(አንድ አድገን የካቲት 26 2005 ዓ.ም)፡- ባሳለፍነው እሁድ የኢትዮጵያ
ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 6ተኛውን ፓትርያርክ በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መሾሟ ይታወቃል ፡፡ በቦታው ላይ ሰዎች ተገኝተው
ስርዓቱን በሚከታተሉበት ሰዓት ከአውደ ምህረቱ ላይ ሁለት አይነት መጽፎች ለምዕመኑ ሲበተኑ ነበር ፤ አንደኛው የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ
ማቲያስ የህይወት ታሪክን የያዘ ከ50 ገጽ በላይ የሆነ መጽሀፍ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽህፈት ቤት “አራተኛው ፓትርያርክና ከእሳቸው ጋር ባሉት አባቶች የተፈጸመው
ስህተትን የሚያጋልጥ መረጃ በጽሁፍ ፤ በመገናኛ ብዙሃን እና በተለያዩ ጉባኤዎች ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል” ባለው መሰረት ከ52 ገጽ
በላይ ያለው አራተኛው ፓትርያርክ አጠፉ ያላቸውን ስህተቶች ነቅሶ የሚያወጣ ጽሁፎች ናቸው፡፡ በዚህ ወቅት በሰዎች ዘንድ ሲነሳ ከነበረው
ጥያቄ አንዱ “እንዴት በሁለት ቀን ልዩነት የአቡነ ማቲያስን የህይወት ታሪክ እንዲህ ሊጻፍ ይችላል? የሚለው አንዱ ነው
፡፡ የ6ተኛው ፓትርያርክ ውጤቱ ሀሙስ ድምጽ ተሰጥቶ ፤ ሀሙስ ከሰዓት
ታውቆ አርብና ቅዳሜን የአንድን ሰው ታሪክ ጽፎ ፤ አስፈላጊ ሰነዶችን አደራጅቶ፤ እርማት አድርጎ ማተሚያ ቤት ገብቶ ለእሁድ ሲመት ደረሰ ማለት “ዶሮን ሲያታልሏት …” ነገር ነው የሚሆነው፡፡ስለዚህ
የህይወት ታሪካቸው ቀድሞ ነው የተዘጋጀው ለማለት ያስደፍራል፡፡
በሌላ በኩል ቅዱስ ፓትርያርኩ
“እርቀ ሰላሙ ይቀጥላል” እያሉ ባሉበት ሰዓት ስለ አራተኛው ፓትርያርክ ይህን አይነት ሰነድ ማውጣት ለምን አስፈለገ ? በማለት
ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎች አልታጡም፡፡ የተበተነውን ሰነድ ካነበቡ በኋላ እውን ሁለቱ ሲኖዶሶች
እርቀ ሰላሙን ይፈልጉታልን ? በማለት የሚጠይቁ ሰዎችንም ተመልክተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰነዱ ፍጹም ኦርቶዶክሳዊ
ያልሆነ በርካታ ሽሙጦች ፤ ፖለቲካዊ አካሄዶችና መባል የሌለባቸው
ነገሮችን ይዞ ተመልክተናል ፡፡ለምሳሌ አንድ ቦታ ላይ አራተኛው ፓትርያርክ ከመንግስቱ ኃ/ማርያር ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ ፎቶ ያስቀምጥና
“የቀድሞ አራተኛ ፓትርያርክ ከደርግ ሊቀ መንበር አብዮታዊ ቡራኬ ሲቀበሉ” በማለት ከፎቶ ስር ሰፍሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም
አራተኛው ፓትርያርክ ደርግ ህዝብ ሲጨፈጭፍ ዝም ብለው ተመልክተዋል በማለት መንግስት ጥፋት ሲያጠፋ አለመናገር በእሳቸው የተጀመረ
ያስመስለዋል፡፡ አቡነ ጳውሎስ ከቅድስተ ማርያርም የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታፍሰው ሲወሰዱ መቼ ተናገሩ ? ዋልድባ አባቶች ሲንገላቱ
ማን አቤት አለላቸው ? በ97 ያ ሁሉ ነገር ሲደረግ ፓትርያርኩ ዝም በማለታቸው በ1998 ዓ.ም የመስቀል በዓል ላይ ፓትርያርኩን
ህዝቡ “ይሁዳ…” “ይሁዳ ..” ሲላቸው እኛም በአይናችን በዘመናችን
ያየነው ነገር ነው፡፡ መጥቀስ ካስፈለገ ብዙ መጥቀስ ይቻላል ፡፡ እርቀ ሰላሙን ቢፈልጉት ኖሮ ይህን ሰነድ ባላወጡት ነበር፡፡ አራተኛውን
ፓትርያርክ ብቻ በመክሰስ ራስን ነጻ ማድረግ አይቻልም ……. ሰነዱ ብዙ የጽሁፍ ማስረጃዎችን ይዟል፤ በዘመኑ ምን እንደተደረገ ለማሳየትም
ይሞክራል ፤ የቤተክህነት ሰው ሳይሆን አብዮታዊ ዲሞክራሲን የተጠመቀ ሰው የጻፈውም ይመስላል ፤ አንድ ወዳጄ “አዲስ ራዕይ” መጽሄት
ቤተክህነት መጻፍ ጀመረች እንዴ ብሎኛል፡፡ ለማንኛውም አንድ አድርገን
ይህን የተበተነውን ሰነድ በቅርብ ሆነው ማግኝት ለማይችሉ ምዕመናን ስካን በማድረግ ለአንባቢያን አቅርባለች፡፡
ያንቡት አስተያየትዎን በሰነዱ
ላይ ብቻ ይስጡ
አላማችን መረጃዎችን ሰዎች
ዘንድ ማድረስ ነው::
ምን ይሄ ብቻ!! ብፁእ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ አገር ጥለው መሰደዳቸውን ከጥፋት ቆጥሮ የሚወነጅለው ይህ መፅሃፍ በርሳቸው ቦታ የተቀመጡት አቡነ ጳውሎስም ሆኑ አቡነ ማትያስ በስደት እንደነበሩ ማስታወስ የተሳነው ነው!
ReplyDeleteWe have to be clear here. Our church is not free; there is a huge pressure from the political power. It has never been free, we have to admit it. However, this time it gets worsen. However, this can bot be taken as an excuse to split our church. That should be underscored. I think it is now becomes clear that these fathers made the truth hidden from the public, and that bitterly confused many church followers. I agree the document contains a lot of inappropriate words, especially not expected from any church affiliated father or employee, but it has valuable documents that may clear the confusion that had been floating around for more than two decades. My question, which I still do not understand, is that “what was the benefit to hide these documents for such a long time?” Had these document been public 20 years ago, we wouldn’t have the so called ‘exile synod’, which is unheard of in any churches’ history. So, the documents gave us a hint who did what? Why? and when? So, just let’s give an elephant ear to those who would like to confuse us again, and hold hand in hand and find a solution to our church together. If we are together, we can do something but if we continue our division with baseless confusing story, then I’m sure you understand what will happen. Woyannie will continue make fest and watch us fighting and at the same time it drags our mother church into trash, continue destroying our monasteries. Because, Woyannie kept us busy with the assignment that it gave us, the power of division!! We do not have to be a rocket scientist to figure this out, just a few months ago, we were trying to be united and make a noise about our Wldeba monastery. That is now evaporated and I do not see anybody talk about it anymore, reason because Woyanie is very smart and it gave us another silly reason to go back to our divided cave. So, let’s be united and convert our ‘just words’ to practical. Whether we like it or not, Woyannie manipulated the election and gave us the patriarch it wanted. The Hollywood movie style election drama is done, and we know our power that we cannot change this. But if we united, we will definitely bring significant and permanent change to our church. Wake up!!!
ReplyDeleteThe person who realy wrote it a member of EOTC? I don't belive!They are EPDRF founder.
ReplyDeleteይድረስ ለቤተክርስቲያን ወንድሞቼ ፦
ReplyDeleteስለቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ ሁኔታ ለመረዳት በየብሎጉ ማየታችን አይቀርም ግን ማወቅ ያለብን ነገር ብሎጉ ላይ የሚጽፈውም ሆነ
አስተያየት ሰጪው ሁሉም ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪዎች በመምሰል የራሳቸውን ሀሳብ ያስተላልፋሉ ፡
ለምሳሌ፦ፖለቲከኞች ፦ኢሃዲግ ፣ ተቃዋሚዋች ...
የሌላ ሀይማኖት ተከታዮች ፦ እስላሙ ፣ጴንጤው፣ተሀድሶው፣ወዘተ
ሁልጊዜ ወንድሞቼ ስናነብ ይህን ግምት ውስጥ ካላስገባን በተቀደደልን ቀዳዳ ሁሉ የምንፈስ ከሆነ ለእኛም ለሀገራችንም ለቤተክርስቲያናች ንም አይጠቅምም ።
እባካችሁ አባቶቻችን ባስተማሩን ስርአት ኖረን ቱፊታችንን ለልጆቻችን እናስረክብ
የቤተክርስቲያናችንን ችግር እኛ ልጆቻ እንሸፍን ከጠላት ዳቢሎስ ጋር አናብር
ማነው ከእናንተ እናቱን መጥፎ ሆነች ብሎ ሰው ፊት ስም የሚያጠፋ ቤተክርስቲያን ከሁሉ ትበልጣለች።
ችግር የለም ማለት አይደለም ሁሌም ይኖራል ችግሩን ለመፍታት ግን እንደ አባቶቻችን እምነት፣ፅናት፣ትእግስት፣ትህትና፣ይኑረን ይህን ካላደረግን ግን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በእግዚአብሄር ቤት ላይ የምንናገር ሁሉ የእግዚአብሄር ፍርድ አለብንና እንጠንቀቅ ሌላውን እዳናስት።
ተመልከቱ በየፖለቲካው ሚዲያ የሚስማው ለቤተክርሲቲያን ተቆርቃሪ በመምሰል አባቶቻችንን ይሰድቡብናል፣ ከአባቶች በላይ ሆነው እከሌ ይመረጥ ፣ አባ እከሌ እንደዚህ ናቸው ፣እራሳቸው ከወንድማቸው እና ከጋደኛቸው ሳይታረቁ ያለ ስልጣናቸው ዘረኝነትንና የፖለቲካ አቋማቸውን
ለማሳካት የቄሳርን ለእግዚአብሄር ሊያደርጉ ሲሞክሩ ይታያሉ እግዚአብሄር ይቅር ይበለን
እውነተኛ የቤተክርስቲያን ልጅ ከሆንን ግን ቋንቋችን ፣ዘራችን ፣የፖለቲካ አቋማችን ኦርቶዶክሳዊት ናት።
በፀሎታችን ላይ ፦እግዚአብሄር ፦ሀገራችንን እንዲጠብቅልን
፦ህዝባችንን ፍቅር እና አንድነት እንዲሰጥልን
፦መሪዎቻችን በጥበብና በማስተዋል እንዲመሩን ልቦናቸውን እንዲመልስ
፦ለእኛም የልቦናችንን አይን አብርቶልን የምናደርገውን እንድናውቅ የድንግል ማርያም ልጅ መድህን ክርስቶስ
ይርዳን አሜን ።
ወንድማችሁ ነኝ ከተሳሳትኩ በእናንተ እታረማለሁ
http://ethiopia.ecadf.netdna-cdn.com/Amharic/wp-content/uploads/2013/05/Response_to_false_claim_from_Ethiopia.pdf
ReplyDeleteእስከመቼ የራሳችንን ሰይጣንነት በፖለቲካ እያሳበብን ዋልጌነታችንን እንደምናነግስ አላውቅም::.... ለእግዚአብሔር አልታዘዝንም:: ከፖለቲካ ሹመኖች የበለጠ እየበደልን ያለነው አራሳችን ሚስጢር የቀመስን ክቡር ሥጋውን ቅዱስ ደሙን የተቀበልን ለሆዳችን ያደርን እበላ ባዮች ነን:: የፖለቲካ ሹመኞችማ መቅጠፍ እና እያታለሉ መኖር ምድራዊ ሥልጣናቸውን ማግነን የቆሙላት ዓላማ ነው:: ለእኔ እነርሱ ማህበረ ቅዱሳን፣ የሲኖዶስ አባል፣ ጳጳስ፣ እያልን ከነብስም ከሥጋም ያልሆንን ዋልጌዎች የተሻሉ ቅዱሶች ናቸው::
እኔ ከአሁን በሁዋላ ጥቁር ተከናንቦ ጳጳስ ነኝ እያለ በቤተ ክርስቲያኔ ቁማር ከሚጫወት የሰይጣን ባለምዋል ሃሳበ ከርስ ጋር ምንም ጥምረት የለኝም:: ክርስቲያንነቴ እነዚህን ከርስ አደሮች ጋር ምንም አይነት ህብረት እንዳይኖረኝ ግድ ይለኛል:: የክርስቶስ ሥጋና ደም መቀለጃ አይደለም:: ለእውነት መቆም የወቅቱ ሰማእትነት ነው:: ከርሳችንን እና ምድራዊ ዝናችንን ማስቀደምን መተው እውነት መናገርን መድፈር ያልቻለ ክርስቲያን ምንም አይነት ክርስቶስን እናቱን ቤተ ክርስቲያኑን እወዳለሁ የሚል ሞራል ሊኖረው አይችልም::
ወገኖቼ በክርስቶስ ቤት መነገድ ይብቃን፤ ሰው ሆነን ውለን ለማደር እንወስን:: ውሸታም ውሸታም ነው የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ስለሆነ፣ የምንወዳት ቤተክርስቲያን ውስጥ ስላደገ፣ ማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ጉብ ቂጥ ስላለ አባት ወይም የቤተክርስቲያን ልጅ እያልን ከዛም በፖለቲካ ጫና እያሳበብን መካካብ ይብቃን::
የራሳችን ከርስ አደርነት ነው ዋናው አንቆ የያዘን፤ ቆራጥ፣ ለተቀበለው ቅዱስ ሥጋ ክቡር ደም ያደረ ክርስቲያ ቤተ ክርስቲያን እያጣች ነው፤ ማሳበብ የትም አያደርሰንም:: እያንዳንዳችን ክርስትናችንን በተግባር እናሳይ: የከፈልነው ገንዘብ የት እንደደረሰ እንጠይቅ፣ የሚዋሽን የቤተክርስቲያን ሃላፊ: ንሰሃ አባትን ደፍረን ነውር ነው አባቴ ማለትን እንጀምር፤ እምቢይ ካሉን ሌላ አባት እንፈልግ፤ ጥቂቶችም ቢሆኑ አባቶች ዛሬም አሉን:: እኔ ዛሬ ወስኛለሁ፤ ለቤተ ክርስቲያኔ በአይነት እንጂ በገንዘብ ምንም አልሰጥም፤ በፖለቲካ እያሳበበ አብሮ የሚቀጥፍ አባት አባቴ አላደርግም፤ ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ የነዚህን ጥቁር ለባሽ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ተብዬዎች ቅጥፈት ደፍሬ ለመናገር ቃል ገብቼያለሁ:: ዋሾዎች ተሰብስበው በተሽዋሽዋሙበት አውደምህረት ላይ ይህ የእኔድርሻ ምንም ላያመጣ ይችላል እኔ ግን ቤተክርስቲያኔ ያስተማረችኝን የክርስቶስ ክብር መመስከር ግዴታ አለብኝ::
አሁንም እላለሁ ይህ የፖለቲካ ተፅእኖ ብቻ አይደለም፤ በክርስቶስ ላይ ያለ የቤተክርስቲያኑ አስተዳዳሪዎች በተለይ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ላይ የሚፈፅም ውንብድና ነው:: አሁንስ በጣም በዛ: ይሄ ምንም ፖለቲካ ጋር የሚያያዝ አይደለም:: ወይ እንመን ወይ እንካድ: በሁለት እግር እያነከስን ክርስቶስ የአፄውንም፣ የደርጉንም ዘመን በፍቅር አሳልፎናል:: አሁን በፖለቲካና በተሃድሶ እያሳበብን ከርሳችንን የምንሞላ የቤተክርስቲያን ወንበዴዎች ወይንም የወንበዴዎቹ ደጋፊዎች ሆነን መጉዋዝ አንችልም:: ፖለቲካ፣ ተሃድሶ፣ በተክርስቲያን ጥበቃ እያልን ከርስ መሙላት ኑሮ አቁመን ነብሳችንን እንመርምር፤ ከዛ ወይ ማመን ወይ መካድ ነው ጥያቄው:: እኛ መጀመሪያ ማን ሆነን ነው የክርስቶስን ቤት ጠባቂ እና አባት የምንሆነው፤ እራሳችን ቤቱን እያራቆትን፤ የተቀበልነውን ክቡር ሥጋና ቅዱስ ደም እያረከስን ምን ሞራል ኖሮን ነው የቤተክርስቲያን አባት፣ የቤተክርስቲያን ጠባቂ፣ አስተማሪና ዘማሪ የምንሆነው????
ሲሳይ