Sunday, November 6, 2011

‹‹ትዝታውን አልመቱትም›› ዘማሪ ሙሴ

  • በያዙት እንጨት ጭንቅላቴን ፈነከቱኝ ደበደቡኝ፤ 
  • አሁን ያለው ብጥብጥ የሀይማኖት ልዩነት የለውም ፤
  • እኔ ምፈልገው የደበደቡኝን ሳይሆን ያስደበደቡኝን ነው፡፡
ትዝታው ሳሙኤል ቅዳሜ 25/02/2004 በወጣ ሎሚ መፅሄት ጋር ባደረገው ቃለ መጠይቅ ከሳምንት በፊት በቅድስተ ማርያም ቤተክርስትያን ውስጥ ‹‹ቤተክርስትያን አትታደስም›› በሚሉ የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እንደተደበደበ የተናገረ ሲሆን በዚያው ሰዓት አብሮት የነበረ ጓደኛው ዘማሪ ሙሴ ግን የሰጠው ቃለ ምልልስ ትዝታው ከሰጠው ተቃራኒ ነበር፡፡ ‹‹በጊዜው በአጋጣሚ እዛው ነበርኩኝ ትንሽ ወጣቶች ትዝታውን እንደከበቡት ተመልክቻለሁ ነገር ግን ወጣቶቹ ከበቡት እንጂ ትዝታን አልመቱትም›› በማለት ነበር የተናገረው፡፡  ትዝታው ግን ‹‹ደበደቡኝ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውብኛል›› በማለት ያልሆነውን ሆንኩ ብሏል፡፡

ፈገግ ያሰኝኝ መልስ
ሎሚ፡- በቤተክርስትያን ውስጥ በመደብደብህ ምን ተሰማ?

ትዝታው ፡- የተሰማኝ ኩራት ነው፡ ሳልሰርቅ ፤ ሳላጠፋ በክርስቶስ ወንጌል ጉዳይ ሐዋርያት ስለወንጌል የከፈሉት ዋጋ የተሰማቸው ልባዊ ኩራ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ እግዚአብሔር ይቁጠርልኝ ብያለሁ፡፡
(እኔ የምለው ሐዋርያት እኮ ወንጌልን ሲሰብኩ ፅኑ መከራ ደረሰባቸው እንጂ ወንጀልን ሲሰብኩ እኮ አይደለም፡፡ ባለቤቱ 33 ዓመት ያስተማራቸውን እንጂ የራሳቸውን አመለካከት ህዝቡ ላይ ሲያሰርፁ አይደለም፤ አባቶቻን ምንፍቅና ተሸክመው አይደለም መከራ የደረሰባቸው፡፡ የምን ጠጋ ጠጋ ነው ፡፡ ዘሎ ራስን ከእነሱ ጋር ማወዳደር ፤ የእነሱን መከራ ከራስ ጋር ማስተካከል የሰውን ስነ ልቦና ለመስረቅ የሚደረግ ፕሮፖጋንዳ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡)
ሎሚ፡-  አላማችሁ ምንድነው?
ትዝታው፡- የኛ አላማ አንድና አንድ ነው ፡፡ የክርስቶስን ወንጌል ለዓለም ሁሉ ማዳረስ የተዋህዶ ሐይማኖትን እውነት ያለገደብ ማወጅ ነው ፡፡ለዚህ ሁሉ አላማ አባቶቻችን የከፈሉትን ዋጋ ሁሉ እከፍላለን::


የዓይን ምስክር
ሎሚ ፡- ትዝታ ተመቷል ይላሉ እውነት ነው?

ዘማሪ ሙሴ ፡- እኔ በአጋጠሚ እዛው ነበርኩኝ ፤ ማርያም ቤ/ያን ውስጥ እንዴት ሰው ለፀብ ይጋበዛል ፡፡ የተለያዩ ወጣቶች ተሰብስበው መጥተው ትዝታውን ከበቡት እንጂ አልመቱትም፡፡

ሎሚ ፡- ከእነ በጋሻውና ትዝታው ጋር ጓደኛህ ነህ ልበል
ሙሴ፡- እንደማንኛውም ሰው እቀርባችዋለሁ ምክንያቱም ወንድሞቼ ናቸው፡፡




የኛ መልዕክት
‹‹የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።
 ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።
መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።
መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።
ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ››የማቴዎስ ወንጌል 7  15-20 ተብሎ በወንጌል ተነግሮናል ሳይላኩ ተልከናል የሚሉ የበዙበት ዘመን ነውና እንጠንቀቅ፡፡

16 comments:

  1. ewenetga kehonek neseha gebetehe kedengele gare tarekehe yemejemeryawe ayente sewe hun alezya menew yemechereshahe baderegew.sewen wede telke gudeguwade kemetetelena kemetasenakel

    ReplyDelete
  2. ebakachehu bertulen angeten aresachehutal tg from canada

    ReplyDelete
  3. yaba serekese guday.endew egehen pawelosen yemfengel ande wend ethiopia teta. wey nedo ere ande aderegen medehanyalem.embachennen abesew

    ReplyDelete
  4. egiziabiher and ken yiferidal ewinet endehu tedebika atiker.

    ReplyDelete
  5. ende ahizab sew bemedebdebina bemegdel aimen ebakacihu

    ReplyDelete
  6. haha,. please . tztaw tedebdbual. I know for sure. dont lie zemari muse

    ReplyDelete
  7. ትዝታው እግዚአብሄር እንኩነ አወጣህ እነዚህ አድመኞች ናቸው ግን ምን ደርጋል ራሳቸውን ነው ያጋለጡት ሰንበት ተማሪዎች እኮ ማንሳይፈቅድላቸው ነው ከቤተክርስቲያን እውቅና ውጭ ልብሳቸውን ለብሰው የተሰባሰቡት ለአድመኞች ጉዳይ አስፈጻሚ የሆኑት ልጆቻችንን ለያሳስሩና ሊያስደበድቡ ነበር ግን አልተሳካም የቤተክርስቲን አባቶች የሚያስተዳድሩትን ቤተክርስቲያን ህዝብና ሰንበት ት/ቤት ሊያዙና ሊቆጣጠሩ ይገባል ይህ ማህበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲንን የማተራመስ ስራ ሊቆም ይገባል ድብቅ አላማው ህዝቡ አልገባውም 3ኛ ሲኖዶስ መሆን ስለሆነ አላማው ያደግሞ ሃይ ሊባል ጋባል፤፤ እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!!

    ReplyDelete
  8. ማፈሪያዎች እርስ በርሳችሁ ስትበላሉና ስትናከሱ መንጋውን ልትበትኑት ነው። ማሕበረ ቅዱሳንም ሆነ ሌላው ለኛ ሀሜትን ብቻ ነው ያስተማረን የገዛ አባቶቻችንን ስድባችሁ ለሰዳቢ ሰጣችሁብን

    ReplyDelete
  9. begashawuna tizitawum hone leloch gwadegnochachew befit yagelegelutin ageligilot asiben bintseliyilachew ayishalim?

    ReplyDelete
  10. መፀለዩስ መልካም ነው ግን ከዚህ በፊትስ ምን መልካም ነገር ሰሩና ነው ያለፈውን የምናስታውስላቸው የዘሩት እንክርዳድ ነው ስንዴው መች በቀለ …
    እኔ ግን በጣም የሚገርመኝ ሰው ወንጌልን መስበክ ሲገባው በተለሳለሰ አንደበት ሆኖ ይህንን የዋህ ሕዝብ ወደ ጉድጉድ የሚመሩት ለምን እንደሆን አይገባኝም
    አባቶቻችን በትህትና ሆነው እራሳቸውን ዝቅ አድርገው ተምረው እኛን አስተማሩ ወንጌሉንም ሰበኩ ስማቸው ሳይተዎቅ የሰበኩትን ዎንጌል ሰብከው ወንጌሉን አስተምረው አለፉ ስንዴውንም ዘሩ ምርታቸውንም ሰበሰቡ
    የአሁኖቹ ደግሞ በወንጌል ስም ዎንጌሉን ሳይሰብኩ እራሳቸውን ሰበኩ ስማቸውን በራሳቸው ከፍ አድርገው በቆሙበት መድረክ ቤተክርስቲያንን እና በጎችዋን ማተራመስ ቀጠሉ አላበዛችሁትም የሚገርመው ደግሞ ነገሩን ሁሉ አዙራችሁ አዙራችሁ ወደ አንዱ ጥቅልል አድርጋችሁ አኛን እንዲህ ያደረገ ይህ ማህበር ነው ማለታችሁ ደግሞ
    “የተሰማኝ ኩራት ነው፡፡ ሳልሰርቅ ፤ ሳላጠፋ በክርስቶስ ወንጌል ጉዳይ ሐዋርያት ስለወንጌል የከፈሉት ዋጋ የተሰማቸው ልባዊ ኩራ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ እግዚአብሔር ይቁጠርልኝ ብያለሁ፡፡” ካልክ ብሁዋላ መልሰህ የደበደበኝን ሳይሆን ያስደበደበኝን ነው የምፈልገው ማለትህ ይገርማል ሐዋርያት እንዲህ ነው እንዴ ያገለገሉት እውነተኛ ወንጌልን የሚሰብክማ እንዲህ ባለሆነ ነበር ተደብቆ ከመሹለክለክ እንደነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተወግሮ ማለፍ በቻላችሁ ነበር… ሁላችንም የሚያስተውል ልቦና ይስጠን

    ReplyDelete
  11. ምነው ልትበላው ነበር እንዴ ገፈህ የጭራቅ መንፈስ ነዋ ለብህ ምን ትተረተራለህ ማህበሩ ምን አስጠራህ መድሐኒያለም እኮ ነው ወጣው እንጂ አንተማ ጭራሽ እግዚያብሄር የሚመራው ቦታ አልመሰለህም ማጂራት ልትመታ ነበራ መጣሀው ግዳይ ልትጥል የሰራዊት ጌታ እግዚያብሄር አመለከተው ለሁላችሁም የስራችሁን ይስጣችሁ ማድላት ለእግዚያብሄር እንጂ ለማህበር አይደለም በቅርብ እናያለን የእናንተ ጉዳይ ጌታ ቅርብ ነው የሰውልጂ ሊፈተን ግድ ነውና

    ReplyDelete
  12. ምነው የመጨረሻው ዘመን ደረሰ እንዴ? እንዲህ በሆነ ባልሆነ፣ በታወቀ ባልታወቀ ጉዳይ መተራመስ በዛ እውነት እውነት እላችኋላሁ በጣም ያስጠላል፡፡ ባለው ችግር ላይ በጋራ መወያየት ሲገባ እንደው በሜዳ መተራመስ ለጌታስ ደስ ይለባዋል፡፡ ጌታ እኮ ለዚች ወንጌል ዋጋ ከፍሎባታል፡፡ ስለዚህ በጰጰሱ ስም ሳይሆን የሚባለው ስለኛ መሰዋት በከፈለው ታላቁ ጌታ ስም ይዥቼኃለሁ ይብቃ መተራመስ፡፡
    ለፔንጤ ደስታ፣ለእስላሞች ደስታ፣ ለጆባዎች ወዘተ…. ደስታ አንፍጠር፡፡

    ከታዛቢ አንዷ

    ReplyDelete
  13. ምነው የመጨረሻው ዘመን ደረሰ እንዴ? እንዲህ በሆነ ባልሆነ፣ በታወቀ ባልታወቀ ጉዳይ መተራመስ በዛ እውነት እውነት እላችኋላሁ በጣም ያስጠላል፡፡ ባለው ችግር ላይ በጋራ መወያየት ሲገባ እንደው በሜዳ መተራመስ ለጌታስ ደስ ይለባዋል፡፡ ጌታ እኮ ለዚች ወንጌል ዋጋ ከፍሎባታል፡፡ ስለዚህ በጰጰሱ ስም ሳይሆን የሚባለው ስለኛ መሰዋት በከፈለው ታላቁ ጌታ ስም ይዥቼኃለሁ ይብቃ መተራመስ፡፡
    ለፔንጤ ደስታ፣ለእስላሞች ደስታ፣ ለጆባዎች ወዘተ…. ደስታ አንፍጠር፡፡

    ከታዛቢ አንዷ

    ReplyDelete
  14. omg what the heak is this!!!

    ReplyDelete
  15. ‹‹የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።
    ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን?
    እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።
    መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም።
    መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል።
    ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ››የማቴዎስ ወንጌል 7 15-20 ተብሎ በወንጌል ተነግሮናል ሳይላኩ ተልከናል የሚሉ የበዙበት ዘመን ነውና እንጠንቀቅ፡፡

    ReplyDelete
  16. ebakahe geta hoye ande aderegen!!!!

    ReplyDelete