Thursday, September 15, 2011

አጥብቀን ልንታገለው የሚገባን እውነታ!

 • ስደተኛው ሲኖዶስ ብለው ሲነሱ፣ ተው አይሆንም ሲኖዶስ አይሰደድም ስንል፥ ዛሬ ደግሞ በአንድ መንበር ሥር በሚያገለግሉ ነገር ግን ግብራቸውን የለዩ ለከርሳቸው ያደሩ ከሃዲያን ተነስተውብናል

ዛሬ ለሥርዓተ ቤተ ክርስትያን ግድ የሌላቸው ለግል ከርሳቸው እና ጥቅማቸው የሚሯሯጡ አባቶች ተብዬዎች፣ የጥንት አባቶቻችን የሰሩልንን ቀኖና ወደጎን በመተው ያለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሥራዎችን እየሰሩ ያሉ ሰዎች እኛ ውስጥ ሆነው የኛ የሆነውን ለጠላት እየሰጡ ያሉበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወልዳ መካን፣ አሳድጋ ለመናፍቃን እረዳት የሆኑበት ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቅ ችግር ውስጥ ያለችበት ጊዜ አሁን ነው፣ ስለዚህ እያንዳንዱ የተዋሕዶ ልጆች በሙሉ በአርባና በሰማኒያ ቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የተወለድን ሁላችን በአንድነት ልንነቃ እና ልንጠብቅ የሚገባን ጊዜ አሁን ነው። ሰዎቹ በአሁን ሰዓት በትልቅ ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ሥራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡ለምሳሌ በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ "የቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት" በሚል የተከፈተ ጽህፈት ቤት አለ፣ ይህ ጽህፈት ቤት በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ልዩ ፊርማ ተፈቅዶ የተከፈተ ጽህፈት ቤት ነው፣ ነገር ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚው ሲኖዶስ እውቅና የለውም ለዚህም ሥራ ሊሠሩ (ሊያስፈጽሙ) የተላኩት ሦስት ግለሰቦች በሃገሩ ነዋሪዎች ናቸው፣ ሕዝቡን ያውቁታል፣ ህጉን ኖረውበታል፣ በቀላሉ ሰዎች ሊቀበሏቸው ይችላሉ ተብለው የመጡ እና ሥራውን በመሥራት ላይ ያሉት ግለሰቦች የሚከተሉት ናቸው
፩ኛ/ አቡነ ፋኑኤል
፪ኛ/ አባ ሰረቀ ወልደ ሳሙኤል
፫ኛ/ ዲ/ን ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን (ከድቁናው የተሻረ)


በመጪው ጥቅምት ወር 2004ዓ.ም ለሚካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ በርካታ ኤጲስ ቆጶሳትን ለመሾም ልዩ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ በቤተ ክህነቱ ሰዎች “ተለዋጩ ቋሚ ሲኖዶስ” የሚል ስያሜ ያገኘው እና ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ፣ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ መጋቤ ምሥጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ፣ ንቡረ ዕድ ኤሊያስ አብርሓ እና የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ሓላፊ እስክንድር ገብረ ክርስቶስ የሚገኙበት ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡ ይህ ኮሚቴ ነሐሴ 15 ቀን 2003 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ በመጪው ጥቅምት ወር በሚደረገው ሲኖዶስ ስብሰባ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት እንዲካሄድ እና ከአንድ ዓመት በኋላ ሊቃነ ጳጳሳት ለማድረግም ታቅዷል፡፡

ትልቁ ችግር እዚህ ጋር ይጀመራል፡፡ እነዚህ የሚሾሙት ጳጳሳት ማንነት ከዚህ በፊት የሰሩት ስራ በቅዱስ ሲኖዶስ እውነተኛ አባቶችና በሊቃውንተ ቤተክርስትያናት ካልተመዘነ እና ካልተለካ፤ ሁሉም ነገር በስርዓተ ቤተክርስትያን ብቻ ካልተካሄደ፤ መንግስት እጁን ከዚህ አይነት ምርጫ ላይ ካላነሳ የአቡነ ፋኑኤልንነና አባ ሰረቀ ወልደ ሳሙኤል አይነት አባቶች በብዛት ተፈልፍለው ቤተክርስያኒቷን ከድጡ ወደ ማጡ የሚወስዱበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡

አባ ሰረቀ በመጪው ጥቅምት ወር ጳጳስ ለመሆን ካሰፈሰፉ ሰዎች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ የኚህ ሰው የቀደመ ታሪክ እንደሚነግረን ትግራይ በነበሩበት ጊዜ ሚስት አግብተው ልጅ ወልደው ስመዋል፡፡ ይህን ታሪኬን ማንም አያውቅም በማለት በአቡነ ጳውሎስ ጠቋሚነት ለጵጵስና ታጭተዋል፡፡ በቤተክርስትያናችን ስርዓት መሰረት ጳጳስ ለመሆን ከሴት የራቀ እና ራሱን የጠበቀ መሆን ይገባዋል፡፡ ይህ ነገር ሲፈፀም ማየት ደግሞ ማንንም ከተጠያቂነት ነፃ ሊያደርገው አይችልም፡፡ 

እኝህ ሰው ኢህአዴግ ከገባበት ጊዜ አንስተው እስከ አሁን ከቤተክህነቱ ጋር በመጣበቅ ውስጥ ሚሰራውን ስራ 4 ኪሎ ቤተመንግስት ላሉ ሰዎች ለዘመናት በመረጃ አቀባይነት የተሳተፉ ሲሆን እንደ ዘመኑ እንደ ሁኔታው ራሳቸውን ከጊዜው ጋር በማመሳሰል ቤተክርስትያናችን ላይ እሾህ ሆነው እስካሁን አሉ፡፡ በቅርቡ በማህበረ ቅዱሳን ላይ ባደረጉት የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከሰው ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን የተከሰሱበትን ጉዳይ ማተባበል ስላልቻሉ ብይን ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ቀጠሮ በሰጠበት እለት ከፍትህ ሚኒስቴር የወጣ ደብዳቤ አማካኝነት ክሱ የቆመ መሆኑን የሚዘነጋ አይደለም፡፡

 እነዚህ ግለሰቦች ገለልተኞችን እናቀራርባለን፣ የራቁትን እናቀርባለን፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነትን እናመጣለን በሚል ሽፋን ዛሬ ሌት ተቀን ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ፥ በጣም የሚያሳዝነው በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ "የቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት" በሚል የተከፈተ ጽህፈት ቤት ሙሉ የሠራተኛ ደሞዝ (ሦስት ደሞዝተኞች)፣ የጽህፈት ቤት ኪራይ፣ ለጽህፈት ቤቱ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ሎጂስቲክ ቁሳቁስ በአጠቃላይ ወጪዎቹ ሁሉ የሚሸፈኑት በዓለም አብያተ ክርስቲያን ጽ/ቤት ነው (ሚኖናይት፣ አድቬንቲስት፣ ፕሪንስተን ቲዎሎጂ ሴሚናሪ፣ በአጠቃላይ ፕሮቴስታንቶች) የሚደግፉት ጽ/ቤት ነው

ሌላው ለጆሮ ጭው የሚያደርገው የጽ/ቤቱ የበላይ ተጠሪ ተብየው የቀድሞው ዲያቆን ያአሁኑ አቶ ኃይለ ጊዮርጊስ ነው፣ መረጃው በእጃችን ባይገባም እንደሰማነው በአሜሪካ ውስጥ ላሉት ሦስቱም ሃገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ደብዳቤ በመፃፍ እርሱ በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ተሹሞ ከመጣ ጀምሮ ሦስቱም ሊቃነ ጳጳሳት ተጠሪነታቸው ለዚሁ አቶ መሆኑን ከማስፈራሪያ ጋር እንደደረሳቸው ይነገራል።

እንዲህ ስርዓት ሲፈርስ፣ ያለህጓ የመጡበት የማይታወቁ ሰዎች መጥተው የአባቶቻንን ሥርዓት ሲያፈርሱ፣ ህጓን ሲፃረሩ፣ ለሌላ ሃይማኖት ሊሰጡን ደፋ ቀና ሲሉ ዝም ብሎ ማየት በታሪክም ያስወቅሳል፣ መጪውስ ትውልድ ምን ይላልስደተኛው ሲኖዶስ ብለው ሲነሱ፣ ተው አይሆንም ሲኖዶስ አይሰደድም ስንል፥ ዛሬ ደግሞ በአንድ መንበር ሥር በሚያገለግሉ ነገር ግን ግብራቸውን የለዩ ለከርሳቸው ያደሩ ከሃዲያን ተነስተውብናል፣ ልብ ያለው ልብ ይበል እነዚህን ሰዎች ዝም ካልን ብቅርብ ቀን ሥራቸው ይገለጣል መረጃዎችን እንሰጣለን፣ ሁላችን እነዚህን የበግ ለምድ ለብሰው በውስጣችን እየተመላለሱ ለጠላቶቻችን የሚሠሩትን ልንነቃባቸው ይገባናል።
የአባቶቻችን አምላክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ከአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ይጠብቅልን አሜን
Posted by Pro Tewahedo 

2 comments:

 1. እግዚአብሔር እጆቹን እና ዓይኖቹን ከዚህች ንፅህት ኃይማኖት ላይ ስለማያነሳ ምንም ያህል በውስጧ ተኩላዎች ቢበዙም አትናወጽም፡፡ ይግዚአብሔር በፅኑ አለት ላይ ያስቀመጣት የኖህ መርከባችንን እንዲጠብቅልን ሁሉም አይኖቹን ወደ ፈጣሪ ማንሳት ይጠበቅበታል፡፡
  በዋናነት ሁሉም በተኩላዎች እንዳይነጠቅ ባለበት ፀንቶ መቆም ዓለበት፡፡ እውነተኛ እረኛችን ከእግዚአብሔር እስኪላክልን ድረስ ባለንበት ፀንተን እንቁም፡፡
  እግዚአብሔር ተዋህዶ እምነታችንን ከተኩላ ነጣቂ እና ከእናት ጡት ነካሽ ይጠብቅልን፡፡
  ኃይለ ሚካኤል

  ReplyDelete
 2. Ayi Aba Abrham, Minew egziabher betelo biwosdiwot yishal neber. Kante yebelete kehadi, Zemawi, ye'arat lijoch abat man ale. Ye'set menekosatin sitasadid, sitasiregiz yenor ahun man ale. Yewond mist yemidefir man ale - Zemari bilo astegeto miseraw sira ahun bemetsehaf melik eyewota new.

  Yilik papas kehonih hideh synodos tesebiseb atawira.

  aba tekilemariam,

  ReplyDelete