Thursday, September 29, 2011

‹‹ ልጄ ቀስ በል ጵጵስናውን ትደርስበታለህ ኋላ ግን ሸክሙን አትችለውም›› አቡነ ቴዎፍሎስ ለአቡነ ጳውሎስ

 • አቡነ ቴዎፍሎስ በ1968 ዓ.ም ለአባ ገ/መድህን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) እንዲ ብለው ነበር …. አባ ገብረመድን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) በነገሮች በጣም ሲቸኩሉ ፤ ለመሾም በጣም ሲጣደፉ፤ ለጵጵስና እንዲያጯቸው እና በጊዜው የነበረው ሲኖዶስ እንዲያፀድቅላቸው ከልክ ያለፈ ምኞታቸውን የተመለከቱት አቡነ ቴዎፍሎስ ‹‹ ልጄ ቀስ በል ጵጵስናውን ትደርስበታለህ ኋላ ግን ሸክሙን አትችለውም›› ብለዋቸው ነበር፡፡.............ኢትዮጵያውያን አብዮትን የምናወቀው በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ሳይሆን በውስጡ አልፈን በቃጠሎው ተገርፈን ወላፈኑን ቀምሰን ነው፡፡ በዛን ወቅት የነበረው የሶሻሊስት ርዕዮት አለም አብዮታዊነትን እንደ ታላቅ ነገር ሲሰብክ የነበረ በመሆኑ ብዙ ወጣቶች አብዮተኛ ተብለው ሀገሪቱንም አብዮታዊት ኢትዮጵያ አስብለዋታል፡፡ በዚህች ተአምረኛ ሃገር አብዮታውያን ወንድሞቻችን ጸረ አብዮተኛ የተባሉ ወንድሞችቻቸውንና እህቶቻቸውን ቅርጥፍ አድርገው በልተዋል፡፡ በዚያ ክፍለ ዘመን አብዮት ልጆቿን ትበላለች በሚል ፈሊጥ ብዙዎች ወጣቶች ጸረ-አብዮት፤ ጸረ ህዝብ ተብለው አይሆኑ ሆነዋል..ጊዜው ጥቁር ጠባሳውን ጥሎ ያለፈው ሁሉም ላይ በመሆኑ የጊዜው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን 2ኛ ፓትርያልክ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ላይ የደረሰው በደል ግን ለየት ያደርገዋል....

በዚያ ወቅት ደርግ ጳጳስ እንዲይሾሙ ትእዛዝ አውጥቶ ነበር።አቡነ ቴዎፍሎስ የደርግን ትእዛዝ ሽረው ሦስት ጳጳሳትን ሾሙ።ደርግም ትእዛዜን አልሰማህም ብሎ ፓትሪያርኩንና ሦስቱን ተሿሚ ጳጳሳት እስር ቤት ጨመራቸው።በወቅቱ የተሾሙት ጳጳሳት አቡነ ባስልዮስ፤አቡነ ጴጥሮስና አቡነ ጳውሎስ ነበሩ።ከጊዜ በኋላ ሦስቱ ጳጳሳት ከእስር ሲፈቱ ፓትሪያሪኩ ብቻ በዚያው ቀርተዋል።


ጥቂት ከመፅሐፉ የተወሰደ......
በእስር ቤት ደረሰባቸውን ፀዋትወ መከራ በዓይን ያዩ በታላቁ ቤተመንግስት አብረዋቸው ታስረው የቆዩ ፤ በአፄ ኃ/ስላሴ ዘመን በስልጣን ላይ የነበሩ ታላላቅ ሰዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ የአይን ምስክሮች መካከል እስካሁን ድረስ በህይወተ ስጋ ካሉት ከአቶ አብርሐም ወርቅነህ እና ከጀኔራል መኮንን ደነቀ በተገኝው የቃል መረጃ መሰረት ቅዱስነታቸው መጀመሪያ የታሰሩት ለብቻቸው በኢዮቤልዩ ቤተመንግስት ነበር፡፡ በዚህ ቦታ ጥቂት ቀናት ከቆዩ በኋላ ........

.......በአንዲት ጠባብ ክፍል ውስጥ አስገብተው እጃቸውንና እግራቸውን ከአልጋ ጋር ጠፍረው አሰሯቸው ፡፡ ቀንም ሆነ ማታ ለሽንት ሲወጡ ካልሆነ በስተቀር ሰንሰለቱ አይፈታላቸውም ነበር በዚህ አይነት ለአራት ቀናት እንዲሰቃዩ ከተደረገ በኋላ ባለስልጣኖች ታስረውበት ወደነበረው ቁጠር 1 እስር ቤት ወሰዷቸውወቅቱ አብይ ፆም ነበር ከጎፋ ገብርኤል ተይዘው ከመጡበት ቀን ጀምሮ ለ40 ቀናት ያህል እህል የሚባል ነገር አልቀመሱም ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ጣታቸውን በውሀ ውስጥ በመንከር ከንፈራቸውን ከማርጠብ በስተቀር ጥም የሚቆርጥ ውሀ እንኳን አልጠጡም፡፡ ምግብ እንዲበሉ አንዳንድ ደርግ ባለስልጣናት እና አብረዋቸው ታስረው የነበሩ አዛውንቶች ለምነዋቸው ነበር ነገር ግን ለመብላት ፍቃደኛ አልነበሩም  እስከ ፋሲካ ማግስት ድረስ ምንም ሳይቀምሱ ቆይተዋል ፡፡ ለፋሲካ ማግስት ግን እስረኞች መካከል አረጋውያኑ አጥብቀውና አስጨንቀው ስለለመኗቸው እህል ሊበሉ ችለዋል፡፡

His Holiness Preaching the word of God at the Harar Academy 

ከላይ በተጠቀሱት ሰዎች መረጃ መሰረት በእስር ቤት ስቃይ ካሳዩአቸው ሰዎች መካከል ሻለቃ ስሜ የተባለ ዘብ ኋላፊ የፈፀመባቸው ግፍ ሳይፀቀስ አይታለፍም ፡፡ ይህ ሰው እርሳቸውን የማበሳጨት ተልዕኮ ስለነበረው በንቀት ‹አባ መልአክቱ›› እያለ ይጠራቸው ነበር፡፡ ሞላል የሚነካ አነጋገርም ይናገራቸው ነበር፡፡ ከወርቅ የተሰራ የእጅ መስቀላቸውን ቀምቶ እስከመውሰድ ደርሷል፡፡ ከሚተኙበት ትንሽ ክፍል ውስጥ ሰቅለውት የነበረውን የጌታችን እና የመድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ስዕልም በስልጣኑ አውርዶ ወስዶባቸዋል፡፡ የዚህ ሰው ድርጊት ከበስተኋላው የሚገፋፋው ጠላት እንዳለ ያመላታል፡፡ የነበራቸው አነስተኛ ግላዊ ነፃነት እንኳን እስከዚህ ድረስ ተገፍፎ እንደነበር የሻለቃው ድርጊት ያሳያል፡፡
ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።
ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።
የማቴዎስ ወንጌል 5፤ (11-12)
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ በብዙ ስቃይ እያዩ በእስር ቤት የቆዩት እስከ  ሐምሌ 7 1971 ዓ.ም ነበር በዚህ ቀን በ5 ሰዓት እስረኛው እንዲሰበሰብ ታዞ ሲሰበሰብ አንድ ዘበኛ መጣና የሁለት እስረኞችንና የብፁእነታቸውን ስም ጠርቶ ብርድ ልብሳቸውን እና የሽንት ቤት ወረቀታቸውን ይዘው እንዲወጡ አዘዘ፡፡ በዚህ ወቅት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ወደ ክፍላቸው ገብተው አጭር ፀሎት ካደረጉ በኋላ ጥቁር ቀሚሳቸውን ለብሰው ነጠላ ጫማ አድርገው ቆባቸውን ደፍተውና ከእንጨት የተሰራ የእጅ መስቀላቸውን ይዘው እስረኞችን ካፅናኑ እና መስቀል ካሳለሙ በኋላ ‹‹ እግዚሐብሔር ያስፈታችሁ›› በማለት ተሰናብተዋቸው ወጡ፡፡..


የበፊት አባ ገብረመድን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) በ1965 ዓ.ም በአሜሪካ ይህን መፅሀፍ ሲያዘጋጁ(ከመፅሐፉ የተወሰደ)

ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ፤አባ ገ/መድህን (አቡነ ጳውሎስ)እና አቡነ አትናቴዎስ የቅዱስ ዮሐንስን ገዳምና ዩኒቨርሲቲ ሲጎበኙ
አቡነ ቴዎፍሎስና አቡነ ጳውሎስ


‹‹ጊዜው ክረምት ነበር አባታችን አቡነ ቴዎፍሎስ ተይዘው ወደ ራስ አስራት ካሳ ግቢ አ.አበባ ከፍተኛ 12 ቀበሌ 22 መጡ በወቅቱ የለበሱት ጥቁር የሐር ቀሚስ ጥቁር ነጠላ ጫማ ጥቁር የመነኩሴ ቆብ ነበር፡፡ እንደ ወትሮ በአንገታቸው ያጠለቁት ወይም በእጃቸው የያዙት መስቀል ግን አልነበረም ፡፡ በተጠቀሰው ግቢ ውስጥ ወዳለው ቤት እንዲገቡ ሲደረግ ከውስጥ የተደበቁ ኮማንዶዎች ባዘጋጁት ገመድ በድንገገት አንገታቸውን ሸምቀቅ አድርገው በማነቅ ገደሏቸው፡፡ወዲያውም አስከሬን የሚያነሱ ሌሎች ሰራተኞች አስከሬናቸውን አንስተው ከቤቱ ውጪ ባለው ግንብ ስር በስተ ምዕራብ በኩል በተቆፈረው እና በርካታ ሬሳ በተጣለበት ጉድጓድ ውስጥ ወርውረው ጣሉት››    በጊዜው የነበረ የዓይን ምስክር ወታደር የሰጠው ቃል

አባታችን አቡነ ቴዎፍሎስ የተቀበሩበት ቦታ ሲቆፈር

ከዚህ በኋላ ቅዱስነታቸው የት እንደደረሱ ምን አይነት ግድያ እንደተፈጸመባቸው ሳይታወቅ ለ13 ዓመት ተዳፍኖ ቆየ፡፡ ነገር ግን ‹‹ የማይገለጥ የተከደነ ፤ የማይታወቅ የተሰወረ ምንም የለም›› ማቴ 16፤26 እንደተባለው ጊዜ ሲደርስ በምን አኳኋን እንደሞቱና አስከሬናቸው የት ቦታ እንደተጣለ ሊታወቅ በመቻሉ በእንጦጦ አውራጃ ከፍተኛ 12 ቀበሌ 22 ከሚገኝው ከራስ አስራት ካሳ ግቢ አስከሬናቸው ተቆፍሮ ወጥቶ በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን በክብር ሊያርፍ በቅቷል፡፡ 
ለአባታችን ለአቡነ ቴዎፍሎስ ጳጳሳት ጸሎተ ፍትሐት ሲያደርሱ

Leaders of the Greek Orthodox Church in Addis Ababa taking part in the funeral serviceአቡነ ጳውሎስ ጳጳስ ሁነው ከመሾማቸው በፊት ስማቸው አባ ገ/መዴህን ይባል ነበር።አባ ገ/መድህን በወቅቱ በነበሩት ፓትሪያሪክ አቡነ ቴዎፍሎስ ተጠቁመው ለጵጵስና የታጩ ቢሆንም በሶስት ምክንያቶች የወቅቱ ሲኖዶስ ሳይመረጡ ቀርተዋል ሲል ምክንያቶቹን ይዘረዝራል፡፡( ‹‹የማይገለጥ የተከደነ የለም›› የሚባለውን መጽሐፍ ውስጥ) ፡፡በጊዜው አቡነ ቴዎፍሎስ ሶስት አባቶችን ለጵጵስና ቢያቀርቡም ሲኖዶሱ ሁለቱን ተቀብሎ ሶስተኛውን  አባ ገብረመድንን(አቡነ ጳውሎስን) ውድቅ አድርጎ ነበር፡፡ በወቅቱ በቤተክርስትያኒቷ ውስጥ የሚታተም አንድ ጋዜጣ የሁለቱን ጳጳሳት ስም ጠቅሶ ዘገባ ሲያቀርብ የአባ ጳውሎስ ስም በዚያ አልተጠቀሰም።ይሄም የሆነው አባ ጳውሎስ በዚያን እለት በተደረገው የሲኖዶስ ስብሰባ ሳይመረጡ ውድቅ ሁነው በመቅረታቸው ነው ይላል መጽሐፉ።ለምን ጋዜጣው የአባ ጳውሎስን ስም አላወጣም ሚለውን ጥያቄ የአባ ጳውሎስ ወገኖች መልስ መስጠት ይጠበቅባቸዋል።

ለሶስት መነኮሳት(ለአቡነ ባስልዮስ፤ለአቡነ ጴጥሮስና ለአቡነ ጳውሎስ) ሲመተ ጵጵስና በሰጡበት ዕለት 

አቡነ ቴዎፍሎስ በጊዜው ለአባ ገ/መድህን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) እንዲ ብለው ነበር …. አባ ገብረመድን (የአሁኑ አቡነ ጳውሎስ) በነገሮች በጣም ሲቸኩሉ ፤ ለመሾም በጣም ሲጣደፉ፤ ለጵጵስና እንዲያጯቸው እና በጊዜው የነበረው ሲኖዶስ እንዲያፀድቅላቸው ከልክ ያለፈ ምኞታቸውን የተመለከቱት አቡነ ቴዎፍሎስ ‹ ልጄ ቀስ በል ጵጵስናውን ትደርስበታለህ ኋላ ግን ሸክሙን  አትችለውም›› ብለዋቸው ነበር፡፡ (ኢትዮጵያ በ20ኛ ክፍለ ዘመን መፅሀፍ)፡፡4 comments:

 1. ስራችሁ መልካም ሆኖ ሳለ " ይጠብቁን......" የምትሉት ነገር ያሰለቻል። እስካሁንም ቃላችሁን አላከበራችሁም። ስለሆነም ወደ እናንተ ገጽ ላለመግባት ወሰንሁ።
  ሰላም ሁኑ።

  ReplyDelete
 2. ኣረ እንጠብቃለን……ግን የውሃ ሽታ እንዳትሆኑ

  ReplyDelete
 3. ezgabeher ewnatun becha endetsefu yerdach

  ReplyDelete
 4. ስለ አባታችን አቡነ ቴዎፍሎስ የሰጣችሁን ማብራሪያ በጣም ገንቢ ነው! ቃለህዎት ያሰማልን:: ስለሌሎች ክሪቲሳይዝ ከማድረግ ግን እራሳችን እንመርምር::

  ReplyDelete