- “ለመሆኑ ከፈቃደ እግዚአብሔር ለምን ትሸሻላችሁ? እናንተንስ እንዴት እንመናችሁ?” አቡነ ዩሴፍ የተናገሩት በቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ምርጫው በእጣ እንዲሆን ከተወሰነ በኋላ በማግስቱ ላስቀለበሱት አባቶች
- አቡነ ዩሴፍ በቤተክህነቱ ካለው ዘረኝነት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ ፍቅረ ንዋይ፣ ስሜታዊነት(ግብታዊነት) ተለይተው ፥አርአያ ክህነትን ጠብቀው ፥ ሥጋ እንዳየ አሞራ በቤተክርስቲየኒቱ ላንዣበቡ ተሐድሶ መናፍቃን መዶሻ የሆኑ ጥሩ አባት ለናፈቀን የቀረቡልን ሲሳይ ናቸው፡
(አንድ አድርገን የካቲት 20 2005 ዓ.ም)፡- የቤተ ክርስቲያኒቱ
አንድነት ይጠበቅ ዘንድ በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ያሉ አባቶች ልዩነት ጠፍቶ በፍቅር በአንድነት መንበረ ፓትርያርኩን ተረክቦ
በአባትነት የሚመራን መልካም እረኛ ከሐሜትና ተንኮል በጸዳ ልቡና ምእመናንም ሆኑ ካህናት እንደልጅነት፤ ፓትርያርኩ እንደ አባት በመሆን በፍቅር እንኖር ዘንድ ያልተመኘና ያልጣረ
ቢኖር የቤተክርስቲያንን ሁለንተናዊ ዕድገት እንዲሁም ሰላምና ፍቅርን የማይወድ የክፋት አበጋዝ ብቻ ነው፡፡ሆኖም ግን የዚህች ርትዕት
ቤተ ክርስቲያን ፈተናዋ ሊቋጭለት አልቻለምና ይህ ምኞታችን በእውነተኞቹ
አባቶችና ምእመናን ጥረት ፈርጀ ብዙ በሆኑ መንገዶች ቢሞከርም ለጊዜው አልሆነም፡፡የፓርትያርክ ምርጫ ጉዳይ ከተወሰነ በኋላ ግን
ከድጡ ወደማጡ እንዳንሔድና ለመናፍቃንና እለከርሶሙ አምላኮሙ /ሆዳቸው አምላካቸው/ ለተባሉት እየበሉ ለሚርባቸው ጭራቆች አሳልፎ
ከመስጠት፣ መንጋውን ከመበተንና የለቅሶውን ዘመን ከማራዘም ያለፈ ረብ ያለው ለውጥ ማምጣት አይቻል ይሆናል የሚል ስጋት ብዙዎቹ
የሚጋሩት ሆኖ ቆይቷል፡፡
ቤተ ክርስቲያናችን ሰማያዊ ዓላማ ያላት ቅድስት፣ ርትዕት ይህ ቀረሽ የማትባል ስንዱ እመቤት መሆንዋ ከእያንዳንዱ ሰው ልቦና የሚጠፋ አይደለም፡፡ በዶግማዋ፣ሥርዓቷና ትውፊቷ ምድራውያን መላእክትን ያስገኘች የነቃች የበቃች መሆንዋን ዓለም የመሰከረው ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሌት ተቀን የሚበላውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ የሚያደባው ጥንተ ጠላታችን ዲያብሎስ እስከ ምጽአት ድረስ የሚፈታተናት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ መሠረት አስተዳደራዊ ችግሯ እግር ከወርች ሰቅዞ በያዘ እሥራት ዝርክርክ አስተዳደር፣ በአካባቢ ጠብ የሚፈላለጉ፣ ሥራቸውን
ሰድደው በመደላደል ቤተ ክርስቲያኒቱን የወንበዴዎች ዋሻ ለማድረግ በጨለማ ቡድንነት የሚንቀሳቀሱ እንኳንስ በኛ ቤት ልናየው በዓለሙ
እንኳ ጸያፍ የሆነውን በተቀደሰው አደባባይ የሚፈጽሙ አሁንም ወስነው ቆርጠው ተነሥተው እርካቡን ረግጠው ወደ ኮርቻ ለመውጣት በፈለጉም
ጊዜ ገንዘብ መድበው የሚመቻቸውን መዋቅር ሁሉ ያለአግባብ በመጠቀም የሚፈልጉትን ፓትርያርክ በማስመረጥ ገዳማቱን ለመፍታት፣ ቤተ
ክርስቲያኒቱንና ምእመናኑን ባለጌ እንደፈረፈረው ዳቦ ለመበታተንና ለመቀሰጥ ተዘርፎ አላልቅ ያለውን ከድኃው የሚሰበሰበውን ለመዝረፍ
ቤተ ክርስቲያኒቱን ዛሬም መካነ ብካይ ሊያደርጓት ደፋ ቀና እያሉ ነው፡፡
ዋናው ጉዳይ በጊዜያችን በዘመናችን ያለን ክርስቲያኖች የአቅማችንን
በመሥራት የሚጠበቅብንን ሓላፊነት እንወጣ ዘንድ በ6ኛ ፓትርያርክነት የሚመረጡት አባት ማን ቢሆኑ ይበጀናል? የሚለው ነው፡፡
በመጀመሪያ እጩ ሆነው የቀረቡ አምስቱ ጳጳሳት ቡራኬያቸው ይደርብንና
የቤተ ክርስቲያኒቱን ችግር አስተዳደራዊና መንፈሳዊ በማለት በሁለት ፈርጅ እናስቀምጠው.. ከምንም በላይ መንፈሳዊ አባት ከሆኑ አስተዳደሩን
በጠንካራ ሥራ አስኪያጅና ቋሚ ሲኖዶስ መደገፍ ይቻላል፡፡ ምእመናን የሚቀበሉት መንፈሳዊ አባትነትን ግን በድጋፍ ልናመጣ አንችልም
የአቡነ ጳውሎስ ችግር የዕውቀት እጥረት ሳይሆን የቅንነትና መንፈሳዊነት እጥረት ነው፡፡ በመሆኑም በእጩነት ከቀረቡት አባቶች መካከል
ከሚከተሉት ነጥቦች አኳያ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
ቢሆኑስ፤
መንፈሳዊ ሕይወት 1. በጾምና በጸሎት፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖትን ሊያስታውሱን
የሚችሉ አባት በመሆናቸው፤
መንፈሳዊ ሕይወት 1. በጾምና በጸሎት፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖትን ሊያስታውሱን
የሚችሉ አባት በመሆናቸው፤
2.ማኅበራዊ ትሩፋቶች፡ በሚሰጣቸው ደመወዝ አሳዳጊ የሌላቸውን ሕጻናት በመኖርያቸው የሚያሳድጉ የድሀ አባት መሆናቸው
3. ንጽሕና፡
በሐሜት ደረጃ እንኳን ምንም የማንሰማባቸውና ሀብተ
ንጽኅ(ንጽሕና) የያዙ ስለሆኑ
ሰብእና፡ በትእግስትና በታረመ ንግግራቸው ብዙ ችግሮችን የመፍታት ጸጋ ስላላቸው
አቋም፡ በቅዱስ ሲኖዶስ
ጉባኤ ምርጫው በእጣ እንዲሆን ከተወሰነ በኋላ በማግስቱ ላስቀለበሱት አባቶች
ለመሆኑ ከፈቃደ እግዚአብሔር ለምን ትሸሻላችሁ? እናንተንስ እንዴት እንመናችሁ? በማለት እስከመጨረሻው በአቋም ከመጽናታቸውም ባሻገር አቋም የሌላቸውን አባቶችን
መገሰጻቸውና ለዕርቀ ሰላሙ የነበራቸው ጽኑ አቋም
በውጭ ዓለም ተሞክሮ፡
በአውሮፓም በጵጵስና በምእመናኑ ዘንድ እጅግ ተወደው ያገለሉ
ደግ
አባት መሆናቸው
ገዳማዊ ሕይወት፡ የገዳም አበምኔት በመሆን ያገለገሉ ጣዕመ ገዳምን የሚያውቁ ለገዳሞቻችንም ትኩረት ሊሰጡ የሚችሉና በተግባር
ታይተው የተመሠከረላቸው መሆኑ
የቋንቋ ችሎታ፡ በኦሮምኛ ቋንቋ በማስተማርና በኦሮሚያ አካባቢ ቤተ ክርስቲያኒቱ የእነገሌ ብቻ ናት በማለት ለተወሰነ አካባቢ በሚሰጡ አጽራረ ቤተክርስቲያን ከእውነት መንገድ ለወጡ በብዙ ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ወገኖቻችን ፈውስ ስለሚሆኑ
ተመራጭ ያደርጋቸዋል፡፡
በአጠቃላይ በቤተክህነቱ ካለው ዘረኝነት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ ፍቅረ ንዋይ፣
ስሜታዊነት(ግብታዊነት) ተለይተው ፥አርአያ ክህነትን ጠብቀው ፥ ሥጋ እንዳየ አሞራ በቤተክርስቲየኒቱ
ላንዣበቡ ተሐድሶ መናፍቃን መዶሻ የሆኑ ጥሩ አባት ለናፈቀን የቀረቡልን ሲሳይ ናቸው፡፡
በመሆኑም በቤተክርስቲያን ፍቅር ለሚቃጠልና የቤተክርስቲያንን ትንሣኤ ለሚናፍቅ ሁሉ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍን መምረጥ ብቸኛና ለድርድር የማይቀርብ የወቅቱ ክርስቲያናዊ ጥሪ መሆኑን የአንድ አድርገን ኢዲቶሪያል ኮሚቴ ያምናል።
ሰላም አንድ አድርገኖች እንደምን ዋላችሁ ስለአቡነ ዮሴፍ ባላችሁት ነገር ሁሉ እስማማለሁኝ እንደውም ከትናንት ወዲያ ከወንድሜጋር ስናወራ ምነው አቡነ ዮሴፍ በሆኑልን በታደልን ነበር እያልኩት ነበር እንደውም አንድ በውስጤ የነበረ ነገር ልንገራችሁ ሁሌ እሁድእሁድ ቅዳሴማርያምን የማንበብ ልማድ አለኝ እና እንደምታውቁት ቅዳሴማርያም ላይ ፓፓሳትን የምጠራበት ቦታ አለ እንዲያውም የስክንድሪያዉን እና የሀገራችንን ፓትርያሪክ እና እኔም እዚህ ቦታላይ ስደርስ ሁሌም አቡነሽኖዳን እጠራና ባረፉት ፓትርያሪክቦታ ሁሌም አቡነዮሴፍን ነዉ የምጠራው እናም ሁሌም እራሴን እጠይቀዋለሁን ትክክል እዳልሆንኩ አውቃለሁኝ ነገርግን አባፓውሎስን ልቤ ስላዘነባቸው የውሸት መጥራቱን አልፈቀድኩም ነበር በዚያላይ አቡነ ዮሴፍ ያኔ የኛም የጀርመኖች አስተዳዳሪ ስለነበሩ የዋህነታቸውንና ቀናነታቸውን ለማየት ችያለሁን ነገር ግን የሚገርመው አሁንም እንኩዋ ከርሳቸው በሁዋላእንኩዋ ሁለት ፓፓሳት ተቀያይረውብን ልቤ ስላልተቀበላቸው ይሁን አፌ ስላለመዳቸው አሁንም በዚያቦታ የምጠራው አቡነዮሴፍን ነው እናም እግዚአብሄር ፈቅዶ ቢመረጡ ንሴብሆ ይደልዎ ይደልዎ ብየ ነው የምቀበላቸው ነገር ግን ስጋቴ በተደጋጋሚ የማነበውና የምሰማው ነገር ያለቀ ጉዳይና የተበላቁብ ነው ስለተባለ ምንዋጋ አለው የኛ ምኞትና የኛምርጫ የት ሊያደርሰን ብየነው ትናንትናም ምእመኑም ሆነ ማህበረ ቅዱሳን በነሱ ዳፋእንዳይተባበሩ ያልኩት ነገር ግን እድሉ ጨርሶ ካልተዘጋ የመምረጥ እድሉያለው ሁሉ አቡነዮሴፍን ቢመርጥ መልካምነው ብየ አምናለሁኝ ለሁሉም የእግዚአብሄር ፈቃድ ይሁን አሜን
ReplyDeleteMay God bless this idea.if what has been said is
ReplyDeletetrue,I have no objection. I shall pray and do my
part this idea come true.
May God bless this idea.if what has been said is
ReplyDeletetrue,I have no objection. I shall pray and do my
part this idea come true.
እግዚአብሄር ለቅሶአችንን አይቶ እኚህን ጨዋ መንፈሳዊ አባት ይሰጠን ዘንድ አሁንም እንለምነዋለን ቸር ነገር ያሰማን
ReplyDeletewey guud are selel Egzihar belachehu ahun le Menfes Qedus qedmiya yaltesetebet mercha wenet tekekel new belachehu letedemedemu new beka .Ye Ethiopia Amlak esu Tewahedon yetebeklen enji betam yemiyasaseb seat nwe kefitachen yemitebeken wegen , betslot enetga.
ReplyDeleteweyane eyale ,.....?
ReplyDeleteSelam Andeadergen Melkame neger asenbebachn CHER TEMENE CHERE ENDETAGEN YEBYLALE! Ehtachen KeGermen endalechew Abeun Yosefen Aweropa benberbet gize
ReplyDeletemelkam abat endeneberu enawqalen selezihe Amelke Eserale yerdanena ersachewen
biyadergelen menotachen new Egizabeher yaseben Amen!!!
Enante chirasunum yefetari emnet yelachihum. Egziabher barko yisten bemalet fanta abune egele miretu blo menager sihtet new. Mengist talka geba eyaln eniqennalen. Enantes talka algebachum wey? rasachihn melsut. Egziabher amlak cher abat ysten.
ReplyDeleteAmen!
So if you have such good information about him, why are you late to inform the wider people? at least we could pray, or voters would be encourage to select him. But I think it is a bit late to inform this today on the selction day.
ReplyDeleteስለ አቡን ዮሴፍ በአውሮፓ ቆይታቸው የማውቀውን ለመናገር፣ በቅድሚያ ቤተክርስቲያንን ከመገንባት የአብነት መምህራንን መገንባት የሚመረጥ ነው ብለው ያምናሉ። ቤተ ክርስቲያንን ወክለው ለአገልግሎት ወደ ተለያዩ ክፍለ አለማት በሚዘዋወሩበት ጊዘ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ተዘግተው ሙዚየም ሆነው ግማሹ ያለ አስፈላጊ ሥራዎች ሲከናወንባቸው አይተው በማዘን ቤተ ክርስቲያን ከመገንባታችው በፊት ትውልዱን ቢገንቡ ይህ ባልሆን ነበር ይላሉ። ብፁዕነታቸው ቅናት፣ ምቀኝነት፣ ዘረኝነትና ጠባብነት ከሰው ልጆች አዕምሮ ፈፅሞ መወገድ አለባቸው ብለው ያምናሉ። ቅናት ሰይጣናዊት ለያዕቆብ ልጆችም እንኩዋን አልጠቀማቸውም። በቅናት ወንድማቸውን ዮሰፍን በሸጡ ጊዘ እግዜአብሔር ክፋታቸውን ተመልክቶ ለባርነት ዳረጋቸው እንጂ፤ ዘረኝነት ለአይሁዳውያንም አልጠቀማቸውም ጠባብ አመለካከት ያለውን ሂትለርን አስነስቶ ጎዳቸው እንጂ እያሉ መልዕክታቸውን የሚያስተላልፉ አባት ናቸው። ብፁዕ አቡነ ዮሰፍ የሀገሬ ልጅ የወንዜ ልጅ ብለው የሚያንፀባርቁትን ወገኖች ሲሰሙ ደስታ አይሰማቸውም። ሀገርና ወንዝ አምላክ የፈጠረው ፍጡር ሁሉ መገልገያ መጠቀሚያ ናቸው እንጂ ወገን መለያ አይደሉም ብለው ያምናሉ። ብፁዕነታቸው በመልእክታቸው በትንሽ ነገር እየተጣላን ትልቁ እያመለጠን ይሄዳል የምንፈልገው ደረጃ ለመድረስ እቅዱንና መንገዱን ማሰብ አለብን ለግባችን መሳካት በመንገዱ ላይ ለሚያጋጥመን መሰናክል መደንገጥ አስፈላጊ አይደለም በተጨማሪም በመለያየት ውስጥ መኖር ከሁሉም በላይ አብዝቶ ይመራል ያለፉበትን ዞር ብሎ በማየት የቆሙበትንም በማስተዋል ወደፊት ሊመጣ የሚችለውንም አሻግሮ በመመልከት ከእግዜአብሔር እርዳታ ጋር ተጠንቅቆ መገኘት ብልህነት መሆኑን በምክራቸው የሚያስተላልፉ አባት ናችው። ብፁዕነታችው ደሀውን በተፈጥሮአቸው ይወዳሉ የሕይወታቸውንም ዘመን ከእነሱ ጋር ቢያሳልፉ ደስ ይላቸዋል ለመርዳትም ወደ ሁዋላ አይሉም አባት እናት የሌላቸውን በርካታ ልጆች በማስትማር ለሀገር እድገት አብቅትዋቸዋል። ብፁዕንታቸው አንድ አመለካክት አላቸው እያንዳንዱ አቕም ያለው ወገን አንዳንዽ የድሀ ልጅ ቢያስተምር ድህነት በተወገደ ነበር የሚሉ አባት ናቸው።
ReplyDelete