- የኢትዮጵያ ታሪክ ከሸፈ ሊባል አይቻልም ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ እኮ የተጻፈው ብቻ አይደለም ፤ ያልተጻፈ ብዙ ታሪክ አለ፡፡
- ፕሮፌሰር መርዕድ ሲሞቱ ፤ ፕሮፌሰር ታደሰ አልጋ ላይ ሲውሉ ጠብቆ የእነሱ ስራ ላይ ሂስ ማቅረብ ተገቢ አይደለም፡፡
- ደርግ እኮ ከወደቀ 21 ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ ታዲያ ለምን ከደርግ ውድቀት በኋላ መጽሀፉን ሳያሳትሙት ቆዩ? ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በምልአት ዛሬ ልትናገር አትችልም ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በአንድ ሰው እድሜ አትጨርሰውም፡፡
- የኢትዮጵያ ሕዝብ ተረድቼዋለሁ የማትለው ልዩ ሕዝብ ነው፡፡ አንድን ጉዳይ በቃ ጨርሷል ስትል ብድግ የሚል ፤ ተኝቷል ስትለው የሚነሳ ነው ፤ ከ1997 ዓ.ም በፊት የነበረውን 97 ላይ ለምንድነው ብድግ ያለው? ለሚለው እንኳን ተንትኖ የሚነግርህ የለም::
- መስፍን በቁጣ ስሜት ለኔ መልስ በማለት የጻፉት ጽሁፍ ምላሽ ያልሰጠሁት ለእሳቸው አክብሮት ስላለኝ ነው፡፡
(አንድ
አድርገን መጋቢት 5 2005 ዓ.ም)፡- በዚህ ሰሞን የብዙዎች መነጋገሪያ ከሆነው ጉዳይ ውስጥ የዲ/ን ዳንኤልና የፕሮፌሰር መስፍን
ጉዳይ መሆኑ ይታወቃል ፡፡ ፕሮፌሰሩ በ83 እድሜ ዘመናቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ያዩትንና ያስተዋሉትን በመጽሀፍ መልክ ለንባብ አብቅተዋል ፡፡ ዲ/ን ዳንኤልም ፕሮፌሰሩ የጻፉት
መጽሀፍን በራሱ እይታ ተችቷል ፡፡ ይህ ጽሁፍ መጻፉ ፤ ለሂስ መቅረቡና ሰዎች የራሳቸው አስተያየት መስጠታቸው ተገቢ ቢሆንም ጥቂት
አስተያየት ሰጪዎችና ሂስ አቅራቢዎች “ዲያቆን” የሚለውን ማዕረግ ከየት እንደተገኝ ፤ ለዲ/ን ዳንኤል ማን እንደሰጠው ያላስተዋሉ
የፕሮፌሰሩን ወይም የዲ/ን ዳንኤልን ሃሳብ ከመሞገት ይልቅ ወደ ሰዎቹ ማዕረግ እና ስብዕና ላይ ያተኮረ አስተያየት ሲሰጡ ተስተውሏል
፡፡ ፕሮፌሰር መስፍንም የፕሮፌሰርነትን መአረግ ከመሬት ወድቆ እንዳላገኙት ሁሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንም የዲያቆንነት
ማዕረግ ዝም ብሎ አይሰጥም ፡፡ ትንሽ ቢመስል ዋጋ ተከፍሎበታል ፡፡ ቤተክርስቲያን ለአንድ አገልጋይ የምትሰጠውን ማዕረግ አንቋሾ
፤ አውርዶ ፤ እንደማይገባው አድርጎ አስተያየት መስጠት “ባለቤቱን(ማዕረግ ሰጪውን) ካልናቁ ….” ነው የሚሆነው፡፡ አንድ ሰው ስለ ዲ/ን ዳንኤል በሰጠው አስተያየት
ላይ የፈለገው ማለት ይችላል ፤ ማዕረጉን ግን ከፍ ዝቅ ማድረግ ተገቢ ነው ብለን አናምንም ፡፡ ለማንኛውም የዲ/ን ዳንኤል አስተያየትን
በአንባቢያ ጥያቄ መሰረት ከላይፍ መጽሄት ላይ በመውሰድ እንዲህ አቅርበነዋል፡፡
ላይፍ፡- በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ በብሔራዊ ቲያትር ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም ባዘጋጁት ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ
ታሪክ›› በተሰኝ መጽሀፍ ዙሪያ ውይይት ተደርጎ ነበር፡፡ በውይይቱ ግምገማቸውን ከሚያቀርቡ ሰዎች አንተ አንዱ ስለመሆንህ ተነግሮ
ነበር፡፡ ነገር ግን በእለቱ በስፍራው አልተገኝህም፡፡ ምክንያትህ ምንድነው ነበር ?
ዲ/ን ዳንኤል፡- ይህንን ነገር ካነሳህው እናውራው፡፡ መቼም አንድ ፕሮግራም
መጋበዝህ ለሦስተኛ ወገን ከመነገሩ በፊት የአንተ ፈቃደኝነት ይጠየቃል፡፡ ፕሮግራምህ እንዴት ነው? በዚያ ወቅት ነጻ ነህ ወይ ? አገር ውስጥ ትኖራለህ? ተብሎ ይጠየቃል፡፡ እነዚህ ነገሮች
ግን ለእኔ አልተደረጉም፡፡ ስለ ፕሮግራሙ መጀመሪያ ደውሎ የነገረኝ ብርሀኑ ደቦጭ ነበር፡፡ እሱም ያለኝ “በፕሮፌሰሩ መጽሀፍ ዙሪያ
ውይይት ተዘጋጅቷል ከቻልክ ሄደን የሚደረገው ነገር እንመለከታለን” ነው ያለን፡፡ ከዚህ ውጪ የተነገረኝ ነገር አልነበረም፡፡ ቀኑ እየተቃረበ ሲመጣ አርብ እለት
አንድ ሰው ከአሜሪካ ደውሎ “በውይይቱ ላይ የምታቀርበውን የመጽሐፍ ግምገማ
ቀድተህ ላክልኝ” አለኝ፡፡ እኔ እኮ አልተጋበዝኩም አልኩት ፤ “ኧረ ተው መጋበዝህን ከፌስ ቡክ ላይ አይቼ ነው የደወልኩልህ” አለኝ ፤ እኔም
“እስኪ ላከውና እኔም ልየው” አልኩት፡፡ እኔም በፕሮግራሙ ጥናት አቅራቢ መሆኔን ከፌስ ቡክ ላይ ተመለከትኩኝ፡፡ ቅዳሜ ቀን አዲስ
አድማስ ጋዜጣ ላይ ስሜ ወጥቶ አየሁትኝ፡፡ የዚያን እለት የፕሮግራም አዘጋጅ ነኝ ያለ ሰው ስልክ ደውሎ ‹‹ነገ ጽሁፍ ታቀርባለህ››
አለኝ፡፡ እኔም “እንዴት ያለ እኔ ፍቃድ ስሜን በጋዜጣ በማውጣት ፈቃደኝነቴን ዝግጁነቴን ባልተጠየኩበት ሁኔታ ፕሮግራም ትይዛላችሁ?”
ስለው ብርሀኑ ደቦጭ አልነገረህም እንዴ አለኝ፡፡ ብርሀኑ ከእኔ ውጪ ከሶስተኛ ወገን ከመስማቱ ውጪ መጽሀፉን በመገምገም እንደምናቀርብ
የሚያውቀው ነገር እንዳልነበረ መጀመሪያ በደወለልኝ ቀን ከነገረኝ ነገር በመነሳት ከማወቄ ውጪ ብርሀኑ ከዚህ ወዲህ አልደወለልኝም፡፡ ሰማያዊ የሚባል ፓርቲ የዝግጅቱ አዘጋጅ መሆኑን ያወኩት ከዚያ በኋላ ነው፡፡
መቼም አንድ ፓርቲ ሰውን ሲጋብዝ በይፋ የፓርቲው ማህተብ በማስፈር እንዴት ደብዳቤ እንዲደርስ አያደርግም? ለአንድ ሰው መብት መከበር እታገላለሁ የሚል ፓርቲስ ያልጋበዘውን ሰው እንዴት እከሌ በፕሮግራሙ ላይ የጥናት ወረቀት ያቀርባል
በማለት በጋዜጣ ያስነግራል?
ለእኔ ነገሩ በጣም አስገራሚ ሆኖ አልፏል፡፡
ላይፍ፡- ‹‹መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ
ታሪክ›› በተሰኝው መጽሀፍ ዙሪያ በመጦመሪያ ብሎግህ ላይ የራስህን ግምገማ ካወጣህ በኋላ ፕሮፌሰሩን ጨምሮ የተለያዩ ምላሾች ተሰንዝሮብሀል፡፡ ነገር ግን እንዴት ጠጠር
ከወረወርክ በኋላ በዝምታ መዋጥህ ብዙዎች ከመጀመሪያው አስተያየቱ
ስህተት እንደሆነ በማወቁ ነው ይሉሀል?
ዲ/ን ዳንኤል፡- በተሰጡት ምላሾች ዙሪያ ብዙ ነገር የምለው ነበረኝ፡፡
እሳቸው እንዳሉት ሳይሆን መጽሀፉን በደንብ አድርጌ አንብቤዋለሁ፡፡ እንኳን አነስተኛ የገጽ ብዛት ያለው መጽሀፍ ይቅርና ብዙ ሺህ
ገጾች ያላቸው መጻሕፍት አነባለሁ፡፡ ከመጽሀፉ ያወጣኋቸው ሁለት ነገሮች
ነበር፡፡ አንደኛ ታሪክ አይከሽፍም፡፡ ምን ማለት ነው? ለምሳሌ እኔ ይህን ቢሮ ለመስራት እቅድ ነበረኝ ፤ ነገር ግን አልሰራሁትም ከሸፈ፡፡ ይህ የቢሮ ክሽፈት ተብሎ ሊነገር
አይችልም፡፡ ክሽፈቱ የዳንኤል ቢሮ ሊባል ግን ይችላል፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ታሪክ
ከሸፈ ሊባል አይቻልም ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ እኮ የተጻፈው ብቻ አይደለም ፤ ያልተጻፈ ብዙ ታሪክ አለ ፤ የኢትዮጵያ ታሪክ የክሽፈት ምሳሌ ሊሆን አይችልም፡፡
በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ እኮ የአክሱም ስልጣኔ ፤ የላልይበላ የመሳሰሉት
ይገኛሉ፡፡
ሌሎቹ ፕሮፌሰሩ የጠቀሷቸው የታሪክ መጻሕፍት ናቸው፡፡ የታሪክ ጸሀፍቱ
መጻህፍቱን ከጻፏቸው 41 ዓመታት ያህል ተቆጥረዋል፡፡ ፕሮፌሰር መርዕድ ሲሞቱ ፤ ፕሮፌሰር ታደሰ አልጋ ላይ ሲውሉ ጠብቆ የእነሱ
ስራ ላይ ሂስ ማቅረብ ተገቢ ነው? ከእነዚህ ሰዎች ጋር ለዓመታት አብረው የነበሩ ሰው ጊዜ ጠብቀው ይህን ማድረጋቸው
በእኔ አስተያየት ትክክል አይደለም፡፡ ፕሮፌሰሩ መጽሀፍቱን በደርግ ዘመን ነው ያዘጋጀሁት በማለት በብሔራዊ ቴአትር መናገራቸውን
ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡መጽሐፉን ለማሳተም ሳንሱር ቢያስቸግራቸው እንኳን የጥናት ወረቀቶቹን በተለያዩ
መድረኮች በማቅረብ እነ ታደሰን መሞገት ይችሉ ነበር፡፡ ደርግ እኮ ከወደቀ 21 ዓመታት ተቆጥሯል፡፡ ታዲያ ለምን ከደርግ ውድቀት
በኋላ መጽሀፉን ሳያሳትሙት ቆዩ? መስፍን በቁጣ ስሜት ለኔ መልስ በማለት የጻፉት ጽሁፍ ምላሽ ያልሰጠሁት አንደኛ ለእሳቸው
አክብሮት ስላለኝ ነው፡፡ ወደድንም ጠላንም በዚች ሀገር ታሪክ ውስጥ የራሳቸውን አሻራ አኑረዋል፡፡ በዚህ ላይ በአደባባይ ከሚናገሩ
ጥቂት ምሁራን አንዱ መሆናቸውን ከግምት በመክተት ነገሩን በዝምታ ማለፍ መርጫለሁ፡፡ አንዳንድ ሰዎች ለፕሮፌሰሩ ምንም ምላሽ አትስጥ
በማለት ምክራቸውን ለግሰውኛል፡፡
ላይፍ፡- ፕሮፌሰሩ በዋናነት “ቤተ መንግሥቱን”
አየሁት በማለት በሰጠህው ምስክርነት ተበሳጭተዋል፡፡ የማላውቀውን ዶክተር በመጥቀስ ነገሩን ሌላ ትርጉም እንዲይዝ አድርጓል ብለዋል፡፡
ዲ/ን ዳንኤል፡- የጠቀስኩትን ታሪክ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያውቁት ስድስት
ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡ ከስድስቱ ሰዎች በአሁኑ ወቅት በህይወት የሚገኙት ፕሮፌሰሩና መንግስቱ ኃ/ማርያም ብቻ ናቸው፡፡ የዶክተሩን ስም መጥቀስ ያልፈለኩት ዶክተሩ በህይወት ስለሌሉ ነው፡፡ ይህንን
መናገር ድብትርና የሚል ትርጓሜ አያሰጥም፡፡ እኔ ለድብትርና አልበቃሁም፡፡ ዮፍታሄ ንጉሴ የጻፈውን ካነበባችሁ ድብትርና ትልቅ ማዕረግ
መሆኑን ትገነዘባላችሁ፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ይህን ሹመት የሚሰጡ በሆኑና በተቀበልኳቸው ደስታውን አልችለውም፡፡
ላይፍ፡- ፕሮፌሰሩ የኢትዮጵያ “ታሪክ
ከሽፏል” ካሉባቸው ነጥቦች አንዱ የአገሪቱ የስኬት ታሪክ መቀጠል ባለመቻሉ ነው፡፡ ለምሳሌ የአክሱም ሃውልትና የላበላ ውቅር
አብያተክርስቲያናት የሰራ ህዝብ እንዴት በደሳሳ ጎጆ ይኖራል ? ይላሉ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ሕዝቤን አላወግዝም በማለት ራሳቸውን ለጥይት
የሰጡላት አገር እንዴት ጠዋት የሚናገሩትን ለማታ መድገም የማይችሉ አባቶችን ታፈራለች ? በማለት ክሽፈቱ በሁሉም የታሪክ አውድ
መኖሩን በመጥቀስ ይሟገታሉ፡፡
ዲ/ን ዳንኤል፡- የኢትዮጵያ ታሪክ በአንድ ሰው እድሜ በሚደረግ ጥናት
የሚደረስበትና ከሽፏል የምንለው አይደለም፡፡ የአክሱም ሀውልት ወይም የአቡነ ጴጥሮስን አይነት የሞራል አርአያ ማጣታችን የታሪካችን
ቁንጽል አካል ነው፡፡ ይህንን በማንሳት ብቻ ታሪካችንን ከሽፏል ማለት
ተገቢ አይደለም፡፡
ላይፍ፡- ፕሮፌሰር መስፍን እኮ አንድ ያልከሸፈ የኢትዮጵያ ታሪክ ለማግኝት አልቻልኩም ነው ያሉት?
ዲ/ን ዳንኤል፡- አልፈለጉም፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ በአንድ ሰው እድሜ
እንደማትጨርሰው ተነጋግረናል፡፡ ምናልባት የምናውቀው የመካከለኛውንና የሰሜን ኢትዮጵያን ጉዳይ ነው፡፡ ብዙ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ያልተዳሰሱ
ጉዳዮች ደግሞ አሉ፡፡ ስለ ኢትዮጵያ ታሪክ በምልአት ዛሬ ልትናገር አትችልም፡፡ በነገራችን ላይ እንደ ባለሙያ ሁሌም መጠንቀቅ
ያለብን ስለ አንድ ነገር በምልአት ልታውቅም ልትደርስበትም አትችልም፡፡ ስለዚህ ይመስለኛል ፤ ሊሆን ይችላል ፤ እገምታለሁ ትላለህ
እንጂ እርግጠኛ ልትለው የምትችለው ነገር በጭራሽ የለም፡፡ ያውም እንደ ኢትዮጵያዊነት ውስብስብ በጣም ብዙ ባህሎች ያሉት ህዝብን
በዛ ደረጃ ማስቀመጥ ትክክል አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተረድቼዋለሁ የማትለው ልዩ ሕዝብ ነው፡፡ አንድን ጉዳይ በቃ ጨርሷል
ስትል ብድግ የሚል ፤ ተኝቷል ስትለው የሚነሳ ፤ ከ1997 ዓ.ም በፊት የነበረውን 97 ላይ ለምንድነው ብድግ ያለው? ለሚለው እንኳን
ተንትኖ የሚነግርህ የለም::
ጽሁፎቻቸውን መሰረት አድርጋችሁ ብቻ አስተያየታችሁን ስጡ
ቸር ሰንብቱ
Both of you are respected and real Ethiopians please forgive each other,I believe no one is happy to hear any negative comment unless devil. we learn a lot what being Ethiopia means from Professor Mesfin and Deacon Daniel in different angles but the same spirit. Don't forget no one is perfect except God.
ReplyDeleteI am bagging you in the name God to listen,learn and forgive each other.
በኔ ግምት ግን ፕሮፌሰሩ ከዲ/ዳንኤል ክርክራቸውን ያራዘሙት ባጋጣሚው መጽሐፋቸው ትኩረት ኢንዲያገኝና ኢንዲነበብ ሰው ሁሉ ምንድን ነው ኢያለ ኢንዲመራመርና ኢንዲያነብላቸው ነው ለመንፈሳውያን ወንድሞችና ኢህቶች የምመክረው የህይወት ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ከ 40 ጊዜ በላይ የተነገረላት አገር መክሸፍ የሚል ቃል የማይመለከታት አገር ናትና ጊዚያችንን በደራሲያን የማስታወቂያ ጥበብ አናባክን ያገር ገደብ ለሌለባት ሃይማኖታችን ጠንክረን ጸንተን በመስራት ራሳችንንም አገራችንንም እናድን።
ReplyDeleteየሁለቱም ሰዎች ተማሪነኝ:: ሁለቱንም ከሚያመሳስላቸው ነገሮች መካከል የአደባባይ ጸሐፍት መሆናቸው ነው:: ይህ ማለት ሁለቱም ለሕዝብ ለሀገር የተቆርቋሪነት ስሜት አላቸው ማለት ነው:: በመሆኑም መልካም የመሰላቸውን ሁሉ በአደባባይ የሚያደርጉ በመሆኑ ለትችት የተጋለጡ ናቸው:: ደጋፊም ነቃፊም አያጣቸውም:: በዚህ መሀል ካለን አንባብያን የሚጠበቅ የሚመስለኝ ይህን መሰል የአደባባይ የክርክር መድረኮች እንዲያብቡ በጎ ሚና መጫወት ነው:: በተለይ የምንሰነዝራቸው አስተያየቶች የታረሙ ሊሆኑ ይገባል:: ፖለቲካችንም ከደጋፊነት ስሜት አልወጣ ያለው ከሚሰነዘሩት ሀሳቦች በላይ የኛ የምንላቸው ሰዎች ተነኩብን በሚል የምንቧደነው ቡድን መሆኑን ያስተዋልን አይመስለኝም:: በሁለቱም ሰዎች ወገን ተኩኖ የሚሰነዘሩ አስተያየቶችን ልብ ይሏል:: ሀሳብ ላይ ብናተኩር ግን የሚልቀውን ለመምረጥ ባልተቸገርን፣ ላመንበት መገዛትን በለመድን፣ የለውጥ ጊዜም ባጠረ ይመስለኛል::
ReplyDeleteእናንተ ግን እንኳን ተጻጻፋችሁ እኛ ብዙ ገብይተናልና:: አስነዋሪ ነገሮች የምንላቸውን ነቅሰን ለማውጣት ያን ያህል የምንቸገር አድርጋችሁ ባትገምቱን ጥሩ ነው:: እናም ጻፉ ክፉና ደግ ለይተናል አጥንት መጋጥም ጀምረናልና ያን ያህል ባትጨነቁ ጥሩነው ጻፉ:: ተወራርፋችኋል ያም የየራሱ ደርዝ ያለው በመሆኑ የእይታችሁን ጥልቀት ከመናገር ያለፈ ማንነታችሁን ያቆሽሸዋል የሚል ሥጋት የለኝም:: ያም ሆነ ይህ እናንተን ዱላ አያማዝዛችሁ እንጂ ክርክራችሁን ወድጄዋለሁ:: በመሀላችሁ ገብቼ ያን እንዲህ ብትለው ያን ባይናገሩ ካልኩ የጠላችሁት ሴንሰር ሺፕ መጣ ማለት አይደለ:: ስለዚህ ይህን አልልም::
እስኪ በየገጻችሁ ተሟገቱ ለምትሉት ሁሉ ሚዛናዊና ምክንያታዊ ሁናችሁ ሀሳብ ተወራወሩ:: የሀሳብ ጦርነት ተሸናፊን የማያንኳስስ አሸናፊንም ሳይገድል ያሸነፈ አርበኛ የሚያደርግ የሰለጠነ መሣሪያ ነው:: ለማሸነፍ ሁሌም በተቃራኒ ወገን መቃብር ላይ መቆም የለብንም:: ሌላው ተዋርዶ ካላየን እኛ የከበርን ካልመሰለን ከዚህ በላይም "ክሽፈት" አይኖርም:: ተነጋግረን ስንጨርስ በሀበሻ ወግ ውሳኔውን ለምንወደው ሕዝብ እንስጥ:: ለሀገር ለወገን ይበጃል የምንለውን የምንሠራ ሰዎች ሌላኛውን ገዳይ ፣ አጥፊ፣ ዘራፊ፣ የማይረባ፣ ወዘተ አድርገን ካላቀረብን እንዴት የኛ ተቀባይነት አይኖረውም የሚል ሊሆን ይችላል? የእኔ በዚህ በዚህ መንገድ የተሻለ ነው፣ በፍጥነቱ፣ በተደራሽነቱ፣ በአገልግሎቱ፣ እያልን በጥቅም መዝነን ልዩነታችንን ማሳየት የምንጀምረው መቼ ነው? ለመምረጥ ከተቸገርንባቸው ነገሮች አንዱ ይህ አይመስላችሁም:: ያልታጠበ ቡና ከነገረፈቱ ለሕዝብ ሲታደል እግዜር ያሳያችሁ? ዓለም እኮ ዱቄቱን እንኳ ማሳየት አቁማለች:: ብዙ ክርክር በተለያዩ መንገዶች በተመረጡ አርእስት እንጠብቃለን::
አቅልሉት እንጂ መምህራነ ኢትዮጵያ!
አክባሪያችሁ ከሰሜን አሜሪካ!!!
I am not trying to be funny but, these two individuals look so much alike on their pictures they can pass for father and son :-))
ReplyDeletefirst of all I appreciate D.Daniel for the respect you have shown to pro.Mesfin.We know he is the one who shaped the minds of Ethiopians children.
ReplyDeleteSince we have scant attention to our heroes,we always defame them.Please let us
change this insignificant attitude and help each other to learn more from the one who has got knowledge and experience.
I used to like and admire Dn. Daniel very much. I still love to listen to his preachings. However, here, it seems that he is the one who is on the losing side of the argument. He has not adduced any credible evidence or convincing argument to discredit the proffessor's points. It appears that he is merely appealing to the readers' emotion and wrongly held belief that we Ethiopians are unique people with unique history.
ReplyDeleteየተወደዳችሁ አንድ አድርገኖች በቅድሚያ ሰላምታየ ሳላውቃችሁ ካላችሁበት ይድረሳችሁ። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን። የብሎጋችሁ ተከታታይ ነኝ የምትለጥፉት ነገር አምልጦኝ አያውቅም አስተያየት ከመስጠት ግን በጣም ቁጥብ ነኝ። አልፎ አልፎ በደጀ ሰላም አስተያየት እጽፋለሁ እንደ እድል ይመስለኛል አያወጡልኝም። አስተያየቴ አይጥማቸውም መሰል። ወይም ቁም ነገር የሌለው ሁኖ ይሆናል። እስኪ እናንተንም ልሞክራችሁ?
ReplyDeleteወደ አስተያየቴ ስገባ በቅድሚያ ፕሮፌሰር መስፍን በጣም የማከብራቸው ሰው ናቸው ዲ. ዳንኤልን ከማድነቅም በላይ ሳያውቀኝ እንደ ወንድም እቆጥረዋለሁ። ወንድም የግድ በስጋ መወለድ የለበትም አይደል? ታዲያ ለወንድሜ የምለግሰው ምክር ቢኖረኝ ከሁሉም ስራዎቹ ለፕሮፌሰሩ መጽሐፍ የሰጠው ትችት ደረጃውን የጠበቀ አልነበረም። ሌሎች ሰዎች ትችታቸውን አቅርበዋል አቀራረባቸው እጅግ ላቅ ያለ ነበር ትችታቸውን ከመጽሐፉ ክፍሎች እያንዳንዱን ነገር እያወጡ በራሳቸው አረዳድና ግንዛቤ ተችተዋል። እኔም በማንበብ ተጠቅሜአለሁ። የወንድሜ የዲ. ዳንኤል ትችት ያኔም አሁንም የሚናገረው ታሪክ አይከሽፍም ከመፈክርነት ያለፈ አይደለም። ላለመክሸፉ እሳቸው ያነሷቸውን ጭብጦች እያነሱ በደንብ መሞገት ይገባል። አለበለዚያ የኢትዮጵያ ታሪክ የተጻፈው ብቻ አይደለም፤ በህይወት የሌሉትን መውቀስ አይገባም የሚሉት ነገሮች ሁሉ አንባቢ ብቻ ለሆን ሰዎች አያረካም። ይልቁንም ካልተጻፉት መካከል በማውጣት እንደማይሞት በማሳየት ብቻ ነው መሞገት የሚገባው በማይጨበጡ ቃላቶች ግን ትችት ማቅረብ አይገባም። በመሆኑም ክርክሩን ከማቆም ወደ ሚጨበጥ ትምህርት በሚሰጥ መልኩ መቀጠል ከቻልክ ብዙ እንማርበታለን አለበለዚያ አሁንም ወንድሜ ዲ. ዳንኤል ተጨማሪ ስተት ከመስራት ማቆሙ ይሻላል።
ተጨማሪ ስተት ያልኩት የደብተራን ትርጉም መጽሐፍ ጠቅሶ ለፕሮፌሰር መስፍን መናገር "ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ" የሚሉት አይነት ነው። እርግጥ ደብተራ በትርጉሙ ለአዋቂ ሰዎች የሚሰጥ ትልቅ ማረግ መሆኑን ፕሮፌሰር መስፍን የማያውቁት ነው ብሎ ለማሰብ አይቻለኝም። እንግዲያውስ ፕሮፌሰርነት አይገባቸውም። እኔ "የደብተራ ተንኮል" የሚለውን ሳነብ የደብተራ ትልቁን ትርጉም ሳይሆን ለደብተራ በህብረተሰቡ ዘንድ ትክክልም ባይሆን ዘልማዳዊውን አገላለጽ ተጠቅመው እንደሆነ ጥርጥር የለኝም። ወንድሜ ዲ. ዳንኤልም እንደዚህ ካልተረዳኸው ወይ የዋህ ነህ አለበለዚያ ግን አሁንም ገብቶህ እያለ ሃኬትን ታደርጋለህ። ሰው በእውነት ብቻ ነው መኖር ያለበት። ደብተራ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚያገለግል አዋቂ ቢሆንም አብዛኞቹ ደብተራዎች በተንኮል ይታወቃሉ በዚህም የተነሳ በህብረተሰቡ ዘንድ ደብተራ ሲባል አብሮ የሚታሰበው አስማትና ተንኮል እንዲሁም ሸር ነው። ሸር ደግሞ ከደብተራዎች ላይ ሲሆን ከበድ ይላል ምክንያቱም ጥፋቱን እያወቁ የሚያደርጉት ስለሆነ ነው። ለማንኛውም ሁላችንንም እግዚአብሔር ከእውነት ጋር ያስታርቀን።
ሌላው ስተት ሰውን በሞራል መሞገት ነው። በህይወት የሌለን ሰው መሞገት በሞራል አይገባም ማለት አይቻለም። ለምሳሌ ከታሪክ ማህደር በ1983/4 ከሆነው በማለት ከወራቶች በፊት አቡነ ዜና ማርቆስ ለአቡነ መርቆሪዎስ የጻፉትን ደብዳቤ አውጥተህ ነበር። ይህም በደብተራ ተንኮል በምዕመናን ትዝብት ውስጥ ለመጣል ነበር። ታዲያ እኔ ያንን ያየሁ ጊዜ እውነትም ቢሆን አኒህን ሰው ከመቃብራቸው ቢያሳርፋቸው ምን አለ ብየ በሆዴ ታዘብኩ። ታዲያ ለዲ. ዳንኤል የሚሰራ ሞራል ለፕሮፌሰር መስፍን እንዴት አይሰራም? ሙትን በሚገባው መውቀስ የማይቻል ከሆነ እንዴት እኛስ? ሞራል ከባድ ነገር ነው የማያውቀውን ሞራል ያመጣል ሲሉ እኔ እንዲህ ነው የተረዳሁት። ባህታዊ አምሃ በቅርቡ ከተናገሩት ያስቀረሁት ትልቅ ነገር "የኢትዮጵያ ህዝብ እውነትን ያውቃል ግን አይናገርም ሃሰትንም ያውቃታል ግን በግልጽ አይተችም" ያሉትን ነው። በልቡ በሚመዝን በዚህ ህዝብ ፊት ታዋቂ ሰዎች ቀላችሁ እንዳትገኙ እግዚአብሔር ይርዳችሁ። እኛ አንባቢዎች ቀላል አይደለንም ያምናውን ተረት ከአሁኑ ጋር እየመዘን ሁሉንም እየታዘብን እንቀጥላለን....
ዳንኤል ክብረት የቤት ስታውን ሰርቷል ወያኔ ያስቀመጠው በድቁናው ሳይሆን በሰላም አምባሳደርነቱ ስለሆነ አቶ እያሉ ቢጠሩት ተገቢ ነው
ReplyDeleteየአዋቂ አባትና ልጅ የሚራመዱበት ጉልበት አንድ ነዉ ጉዞቸዉ ባንድ ሃሳብ ባንድ አቅጣጫ ነዉና ስለዚህ.......
ReplyDeleteDani Debetera malete min ayenet maereg newu?
ReplyDeleteBless your heart dear deacon daniel I really admire your patience.
ReplyDeleteKeep it up! You are a man!
Dear Anonymous, I don't think they are in the same spirit. Even though Prof.Mesfin is not religious, his moral value, integrity, love for truth and the country is very unique and unwavering. In contrast Daniel (from his writings and interviews in recent days, he is superficial and not firm on issues) don't have the moral, integrity; he also speaks without appropriate knowledge...I know the appropriate meaning of Debtera. But in professor's writing what i understand, Debtera means who want to be believed by hiding something and create some secrete ( ewuketin mithatawi mistir bemadreg medemet yemifeligu) LE ZEMENAT HAGER YADENEKORU NACHEWU. They were and they are the problem of the church. I don't mean the real DEBTERA in old meaning. Debtera is also who doesn't fulfill the criteria for the full priesthood...not qualified to be priest (yaferesu). Daniel should read the book in good spirit again. It touches the real problem of the country. Daniel erasu yekeshefe menfesawi sebaki tsehafi endayihon?!
ReplyDeletethanks Dear, Daniel is on the way to 'mekishef' he is so selfish!
DeleteI think Daniel only wants to appeal for the emotion of the readers without credible point...this may help to convince those with simple heart with out evidence. As educated please argue on the points.
ReplyDeleteይገርማል!
ReplyDeleteሃሳብን በሃሳብ መሞገት ብስለት ሆኖ ሳለ ስብዕናን የሚነኩ፣ የማያንጹ ቃላትን በመወራወር ጀግንነት የሚመስላቸው እልቆ መሳፍርት መኖራቸውን ነው ከቃለ ምልልሱ የተረዳሁት!
ዲያቆን ዳንኤል ለፕ/ር መስፍን አንድ ውለታ የዋለላቸው ነገር ምንድን ነው- መጽሃፉ ተነባቢ እንዲሆን ማሳለጡ! ነገር ግን ብሎጉ ላይ በብዛት በሚጽፋቸው የማህበረሰቡን ገጽታ ትችት ላይ ያተኮሩ አንኳር ጉዳዮች (አንዳንዴም ተራ)፣ ያለንን ማበርታት ሳይሆን የሌለንን እንዲኖረን ማስመኘት፣ ሃገር ቤትን ሳይሆን የሰለጠነውን ዓለምን ለኑሮ መመኘት፣ ሌሎች ሁል ግዜ ከኛ የተሻሉ መሆናቸውን እንጂ የምንሻልባቸው ጉዳዮች እምብዛም እንዳልሆኑ የሚያሳዩ፣ ተሽሎ መገኘትን ከሰማይ የወረደ ጸጋ ወይም በተአምር የሚገኝ እንጂ በልፋት፣ በጥረት እንዳልሆኑ ሹክ የሚሉ ሆነው መገኘታቸው ‹የታሪክን ክሽፈት› በሌላ አገላለጽ የሚናገር ሆነው የሚታዩት፡፡ እናም በሁለቱም መካከል ያለው እሰጥ አገባው በራሱ የከሸፈ ያስመስለዋል፡፡ አንድ ቦታ ያነበብኩት ጽሁፍ ሁሌ ትዝ ይለኛል- ደራሲነት ከውስጥ የመነጨ ክህሎት ካልሆነና ተምረው ያገኙት ከሆነ ሒሰኛ ከመሆን ወደኋላ ማለት አይቻልም፡፡ ግና ግን ነገሩ ካንድ ወገን ብቻ የያዘውን መረጃ ሳያጣሩ ያውም የድርጊቱ ተካፋይ የሆኑት በህይወት እያሉ- ምናለ ፕ/ሩን ሁኔታውን ጠይቆ ሂሱን ምሉዕ ባደረገው ያሰኛል፡፡
Ato Danniel; starting before you were in the mind of your parents if your parents are as old as Proff. Mesfin ( I doubt it)he was struggling for freedom in Ethiopia. He is few of the scholars who was conscious enough to understand what is going on in Ethiopia in the past three governments . In all of them he was considered as enemy because of were he stands. Proff. Mesfin is an accomplishes world renowned professional whom is said to be nobody knows better than him in his field of specialization now may be for generations to come. May be he is one of those people who appear ones in a century. Having Said this about Proff. Mesfine. Let us come to you; Who are you Ato Daniel? , really tell me who on Earth are you to say a single word about HIM ? I know that your communication skill is very good . Because of that there are many MK members who adores you respects you and idol you and other Orthodox followers respect you because of our relegion and for love of God . Most of us (Ethiopians) are hero worshipers . Everybody admires hero's but we don't have limit for it because of that our hero/hereon spoiled.
ReplyDeleteTrust me if there was any thing wrong it wouldn't have been you who criticize him it would have been others who understands him better than you do. I am sure what happened is you didn't understand what he has written because it is beyond you do comprehend, Don't feel inferiority a smart man with this extensive knowledge and incomparable years of scholastic can write any thing.
What is not good is even if you will be luck enough to live like him I am sure you don't understand him he is the smartest guy you ever know.
I want to conclude my points in Amharic you understand it better and I say my mind the same : አንተን በሳቸው አይን ሳይህ የምትመስለኝ ሰፈር ውስጥ ያሉትን እረኛ ጉአደኞቹን በሆነ ነገር የሚያስደንቅ እና እነኛ ጉአድኞቹ ሊቁ እያሉት የሚያደንቁት እረኛ ማንነቱን ሳያውቅ በሰፈር በስራቸው በውቀታቸው በልምዳቸው በአልም ላይ አሉ ይህንን ጠንቅቀው ያውቃሉ የሚባሉ አዛውንትን የሰፈሩ ሰው ስልሆኑ ብቻ አግኝቶአቸው እስቲ በውቀት እነለካካ ያላቸው ይመስለኛል፥፥ አቶ ዳንኤል የምትጽፍበት ቦታ ላይ የሚያነቡት ሰዎችም ያው _____ ስልሆኑ አድናቂ አታጣም ፥፥
Diakon Daniel yemiyawkewn ewnetegna neger lemenager befrat wst yale sew new....diakon Daniel yawkal gin yemiyawkewn sayhon yemayasmetawn yamaytekabetn neger bcha new yeminagerew.....profesor msfin point is real and exact.
ReplyDeleteፕሮፌሰር ምን ነካዎት በቅድሚያ የአይኖን ጉድፍ ሣያወትጡ የማይመስል ነገር መናገሮ ይገርማል እንኳን የኢትዮጵያ ታሪክ እርሶም የሠሩት ታሪክ፤ ባይኖርም!!! ለትውልድ ስሞ መነሳቱ አይቀርም በተቻለ መጠን ቆም ብለው ከኔም ቦኃላ ታሪክ ሠሪ ይነሳል ብለው
ReplyDeleteፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያምን ለመክሰስ ብቻ አንድ የዳንኤል ጀሌ ያላሉትን ከመጸሐፍ እንዳገኝ አስመስሎ ጽፏል:: ይህ እውነት ነው ወይ?
ReplyDelete‘’ሥልጣን ባህልና አገዛዝ ፖለቲካና ምርጯ ‘’ እና ‘’የክህደት ቁልቁለት ‘’ በሚሉ ርእሶች ፊት እና ጀርባ አትመው ሰሞኑን ለንባብ ባበቁት መጽሐፍ ገጽ 33 የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን ላይ የሚከተለዉን አሳብ ሰንዝረዋል አስተያየቶ ምንድን ነው?
“የኢትዮጵያ ቤተ ክርስትያን በምሥጢሮች የታፈነች ናት : የእምነት መሰረትን ለመጣል ተብሎ የሚደረገው ማስፈራራት ሁሉ በዘንዶና በገሃነመ እሳት የሚያሰቃይና በሙሉ ሰውነታች ን ፍርሃት እንዲሰርጽ እየራድን ሰውነታችን እንዲፈርስ የሚያደርግ ነው: የማይደበቀዉን ለመደበቅ የማይመስለዉን ለማስመሰል የሚደረገው ጥረት ሁሉ የራስን የማስተማርና የማሳመን ጉድለት ለመሽፈን ሳይሆን አይቀርም : አብ :ወልድ : መንፈስ ቅዱስ ሦስት ብሎ ለማሳመን የማይቸግራቸው ሰዎች ወይም ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ያላባት ተወለደ ብለዉ የሚያስተምሩ ሰዎች ሥጋ ወደሙ የሚባለው ኅብስትና የወይን ጭማቂ መሆኑን ግልጥልጥ አድርጎ ለማስተማር በጣም ይቸገራሉ : ጥረቱ ሁሉ በመቅሰፍት በማስፈራራት ጭፍን አማኝ ለማድረግ ነው: በዚህ የተነሣ ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ ችግር አልተፈጠረም የሚል አለ?” . . .
http://tesfabelaynehh.blogspot.de/2013/03/blog-post.html?spref=fb
ReplyDeleteበመንገድ መጽሐፍ ቅዱስ ወድቆ ያገኘ አንድ ሰው ባጋጣሚ ሲገልጥ ማቴዎስ ሃያ ሰባት ቁጥር አምስት ላይ “ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።” የሚል ንባብ ያገኛል:: ገለጥ ያደርግና ደግሞ አይኑን ወርወር ያደርጋል:: ሉቃስ አሥር ቁጥር ሰላሳ ሰባትን ያነባል:: ምንባቡ “ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ” ይላል:: በዚህ ምክንያት ለካ የጣሉህ በዚህ ተግባርህ ነው ብሎ ጠቃሚውን የሕይወት መጽሐፍ ጥሎት ሄደ:: ቃላት የሀሳብ መግለጫ ናቸው እንጂ በምልአት አንድን ሁነት የሚያሳዩ አይደሉም:: ምስል ከሳች አድርገን ብንጻጽፋቸው እንኳ ብዙ የሚያጎድሉት አላቸው:: የአንድን ጽሑፍ ዓረፍተ ነገሮች በመነጠል የምናየው ከሆነ ከአውድ ውጪ ይሆኑና ለግልብ ትርጉም የተጋለጡ ይሆናሉ:: በዚህ መንገድ የማይጋጨውን መጽሓፍ ቅዱስ እንኳ ልናጋጨው እንችላለን:: በዚህ መንገድ ስህተት የማይሆን ነገር ፈልጎ ማግኘት የሚያስቸግር አይመስሎትም?
ReplyDeleteTadiya yan hulu korto ketel tsehuf ena cd endet serachehu?
ReplyDelete