Monday, November 21, 2011

ቤተክርስቲያኑ አሁንም የእኔ ነው ወደፊትም የራሴው ነው ( አቡነ ፋኑኤል)

የደብረ ምሕረት የትላንትናው ትዕይንት ይሄን ይመስል ነበር
  • እኔን ቀበሌ አላከኝም፣ የላከኝ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው:: 
  • 14 ዓመት ደክሜ ከሰራሁት ቤቴ የትም አልወጣም ::
  • ወደዳችሁም ጠላችሁም ከዚህ የትም አልሄድም:: 
  • አዎ አዲስ አበባ ላይ ቪላዎች ቤቶች አሉኝ፣ ያንን ትቼ ይህንን ህዝብ ላገለግል መጣሁ::
  • ከዋሺንግተን ዲሲ እስከ ካሊፎርኒያ የኔ ግዛት ነው::
  • ከዚህ በኃላ ስደተኛ፣ ገለልተኛ፣ መፃተኛ የሚባል ቤተ ክርስቲያን የለም

    በትላንትናው እለት በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ላይ የተገኙት አቡነ ፋኑኤል በአዋሳ ላይ  እንዳደረጉት ‹‹ምንም የምታመጡት ነገር የለም ፤ እኔን የላከኝ ቀበሌ አይደለም ቅዱስ ሲኖዶስ ነው›› በማለት ለበዓል የታደመውን ምዕመን አስገርመውት ውለዋል። 

    ትላንት በጠዋት የተጀመረው የቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የቤተ ክርስቲያኑ መግቢያ በፓሊስ ሲታጠር ፤ ውጪው ደግሞ በተቃዋሚ ታውኮ ውሏል። ከሥርዓተ ቅዳሴው በኃላ በመምህር ዘላለም ወንድሙ አማካኝነት የማስፈራሪያ መልዕክት እንዲያስተላልፍ በተሰጠው ጥብቅ መመሪያ መሰረት እግሩ ረግጦት በማያውቅበት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ በመቆም ባለሟልነቱን በሚገባ አረጋግጧል፡፡  እንደሚታወሰው መምህር ዘላለም ወንድሙ ከዚህ በፊት በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ፈቃድ በአቡነ ፋኑኤል አደራጅነትና አዋቃሪነት በተከፈተው ‹‹የቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት /ቤት›› በሚባለው የሰሜን አሜሪካ የሰባኪያን እና ዘማሪያን ባለሙሉ ሥልጣን የበላይ ኃላፊ በሚል እንደተሾመ ይታወሳል። በትላንትናው ድራማ ላይ አቡነ ፋኑኤል ‹‹ለእኔ የሚናገርልኝ ሰው ከሌለ እኔው ራሴ ስለ  ማንነት እነግራችኃለው›› ብለው ተሰበሰበው ምዕመን ስለራሳቸው ገድል እና ድርሳን ሲናገሩ የምዕመኑን ጆሮ ሲያደነቁሩ ፤ ከግማሽ ሰዓት በላይ አሳልፈዋል፡፡

በዚህም መሠረት ‹‹እኔ ልሰራ እንጂ ልከፋፍል አልመጣሁም ፤ ስለዚህ ከዚህ በኃላ ስደተኛ ወይም ገለልተኛ ሳንል በተጠራንበት በመሄድ እናገለግላለን›› በማለት አስጨብጭበዋል፣ እንደ እውነቱ ከሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ ከለየው ጋር ሄዶ መባረክም ሆነ ፤ እናቀራርባለን ብሎ ማለት ሥርዓት አልበኝነታቸውን የበለጠ ያጎላዋል እንጂ የሥራ ሰው መሆናቸውን አያስመሰክርም፡ ከዚህ በተጨማሪ ‹‹እኔ የሁሉም አባት ነኝ›› ማለታቸውም ነገ የአባ ሰላማ ብሎግ ባለቤቶች (ፕሮቴስታንቶቹም) ቢጠሯቸው የሁሉም አባት ስለሆኑ ሄደው ሊባርኩ ነው ማለት ነው ? አንባቢ ያስተውል።
በእለቱ ከታዩት በርካታ ካሜራዎች እና ተቃዋሚዎች ጥቂቱ
አቡነ ፋኑኤልና ካሕን መስሎ ከቆመው BODY GUARD ጋር

‹‹የዛሬ 5 ዓመት ቅዱስ ሲኖዶስ መድቦኝ እዚህ መጥቼ ነበር፣ ነገር ግን ሕዝቤን በሀገሩ ማገልገል አለብኝ ከሚለው ጽኑ ፍላጎቴ የተነሳ ለቅዱስ ሲኖዶስ ደብዳቤ ጽፌ አዛውሩኝ በማለት ተዛውሬያለሁ›› ያሉት አቡነ ፋኑኤል ፡፡  አሁን ደግሞ ‹‹ለ17 ዓመት ደግሜ በገዛ ገንዘቤ ያቋቋምኩትን ቤቴንና ሕዝቡን ላገልግል ብዬ አዲስ አበባ ላይ ካሉኝ ቪላዎቼ እናንተን መርጬ ላገለግላችሁ መጥቻለው›› ብለዋል።

ትላንት ከታዩት አስገራሚው ትዕይንት የህዝቡን ቀልብ የሳበው አባ ፋኑኤል ልክ እንደ ቅዱስ ፓትሪያሪኩ የግል ጠባቂ (Body Guard) የካህን ልብስ አልብሰው ፤ ጥቁር መነጽሩን ደንቅሮ ፤ በተጠንቀቅ ሲጠብቅና የሙያውን ሥራውን በሚገባ ሲወጣ ቆይቷል፡፡ የፓሊሱ ግርግር፣ የቦዲ ጋርዱ ጥበቃ፣ የተቃዋሚዎች ስድብ በቤተ ክርስቲያናችን እስከ መቼ እንደሚቀጥልና ታቦታችን ፊት እንዲህ አይነት ስድብና ውርደት መቀጠል እንደሌለበት የሁላችንም እምነት ቢሆንም አቡኑ ግን ‹‹ወደዳችሁም ጠላችሁም ከሰራሁት ቤቴ ማንም አያስወጣኝም›› በማለት ‹‹ደርግ እንኳን ሁለት ያለውን አንዱን ነው የነጠቀው፣ እኔ ግን አንድ ስለሆነ ያለኝ እሱንም ስጥ የሚል ህግ የለም›› ነበር ያሉት።
 
ሌላው አስገራሚው ትዕይንት ደግሞ አቡነ ፋኑኤል እስከ ዛሬ ድረስ እርሳቸውንም ጨምሮ በተለያየ ጊዜ የተለያዩ ሊቃነ ጳጳሳት በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ተቀማጭ ሆነው ብዙ ሥራዎችንም የሰሩም ነበሩ፡፡  ነገር ግን አቡነ ፋኑኤል እርሳቸው የመጀመሪያው ለሥራ የመጡ የቅዱስ ሲኖዶስ ተወካይ እንደሆኑ ሲናገሩ ምዕመናኑን ሁሉ አስገርመዋል፡፡ በተለያየ ጊዜ እየመጡ ያደራጇቸው የገለልተኛ አስተዳደር በሙሉ ምንም ነገር እንዳልተፈጠረ ነበር የተናገሩት በመቀጠልም ሁሉንም ይዘው ሥራ ለመስራት እንደተዘጋጁና ምዕመናኑንም ገንዘብ ያለህ በገንዘብህ ፤ ሙያ ያለህ በሙያህ ፤ ተባበረኝ ብለው ነበር የተናገሩት።

እንደሚታወቀው የራሳቸውን ዝናና ክብር ሲወራ የሚወዱት አቡነ ፋኑኤል ትላንት የርሳቸውን ገድለ ፋኑኤል የሚያወራ ስለጠፋ ‹‹ስለ እኔ የሚናገር ከሌለ እኔው ስለራሴ ልናገር›› ብለው ነበር፡፡  ስለ እኔ ገድል ተናገሩ ያሏቸው በሙሉ ለመናገር ባይደፍሩም ሕዝበ ክርስቲያኑን ከንቀታቸው የተነሳ ‹‹ይሄንን ቤተ ክርስቲያን ተቃዋሚዎች ጥይት ግዛ ብለው ሲሰጡኝ፣ እኔ ቤተ ክርስቲያን ገዛሁበት ፤ በመሆኑም አሁንም የእኔ ነው ወደፊትም የራሴው ነው›› ነበር ያሉት፡፡

 ታዲያ እንዲህ አይነት "እኔነት" የተጠናወታቸው አባት እንዴት ነው ይህንን የተለያየ አላማና አካሄድ ያለውን ሕብረተሰብ እመራለሁ ብለው የተነሱት ? ሲሆን እንደ ጥንት አባቶቻችን በትህትና እና በፍቅር መጀመር ሲገባቸው ገና ሲጀምሩ በትዕቢትና በማናለብኝነት የጀመሩት አቡነ ፋኑኤል በአዋሳ ሕዝብ ላይ ያደረሱትን በደል በዋሽንግተን ሕዝብ ላይ እንደሚያደርጉት ይጠበቃል።

በዋሽንግተን አካባቢ በተለያዩ አስተዳደር ስር ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ጥቂቶቹ
፩/ በእናት ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ስር ያሉ
፪/ በስተደኛው ሲኖዶስ አስተዳደር ስር ያሉ
፫/ በገለልተኛ አስተዳደር ስር ያሉ
፬/ ስደተኛውም ሲኖዶስ ወይም የሀገር ውስጥ ሲኖዶስ የማይመሩ ነገር ግን በራሳቸው የቦርድ አስተዳደር ያሉ
፭/ በእናት ቤተ ክርስቲያን ያሉ ነገር ግን የፓትሪያሪኩን ስም በጸሎት የማይጠሩ
፮/ በገለልተኛ አስተዳደር ያሉ ነገር ግን የባለቤቶቻቸውን የቅዱስ ሲኖዶስ ጥቂት አባላት ስር የሚተዳደሩ

እውነት ታዲያ አቡነ ፋኑኤልን መሪ አድርጎ ተቀብሎ የሚሰራ የትኛው ክፍል ነው? እንደ እርሳቸው አባባል የመጡት ለሁሉም ነው ብለዋል ፤ ታዲያ ይሳካላቸው ይሆን? ለጊዜው አሸንፈው የገቡት የራሴ ነው ፤ የግል ንብረቴ ነው ፤ ታክስ እከፍልበታለሁ ፤ ወይም መጦሪያ ቤቴ ነው፤  በሚሉት ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነው፣ ቀጥሎስ የትኛውን አሸንፈው ወይም ብልጣ ብልጣ ብልጥነታቸውን  ተጠቅመው ማስተዳደር ይችሉ ይሆን? ጥያቄውን ለአንባቢ በመተው የወደፊቱን አብረን ለመመልከት የዛሬውን በዚህ እያጠቃለልን በመቀጠል የአቡነ ፋኑኤልን አካሄድ  እየተከታተልን ለማቅረብ ቃል እንገባለን።


መልዕክት አለን
የሰውዬው ማንነት በሚዛን ተመዝኖ ክፉ ስራቸው ያደላባቸው አባት ናቸው ፡፡ ሰው ስህተት ይሰራል ፤ ነገር ግን ከስህተታቸው አልታረምም ያሉ አባት ናቸው፡፡ የሀዋሳውን ህዝብ እንዴት እንደተጫወቱበት አሁን ላይ መናገር ለቀባሪው ማርዳት ነው የሚሆነው ፤ ልባቸው ደንድኗል ፤ በማን አለብኝነት መምራት እና ማተዳደር ነው የሳቸው ፍላጎት፡፡  ይህ አይነት አካሄድ ደግሞ በዚህ ዘመን የሚቻል አይመስለኝም፡፡ መረጃ በደቂቃዎች ውስጥ ከአንዱ ጫፍ ወደ አንዱ ጫፍ በሚወነጨፍበት ፤ ሰዎች ምን እንዳሰቡ ፤ ምን እንዳደረጉ በቀላሉ መረጃ የሚለዋወጥበት ጊዜ ስለሆነ ….

በሀዋሳ ያሉትን አባቶቻችን የእንጨት ላይ  ሽበት እያሉ ያሰደቧቸው እሳቸው በፈቀዱት መድረክ አማካኝነት ነው ፤ ሰዎች እንባቸው የፈሰሰው በእሳቸው ፍትሀዊ ባልሆነ ስርዓት የተነሳ ነው ፤ቤተክርስትያኗን የተገዳደሯት ሰዎች ብቅ ብቅ ያሉት እሳቸው ባጠቧቸው ጡጦ አማካኝነት ነው ፤ክርስትያኖችን በዘር መከፋፈል አፍን ሞልቶ መናገር የተጀመረው በአቡኑ ያልተገባ አካሄድ አማካኝነት ነው ፤እኛ የምናውቀው ቤቱ በእጣን ሲታጠን ነበር እሳቸው ግን በከብት ኩበት ያሳጠኑት እኝህ ሰው ናቸው ፤ ከሰባኪዎች ጋር ያልተገባ ዝምድና በመፍጠር ወንጌሉ በአግባቡ እንዳይሰበክ ያደረጉ ሰው ናቸው ፤ ለሰባኪያን ከቤተክርስትያን ስርዓት ውጪ መጋቢ ሀዲስ ፤ መጋቢ ብሉይ ፤ እያሉ መአረጓን ለማይገባቸውና ለማይመጥናቸው የስሙንም ትርጓሜ በአግባቡ ለማያውቁ ሰዎች በስጦታ አማካኝነት የሰጡ እኝህ ናቸው ፤ ከስርዓተ ቤተክርስትያን ውጪ ያለ ሀገረ ስብከታቸው በመሄድ ቅስና እና ድቁና የሰጡ እኝህ ሰው ናቸው ፤ታዲያ በምን መስፈርት ነው አሜሪካ የተመደቡት? ብለው እንዳይጠይቁ ፡፡ እሳቸው የአቡነ ጳውሎስ ታማኝ ስለሆኑ ብዙ Business በእነሱ አጠራር የሚታፈስበት ቦታ ስለሆነ ፤ ‹‹ታማኝ የሆነ ሰው›› ነው መላክ ያለበት ከሚል እሳቤ የተነሳ ነው ፡፡ እኛም መሰሪነታቸውን እናውቃለን ፤ ህዝበ ክርስትያ እንዲየውቅ እናደርጋለን ፡፡ የእስከዛሬ ስራዎት ይብቃዎት ልንላቸው ይገባል ፡፡ ህዝቡንም ልናነቃው ግድ ይለናል፡፡ 

ኢትዮጵያ ሀገራችንን፣ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ከአጽራረ ቤተክርስቲያን ይጠብቅልን አሜን

የመላው ዓለም የተዋሕዶ ቤተሰብ
Posted by ቁርጠኛ የተዋሕዶ ልጆች 

20 comments:

  1. umm!!! surprised
    i don't think that it is difficult to get a digital camera in USA, so please from now get a video and share to all us. it is more powerful than the words that you wrote.

    ReplyDelete
  2. Please Andadrgan, try to be religious people as much as possible, you are absolutly looks like politician. we have never heared or seen like you who believe that you only know the truth and are a holly and others are stupid and they do not the right way or does not have sound mind and they are going to hell.
    Hi men ! Donot forgget u r also human being, u have disire , imosion, and so on like others, just give us the information without adding or modifing the reality. If u do that u r helping us.otherwise u wanna control our wind and heart

    ReplyDelete
  3. Okay he has villa as you put it on "አዲስ አበባ ላይ ቪላዎች ቤቶች አሉኝ" Abune Abrham has villa too. Can we have a pope devoid of properties? Because that is what Pops were supposed to be if they wanted to be true leaders? I think you guys are looking for a pope that doesn't exist on this planet.

    ReplyDelete
  4. Good information. But sadly, your writing is not well edited and poor Amharic usage. Try to improve. especially the punctuation aspect.

    Stay blessed,

    ReplyDelete
  5. "በመምህር ዘላለም ወንድሙ አማካኝነት የማስፈራሪያ መልዕክት እንዲያስተላልፍ በተሰጠቅ ጥብቅ መመሪያ መሰረት መጥቶ በማያውቅበት የደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አውደ ምህረት ላይ ቆሞ ባለሙዋልነቱን በሚገባ አረጋግጧል"
    Abet Qnat MK Yale Enante Sebaki Aynur new ende belu belu belu zelalemn tewet adrgut medhanealem endayatefachu bedani bedejene ena bezelalm keld yelem.

    ReplyDelete
  6. Before this occasion, you have expected a great evil, but nothing happen. Suppose you have thank your God if you are a good and true believer. However, I think you guys are a threat not only to Tahadso but also our country, Ethiopia.

    SALAM

    ReplyDelete
  7. gena bizu enayalen abatochin yawaredu abat nachew wuloachew rasu kemaymetinachew tera sew gar new wondimoche egziabher yatsinachihu azenkulachihu . betam bertu egziabhern yeyaze aywedkim dilu yebetekirstiyan new mechem bihon!!!!
    from Hawassa

    ReplyDelete
  8. This blog is copy of Dejeselam and dejeselam is copy of MK.

    ReplyDelete
  9. koy ande adregen zegebaw endale ke economy ga yeteyayaze new ende weyes ezihm cheger ale Sele Egziabher mesgana mawratu ayeshalem abzagnawen post yaregachehuten ayechewalehu menem techebache neger yelewm Egziabher mastewalun yestachehu

    ReplyDelete
  10. እናንተ ከየት የመጣችሁ ናችሁ አባት አይደሉም ክህነት እኮነው የያዙት እንዴት ነው ነገሩ የስድብ አፍ ተሰጠው ለእናንተ ነው እንዴ እረ ቀስ

    ReplyDelete
  11. እናንተ ከየት የመጣችሁ ናችሁ አባት አይደሉም ክህነት እኮነው የያዙት እንዴት ነው ነገሩ የስድብ አፍ ተሰጠው ለእናንተ ነው እንዴ እረ ቀስ

    ReplyDelete
  12. please yalachihut be egzihabeher bet newuna afachihu endameta atinageru......please ande adirgen this is abig shame!!!!

    ReplyDelete
  13. lewshet yefeteracheh nachehuna lenanete melse ayasflegeme ye balege sebesebe nachehuna

    ReplyDelete
  14. bemegemeriya dereja le hulachenem geta masteway leb yisten. ebakachu wed ande neger azenbelen antech aneboden. kehulum belay aymero yeseten lemastwal newena hulunem mereja enmermer. klay yemtayew asteyayet yetewesene buden yemiyaramedew asteyayet new yehe demo yetem ayadersem kemeferekakes besteker.

    ReplyDelete
  15. ይሄ አንድ አድርገን መድረክ ከስሙ ጋር የሚሄድ ነገር ለውም ምክንቱም ያየነው ነገር ሁሉ አባቶችን የሚሳደብና የሚያናንቅ ለጠላቻ ዘመቻ የሚከፍት ነው ክህነት ምን ማለት እንደሆነ የገባው አደለም ካህን ማለት አባት ማለት ነው ‹‹አባቴ ሌባነው ፣ሰካራም ፣ አጭበርባሪ ››ብለን ለሰው እንደማናወራ ሁሉ የነሱንም ችግር ካለ በሚመለከተው መንገድ መንገር ነው አለበለዚያ ለህዝብ አውጥቶ ባደባባይ መጋበዝ ይህ ነው መናፍቅነት ፣ሀይማኖቷን ባለቤት የለሽ ማስመሰል ነው ባለቤት አላት እናንተ ከመንገዱ ዞር በሉላቸው ባለቤትነት የተሰማችሁ ከሆነ የምትጽፉት በታኝ ነውና ታረሙ ፡፡

    ReplyDelete
  16. ኢትዮጵያ ሀገራችንን፣ ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ከአጽራረ ቤተክርስቲያን ይጠብቅልን አሜን

    ReplyDelete
  17. እኔን የሚገርመኝ ይሄ የአድርባዩ ብዛት ነው እንዲህ "አባት እኮ ናቸው" ለምን እንደዚህ ይባላሉ የሚሉት ነገር አይገባኝም እረ ለመሆኑ መቼ ነው እንደ አባት ሃይማኖታችንን አክብረው ሊያስከብሩ የተነሱበት ጊዜ የዛሬ 17 ዓመት እኔ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ አይደለሁም ሲሉ መስቀሉም ቀሚሱም የራሴ ነው ሲሉ የነበሩ አባት ተብዪ፣ ቀጥለው ደግሞ ቅዱስ ፓትሪያሪኩን የወያኔ ቡችላ ባሉበት አፋቸው ቅዱስ ፓትሪካችን ሲሉ መሰማቱ በእጅጉ የእስስት ፀባያቸውን በደንብ ገልጾ ያሳያል።
    አንዳንድ ተላሎች ደግሞ እስቲ ሰውየው እስከ ዛሬ "ማሪያም አታማልድም" ወይንም "ቅዱሳን ሰማዕታት አያስፈልጉን" ብለው አያውቁም ወይም ህፀፅ የለባቸውም ለምን እኝህን አባት አይተዋቸውም ይላሉ፣ ልንገነዘበው የሚገባን እውነታ ምንመሰላችሁ
    ያኔ አሪዮስ ወልድ ፍጡር ነው ብሎ ሲያስተምር፣ ሊቃውንቱ ተው ተመለስ አሪዮስ ሲሉት እምቢ ብሎ ቀጠለ ስለዚህ አውግዘው ለዩት እነዚህ የዘመናችን ተረፈ አሪዮሳዊያን ከአባታቸው ከአሪዮስ ትልቅ ትምህርት ተምረዋል እሱም ምንድነው አሪዮስ በተናገረው ተወግዞ ሲባረር ተከታዮቹም ተከትለውት ከቤተክርስቲያን ከነሰንኮፋቸው ተነቅለው ወጡ ያትምህርት ለዘመኑ ትልቅ ትምህርት ስለሆነ ከነሱ አፍ እንዲህ ዓይነት የክህደት ትምህርት መጠበቅ የዋህነት ነው ነገር ግን የክህደት ትምህርት የሚያስተምሩትን ያበረታታሉ፣ ይደግፋሉ፣ ሳይገባቸው የመዓረግ ስም እየሰጡ ከፍከፍ ያደርጓቸዋል። ምክንያቱም አንድ እና አንድ ነው እነዚህ ሰዎች ቢወገዙ ምንም ችግር የለም ሰንኮፋቸው ወይም መሪዎቻቸው በቤተክርስቲያን ውስጥ ስለሆኑ ያንን የምንፍቅና ትምህርታቸውን ለሌላ ደቀ መዝሙር አስተላልፈው በእነሱ አንደበት ይናገራሉ ስለዚህ እነሱን ማንም ጣቱን ሊጠቁምባቸው አይችልም ነገር ግን ልብ ብለን ስንመለከት እንዲህ ያሉት አባት ተብዮዎች ጠባያቸው አንድ ነው ተመሳሳይ ነው እርሱም እንደሚከተለው ነው
    ፩/ ለሕገ ቤተ ክርስቲያን ግድ የላቸውም
    ፪/ የራሳቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ እንደሚደክሙት ለቤተክርስቲያን እሩቡን እንኳን አያደርጉም
    ፫/ ማዕረግ በየደረሱበት የመስጠት እና ያልሆኑትን ሆኑ በማል የሚወዱ
    ፬/ ከንቱ ውዳሴ የሚወዱ
    ፭/ ምንም ሳይሰሩ እና በቅድስና ሳይኖሩ ቅዱስ፣ ወይም ጻድቅ መባል የሚወዱ
    ፮/ እራስ ወዳዶች (ከራስ በላይ ነፋስ) የሚሉ
    ፯/ ለጓደኞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ክብር ግድ የሌላቸው
    ፰/ ቂመኞች አሳዳጆች የተንኮል ሰዎች
    ፱/ ለሀገርም ሆነ ለወገን ግድ የሌላቸው
    ፲/ እኛ የሁሉም አባት ነን ማለት የሚወዱ (ለፕሮቴስታንቱም፣ ለሙስሊሙም፣ ለካቶሊኩም፣ ለኤቲየስቱም፣ ለቡዳውም፣ ለካልቪኒስቱም፣ ለሉተራዊያኑም፣ አባት መሆኑ የሚፈልጉ)

    እነዚህ ከላይ የዘረዘርናቸው መላየቸው ነው ስለዚህ እነዚህ ሰዎች አሁንም ነገም ቢሆን ቤተክርስቲያንን ሊያፈርሱ ከተነሱ ሃይሎች ጋር ወግነው በጥቅም ወይም በአርቆ አስተዋይነት ማነስም ወይንም በስግብግብነታቸው ሊሆን ይችላል። የሆነ ሆኖ እነዚህን ሰዎች ልናውቅባቸው እና ነቅተን ከሐዋሪያት የተቀበልናትን ተዋሕዶ ሃይማኖታችንን ልንጠብቅ ይገባል እላለሁ
    ቸር ይግጠመን

    ReplyDelete
  18. WHAT A SHAMEFUL YOU ARE? DO YOU KNOW ABOUT THE PERSON YOU SAID" BODY GUARD"? HE IS ONE OF THE THEOLOGY COLLEGE GRADUATE AND A PRIEST AS WELL AS ADMINISTRATOR OF ONE OF THE CHURCHES IN ARLINGTON,VIRGINIA. THE NAME OF THE BLOG AND ITS WORKS ARE TOTALLY DIFFERENT. GOD SHOWS YOU THE TRUTH.

    ReplyDelete
  19. Write mοre, thats all I have to say. Liteгally, it seems as
    though уou relied on the vіdeo
    to make уour point. You сleаrly knоω ωhat youre talking about, whу throw away your intelligencе on
    just pοstіng videos to your site when уοu could be giving us something informative to read?


    Alsο vіsit my blog post - Pay Day Loans
    My weblog ; Payday Loans Online

    ReplyDelete