾሙ በ16 የሚገባው የገና ጾም በ29 በሚሆንባቸው በዘመነ ማቴዎስ፤ማርቆስና ሉቃስ ነው፡፡ በዘመነ ዩሐንስ ግን የገና ጾም በ28 ስለሚሆን አንድ ቀን አስቀድሞ በ15 ይገባል፡፡
Enquwan abiro aderesen ke'hatiyat beshita yeminidinibet tsom yadirigilin. Amen!!!
ReplyDeleteስለ ጾም ብዙ የማናውቀውን አስውቀውናል እናመሰግናለን
ReplyDeleteበርቱ በዚሁ ቀጥሉ