Friday, November 11, 2011

የአቡነ ጳውሎስ ገድል

 • ‹‹...የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ስለ ቤተክርስትያን ሲል በቀድሞው ፓትሪያሪክ ላይ የወሰደውን እርምጃ ደግፈናል››
 • ‹‹ከሰው ጋር ተስማምተው ሥራ መሥራት ስላልቻሉ በነጻ ቀለብ እየተሠፈርላቸው ሲኖሩ ነበር››
 • አባ ጳውሎስ የደርግና የወያኔ ሰላይ ነበሩ፡፡
 • አባ ጳውሎስ ወደ ውጭ አገር ሲሄዱ መኪናቸው በአውሮፕላን ተጭኖ እንዲሄድ ያደርጋሉ

ክፍል 1
(አንድ አድርገን ፤ ህዳር 1 2004 ዓ.ም) ገድል ጥሩ ለሰሩ ሰዎች ብቻ ይፃፋል ያለው ማነው? አሁን ባለንበት ሰዓትም ቤተክርስትያን ደም እንባ ያስለቀሷት አባቶች ገድላቸው እንደ ስራቸው ተመዝኖ ለታሪክ መቀመጥ መቻል አለበት የሚል አመለካከት አለኝ ፡፡ የአቡነ ተክለሃይማኖት ገድል 25ኛ ካህን ሆነው የስላሴን መንበር ለማጠን የደረሱ ምድራዊ መላእክት የተባሉ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው የእምነታችን እንቁ አባት መሀሆናቸውን ይነግረናል ናቸው፡፡ ለአቡነ ጳውሎስ እንደ ቀደሙት አባቶቻችን ስራቸው በእግዚአብሔር ፊት ሚዛን የደፋ፤ የተሰጣቸውን አደራ በቅጡ ያልተወጡ ፤ እግዚአብሔርን እና ምዕመኑን ደስ የሚያሰኝ ስራ ባይሰሩ እንኳን  ያደረጉት እኩይ ተግባር ተፅፎ መቀመጥ አለበት ፡፡የአባ ጳውሎስም ስራቸው አንዲት ሳትቀር ትክክለኛ ማንነታቸውን የሚናገር ለትውልድ በመፅሀፍ መልክ ቢዘጋጅ ነገ ለሚነሱ አባቶች እንደመማሪያ ፤ ቤተክርስትያን ያለፈችበትንም የመከራ ዘመን ያውቁበታል፤ የውጩን ሳይሆን የውስጥ ችግሯን ይረዱበታል ፤ ከመሰል አባቶች ራሳቸውንንም ትውልዱን ይጠብቁታል የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ እኛ ግን ጥሩ ጥሩውን እንጂ በዘመናችን ጥሩ ያልሆነውን ፅፈን ለትውልድ የማስተላለፍ ባህሉን ያዳበርነው አይመስለኝም ፡፡ ቤተክርስትያን በዩዲት ጉዲት ፤ በግራኝ መሀመድ ዘመን የደረሰባትን መከራ ፤ ችግር፤ ስቃይ አባቶቻችን ለኛ ከትበው አስቀምጠውልን እኛም ልናውቀው ችለናል ፡፡ የአቡነ ጳውሎስ ትክክለኛ መልካቸውን ሳንጨምር፤ ሳንቀንስ ፤ሳናጋንን ፤ ሳናሳንስ ለመጪው ትውልድ ብናስቀምጥለት ምን ጉዳት አለው? ብዬ በማሰብ ስለሳቸው የማውቀውን ያህል ፤ ካነበብኩት ፤ መጽሀፍቶች ከነገሩኝ ፤ እውነታ ያላቸው ሰነዶች ካስረዱኝ ፤ አንደበታቸው ከተናገረው ፤ የተለያዩ እውነትን መሰረት ያደረጉ ድህረ ገፆች ካነበብኳቸውስለ እሳቸው  ለመፃፍ አሰብኩ፡፡

እኔ ሁሌ ቤተክርስትያናችን ስላለችበት ሁኔታ ሳስብ ፤ አባ ጳውሎስ በሳቸው አገዛዝ የቁልቁል ወደታች ስትንደረደር ስመለከት ፤ ህዝበ ክርስትያኑን ግራ ሲያጋቡት ሳስተውል ፤ እኔ ነኝ ፈላጭ ቆራቹ በማለት የማይገቡ ለቤቱ የማይመጥኑ ሰዎችን ሰብስበው ቤተክርስትያኒቷን ሲያስቦጠቡጧት ሳይ ። ትብያም በራሴ ላይ እነሰንስ ማቅም እታጠቅ ዘንድ ተመኘሁ።እንዲህ ያለ ነገር በቤተክርስትያን ውስጥ ሲፈፀም እንደ ሰቆቃው ኤርሚያስ አለቀስ ዘንድ ተክዤ ተቀመጥሁ።

ከዚያም የሰቆቃው ኤርሚያስ ጸሎት ትዝ አለኛና የመጀመሪያውቹን አራት ስንኞች እንዳህ እያልኩ አነበነብኩ፤
አቤቱ የሆነብንን አስብ፤
ተመልከት ስድባችንንም እይ፤
ርስታችን ለእንግዶች፤
ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።
ስል ሮሮየን እግዜር ወዳለበት ወደ ሰማይ አሰማሁ።

አባ ጳውሎስ በአሁኑ ሰአት ለያዥ ለገናዥ ያስቸገሩ ሰው ሆነዋል ፤ ‹‹አንገታቸውንም አደንደኑ፥›› ይላል መጽሐፈ ነህምያ 9፤7 ላይ በሲኖዶስ ተመክረውም ተዘክረውም እንቢ ብለዋል ፤ ሲኖዶስ ለቦታው አይመጥኑም ብሎ ሰዎችን ከቦታቸው ሲያነሳ እሳቸው ደግሞ ውለው ሳያድሩ መሾሙን ተያይዘውታል፡፡ እና ምን ይሻላል ? አንዳንዴ ግራው ሲጠፋኝ ‹‹ እግዚአብሔር እኝን አባት ብሎ የሾመልን በእኛ ክፋት ይሆን ብዬ አስባለሁ›› በአንድ ወቅት አባ ጳውሎስ እንዳህ ሲሉ ተደምጠዋል። ‹‹ክፉ መሪ ተሰጠን ብላችሁ አታጉርምርሙ።ክፉ መሪ ካለም የእናንተ ውጤት ነው።This is what you deserve።ደግ መሪ ለማግኘት መጀመሪያ ደግ ሆኖ መገኘት ያስፈልጋል›› ማለታቸውን ሰምቼ እህህ ብዬ ዝም ማለቴን አስታውሳለሁ።

መቸስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህድ ቤተክርስትያን ላይ በዚህ ሃያ ዓመት  የደርሰው ውርደት መቸም ደርሶ የማያውቅ ወደ ፊትም ይደርሳል ተብሎ የማይጠበቅ ነው።ቤተክርስትያኒቷ ለሶስት ተሰንጥቃለች። ህጋዊ ሲኖዶስ ፤ ህገወጥ ሲኖዶስ እና ገለልተኛ በማለት እንዳሻቸው ስም በመስጠት ከህገ ቤተ ክርስትያን ውጪ ሁሉም በየፊናው መንገድ የጀመረበት ጊዜ ላይ ነን ፡፡ የሐዋርያት ሥራ 4 ፤32 ላይ ‹‹ያመኑትም ሕዝብ አንድ ልብ አንዲትም ነፍስ ነበሩአቸው ›› ይላ በአባ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርያርክነት ግን ይህው ሶስት ልብ እንዲኖረን አድርገውናል፡፡

ለዚህ ሁሉ ውርደት ኃላፊነቱን የሚወስደው ማን እንደሆነ አናውቅም።ካህናት ይሁኑ፤ምእመናኑ ይሁኑ፤መንግስት ይሁን ፤ ቤተክህነቱ እስከ አሁን አለየለትም።ነጻ አገር የሌለው ህዝብ እውነቱን ለማወቅ መብት የለውምና ሁል ግዜ በግምትና በብዥታ ውስጥ ይኖራል እንጂ አቋም ወስዶ ለስህተቶች መፍትሄ ማግኝት አይችልም። ‹‹እውነትን›› ሁልጊዜ ከላይ ያሉ ሰዎች ዘንድ መራራ ናት ለምን እንዲህ እደሆነባቸው ግን አይገባኝም፡፡

እስከ አሁን ድረስ ሰድቦ ለሰዳቢ አንሰጥም ብለን የሳቸውን ጉድ እያወቅን እንዳላወቅን ሆነን ዝም ጭጭ ብለን ቁጭ ብለናል፡፡ አሁን ግን ሳልናገረው ዝም ብል ወይንም ሰው እንዳያውቀው ባደርግ ውስጤ እረፍት ስለማይሰማው ስለሳቸው የማቀውን በመፅሀፍት የተፃፉትን በፎቶ ተቀርፆ እጄ ላይ የሚገኝውን ፤ የተናገሩትን ፤ በመፅሀፍ የተፃፉላቸውን ፤እሳቸውም የፃፉትን በማስማማት መፃፍ እጀምራለሁ ፡፡

ጵጵስና ሹመት
ከሃይስኩል በኋላ ባገኙት ዕድል የቲዎሎጂ ዲግሪ ይዘው ቅዳሴ ተምረው ጵጵስና ለመቀበል እንዴት እንደቻሉ መጠናት ያለበት ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱ ደግሞ ዕድሜያቸው ለጵጵስና ያልደረሰ፣ ቅስና እንኳ ለመቀበል የቤ/ክ/ ጥልቅ ሙያ በሚጠየቅበት በ1960ዎቹ ጊዜ ተጠይቆም ሲገኙ አልሾምም እያሉ በሚሸሹበት ዘመን በወጣትነታቸው ለኤጲስ ቆጶስነት መታጨታቸው ጥያቄ ያስነሳል፡፡ እኔ መጽሃፍቶችን ሳገላብጥ ትንሽ መረጃ ቢጤ አግይኝቻለሁ እሷን ላመላክታችሁ፡፡

ጳጳስ ሁነው ከመሾማቸው በፊት ስማቸው አባ ገ/መድህን ይባል ነበር።አባ ገ/መድህን በወቅቱ በነበሩት ፓትሪያሪክ አቡነ ቴውፍሎስ ተጠቁመው ለጵጵስና የታጩ ቢሆንም በሶስት ምክንያቶች የወቅቱ ሲኖድስ ሳይመርጡ ቀርተዋል ፡፡

1ኛ.አባ ገ/መድህን ቆባቸውን ጥለው በምትኩ የህንዶችን ኩፍታ ያደርጉ ስለነበር (ይህ ስራቸው ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው)

2ኛ.ቀሚሳቸውን ጥለው በምትኩ መኳንት ለመምሰል የመኳንቱን ዓይነት ካፖርት ይለብሱ ስለነበር

3ኛ.ገዳማዊያን አባቶች ከሚኖሩበት ክልል ወጥተው በቡና ቤት ይኖሩ ስለነበር በወቅቱ በነበረው ሲኖድስ ሳይመርጡ ቀርተዋል ፡፡ይህ የሆነው በ1968 ዓ.ም ነው።

ታዳያ በምን ተዓምር ጳጳስ ሁነው ተገኙ? የሚል ጥያቄ ሲመጣ ሁለት መላ ምቶችን በጊዜው የነበሩ ሰዎች ያስቀምጠሉ።
 • አንደኛው እጩ ሁነው እንደቀረቡ ለማስመስል በፓትሪያሪኩ ግቢ ሲታዩ ውለው አድርዋል።ከዚያም የሹመቱ እለት ከእውነተኛ ተሿሚውች ቀድመው በቦታው በመገኘት የመካከለኛውን ወንበር ይዘው ተቀምጠው ተገኝተዋል የሚል መላ ምት አለ።በእውነት እንዲህ ሞገደኛ መንኩሴ ነበሩ ይህኙ ሰውዬ? ምክንያቱ ግን ውሃ የሚቋጥር ሆኖ አላገኘሁትም።ምክንያቱም የጵጵስናው ሹመት ሲካሄድ መጀመሪያውን ውድቅ ያደርጓቸው ጳጳሳት በዚያ ስነ ስርዓት ላይ ስለሚኖሩ ይሄ እንዴት ይሆናል የሚል ጥያቄ ሳያነሱ እንዴት ዝም ይላሉ የሚል ጥያቄ ስላለኝ ነው።
 • ሁለተኛው ደግሞ ራሳቸው አቡነ ቴውፍሎስ ከሲኖድሱ ፈቃድ ውጭ ሹመቱን እንዲፈጸም አድርገዋል የሚል ነው።ይሄ ይሻላል።ፓትሪያርኩ ከሲኖዶሱ ውሳኔ ውጭ ሹመቱን አከናውነው ሊሆን ይችላል።እንዲህ ሲሆን ደግሞ የሲኖዶስን ውሳኔ መሻር የተጀመርው በአባ ጳውሎስ ሳይሆን ከቀድሞም የኖረ ልማድ ነበር ማለት ነው።ይህም ቢሆን የራሱ ችግር አለው።

በወቅቱ ለሹመት አለመመርጣቸውን የሚያስርዳ አንድ ጥሩ መረጃ አለ።ይሄውም በወቅቱ በቤተክርስትያኒቷ ውስጥ የሚታተም አንድ ጋዜጣ የሁለቱን ጳጳሳት ስም ጠቅሶ ዘገባ ሲያቀርብ የአባ ጳውሎስ ስም በዚያ አልተጠቀሰም።ይሄም የሆነው አባ ጳውሎስ በዚያን እለት በተደርገው የሲኖድስ ስብሰባ ሳይመርጡ ውድቅ ሁነው በመቅርታቸው ነው ።ለምን ጋዜጣው የአባ ጳውሎስን ስም አላወጣም? ለሚለው ጥያቄ የአባ ጳውሎስ ወገኖች መልስ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።

አቡነ ቴዎፍሎስ በ1968 ዓ.ም ለአባ ገ/መድህን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) እንዲ ብለው ነበር …. አባ ገብረመድን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) በነገሮች በጣም ሲቸኩሉ ፤ ለመሾም በጣም ሲጣደፉ፤ ለጵጵስና እንዲያጯቸው እና በጊዜው የነበረው ሲኖዶስ እንዲያፀድቅላቸው ከልክ ያለፈ ምኞታቸውን የተመለከቱት አቡነ ቴዎፍሎስ ‹‹ልጄ ቀስ በል ጵጵስናውን ትደርስበታለህ ኋላ ግን ሸክሙን አትችለውም›› ብለዋቸው ነበር፡፡ እውነት ነው አቡነ ቴዎፍሎስ በህይወት ባይኖሩ እንኳን የተናገሯቸው ነገር ግን አሁን ከ40ዓመት በኋላ ሲደርስ እያየን ነው ፡፡ ሸክሙን አልቻሉት፤ ቤተክርስትያኒቷን በህጋዊ መንገድ ማስተዳደር አልቻሉም ፤ ልባቸው ከመጠን በላይ ደንድኗል ፤ ‹‹እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል›› አይነት አካሄድ በዚች ንፅህት በሆነች እምነታችን ላይ የያዙት መንገድ ነው ፤ ሹም ሽር በፍቃዳቸው እንጂ የሲኖዶስ ድምፅ ዋጋ እንደሌላው ደጋግመው አሳይተውናል ፤ ቤተክህነቱን እንደ ጋዳፊ አስተዳደር በቤተዘመድ አስከብበውታል ፤ ከፋፍለህ ግዛው የሚለውን የገዥው ፓርቲ መስመር ሲተገብሩ አይናችን እያየነ ነው ፤ ባለፈው አመት የአዲስ አበባን ሀገረ ስብከት በ4 ለመክፈል ለሲኖዶስ ሀሳብ አቅርበው ሲኖዶሱ አለመቀበሉ የዛሬ ዓመት ትውስታችን ነው ፤ በሀይማኖት ህፀፅ ያለባቸውን ሰዎች የቤተክርስትያኗ አስተዳዳሪ አድርገው በመሾም ለምዕመኑ እና ለወንጌል አገልግሎት እቅፋት ሆነዋል ፤ መናፍቃኑ(ተሀድሶያውያኑ) የልብ ልብ የተሰማቸው በእርሳቸው ዘመነ ፕትርያርክነት ነው ፤ ከዚህ በላይ ብዙ ማለት ይቻላል ፡፡ አዎን ሸክሙ ከብዷቸዋል ፡፡ አንድ አባት ስለ እጩ መነኮሳትና  ጳጳሳት ሲያስተምሩ ሳይገባቸው በድፍረት ለዚህ ክብር የበቁ ሰዎች ‹‹ሰይጣን በተቀበሉት የማይገባ ሹመት መጠን ነው ሚሰፍርባቸው›› ያሉኝን አስታውሳለሁ፡፡

የአባ ገ/መድህን ጵጵስና በእንዲህ መልኩ ተጠናቆ በ1968 ዓ.ም ጳጳስ ሁነው አባ ጳውሎስ ተብለው ተሾሙ ። በዚህ ወቅት ደርግ ጳጳስ እንዳይሾሙ ትእዛዝ አውጥቶ ነበር።አቡነ ቴውፍሎስ የደርግን ትእዛዝ ሽርው ሦስት ጳጳሳትን ሾሙ።ደርግም ትእዛዜን አልሰማህም ብሎ ፓትሪያርኩንና ሦስቱን ተሿሚ ጳጳሳት እስር ቤት ጨመራቸው።በወቅቱ የተሾሙት ጳጳሳት አቡነ ባስሉዮስ፤አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ጳውሎስ(አወዛጋቢው ጳጳስ) ነበሩ።ከግዜ በኋላ ሦስቱ ጳጳሳት ከእስር ሲፈቱ ፓትሪያሪኩ ብቻ በዚያው ቀርተዋል።

የማይዋጥ እውነት
በቤተክርስትያኒቷ ጉዞ ውስጥ የሚያሳዝነውንና አንገት የሚያስደፋውን ታሪክ እዚህ ላይ አንባቢ ቢያውቀው መልካም ነው።ደርግ አቡነ ቴውፍሎስን ወስዶ ገድሎ ጣላቸው።በወቅቱ የነበሩ ጳጳሳት ቀጥሎ ያለውን ዓርፍተ ነገር የያዘ ደብዳቤ ለደርግ ጽ/ቤት ላኩ፡፡ ‹‹...የኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግስት ስለ ቤተክርስትያን ሲል በቀድሞው ፓትሪያሪክ ላይ የወሰደውን እርምጃ ደግፈናል›› ይህ ደብዳቤ ሲፃፍ በጊዜው የነበሩ አባቶች በፖለቲካዊ እጅ ጥምዘዛ አካሄድ ይሁን ወደውና ፈቅደው በማይታወቅ ሁኔታ ደብዳቤው ላይ ፊርማቸውን ያኖሩ  አባቶች ነበሩ፡፡ ይህን ደብዳቤ እዚህ ላይ ፖስት ማድረግ ከጥቅሙ ጉዳቱ ስለሚያመዝን አታች ሳላደርግ አልፌዋለሁ ፡፡
  
የአቡነ ቴውፍሎስ ሞት ለደርግ ፅህፈት ቤት ከደገፉ 16 ጳጳሳት ውስጥ ሰባቱ እነዚህ ናቸው ፡፡ ይህን እውነት አሁን ላይ ደርሰው መካድ ቢሞክሩ እንኳን በጊዜ የተፃፈው ደብዳቤ ስለመፈረማቸው ያረጋግጥልናል፡፡ ከ16ቱ ጳጳሳት ግማሾቹ በህይወት እንደሌሉና ገሚሶቹ ደግሞ አሁንም እንዳሉ ለማወቅ ችለናል፡፡  
1ኛ.አቡነ አብርሃም የሃርርጌ ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ
2ኛ.አባ መቃሪዎስ የጎጃም ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ
3ኛ.አባ ማርቆስ በጡርታ ላይ የነበሩ
4ኛ.አባ ማቴዎስ በጡርታ ላይ የነበሩ ወደ ሥራ የተመለሱ
5ኛ.አባ እንድሪያስ በጡርታ ላይ የነበሩ ወደ ሥራ የተመለሱ
6ኛ.አባ ዮሴፍ በጡርታ ላይ የነበሩ ወደ ሥራ የተመለሱ
7ኛ.አባ ሚካኤል በጡርታ ላይ የነበሩ ወደ ሥራ የተመለሱ

እነዚህ ጳጳሳት የፓትሪያሪኩን መገደል የደገፉ ናቸው።ታድያ እነዚህ በምን መስፈርት ነው መልካም እረኛ የሚሆኑት ? ‹‹... እኔ ከሄድኩ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች እንደሚነሱ እኔ አውቃለሁ›› ያለው ጌታ እነዚህን ይሆን ? ይሄንንስ ስንሰማ ማቅ ለብሰን ትብያ ነስንሰን ለማልቀስ ከመሞከር ባሻገር ምንም ማድርግ አንችልም ማለት ነው ? እንዴት አንድ ጳጳስ ንጹህ ሰው ሲገደል እደግፋለሁ ብሎ ግድያን የሚያበረታታ ድርጊት ይፈጽማል ? ለዚህ ነው ሹመታቸው የነበረው ? ለዚህ ነው በትረ ሙሴን እንዲይዙ የተደረገው ? እንዲህ ዓይነት አድር ባይነትን ነው ለትውልድ የሚያሰተምሩት ? አሁን ያሉትስ እንደ እነ አባ ጳውሎስ ፤ አቡነ ፋኑኤል ፤ አባ ሰረቀ፤ አባ ገሪማ ፤  ፋንታሁን ሙጬ  ሌሎችም  ከዚያ የተለየ የሚያደርጉት ምን አዲስ ነገር አለ ? ብለን ብንጮህም የሚሰማን የለም።እውነትና ፍትህ ሞቶ የተቀበረባት አገር ውስጥ ማን የማንን ጩኸት ያዳምጣል ? 

እስኪ ደግሞ የአባ ጳውሎስ የአሜሪካ ኑሯቸው ምን ይመሰል እንደነበር እንመልከት፤
አባ ገመድህን በአሜሪካ
አባ ጳውሎስ ወደ አሜሪካን የመጡት የትምህርት እድል አግኝተው በክብር ተሸኝተው እንደሆነ  ይታወቃል። ከሰው ጋር ተስማምተው ሥራ መሥራት ስላልቻሉ በነጻ ቀለብ እየተሠፈርላቸው ሲኖሩ ስኮላር ሺፕ ያገኛሉ።ከዚያም ወደ ደርግ ጽ/ቤት ሂደው ቤተክህነት ስለተጣላኝ አይሰደኝምና እናንተው ስደዱኝ ብለው ደርጎችን ይማጸናሉ።ከዝያም ደርግ ሰውየው ለትምህርት ውጭ ሀገር ቢሄድ ትቃወማላችሁ እንዴ ? ብሎ ቤተክህነትን ይጠይቃል።ቤተ ክህነትም እንደማትቃወም ታስታውቃለች።ከዚያም የመጓጓዢያ ተከፍሎላቸው፤የመንገደኛ ወጪ የኪስ ገንዘብ ተስጥቷቸውና ደብዳቤ ተጽፎላቸው በክብር ነው የወጡት ።

አባ ጳውሎስ ግን በመዋእለ ዜናውቸው ላይ ያጻፍት ከዚህ የተለየ ታሪክ ነው።እንዳህ ይላል ‹ብጹእ አቡነ ጳውሎስ ከብዙ ስቃይና መከራ በኋላ ለስም ያህል ከእስራት ቢፈቱም በዓይነ ቁራኛ እየተጠበቁ...በአገር ውስጥ መኖር ስላልቻለ በስደትና በመከራ ወደ ሚገኙት ወገኖቻቸው ተሰደዱ›› ይላል ዜና አባ ጳውሎስ።ገጽ 95 እና 96 ላይ።የአባ ጳውሎስ ዜና መዋእል ጸሃፊ ዛሬ ስንት ንጹሃን ዜጎች በወጡበት እንደሚቀሩ የሚያይ ዓይን የሚሰማ ጆሮ ይኖረው ይሆን ? ለነገሩ ሰው እንዲያውቀው የምፈልገው ከእሳቸው ጋር በጥቅም የተሳሰሩ ሰዎች ጠቀም ያለ ብር ከተሰጣቸው አይደለም የአባ ጳውሎስን ዜና መዋዕል ይቅርና የስይጣንን ገድል ለመጻፍ ወደ ኋላ የማይሉ ሰዎች ናቸው፡፡  በእሳቸው  ዘመን ስንቱን ነው ከስራ ገበታ ያፈናቀሉት ፤ አለቃ አያሌው ታምሩን የመሰለ ሊቅ እንዴት አድርገው ነው የገፏቸው? ፤ አለቃ አያሌው ሲያርፉ በአዲስ አበባ በየትኛውም ደብር ፍትሀት እንዳይደረግላቸው ሲሉ ትዕዛዝ ያስተላለፉት አቡነ ጳውሎስ አይደሉም እንዴ ? ፤ ህገወጥነት የተንሰራፋው በማን ጊዜ ሆነና ነው ? በቅርቡ በተፃፈ የልደታ ቤተክርስትያን የሂሳብ ዝርክርክነት አሰራርን የሚናገር መጽሀፍ ፀሀፊ በማን ትዕዛዝ ነው ፍርድ ቤት ሳይቀርብ 4 ቀን ታስሮ የወጣው?፤ የአባ ሰረቀን ክስ ፍርድ ቤት የያዘውን ፋይል የማን እጅ ነው ፋይሉን ወደ መዝገብ ቤት ያስመለሰው? ፡፡ የሳቸውን ዜና መዋል የፃፉ ሰዎች  የእነዚህ ዜጎች እስር ስቃይና መከራ የሚናገርበት አንደበት ይኖራቸው ይሆን ?  ብለን ከመጠየቅ ውጭ መልስ የሚሰጠን ሰው ስለሌለ እህህ ብለን ዝም ከማለት ባሻገር የምንለው ነገር የለንም።

መቸስ የአባ ጳውሎስን ጉዳዮች አውርተን አንጨርሰውም።አንድ አስገራሚ ነገር አለ።አባ ጳውሎስ ደርግን እንዴት እንደሚጠሉ እናውቃለን።ብዙ ግዜም ስለ ደርግ አስከፊነት ሲናገሩ ስምተናል።አሜሪካን አገር በነበሩ ግዜ የተለየ መልክ ነበራቸው ።አንዱን አንቀጽ እንዳለ አስፍሬዋለሁ።
‹‹በዚያን ወቅት ኒዮርክ የሚገኘው የዓለም አብያተ ክርስትያናት ጽህፈት ቤት ሠራተኞች መታሰራቸውን ምክንያት አድርገው በእስር ቤት ስለደርሰባቸው ችግርና በሌሎችም ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ እስርኞች ላይ ደርግ ስለሚፈጽመው የጭካኔ ሥራ እንዳገልጽና ደርግ በዓለም አደባባይ በጳጳስ ስም እንዳጋለጥ ቢጠየቁ ደርግ እርሳቸውን ያሰራቸው ለህይወታቸው ጥበቃ እንዳደርግላቸው እንጂ ለጉዳት እንዳልሆነ አስርድተው ጥያቄውን ሳይቀበሉት ቀርተዋል።
ይህ ነገር እውነት ከሆነ አባ ጳውሎስን ምን እንበላቸው ? እንደ ለደርግ ታማኝ ስለመሆናቸው ምስክር ሆኖ የሚጠራው ኒዮርክ የነበረው የቋሚ መልእክተኛው ጽ/ቤት ሠራተኞች ናቸው።። አባ ጳውሎስ የደርግና የወያኔ ሰላይ ነበሩ ።በዚያን ጊዜ አቡነ ይስሃቅ ከሚባሉ ሌላ ጳጳስ ጋር ይጋጩና አቡነ ይስሃቅ እባካችሁ እናንተ ገላግሉን ብለው የወቅቱ አምባሳደር ጋር ይሄዳሉ።አምባሳደሩም ገርሞት እርሳቸው (ጳውሎስ) የእኛ ሰው ናቸው።ለመንግስት የሚሰሩት ሥራ አለ።እርስዎ ግን ደርግን እንደሚጠሉ ነው የሚታወቀው ወደ ፊት ሚንስትሩ ሲመጡ ጥያቄውን ይዘው ይምጡ ብለው ያሰናብቷቸዋል።ይህ እንግዲህ ጳጳስ ጳውሎስ ደርጎችን እያጃጃሏቸው እንደነበር የሚያመለክት ነገር ነው ማለት ነው።

ከወያኔ ጋር ደግሞ የሚያስጠርጥራቸው ወደ ካርቱም የሚደወለው ስልክ ብዛት ነው።ባንድ ወቅት የአንድ ዓመት የስልክ ቢል ሃያ አምስት ሺህ ድላር ደርሶ ነበር ።የሚደወለውም ካርቱምና አዲስ አበባ ነበር።አዲስ አበባስ እሺ ለሥራ ነው ይባል ካርቱም ግን ማን ጋ ነው የሚደወለው ? ይህን የምንጠይቅበት ነጻ ሚዲያ ቢኖርን እንዴት መልካም ነበር።

ኒዮርክና የጳጳስ ምሳ
ይህች የጳጳስ ምሳ ማለት ለጳጳሱ ቀለብ የሚሆን ገንዘብ ማሰባሰቢያ ዘዴ ነች።አባ ጳውሎስ ኒዮርክ በነበሩ ግዜ የወር ደመወዝ አልፈልግም ብለው ግን ደግሞ ሁለም ወጪያቸው በሰበካ ጉባኤው እየተሸፈነላቸው ይኖሩ ነበር።ከዚያም እኔ ደሞዝ አይከፈለኝም እያሉ በዓመት ሁለት ግዜ የጳጳስ ምሳ እየተባለ ፈንድ ሬይዝንግ ይደርጋል።ከዚህ ፈንድ ሬይዝንግ የሚገኘው ገንዘብ ቀጥታ በእርሳቸው አካውንት ይገባል።ከእርሳቸው ውጪ ማንም አያዘውም።ያ የእርሳቸው ገንዘብ ነው። በአንድ ፈንድ ሬይዝንግ ከ60 እስከ 70 ሺህ ዶላር ይሰበሰብ ነበር።በሁለት ዙር ከ120 እስከ 140 ሺህ ዶላር ቀጥታ ወደ አካውንታቸው ይገባ ነበር።
መች በዚህ ብቻ ያበቃሉ ባህልን ማዳበር ብለው ህዘበ ክርስትያኑን አስተባብርው የያሬዳዊ ዜማ ድራማ እያሳዩ ቢዝነስ መሥራት ጀመሩ።ከዚያም በወንድማቸው አማካኝነት እያንዳንዷን ድርጊት እያስቀረጹና በካሴት እየደርጉ ንግዱን አጧጡፈውት ብዙ ሃብት አገኙ ።መፅሀፍ ቅዱስ ግን ለመነኩሴ ምንም ሀብት እንዳይኖረው ሲል ይመክራል፡፡

ተገነባ የተባለው ቤተክርስትያን
መዋእለ ዜናቸው እንዳህ የሚል ዜና ጽፎላቸዋል።‹‹በስምንት ዓመት ውስጥ ይሆናል ተብሎ በማይታሰብ አስገራሚ ሁኔታ በሃገረ ባእድ የሚከተለትን ሰባት የኢትዮጵያ ኢርቶድክስ ተዋህድ አብያተ ቤተክርስትያናትን አቋቁመዋል›› ይላል።
ከተጠቀሱት ሰባት ቦታውች ውስጥ ፤
 1. በአሪዞና ኪዳነምህርት አስርተዋል ተብሎ ዜና ቢነገርላቸውም በአሪዞና ኪዳነምህርት የምትባል ቤተክርስትያን የለችም።
 2. የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስትያን በታምፖ ፍሎሪዳ ተሰርቶ አገልግሎቱ ሳይቋርጥ የምእመናን ቁጥር በዝቶ የእግዚአብሄር መንግስት በሰፊው እየተሰበከ ይገኛል ይላል የአባ ጳውሎስ ዜና መዋእል።ሆኖም ግን እንዲህ የሚባል ቤተክርስትያን በታምፖ ፍሎሪዳ የለም ተብሏል።
 3. የቅደስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን በላስቬጋስ ኒቫዳ አቋቁመዋል ቢባልም በኔቫዳ በዚህ ስም የሚታወቅ ቤተክርስትያን እንደሌለ እኔ ራሴ እዚያ ያለ ክርስትያን ጓደኞቼን ጠየቄ ተርድቼአለሁ።

ሌሎቹ አራቱ ደግሞ ቀድሞ የነበሩ ሲሆኑ አባ ጳውሎስ የእኔ ናቸው ብለው በራሳቸው ስም በማድርግ የማይገባቸውን ዝና አግኝተውበታል ።በኒዮርክ፤በሎስ አንጀለስ፤በሳንዲያጎ፤በዳላስ ያለት ናቸው ቀሪውቹ አራቶቹ።

 ይህን ስፅፍ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሲበርድ በእጃቸው ሲሞቅ በማንኪያ የሚበሉት አቡነ ፋኑኤል ሲኖዶስ ፊት ቀርበው የጵጵስና ማዕረግ በተሾሙበት ዕለት የዋሹት ውሸት ትዝ አለኝ ፤ አባቶችም ዋሹ ልጆች ውሽት ውሸት ነው የተሸለ ትርጓሜ ልንሰጠው አንችልም፡፡በአሜሪካ ሀገር የዋሽንግተን ዲሲ የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስም ሰርቼ አስረክቤአለሁ ብለው ፤ምልዓተ ጉባኤው በደስታ ተቀብሎት ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ተጨብጭቦላቸው ነበር ፡፡ “ሰርቼ አስረክቤያለሁ” የሚሉት ቤተ ክርስቲያን ግን፤ በባለቤትነት የተመዘገቡት ከሶስቱ ግለሰቦች አንደኛው  አቡነ ፋኑኤል ናቸው፡፡ የአቡነ ፋኑኤል ውሸት እንኳን ሊገርሞት አይገባም ፤ የአባ ጳውሎስ ነው እንጂ ፤ ይችን የመሰለች አካሄድ አቡነ ፋኑኤል ከአባታቸው ከአቡነ ጳውሎስ ይሆን የተማሯት? ፡፡ በጊዜው የነበሩ አባቶች ላያውቁ ይችላሉ ለምሳሌ ምስራቅ ሐረርጌ ላይ የተመደቡ አንድ አባት ዋሽንግተን ስለተሰራው ስራ በአገልግሎት ድካም ሙሉ መረጃ ላይኖራቸውና ላያውቁ ይችሉ ይሆናል፡፡  እውነት መስሏቸው ደስ ተሰኝተው ቢያጨበጭቡላቸው አይገርምም  መረጃው ስለሌላቸው ነው ፡፡ ይቺ ይች ደግሞ ከእኛ አታመልጥም፡፡

የአባ ጳውሎስ ዘርኛ ጸባይ
ቦታው ሎስ አንጀለስ ማሪያም ቤተክርስትያን ውስጥ ህወሃት አገሪቷን ከተቆጣጠር በኋላ ነው።አባ ጳውሎስ አውደ ምህርት ላይ ቆሙ።ታዳሚው ብዙ ነው።ማንንም ከመጤፍ ሳይቆጥሩ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንደዲህ አሉ ፤
‹‹እስከ ዛሬ የወገኖቼን ቋንቋ ሳልናገር ንቄያችሁ በመኖሬ ይቅርታ ልጠይቅ ይገባኛል።ቋንቋችሁ ከሁሉም ቀዳሚ ሆኖ ሳለ ተንቆና ተርግጦ በመኖሩ ይቅርታ ልትጠየቁ ይገባችኋል›› ብለዋል ፡፡ጉድ ነው።ቋንቋችሁ ከሁለም ቀዳሚ ሆኖ ሳለ ?!! ምን ማለት ይሆን ? ይህ የፈጠራ ወሬ ወይም ድርሰት አይደለም የተናገሩት ቃል በቃል ከድምፃቸው ተገልብጦ እንጂ
 

አባ ጳውሎስ የሚናገሩትን ቋንቋ የማይናገሩ ቡዙ ምእመናን በዚያ ቤተክርስትያን ውስጥ እንደሚኖሩ ይገመታል።ታዲያ ሌሎች ባሉበት እንዲህ ያለ የዘርኝነት ስሜት ያለውን ነገር መናገር ነውር አይሆንም ወይ? ተብለው አባ ጳውሎስ ስለማይጠየቁ ጸጥ ብለናል።የሰውየውን ጤንነት ተጠራጥሮ ከማለፍ ባሻገር እስከ ዛሬ የተደርገ ምንም ነገር አላየንም።መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ዓይነቱን ግልሰብ እንዴት ጳጳስ አድርጎ እንደሾመው ግን ይገርማል።በእውኑ እንዲህ ዓይነት ሰው የቤተክርስትያን ራስ እንዲሆን የእግዚአብሄር ፈቃድ ነውን ?

ክፍፍልና ክስ ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተክርስትያኗ ታሪክ ውስጥ በአባ ገ/መድህን ዘመን ነው የተጀመረው ፡፡በፊት በነበሩ አባቶች መሀል ትንሽ ግጭት ባይጠፋም እንደ አሁኑ ግን ከመንግስት ባለስልጣናት ከፖሊስ ኮሚሽነር ፤ ከፀጥታ እና ደህንነት ቢሮ ፤ ከውጭ ጉዳይ ቢሮ  ተመድቦ የተታረቁበት ጊዜ የለም ፤ አላየንም አልሰማንም።ከዚያ በፊት በቤተክርስትያኒቷ ታሪክ ውስጥ ክስ አይታወቅም ነበር።በእሳቸው ጊዜ የተጀመረው ክስ ሲወርድ ሲዋርድ ይህው እስከ ዛሬ ቤተክርስትያኒቷን በየቦታው እያዋረደ እየከፋፈለ ይገኛል። 

ሕገ ወጥ ፓትሪያርክና
በዚህ ሥር ብዙ ነገሮች አሉ።የአባ ጳውሎስን በዓለ ሲመት የታወጀበትን ሐምሌ 5 ቀን 1984 ዓ/ም የመከራ አዋጅ የታወጀበት ቀን ነው።ይህ ሮሮ ይባላል።በዚህ እለት ንግግር ካደርጉት ጳጳሳት መካከል የበፊት ጓደኛቸው አባ ገሪማ ዋንኛው ናቸው።እርሳቸውም እንዲህ ብለው ነበር ‹‹. . . የቸር ጠባቂነት ግዴታውን የፈጸሙ መሆንውን ከተገልጋዮች መርዳት ችለናል. . .›› ይህ የአባ ገሪማ ምስክርነት ከምናየው ከአባ ጳውሎስ ድርጊትና ባህሪይ ጋር አይገጥምም።ይህም ሌላ ውሸት ነው።እግዚኦ መሃርነ ክርስቶስ እንበል አሥራ ሁለት ብለን እንቀጥል። (ይችን ሌላ ጊዜ በቪዲዮ በምስል ፤ ከዊኪ ሊክስ ባገኝነው መረጃ ፤ ከቤተ ክህነት ተበላሽቷል ተብሎ ከተጠጣለ HARD DISK  ማህተብ ባያርፍባቸው እንኳን በsoft copy recover  የተደረጉ ማስረጃዎች ፤ የጊዜው ጋዜጦች የዘገቡትን ዘገባ ይዘን እንመለሳለን፡፡)

‹‹ፈጽሞ ቂመኛ የሆነ ወይም በየጊዜው ሁሉን እስከ ማሰርና እስከ ማውገዝ ድረስ ፈጥኖ የሚቆጣ ኤጵስ ቆጶስ ቢኖር ይህን ባይተው ክብርን የሚወድ ሁልጊዜ ፈጥኖ ለማውገዝ ቂሙን የማይርሳ ቢሆን ከሹመቱ ይሻር።እርሱንም የሚመስሉት ሁሉ የተለዩ ይሁኑ››የሚል ትእዛዝ በፍትሃ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁ 182 ላይ ተቀምጧል። ይህ ትእዛዝ ለአባ ጳውሎስ መወገዝ መነሻ ምክንያት ሆኗል እሳቸው ግን አሁንም አሉ፡፡

አሁን በህይወት ባይኖርም ለስብሰባ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ መኪናውን በአውሮፕላን እየጫነ የሚመጣው ጋዳፊን ተመልክተን ተደንቀን ነበር።አሁን በጣም ዘይግቶን የሰማነው አዲስ ነገር የሚያስደንቅ ሳይሆን የሚያስደነግጥ ነው።‹‹አባ ጳውሎስ ወደ ውጭ አገር ሲሄዱ መኪናቸው በአውሮፕላን ተጭኖ እንዲሄድ ያደርጋሉ›› ይባላል። በእውኑ ይህን አድርገዋል ? ይህ ጉዳይ ተጨማሪ ማስርጃ የሚያስፈልገው ነገር ነው ፡፡ ባገኝሁት መረጃ መሰረት ይህን አስረግጬ መናገር አልችልም ፡፡ ወሬም ደግሞ ዝም ብሎ ከመሬት አይነሳም ፤ ለምን ይህን አልክ ብትሉኝ የዛሬ ዓመት በ18ኛ ዓመት ሲመታቸው ላይ በረሀ ላይ ያሉ ቤተክርስትያኖች አንድ ጧፍ በሚያጡበት ጊዜ የአዲስ አበባ አድባራት እስከ 100,000 ሺህ ብር በማዋጣት ከ3-4 ሚሊየን ብር የሚያወጣ መኪና እንደገዙላቸው ስለማውቅ ፤ በተጨማሪ ደግሞ አጠገባቸው የሰበሰቧቸው የቀን ጅቦች ፤ ህሊና የሌላቸው ሰዎች ፤ አውሮፕላን እንደሚገዙላቸው በቀን ያለሙትን ይሁን የቃዡትን ቃል እንደገቡላቸው ስለማውቅ ነው፡፡ ይህን ሁሉ ነገር ይገባኛል ብለው የተቀበሉ አባት በአውሮፕላን መኪናቸውን ጭነው አይሄዱም ፤ አያደርጉትም ብዬ ስለ እሳቸው መከራከር አልችልም ፤ ሌላ ደግሞ ፍላጎት ካላቸው ለማድረግ ምንም እንደማያግዳቸው አውቃለሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሶስተኛው ፓትርያርክ አቡነ ተክለሃይማኖት ውጭ ሀገር ቤተክርስትያናችንን ወክለው ሊሄዱ ሲሉ ጫማ ስለማያደርጉ ጫማ አድርጉ ሲባሉ ‹‹እኔ ጫማ አላደርግም›› ብለው  ነበር ፡፡ ብጹእ አቡነ ተክለሃይማኖት በፀሎትና በፆም ብዛት አጥንታቸው ይቆጠር ነበር፡፡ በህይወት ሲለዩን 25 ኪሎ ይመዝኑ ነበር ፡፡ አሁን ደግሞ መኪና በአውሮፕላን የሚጭን አባት ተሰጥቶናል፤  ይገርማል...

አባ ጳውሎስ በድሃው ህዝብ ያሠሩትን ሃውልት እንዲያስፈርሱና የሲኖዶሱን ውሳኔ እንዲያከብሩ እጠይቃለሁ።ዛሬ እርስዎ አፍርሰውት ትንሽም ቢሆን ትህትናውን ለህዝቡ ቢያሳዩ መልካም ነው፡፡  ካልሆነም እውነት እውነት እልዎታለሁ ነገ መፍርሱ አይቀርም።እጅጋየሁ የምትባል ባልቴት ግን  አይፈርስም ስትል ሰምተናታል።ምእመናን የምንለው ደግሞ ቤተክርስትያን የደራ ሜዳ አይደለችም።የአቡነ ጴጥሮስ ሃውልት ያለበት ከተማ ውስጥ የአባ ጳውሎስ ሃውልት ግርማ የለውም።በምእመናኑ ዘንድም ስፍራ የሚሰጠው ሃውልት ስላልሆነ ግዜው ሲደርስ ይፈርሳል።

‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስትያን ይጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅደስ ጳጳስ አድርጎ የሾማቸውን እውነተኛ አባቶች ይስጠን።ለመንጋው ከማይራሩ ጨካኝ ተኩላውችም ይሰውርን። አሜን።

ቁጥር ሁለትን በቅርብ ቀን…. ያልተሰሙ ወሬዎችን ይጠብቁ


ስለመረጃው እውነትነት አንዳች አይጠራጠሩ... ገና ምንም አልሰሙም ፤ እኔም ምንም አልፃፍኩም
እንወቀው ካሉ እፅፋለሁ አንፈልግም ትርፉ ወሬ ነው ካሉ መፃፍ አቆማለሁ


ሰላም ይብዛላችሁ!!

25 comments:

 1. እንዴ! የሚገርም መረጃ ልሰማ ነው መሰለኝ። ግን ይሄ ጽሁፍ ጠቃሚ የመሆኑኑ ያክል ጉዳቱም የዛኑ ያክል ይመስለኛል። ስለሆነም በጥንቃቄ ቢሰራ ጥሩ ነው ባይ ነኝ።
  መ.ዘ ከሽሮሜዳ

  ReplyDelete
 2. ርብቃ ከጀርመንNovember 11, 2011 at 10:59 AM

  ሰላም አንድአድርገኖች እንደምን ከረማችሁ ስላቀረባችሁLን በመረጃየተደገፈ ጽሁፍ በጣም እናመሰግናለን የማናውቀውን እንድናውቅ ስላደረገን:: ምክንያቱም ብዙሰው ስለሳቸው የሚባለውን ነገር ሲሰማ በሬወለደ እየመሰለው እንቸገር ነበር ስለዚህ እባካችሁ ምእመናንን ላማንቃትና ሰውየው ማንእነደሆኑ ለማሳወቅ ብሎም የተኛውን ለመቀስቀስ ይረዳልብየ አምናለሁኝ እባካችሁ የሚቀጥለውንም ክፍል ሳትቀናንሱ ለማውጣት ሞክሩ እንዲህያልኩበት ምክንያት ከላይ አስተያየት የሰጠሰው ይህንይፋማድረግ ጉዳትም ሊኖረው እንደሚችል ስለጠቀሰነው እንደኔ እንደኔግን በጣም ዘግይተናል ባይነኝ ቤተክርስቲያንን ምንምላንጠቅማት እስካሁን ታግሰናቸዋል እነደተረቱ በእነቁላሉ ጩህንቢሆን አሁን ቤተክርስቲያን ባለችበት ቅሌት ባልተገኘችነበ ብየአስባለሁኝ::

  ReplyDelete
 3. አቤቱ አምለካችን ሆይ እግዲህስ ምን እንላለን ምንምን እንካልን በእኛ ስራና ተግባር ባትደሰትም በህይወታችንም ምንም ፊሪ ባታገኝብን በደምህያፅናሃትን ቤተክርሰቲያንን ጠብቅል ለአባቶቻችንም ምህርትን በጎነትን በልብቸው አኑርልን፡፡ አቤቱ አምለካችን ሆይ እግዲህስ ምን እንላለን ምንምን እንካልን በእኛ ስራና ተግባር ባትደሰትም በህይወታችንም ምንም ፊሪ ባታገኝብን በደምህያፅናሃትን ቤተክርሰቲያንን ጠብቅል ለአባቶቻችንም ምህርትን በጎነትን በልብቸው አኑርልን፡፡

  Terefe Taye From Ethiopia

  ReplyDelete
 4. እግዚአብሔር ላይክስ አይበድልም ይላሉ አበው፡፡ለካንስ ሃዋሳዎች ላይ በደረሰው ግፍ የተነሳ ምንጩ የት እንደሆነ ባላውቀውም ከግፉ ማግስት አንድ አድርገን በሚል የጡመራ መድረክ እንዲከፈት ሆነ፡፡ይህ ነው የጌታ ስራ እንግዲህ፡፡አሁን ከአንድ አድርገን የጡመራ ብሎግ ብዙ እጅግ ብዙ ነገሮችን እንጠብቃለን፡፡በተለይም ቤተክህነት አካባቢ ሲሰሩ የነበሩ እና እየተሰሩ ያሉ የኃጢያት ክምሮች ዘርዝረህ/ዘርዝረሽ/ዘርዝራችሁ በመጻፍ የዋሁ ምዕመናን እንዲያዉቃቸው አድርጊ/አድርግ/አድርጉ፡፡ሰው ካወቀ የሚደግፈውን እና የሚጠላውን የሚያውቅ ይሆናል እና፡፡
  ሆኖም 1)የአባ ቴዎፍሎስን ሞት የተቀበሉ 16ቱ ጳጳሳት ብላችሁ የሰባቱን ብቻ መጥቀሳችሁ ለምንድን ሆነ፤ሁሉም መጠቀስ አለባቸው ባይ ነኝ እኔ፡፡ምን አልባት ገሚሶቹ በዚያ አይነት የተዋረደ ስራ አሁንም ገፍተውበት ሊሆን ይችላል፤ሌሎቹም በንስሃ ተመልሰው ይሆናል፡፡ግን ማንም ይሁን ማን መጠቀስ ነበረባቸው፡፡ይህ አይነት ክፍተት ካላችሁ ብሎጉ አሜነታ ያጣል፡፡
  2)ስለ አባታችን አቡነ ተክለኃይማኖት ስትጽፉ ሲያርፉ 25 ኪ.ግ ነበሩ የተባለው አልጣመኝም፡፡ጫማ የማይለብሱ የነበሩ አባት እንደት ኪሎ ተመዘኑ፤እሽ ይመዘኑ እንበል በተለይ ከማረፋቸው በፊት ሃኪም ቤት ሂደው ሊሆን ይችላል፤ግን እንደዚያ ብሎ መጻፍ በጥቂት ነገር ለሚሳሳቱት ሰዎች የነገር ማራገቢያ እንዳይሆን መጠንቀቅ አለብን፡፡የተመረጠ ቃላትን ለመጠቀም ሞክሩ፡፡እውነታን አትደብቁ፡፡ማንም ይስራው ማን እውነታ ካለው እና እኛን የሚያስተምር ነገር ካለ ወደ ኋላ አትበሉ፡፡በበኩሌ አሁን ባለው ሁኔታ እናንተ የብሎጉ አዘጋጂ/አዘጋጅዎች/ ለእኛ ለምዕመናኑ ትክክለኛው የመረጃ ምንጭ እንደምትሆኑ ተስፋው አለኝ፡፡ወጣ ወጣና እንደ--- ተባለው እናንተም አሁን በጥሩ የጀመራችሁት መረጃ ማቀበል ወደኋላ ነገሮች እንዳይለውጧችሁ አደራ፡፡
  ውብሸት

  ReplyDelete
 5. ጉድ በል ክርስቲያን !አሁን እውነት እየወጣች ነው:: ቀኑ ደረሰ መሰለኝ ::እፎይ!ትንሽ ተስፋ ብልጪ አለለኝ:: ቀጥሉ ጥሩ ነው ነገር ግን ሁሉም እውነት ይሁን ::

  ReplyDelete
 6. egezere yebarekachehu yakeberachehu.endehe ayenete techebache yehone masereja eyawetachehu asetemerun.yemenawekema enawekalen neger gen ende aba selama ayenet kebatare bloge afun aseyzulege.emeberehane teredan yetewahedo ljoche bertu

  ReplyDelete
 7. Geta hoy ''ye'kedeemewin bedelachinin atasibibin abetu yikiritahi fetino yideregilin''
  gena bizu gud enisemalen man yawikal yemechereshaw gize lihon yichilal.

  ReplyDelete
 8. yekedusan amlak yeker yebelen behawareyat mehakel yehuda enedeneber hulu zarem terefe yehudawoche menorachew ged new ega gen betewahedo senetn menor bech new geta hoy adenene enebelew.

  ReplyDelete
 9. mejemeriya ayeneh lay yalewun meseso anseteh selesewu gudfe betawora yikelal....mastewalun lehulachinim yadelen

  ReplyDelete
 10. ሰዎችን ሰለ ነገሮች ማስታወቅ ትሩ ነው ። ነገር ግን የምናቀርበው መራጃ ሰዎችን አይጎዳም ወይ የሚለውን በጥንቃቄ መመልከት አለባችሁ። በገድሉ ጫፍ ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን ማሰብ ያስፈልባል። ሰዎችን በእንደዚህ መረጃ አቅርቦ ከማደናገር ይልቅ በፀሎት ሕዝቡ እንዲተጋ ማሳሰም ይሻላል። ምንም እንኳን ነገሩ እውነት ቢሆንም ትርፉ ሀሜት ነው። ይህ ደግሞ ከእዚአብሔር መንገድ ያርቀናል እንጂ አያቀርበንም። በተለይ ደግሞ አሁን ባለው የቤቴክርስቲያናችን ችግር እንደዚህ ያለው መረጃ ነገሮችን ያብሳል እንጂ አያቀልም። ስለዚህ እባካችሁ ጊዚያችንን በእንደዚህ ከምናጠፋ የተለያዮ መንገዶችን በመፍጠር የቤቴክርስቲያናችንን ልጆች በጸሎት እና በፆም እንዲተጉ ማስተማር ይሻላል።

  ReplyDelete
 11. ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት የተነሳ አለ ማን እንደሆነ ግን ማንም አልደረሰበትም፡፡አስቲ ሁላችሁም ለመረጋጋት ሞክሩ ፤ለማሰብ ጊዜ ዉሰዱ፤ ሁላችሁንም ግራ የሚያጋባ አንድ የተሳሳተ ሀይል ገብቶባችሆል፡፡

  ReplyDelete
 12. ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለማጥፋት የተነሳ አለ ማን እንደሆነ ግን ማንም አልደረሰበትም፡፡አስቲ ሁላችሁም ለመረጋጋት ሞክሩ ፤ለማሰብ ጊዜ ዉሰዱ፤ ሁላችሁንም ግራ የሚያጋባ አንድ የተሳሳተ ሀይል ገብቶባችሆል፡፡

  ReplyDelete
 13. ሰዎች ሞት የሚመኙበት ጊዜ ይመጣል:: ምን ልበላችሁ ወገኖቼ አንዳዴ ልጅ የወለዳችሁ ጰጰሳት ዝርዝራችሁ በአደባባ እናወጣለን ትላላችሁ:: እናንተም እነዚያም ነገሮች ስታዋክቡ ሕዝቡ ሙልጭ ብሎ ፕሮቴስታቱ ጥልቅ ብለዋል:: ማንን ለመምራት ይሆን ይህ ሁላ ትግል? ሳታውቀው የሚሠርቅህ ሰይጣን በቀላል አይለቅህም እልከኛ ልብ ይፈጥርብሃል:: እውነተኞች የሃይማኖት ተቆርቃሪዎች ከሆናችሁ ለምእመናኖቻችሁ ወይም ላላመኑ ትክክለኛ ነው የምትሉት ክርስቲያናዊ (ኦርቶዶክሳዊ)ትምህርት አስተላልፉ የተቀበላችሁ ይከተላችሁ አልያም የእግራችሁ ትብያ አራግፋችሁ ውጡ:: መገዳደል ነፍስን ከስጋ መለየት ብቻ አይምሰላችሁ ይህ በምእመናን መካከል መለያየት መፍጠር ራሱ መገዳደል ነው::

  ReplyDelete
 14. Please my dear old friend, I think you are by the side of the so called the exile synod in abroad. Because you have tried to protect those people and made them out of the picture. The other thing is ,you are judgmental.You haven't written even any new thing other than what we heard before and this was worsening the existing problem in the church. If you believe that there are many churches with out the proper clothing and the like, It is better to try to help those churches with all your power, rather than weakening the church sowing the seed of hatred.Many people will refrain from going to church even, because they have enough household problems. Stop this nonsense, my beloved old friend.

  ReplyDelete
 15. እግዚኦ መሃርነ ክርስቶስ

  ReplyDelete
 16. the way you write it seems "real",but this is not the truth. this is fabricated from the arogant politicians like you and some primitive thinker of the church.why do u became rasist.what is wrong with u b/c they are from tigray?
  please now adays to protect the church u should have to very active and be smart.we ethiopians have one culture that should be eradicate"we don't like strong and skilled leader"
  wake up

  ReplyDelete
 17. አቤት ማዳነቅ ህይወትን ስበኩ አሉባልታ ተዉ አባቶችን አክብሩ

  ReplyDelete
 18. BEMETSHAF KIDUS YESEWUN HATYAT BEMEGILET YETSDEKE
  YINOR YIHONE WEYIS KE ENANITE HATIYAT YELELEBET BINOR ERSU YIWUGERAT..
  BICHA YIKIR YIBELEGN ENA DEDEBOCH MESELACHIHUGN AHUNIS..

  ReplyDelete
 19. this is al about hatred. i hate this website. come with something spirirual

  ReplyDelete
 20. please go ahead!!!! zim atibel minalibat minim latifetir tichilaleh gin ke hilina dagnet netsa neh ina atakumewu be emebete yizehalehu...

  ReplyDelete
 21. EGIZIO MEHARENE KIRISTOSE

  ReplyDelete
 22. ‹‹በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስትያን ይጠብቋት ዘንድ መንፈስ ቅደስ ጳጳስ አድርጎ የሾማቸውን እውነተኛ አባቶች ይስጠን።ለመንጋው ከማይራሩ ጨካኝ ተኩላውችም ይሰውርን። አሜን።

  ReplyDelete
 23. መረውጃን በጥንቃቄ አንብቤዋለሁ የታዘብኩትን አንድ ነገር ልንገራችሁ የኢትዮጵያ ምእመናን ከሌላ አማኝ የምንለየው አባቶቻችን ሲሰደቡ በሚሰማን ደስታ ነው።ይህ ደግሞ መዘዙ የከፋ ነው በስተመጨረሻ ኑፋቄን ያስከትላል ይህን ስል ፓትርያርካችን ጥሩ ናቸው ወይም አይደሉም ለማለት አይደለም ነገር ግን ማንም ሰው "አባቴ ታናሽ ድሪቶ ለባሽ"አይልም። እስቲ እባከችሁ የሌላ እምነት መሳቂያ አንሁን ፍርዱን ለፈጣሪ ትተን እናንተም በጎ በጎውን ጻፉ እኛም በጎውን እናንብብ ሌላው አያንጽምና.......

  ReplyDelete
 24. zim enibel yemibalew neger ayigebagnim.leleloch eminet mesakiya anihun yemibalew,mesakiya kemehon mech danina? yilikunus bebetachin gebtew endizerfun fekedinilachew enji.mi-emenun kebetekiristian netikew lemewxat yetezegajut sineqabachew enikuan defro lemaswexat ye-abatoch zimita lemin yihon?ye-alama anidinet silalachew yihon?
  ebakachihu yejemerachihutin mereja ketilubet.EGIZIABIHER yirdan!!!

  ReplyDelete
 25. yerasin menagerim yilemed!!!!!!!

  ReplyDelete