-
‹‹እነ በጋሻው በሚገኙበት ጉባዔ አልገኝም›› ዘማሪ ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
(አንድ
አድርገን ጥር 25 2006 ዓ.ም)፡- አቶ በጋሻው ደሳለኝና ግብር አበሮቹ ከተገለሉ በኋላ የመጀመሪያውን ጉባኤ በወላይታ ሶዶ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የስብከትና የመዝሙር መርሀ ግብር ለማካኼድ እንደተዘጋጁ ፤ በሰው
ውስጥ ያለውን የጠለሸ ስማቸውን ለማጽዳት አንድ ብለው እንደተነሱ ገልጸን መጻፋችን ይታወቃል፡፡ይሁንና በድርጊቱ ጉዳያቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ተይዞ ሳለ ሲኖዶሱ ውሳኔ ሳይሰጥበት በሀገረ
ስከታቸውና በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው ይህን የመሰለ መርሀ ግብር ለመካኼድ በመዘጋጀቱ ያዘኑት የደብሩ ካህናትና ፤ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ኃላፊዎች ስለ ጉዳዩ አሳሳቢነት ብጹዕነታቸውን ባነጋገሩበት ወቅት ብጹዕ አቡነ ማቴዎስ ‹‹ቤተ ክርስቲያኒቱ በመሰራት ላይ ስለሆነ በጋሻው ደሳለኝ ገቢ እንዲያሰባስብ እንጂ እንዲያስተምር አልፈቀድኩም›› በማለት መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡ በዚህ ጉባኤም የዝማሬ
አገልግሎት እንዲሰጥ ቀድሞ የተጠየቀው ዘማሪ ዲያቆን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ‹‹እነ በጋሻው በሚገኙበት ጉባዔ አላገለግልም›› በማለት አጭር መልስ ሰጥቷል፡፡
ብዙዎቻችን ቤተ ክርስቲያን
በረብጣ ብር መጠን ብቻ የሚሰራ የሚመስለን አለን ፡፡ መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 28 ላይ ቅዱስ ዳዊት ለእግዚአብሔር ለቃል
ኪዳኑ ታቦት ማረፊያ መስራት አስቦ እግዚአብሔር የመለሰለትን መልስ እንይ
‹‹ 1 ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉ፥ የነገዶቹንም አለቆች፥ ንጉሡንም በክፍል የሚያገለግሉትን የጭፍሮች አለቆች፥
ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆችንም፥ በንጉሥና በልጆች ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን፥ ጃንደረቦችንም፥ ጽኑዓን ኃይላኑንም ሁሉ ወደ
ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።2ንጉሡም ዳዊት በእግሩ ቆሞ እንዲህ
አለ፦ ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ፥ ስሙኝ ለእግዚአብሔር ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የዕረፍት ቤት ለመሥራት እኔ
በልቤ አስቤአለሁ ለሥራም የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ ፡፡ 3እግዚአብሔር
ግን፦ የሰልፍ ሰው ነህና፥ ደምም አፍስሰሃልና ለስሜ ቤት አትሠራም ብሎኛል። 5እግዚአብሔርም
ብዙ ልጆች ሰጥቶኛልና ከልጆቼ ሁሉ በእግዚአብሔር መንግሥት ዙፋን ላይ ተቀምጦ በእስራኤል ላይ ይነግሥ ዘንድ ልጄን ሰሎሞንን
መርጦታል። 6እርሱም፦ ልጅ ይሆነኝ ዘንድ መርጬዋለሁና፥
እኔም አባት እሆነዋለሁና ልጅህ ሰሎሞን ቤቴንና አደባባዮቼን ይሠራል።›› ነበር
ንጉሡ ዳዊት የተባለው
መጽሐፉ እንደሚነግረን ከሆነ ካለ ፍቃደ እግዚአብሔር ቤቱን መስራት አይቻልም ፤ ሕንጻ
ቤተ ክርስቲያን ለማስፈጸም ብሎ የእግዚአብሔር ማደሪያ የሆኑ ምዕመናን ላይ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ የሆነ በስህተት ጎዳና የሚያነጉድ ፤
ሰውን እንዲጠነክር ሳይሆን ያለውን እንዲጥል ፤ የቆመበትን ሳይሆን ራሱን እንዲቀይር የሚሰብኩ ሰዎችን መጋበዝ የሚታየውን እየገነቡ
የማይታየውን ማፍረስ ነውና ሊታሰብበት ይገባል፡፡ሰዎቹ ከ5 ዓመት በፊት በቤተክርስቲያን ስም በሚሊኒየም አዳራሽ ጉባኤ አዘጋጅተው
የሰበሰቡትን ከ1.2 ሚሊየን በላይ ገንዘብ ለራሳቸው ጥቅም እንዳዋሉት የሚታወቅ ነው ፤ አባ ዶ/ር ኃ/ማርያም በወቅቱ በተደጋጋሚ
የተሰበሰበውን ብር ገቢ እንዲያደርጉ በደብዳቤ በሰው ቢሏቸውም ጆሮ ዳባ ልበስ ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ አሁን እኛን እያሳሰበን ያለው
ነገር የአላፊው የብር ጉዳይ አይደለም፡፡ እኛን እያሳሰበን ያለው ስርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ወደፊት በነዚህ ሰዎች አማካኝነት ቤተክርስያን
ላይ የሚፈጠረው ሌላኛው አምቧጓሮ ብቻ ነው፡፡
እውነት ነው ወላይታ ሶዶ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እጅግ ለአይን በሚያምርና ዘመን ተሻጋሪ የሆነ ሕንጻ ቤተክርስቲያን
የአካባቢው ምዕመን ፤ ሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ እና ሰበከ ጉባኤው አንድ ላይ ሆነው እንደ አምላክ ፍቃድ እየገነቡ መሆኑ ይታወቃል ፤
ነገር ግን እስከ አሁንም እዚህ ደረጃ የደረሰው እነ በጋሻውን በአውደ ምህረት ስብከት እንዲሰብኩ መዝሙር እንዲያቀርቡ ተደርጎ አለመሆንን
መዘንጋት አያስፈልግም፡፡
ለአንዲት መርከብ መስጠም ምክንያት በአንዲት ሽንቁር የምትገባ ውሃ
በቂ ናት፡፡ ሳይታሰብ ለረዥም ሰዓታት ወደ መርከቢቱ በቀዳዳ የገባ ውሀ ከሰዓታት በኋላ የመርከቢቱን ጉዞ መገዳደር ይጀምራል ፤
በስተመጨረሻም ወደ መርከቢቱ የዘለቀው ውሃ መርከቢቱ መሸከም ከሚገባት መጠን በላይ ሲደርስ ቀስ በቀስ እያዘቀዘቀች ለባህር ጥልቀት
ትዳረጋለች፡፡ የእኛ የመሰብሰቢያችን አንድ የመሆናችን ምሳሌ መርከብ በሰው ያልተሰራች ፍጹም የማትሰምጥ ባለቤቱ የማያንቀላፋላት
ብትሆንም በርካቶች ስምጠቷን ተመኝተው ብዙ ጉድጓድ ቆፍረውላታል ፤ ክፍተቶችን ተጠቅመው ብዙ ርቀት ተጉዘውባታል፡፡
‹‹እነሆ፥ እስራኤልን የሚጠብቅ
አይተኛም አያንቀላፋምም።›› መዝሙረ ዳዊት 12፡14
እነዚህ ሰዎችም ቀድሞ ከእኛ ወገን ሆነው መስለው የታዩን ፤ በጊዜ
ሂደት ብዙ ቀዳዳ ፈጥረው ፤ ብዙ ምንፍቅና በስብከቶቻቸው ዘርተው ፤ ምዕመኑ አባቶችን አለማክበርን አለማምደው ፤ ብዙ ደጋፊዎችን
አፍርተው ፤ የተመረጠ መስዋእት የሚቀርብበትን ስፍራ የከብቶች ፍግ እዳሪ አጢሰው ፤ ፍጹም ሰላማዊ የሆነውን ምዕመን ሁለት ቦታ
ከፍለው ፤ የቻሉትን ከቤተ ክርስቲያን አስኮብልለው በአዳራሽ ሰብስበው ፤ እንደ መናፍቃን የመቅደሱ መዓዛ እጣኑ ሽታ በሌለበት ፤ ቅደሴና ሰዓታት በማይሰማበት
፤ ገድላት ተዓምራት በማነበቡበት በእንጨትና ለዝብና ለፀሀይ መከላከያ ብቻ በተለበጠ የላስቲክ አዳራሽ ውስጥ ወስደው ካበቁ በኋላ
፤ የሄዱበት መንገድ የቆሙበት ቦታ እንደማያዋጣቸው ሲያውቁ በለበጣ ይቅርታ ተመለስን አሉ፡፡
አውደ ምህረት መፍቀድና መከልከል መጀመሪያ የየአብያተ ክርስቲያናቱ የሰበካ
ጉባኤ ኃላፊነት ቢሆንም ፤ ከስርአተ ቤተ ክርስቲያን ውጪ የሆኑትን ፤ ስማቸው እና ግብራቸው በምዕመኑ ዘንድ በመልካም የማይታወቁትን
፤ ጉዳያቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ የበላይ በሆነው ቅዱስ ሲኖዶስ ዘንድ ቀርቦ መፍትሄ ያላገኝውን ሰባኪያንም ይሁን ዘማሪያን ያለማስተናገድ
መብት የሰንበት ተማሪዎች ፤ የቤተ ክርስቲያኑ አገልጋይ ካህናትና የአካባቢው ምዕመን እንዳላቸውም ልንዘነጋ አይገባል፡፡
በመሆኑም ‹‹አንድ አድርገን›› የምትሰምጥ መስሏቸው በየቀዳዳው በዛሬ
ተግባራቸው ወደፊት ቤተ ክርስቲያን ላይ ችግር ሊፈጥሩ የተነሱ ሰዎችን ፊት ለፊት በመጋፈጥ ምዕመኑ በአጥቢያው በሚገኙት አብያተ
ክርስቲያናት ላይ የራሱን ኃላፊነት ይወጣ ዘንድ መልዕክቷን ታስተላልፋለች፡፡
‹‹እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን ይጠብቅልን››
hay yichi betekiristian huuuuu
ReplyDeletenegeru yetebelashew kehadi papas teblo sishom new. "yewshet papas''
ReplyDeleteLike Mezemiran Tewodros has a good stand to keep hiself away from the Satanist group of begashaw
ReplyDeletebegashaw yemibal gileseb quchi bilo memar enji mastemar yelebetm
ReplyDeleteknow nothing. who is Like Mezemiran Tewodres? do know the meaning of Like Mezemran? how can you call him like mezemran? sham on you. you see! you are really jealous of Begashaw. believe it or not Begashaw is not Tehadso or something else he is the son of our beloved mother Church which is the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church.
ReplyDeleteWho are you to say that !!!!
Delete"Yeamlko Melk alachew, Haylun gin kidewal..." yemilew kidus kal eneho bezemenachin bemangnawm sfra, kdst betekestiyann chemero, betegbar eyayenew yalenew huneta new. Bzum rken mehed saynorbn ezih PAGE lay, lebetekrstiyanachin yaderegew astewaso endih new teblo bekelalu linegerlet yemaychalewn Megabi Hadis, Diyakon Begashaw Desalegnn... "Ato" blo metrat menfesawi negern astemralehu, asawkalehu blo kemisera Web Site yemaytebek RKASH tegbar new,... sle Begashaw hulum yemiyawkewn yawkal.... rasachihun endeferaj mayet yikrbachihu... Egzuabhern "1 Adrgen..." eyalu bekentu kemelemen, "1 lemehon, biyans kalachihubety 1 dereja rasachihun ZIK adrguna thtnnan telabesu.... Kezam 1 yemehon kurtegnnet kalachuhu... "Esme Albo Neger Zyiseano LeEgziabher..."...!!!
ReplyDelete(HB zMedhanialem, M2743)
ጐበዝ እስኪ እናስተውል
ReplyDelete