Wednesday, January 29, 2014

ከለበጣ ይቅርታ በኋላ አቶ በጋሻው ደሳለኝ ወደ አውደ ምህረት ሊመለስ ነው


(አንድ አድርገን ጥር 21 2006 ዓ.ም)፡- አቶ በጋሻው ደሳለኝ በሲኖዶስ ዘንድ ከሁለት ዓመት በፊት በአቡነ ጳውሎስ ዘመነ ፕትርክና ስለ ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ትምሀርቱ ፤ ስለ ተሃድሶ አቀንቃኝነቱ እና መሰል ጉዳዮችን በሰፊው የያዘ የድምጽ ፤ የምስልና የሰነድ ማስረጃዎች እንደቀረቡበት ይታወቃል ፡፡ ክሱ የቀረበው ከበርካታ መናፍቃንና ተሀድሶ አቀንቃኞች ጋር ሲሆን ግማሾቹ ታግደው ግማሾቹ በይደር መቆየታቸው አይዘነጋም፡፡ ክሱንም በአካል መጥቶ እንዲያስረዳ ለቀረበበት ጉዳይ መልስ እንዲሰጥ የተጠየቀው አቶ በጋሻው ጉዳዩን የማስረሳት መንገድ በመከተል የሀዋሳ ምዕመናን ባልገመቱትና ባልጠበቁት ሁኔታ ጉዳዩን ከውስጥ ሰዎች ፤ ከአባቶችና ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር በመሆን የለበጣ ይቅርታ መጠየቁ በይቅርታውም ብዙዎች እንዳዘኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ውሃ በማያዝል የለበጣ የይቅርታ ጉባኤ በኋላ ወደ አውደ ምህረት ይመለሳል ወይስ አይመለስም? የሚለው ጉዳይ በምዕመኑ ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል፡፡ አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት አቶ በጋሻው ደሳለኝ ከለበጣው የይቅርታ ጉባኤ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ግብር አበሮቹን በማስከተል ከጥር 23-25 2006 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ጦና ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የስብከትና የመዝሙር መርሀ ግብር ማዘጋጀታቸውንና ምዕመኑ ከጉባኤው እንዳይቀር ማስታወቂያ እየሰሩ እንደሚገኙ ለማወቅ ችለናል፡፡ ዛሬ ጥር 21 በተከበረው የእመቤታችን የአስተርእዮ(የእመቤታችን በዓለ እረፍት) በዓል ላይ የዕለቱ መርሀ ግብር መሪ ‹‹ከጥር 23 እስከ 25 ድረስ ታዋቂ ሰባኪያን እንደ መጋቢ ሀዲስ በጋሻው ደሳለኝ ፤ ዘማሪ ምርትነሽ እና ሌሎችም አገልጋዮች ስለሚገኙ እልል ብላችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑ ፤ በጉባኤውም ተሳተፉ›› የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

እንደ ‹‹አንድ አድርገን›› ሃሳብ ምንፍቅና በይቅርታ አይፈታም ፤ ተሀድሶያውያን ባገኙት አጋጣሚ የነበራቸውን ቦታ ለማግኝት የማይፈነቅሉት ድንጋይ ፤ የማይወጡት ተራራ ፤ የማይገቡበት ቢሮ ፤ የማይከፍሉት ዋጋ አለመኖሩን አስረግጠን መናገር እንችላለን፡፡ ይህ ጉዳይ በለበጣ በብልጣ ብልጥ እርቀ ሰላም ተፈትቷል ማለት ራስን ከማሞኝት በላይ ቤተ ክርስቲያኒቱንም አደጋ ላይ መጣል ነው ፡፡  ቤተ ክርስቲያን አንድም ሰው እንዲጠፋባት አትፈልግም ፤ ሰዎቹ ቀድሞም ከእኛ ዘንድ አልነበሩም ፤ አይን ባወጣ በክህደት ጎዳና ነጎዱ በአንድም በሌላም መንገድ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተምህሮ በማጣመም እና በመበረዝ በርካታ ደጋፊዎችን በማፍራት በርካታ ጉዳቶችን ምዕመኑ ላይ እና ቤተክርስቲያኒቱ ላይ አደረሱ ፤ የምንፍቅና እና የክህደት ትምህርታቸውን በመጽሐፍቶቸቸው ፤ በሲዲዎቻቸው እና በተለያዩ መናፍቅ መናፍቅ ከሚሸቱ ብሎጎቻቸው ማር የተለወሰ መርዛቸውን ሲረጩ ከከረሙ በኋላ ያሉበት ጎዳና የት እንደሚያደርሳቸው ፤ የቆሙበት ቦታ የት እንደሚወስዳቸው ሲገነዘቡ ፤ ‹‹እርቅ›› ብለው መጥተው ይባስ ሰውን አነደዱት ፡፡ ቤተክርስቲያን ለመናፍቅ ፤ ለከሃዲ እና ለእናት ጡት ነካሽ ይቅርታ አታደርግም አይደለም ፡፡ ነገር ግን አካሄዱ ጉዳያቸው በሊቃውንት ጉባኤ ታይቶ ፤ ስራቸው ተመዝኖና በቅዱስ ሲኖዶስ መክሮበት ከሚሰጠው ውሳኔ አንጂ በለበጣ ይቅርታ አውደ ምህረት ላይ እንዲመለሱ መፍቀድ የሚመጣው ችግር ከቀድሞ ሊብስ እንደሚችል መናገር ነብይነትን አይጠይቅም፡፡ የለበጣ ይቅርታው በ5ተኛው ፓትርያርክ ሞት የተነሳ የተስተጓጎለውን መዝገብ ዳግም እንዳይነሳ የማድረግ ሃሳብ የማስቀየስ ሥራ ነው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች አውደ መህረት የፈቀደ ራሱ ይጠየቅበት ፤ ነገር ግን በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የምትገኙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች የእግዚአብሔር ስም ዘወትር የሚጠራበትን ቦታ ለማን እንደምትፈቅዱ አስተውሉ?
 ‹‹ምንፍቅናን ይቅርታ ይመልሰው ይሆን!››

10 comments:

 1. Thanks God! Geta be betekerestianachen legelese newe. Wongel, wongel! Wongel!

  ReplyDelete
 2. ለእነዚህ ሰዎች አውደ መህረት የፈቀደ ራሱ ይጠየቅበት ፤ ነገር ግን በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት የምትገኙ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች የእግዚአብሔር ስም ዘወትር የሚጠራበትን ቦታ ለማን እንደምትፈቅዱ አስተውሉ?

  ReplyDelete
 3. የእግዚአብሔር ስም ዘወትር የሚጠራበትን ቦታ ለማን እንደምትፈቅዱ አስተውሉ? ወንድሜ ለማን ንፍቀድለት ለማህበረ ቅዱሳን? ካሁን በኋላማ ሁሉም ነገር ጎብቶብናል የተሳሰትንበት ግዜ ይበቃናል አንተና ማህበርህ በጣም መማር አለባቹ ok
  weak up !

  ReplyDelete
 4. በጋሻው እውነተኛ አገልጋይ ነው እሺ

  ReplyDelete
  Replies
  1. Geta yibarkh(sh)....

   Delete
  2. በጋሻው እውነተኛ አገልጋይ ነው እሺ

   Delete
 5. asteyayet sechiwoch, meche new iwnetegna kirsitna yemigebachihu?

  ReplyDelete
 6. እናንተ የቤተክርስትያንን ሃሳብ ሳይሆን የማህበር ሃሳብ ነው የምታራምዱት በሥርዐት ይጠበቅ ሰበብ ወንጌልን መቓወም ነው የያዛችሁት የወንጌል ጠላት ደግሞ ማን እንደሆነ እናውቃለን፡፡አይምሰላችሁ ከእግዚያብሄር ጋር ነው ዕየተጋፋችሁ ያለችሁት ትንሽ ቆምብላችሁ አስቡ በነገራችን ላይ በቅርቡ መጋቤ ሃዲስ በጋሻው ደሳለኝ ሃዋሳ ደብረ ምህረት ቕዱስ ገብርኤል ገዳም ሊሰብክ ስለሆነ እንዳያመልጣችሁ ተጋብዛችኃል፡፡እንደሚታወቀው በጋሻው ደሳለኝ ወላይታ እንደሰበከ ይታወቀል ዲላም እንደዚሁ አሁን ድግሞ ሀሀዋዋሳሳ….ቂ…ቂ….ቂ ፡፡ መቼም ቢሆን ወንጌል ያሸንፋል;;

  ReplyDelete
  Replies
  1. Abo Yeman Egziabher yibarkh... Endene Megabi Hadis Diyakon Begashaw yalutnm Fetari yabzaln...Amen...!!!

   Delete
 7. zimi bileh sew kemeketeli kiristosini teketeli,begashaw sebeke mani sebeke jst think abt yeegiihabher kali mahonuni. mk vs begashaw keminili egna maneni bileni eniteyiki megemeriya!!!

  ReplyDelete