Sunday, January 12, 2014

ሊጎበኙ የሚገባቸው መካነ ድሮች

  •    “ዘመኑ ባፈራው ቴክኖሎጂ ተጠቅመን ያዘኑትን እናጽናናቸው፤ የደከሙትን እናበርታቸው፤በአፍአ ላሉትም እንመስክርላቸው፡፡” መቅረዝ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ

(አንድ አድርገን ጥር 3 2006 ዓ.ም)፡- ከጥቂት ዓመታት በፊት በተለያዩ ሀገራት ለሚገኙ የቤተክርስቲያን ልጆች ከመረጃ ምጭነት በተጨማሪ ለመማሪያነት እያገለገለ የሚገኝው የዘመናችን የቴክኖሎጂ ፍሬ ድረ-ገጽ ነው፡፡ ቀድሞ እንደ ደጀ-ሰላም  የመረጃ ሰሌዳ ፤ እንደ ቤተ-ደጀኔ የመማሪያ አውደ ምህረት ፤ እንደተዋሕዶሚዲያ የመዝሙር እና የስብከት ቋት እና  እንደ ስንክሳር  ያሉ መካነ ድሮች ነገረ ቅዱሳን የሚለጠፉበትና ለምዕመናን በቀላሉ የሚደርስበት ወቅት ነበር፡፡ በጊዜውም በርካቶች የመካነ ድሮቹ አባላት በመሆን ዜና የሚፈልገው የዜና ገጾችን ሲዳስስ ወንጌል ፤ ስርአተ ቤተክርስቲያን ፤ ነገረ ማርያም እና ነገረ ቅዱሳን በማንበብ ውስጡን በሃይማኖት ትምህርት ማነጽ የሚፈልገውም እንደ ፍላጎቱ መካነ ድሮችን ሲጠቀምባቸው ነበር፡፡ አሁን አሁን ግን ቀድሞ የተከፈቱት በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት የመዘጋት እጣ ፋንታ በራቸው ላይ ሲቆም ሌሎቹ ደግሞ የመደንዘዝ እና ወደፊት ያለመቀጠል ነገር ይታይባቸዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የቤተክርስቲያኒቱ ጥልቅ እውቀት ያላቸው መምህራንን በመደገፍ እና በማበረታታት ወደ መካነ ድር አገልግሎት እንዲመጡ እና የማኅበራዊ ድረ-ገጽ አባል በማፍራት ዘመኑን የዋጀ አግልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ያስችል ዘንድ እውቀት ያለን በእውቀታችን ፤ ገንዘብ ያለን በገንዘባችን ልንረዳቸው ያስፈልጋል፡፡ 

ዛሬ በአዲስ አቀራረብ እና በአዲስ ይዘት ወደ አንባቢያን የመጡትን ገጾች ለአንባቢዎቻን ለማስተዋወቅ ወደድን፡፡

1.    መቅረዝ  ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ (http://mekrezzetewahdo.org)

የዚህ ብሎግ ጸሀፊ ቀድሞ ባወጣው ብሎግ አማካኝነት (http://mekrez.blogspot.com) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፤ በእንተ ቅዱሳን ፤ ስብከት ወተግሰጽ ፤ ብሂል ወምክረ አበው ፤ ነገረ ማርያም ፤ ትምህርተ ሃይማኖትንና ለህጻናት በሚሉ በተለያዩ ክፍሎች በመከፋፈል ከዲሴምበር 2011 ጀምሮ ጽሑፎቹን ለአንባቢያን ማድረስ መጀመሩን የብሎጉ ፕሮፋይል ይናገራል፡፡ ጸሀፊው የመጻፊያ ገጹን ከብሎግ ወደ መካነ ድር በመለወጥ(http://mekrezzetewahdo.org) ስርአተ ቤተክርስቲያንን የተከተሉ የበሰሉ ጽሁፎች ለምዕመናን ማድረሱን ቀጥሏል፡፡ ይህ ገጽ ከሌላው ለየት የሚያደርገው በአራት ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ ፤ በትግርኛ ፤ በኦሮምኛ እና በእግሊዘኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ስርዓተ እምነት ማስተላለፍ መቻሉ ነው፡፡ ጸሐፊው የመጨረሻ ዓመት የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪ ሲሆን አንባቢያን ይህን ገጽ ይጎበኙ ዘንድ ‹‹አንድ አድርገን›› ትጋብዛለች፡፡

2.  አትሮንስ (http://www.atrons.com፣ የዲያቆን ኤርምያስ ነቢዩ ገጽ )

የአትሮንስ መካነ ድር ባለቤት  ዲያቆን ኤርምያስ ነቢዩ ይባላል ፡፡በአሁን ሰዓት በሲያትል ከተማ ሲኖር በዚያው አካባቢ ባለው ደብረ አሚን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን እግዚአብሔር በሰጠው ጸጋ እያገለገለ ሲገኝ ከዚህ በተጨማሪ አቡን ቤት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጎንደር //ቤት አያገለገለም ይገኛል ፡፡ የአትሮንስብሎግ ዓላማ ከጸሀፊው እንደተረዳነው የተለያዩ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን ስለ ነገረ ሃይማኖት፤ ቅዱሳን፤ የቤተክርስቲያን ታሪክ፤ ቃለ መጠይቅ ማድረግና በጽሑፍም ይሁን በቪዲዮ መልኩ ለአንባቢያን ማድረስ ፤ የአብነትትምህርት ቤትን ለመርዳት የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመንደፍ አሜሪካ ውስጥ የሚገኙትን የቤተ ክርስቲያን ወንድሞችን በማስተባበር መርዳት(የተጀመረ ፕሮጀክት) ፤ እለት እለት የሚከበሩ በዓላትን በቪዲዮ ለተመልካችማቅረብ ፤ በኢ//// አስተምህሮ መሰረት ተዘጋጅቶ የሚቀርቡ የቪዲዮ ስብከቶች እና መዝሙሮችን ማቅረብ፤  ገዳማትን ማስተዋወቅ ነገረ ማርያም፤ ነገረ ቅዱሳንን በጽሑፍም ይሁን በኦዲዮ፤ ቪዲዮ ለምዕመናንማስተላለፍ ሲሆን ወደፊት “መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት” እ “ኦርቶዶክስ መልስ አላት” የሚል ፕሮግራሞችንበመክፈት የተቻለውን ያህል በመጣር ጽፎቹን ለአንባቢያን ለማድረስ እቅድ አለው፡፡

‹‹አንድ አድርገን›› ቀድሞ ጥሩ አገልግሎት እየሰጡ ሲገኙ የነበሩትን ለመካነ ድሮች Admin የቀድሞ ሥራቸውን እንዲቀጥሩ በተለያየ ሀገር እና ቦታ ለሚገኙ ምዕመናን ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ መልዕክቷን እያስተላለፈች ፤ አዲስ ሆነው በአዲስ አቀራረብ በመምጣት ላይ ካሉ መካነ ድሮች ጋር ወደፊት አብራ ለመሥራት የተዘጋጀች መሆኑን ለማስተላለፍ ትወዳለች፡፡


በመጨረሻም…….
ቤተ-ደጀኔ የአባታችን የመላከ ሰላም የቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው መካነ ድር መሆኑ ይታወቃል ፡፡ መካነ ድሩ በአገልግሎት ላይ በነበረበት ጊዜ እጅግ የበሰሉ ከሕጻናት እስከ አዋቂ ድረስ ትምህርት የሚሰጡ በርካታ ጽሁፎች በሳምንት ቢያንስ ሁለት ጊዜ ሲለቀቁ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ጀምሮ የአባታችን የአገልግሎት አውደ ምህረት አገልግቱ እንደተቋረጠ ለማወቅ ችለናል፡፡ እንደ ‹‹አንድ አድርገን›› ሃሳብ ይህ አገልግሎት ሊቋረጥ የቻለበት ምክንያት የመላከ ሰላም የቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ፍላጎት ሳይሆን መካነ ድሩ በጊዜው መታደስ አለመቻሉ መሆኑን በግምታዊ መልክ ታስቀምጣለች ፡፡ የመካነ ድር አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት እንደ መካነ ድሩ ባለቤት ፍላጎት እና ዓመታዊ የመጠቀሚያ ኮታ (MB) ብዛት የተለያየ ክፍያዎችን እንደሚያስከፍሉ ይታወቃል ፤ በጊዜው ያልታደሰ መካነ ድር በማንኛውም Search engine (like Google..) በሚፈለግት ጊዜ የቀድሞው ጽሁፍም ሆነ አድራሻ ተጠቃሚው እንዳያገኝ እንደሚያደርጉ ይታወቃል ፤ አሁንም ቢሆን ችግሩ ይህ ከሆነ ተቋማቱ ከነቅጣቱ የሚያስከፍሉት ከ100 ዶላር ያልበለጠ ገንዘብ ከፍሎ ከማስቀጠል ውጪ ሌላ መንገድ ያለ አይመስለንም፡፡ እነዚህ ድርጅቶች የተቋቋሙበት አላማ መካነ ድር አውጥቶ ለተጠቃሚዎች  በመሸጥ ዓመታዊ የማደሻ ክፍያ በማስከፈል ገቢ ማግኝት ነው፡፡ የአባታችን የመላከ ሰላም የቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው መካነ ድር ያጋጠማትን ችግር ይህ ከሆነ ችግሩን በመቅረፍ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ቀድሞ ይዞታዋ እንደምትመለስ ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ለአንባቢዎቻችን የመላከ ሰላም የቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው ሃያ አንድ በተለያዩ ጊዜ የተሰበኩ ስብከቶችን ከተለያዩ ሊንኮች በመውሰድ  እንዲህ አቅርበንዎለታል፡፡


  1.    ወዮልኝ
  2. ጸጋዬን ትቼ አልሄድም
  3. http://www.youtube.com/watch?v=SS51ByIwFAc 
  4.  በኃይማኖት ብትኖሩ ራሳችሁን መርምሩ
  5. የሚበላውን የማይበላውን አይናቀው፤ የማይበላውም የሚበላውን አይንቀፈው 
  6. ባልንጀራዬ ማነው
  7.  "ናሁ ሰናይ ወናሁ አዳም"

  8.  ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ….

  9. የመላከ ሰላም የቀሲስ ደጀኔሽፈራው አስራ ሦስት ተጨማሪ ስከቶችን እዚህ ላይ ያገኛሉ፡፡


 

No comments:

Post a Comment