Sunday, February 9, 2014

“ዳግም ልደቱ ለግእዝ” የተሰኘ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተቋቋመ


ድርጅቱ ለግእዝ ቋንቋ ዘመናዊ ሥርዐተ ትምህርት ይቀርፃል ፡፡
ቤተ ክህነትየሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ነውበማለት ተቃውማለች
• “ለቋንቋው መጠበቅ ባለውለታ በኾነችው ተቋም ታቃውሞ አዝነናል

አዲስ ጉዳይ ቅጽ 8 ቁጥር 202 የካቲት 2006
 (አንድ አድርገን የካቲት 3 2006 ዓ.ም)፡- ከጥንታዊ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የጋራ ቋንቋ አንዱ የነበረው የግዕዝ ቋንቋ ማስተማርና ማስፋፋት ዓላማው ያደረገዳግም ልደቱ ለግእዝየተሰኘ በጎ አድራጎት ድርጅት ተቋቋመ፡፡ በሥነ ልሳን፣ በሥነ ጽሑፍ፣ በሥነ ድርሳን በሥነ መለኮትና በትውፊታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአብነት ትምህርት ሊቃውንትና ምሁራን እንደተቋቋመ የተነገረለው በጎ አድራጎት ድርጅት በዐይነቱ፣በተቋም ደረጃ ከመንግሥት ፈቃድ የወሰደ የመጀመሪያው ማኅበር ነውተብሏል፡፡ ድርጅቱ ለአዲስ ጉዳይ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ዐዋጅ .209/1992 መሠረት ኢትዮጵያውያን መንፈሳዊ ቅርስ ለኾነው የግእዝ ቋንቋ ዘመናዊ ሥርዐተ ትምህርት ይቀርጻል፤ ቋንቋው እንዲያድግ፣ እንዲስፋፋ፣ እንዲዳብርና የኹሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ መግባቢያ ቋንቋ እንዲኾን ለማድረግ ይጥራል፤ ጥንታዊውን የግእዝ ጽሑፎች እንዲነበቡና እንዲመረመሩ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲያበረክቱ፣ ከትውልድ ወደ ትውልድም እንዲተላለፉ በብርቱ ይሠራል፡፡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት /ቤት በበኩሉዳግም ልደቱ ለግእዝለተሰኘው የበጎ አድራጎት ድርጅት የተሰጠው የምዝገባና የሥራ ፈቃድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 ንኡስ ቁጥር 3 መንግሥት በሃይማኖትና ሃይማኖትም በመንግሥት ጣልቃ እንደማይገባ የሰፈረውን ድንጋጌ የሚፃረር በመሆኑ ያለ ቤተ ክርስቲያኒቷ ዕውቅና የተሰጠው ፈቃድ እንዲሰረዝ ወደፊትም እንዳይሰጥ ጥያቄ አቅርቧል ተብሏል፡፡


ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሃያማኖት ድርጅቶችና ማኅበራት ምዝገባ ዳይሬክቶሬት በጻፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው የግእዝ ቋንቋ ቤተ ክርስቲያኒቱና አገሪቱ የተስተካከለ ፊደልና ቋንቋ እንዲኖራቸው ያስቻለ ብቸኛ የቤተ ክርስቲያኒቷ ቅርስ መሆኑን ገልጾ ድርጅቶችም ይኹኑ ግለሰቦች የግእዝ ትምህርት ለመስጠት የፈቃድ ጥያቄ ሲያቀርቡ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ማሳወቅ አግባብነት ይኖረዋል፤ ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈቃድና ዕውቅና ፈቃድ ሊሰጣቸው አይገባም ይላል፡፡ ድርጅቱ ይህን አስመልክቶ ከአዲስ ጉዳይ ለቀረበለት ጥያቄ ሲመልስ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ተቃውሞ የተሰነዘረው የግእዝን ቋንቋ ለዘመናት ጠብቃ በመቆየት ባለውለታና የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ዋነኛ ባለድርሻ አካል ለኾነቸው ቤተ ክርስቲያን የቢሮ እገዛ ጥያቄ በቀረበበት ወቅት ነው ብሏል፡፡ የድርጅቱ መሠረታዊ ዓላማ ግእዝን እንደ ቋንቋ ፍላጎት ላላቸው ወገኖች ያለልዩነት ማስተማር መኾኑንና ከማንኛውም የሃይማኖት ተጽዕኖና ጣልቃ ገብነት ነጻ መሆኑን ተናግሯል፡፡ ተቃውሞው የተጻፈለት የሚንስቴር መሥሪያ ቤት ጉዳዩን የሚመለከትበት አግባብነትና ሥልጣን የለውም፤ ያለው ድርጅቱ የግእዝ ቋንቋ መንግሥታዊ ዕውቅና የተሰጠው የሕዝቦች ቋንቋና የአገር ቅርስ በመኾኑ በቤተ ክርስቲያኒቱ ባለቤት የተያዘ እንዳልሆነም ተናግሯል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ድርጅቱ የተመሠረተበትን በዘመናዊ ሥርዐት ትምህርት ቀረጻው የባለሞያ እገዛ ለማድረግ ዝግጁነቱን በገለጸበት ኹኔታ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱን ፈቃዱን መቃወሙና እንዲሰረዝ መጠየቁ ፈጽሞ ያልተጠበቀ እንደሆንም ድርጅቱ ለአዲስ ጉዳይ ተናግራል ፡፡


1 comment:

  1. wey bete Kihnet??? yebetekrestiyanachin antura habtoch yehonu beketitam betezewawarim betekrestiyanin ena lijochwan yemigoda neger malete lemesale KEBERO, TSENASIL, MEKUAMIYA, TIMTIM.......etc eyaderegu yaleagbab yemicheferubetin menafikan lemin nebrete teneka balebetenete yekeber lemin atelim yehen bego yehone alama mekawemun teta. eshi Geez end Geez enditawek endisfafam endihum saytefam koyeta yakoyechiw yechiw yegna betekrestiyan nat yehen enamnalen gin gin endaysfafa mekawem gin yalebat aymeslegnim endiyawim endisfafa esuwa neberech yesenbet temehrit bet lijochwan wetatochwan hetsanatochwan sebseba mastemar yeneberebat ahun gin ene salseraw lela seraw aynet neger becha new enji lela libal aychilim. lemanegnawim bezu yebet serawoch alubin ena ensu layim enatekur elalehu. Menafekanun anid enbelachew balebet endelelew bet begna nebret sichawetubet eyayen endalayen anehun.

    ReplyDelete