Wednesday, September 7, 2011

መዝሙረ ዳዊት 1


1    ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ 
     በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ 
     በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
2    ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ 
      ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።
3    እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለች፥ 
     ፍሬዋን በየጊዜዋ እንደምትሰጥ፥ 
      ቅጠልዋም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
4   ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥
     ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው።
5   ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥ 
     ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።
6    እግዚአብሔር የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥ 
     የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።


መዝሙረ ዳዊትን ከነትርጓሜው በሳምንት አንድ አንድ ምዕራፍ ማቅረብ መጀመራችንን ለመግለፅ እንወዳለን

‹‹እግዚሐብሔር ቤተክርስትያንን ይጠብቅ ››

1 comment:

  1. ሀብተ ገብርኤልAugust 10, 2014 at 9:13 PM

    ቃለ ህይወት ያሰማልን

    ReplyDelete