Saturday, June 6, 2015

“ሃይማኖታዊ ግጭት ለማስነሣት ተንቀሳቅሳችኋል” የተባሉ የሰበካ ጉባኤ አባላት ፍርድ ቤት ቀረቡ





  •   ፖሊስ10 ቀንየምርመራጊዜጠይቆባቸዋል

   
በደቡብ ክልል የስልጤ ዞን ምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ፣ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤና የደብሩ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላትሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት ተንቀሳቅሳችኋልበሚል በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

የወረዳው ፖሊስ፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ እና በዚኽ ሳምንት ሰኞ ስድስት የሰበካ ጉባኤውንና የቤተ ክርስቲያኒቱን የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት በቁጥጥር ሥር በማዋል በቂልጦ ወረዳ ፍርድ ቤት አቅርቧቸዋል፡፡
ግለሰቦቹየድረሱልኝ ጥሪበሚልሃይማኖትን ከሃይማኖት የሚያጋጭ ጽሑፍ ጽፈው በፌስቡክ አሰራጭተዋልሲል ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል፡፡ ግለሰቦቹየድረሱልኝ ጥሪ”  በሚል ደብዳቤ መጻፋቸውን ቢያምኑም በፌስቡክ አለመልቀቃቸውን ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር በዋሉት ግለሰቦች ላይ የማጣራው ነገር አለ በሚል 21 ቀን የምርመራ ጊዜ የጠየቀባቸው ቢሆንም ፍርድ ቤቱ 10 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ፈቅዶለታል፡፡

የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሓላፊ አቶ ቶፊቅ ከድር፣ ስለ ጉዳዩ በስልክ ጠይቀናቸው፤በሕግ የተያዘ ጉዳይ በመሆኑ አስተያየት ለመስጠት አልችልምብለዋል፡፡

በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙት የቂልጦ ቅድስት ማርያም ሰበካ ጉባኤ እና ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አባላት÷ ሊቀ መንበሩ / የማርያም ወርቅ ተሻገር፣ / ሀብታሙ ተካ፣ አቶ ሙሉጌታ አራጋው፣ /ሪት ንጋት ለማ፣ አቶ ማስረሻ ሰይፈ እና አቶ ማሩ ለማ ሲሆኑ በወረዳው የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ /ቤት፣ የፖሊስ፣ የጤና እና የግብርና /ቤቶች እንዲሁም የባንክ ቅርንጫፍ ሠራተኞች ናቸው፡፡

‹‹
የድረሱልኝ ጥሪ›› በሚል ርእስ የተሰራጨውና የደብሩን የሰበካ ጉባኤ /ቤት ማኅተም የያዘው ጽሑፍ÷ በስልጤ ዞን በምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመናን፣ በሃይማኖታዊ ማንነታቸው ላይ ባለሥልጣናት ይፈጽሙብናል ባሏቸው ግፎች መማረራቸውን፣ የአምልኮ ነጻነታቸው እና ሠርተው የመኖር ዋስትናቸውም አደጋ ላይ መውደቁን ያስረዳል፡፡

ኢትዮጵያ የሃይማኖት እኩልነት የተረጋገጠባት መሆኗን በፅሁፋቸው የጠቆሙት ምእመናኑ፣ ስለሚፈጸምባቸው ግፍና ሥቃይ ለወረዳው የፖሊስ እና የሕግ አካላት በየደረጃው ቢያመለክቱም የአስተዳደሩ መዋቅር እና አሠራር ያልተገባሕጋዊ ሽፋንበመስጠቱ የጥቃቱ ስልት ዐይነት እየጠነከረ መጣ እንጂ መፍትሔ አለማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

በየመኖሪያ አካባቢያችንና በሥራ ቦታዎች እየደረሰብን ነው ያሉት እስር፣ እንግልት፣ ዛቻ፣ እንዲሁም በመ/ቤት ከደረጃ ዝቅ መደረግና መታገድ እና መባረር እየተጠናከረ መምጣቱን የገለጹት ምእምኑ፣ ድርጊቱ የተባባሰው፤ የቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ተረክበው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ የመሠረት ድንጋይ ካስቀመጡበት ከጥቅምት 24 ቀን 2007 ወዲህ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ለመንግሥት እና ለቤተ ክህነት አካላት አቤቱታቸውን ያሰሙበትየድረሱልኝ ጥሪየሚለው ይኸው ጽሑፍ፣ የሀገረ ስብከቱን ፈቃድ በመጠየቅ የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት ምእመናኑ በአንዳንድ ባለሥልጣናት የሚደርስባቸውን ሥቃይ በመዘርዘር መፍትሔ የጠየቁበት እንደሆነ ጠቁመው፤ታምኑበታላችኹ ወይስ አታምኑበትምእየተባለ ሃይማኖታዊ ግጭት እንደቀሰቀስንና የወረዳውን ስም እንዳጠፋን ተደርገን መታየታችን አሳዝኖናል ሲሉ ርምጃውን ተቃውመዋል፡፡

ቀድሞ ያስቀድሱበትና የመካነ መቃብር አገልግሎት ያገኙበት የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን 20 ዓመት በፊት መቃጠሉን ያስታወሱት ምእመናኑ፣ በምትኩ የሚያሠሩት የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኒቱ መቃኞ በመጪው ሰኔ 21 ቀን የሚመረቅ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የሃዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ የወረዳ ቤተ ክህነቱ ሓላፊዎች እንዲሁም የሰበካው ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከወረዳው አስተዳደር ጋር በጉዳዩ ላይ እየተነጋገሩበት እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በሌላ በኩል ‹‹የድረሱልኝ ጥሪ›› በሚል በፌስቡክ ተሰራጭቷል ለተባለው ጽሑፍ የታሰሩት የሰበካ ጉባኤ አባላት ማስተባበያ እንዲሰጡና መሳሳታቸውን አምነው ይቅርታ እንዲጠይቁ በማግባባት ከእስር ለማስፈታት ጥረት እየተደረገ መኾኑንም ምንጮቹ አክለው ገልፀዋል፡፡

Source :- Addis Admass

No comments:

Post a Comment