Thursday, September 8, 2011

ድንቅ ተአምር

ይህ የእመቤታችንን ድንቅ ተአምር የተነገረው  ነሐሴ 19/2003 በግቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የማታ ጉባኤ ሲሆን ነገሩም እንዲህ ነው::
  • “እማየ” ብሎ ጠራኝ እኔም “አቤት” አልኩት “ጆሮወቼ ሰሙልኝ” አለኝ፡፡ እኔም “ልብህ ቢሰማ ነውንጅ የሚሻለው” አልኩት፡
ይህ የእመቤታችንን ድንቅ ተአምር የተነገረው ትናንት ነሃሴ 19/2003 በግቢ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የማታ ጉባኤ ሲሆን ነገሩም እንዲህ ነው ፦ ተአምሩን የመሰከሩት አንዲት እናት ሲሆኑ “የእመቤቴን ስም እየጠራሁ ያለአባት ያሳደግኩት ልጅ ነበርኝ ፡ እኔም ልጄም እመቤታችንን በጣም እንወድ ነበረ ፡ ያለአባት በእመቤቴ ስም ያሳደኩት ልጄ ተምሮልኝ ጥሩ ስራ ያዘልኝ ፡ በዚህ ደስ ብሎኝ ሳለ ልጄ በስራ ቦታ ካልሆኑ ልጆች ጋር ገጥሞ አዲስ ነገርን ተማረብኝ ፡ አንድ ቀን ማታ ሲመጣ “ እናቴ ሆይ ጌታን ተቀበይ” አለኝ ይህን ሲለኝ ደነገጥኩ “እመቤታችንስ” ስለው “ዙሪያ ጥምጥም መሄዱ ይበቃናል አንቺም እኔም ጌታን መቀበል አለብን” አለኝ ፡ እኔም ጧት ማታ አለቅስ ጀመር ፡ ለልጄም ይህ የነፍስ በሽታ ለስጋውም ተርፎ ሁለቱ ጆሮወቹ አልሰማም አሉት፡፡ በዚህም የተነሳ ጴንጤወች እንፀልይልህ ብለው በአዳራሻቸው ወሰዱት ፡ ጆሮወቼ ይድኑ ይሆን ብሎ ተስፋ ያደረገው ልጄም ይባስ ብሎ ሁለቱም አይኖቹ ጠፉ ፡ ከዚህ በኅላ እቤት ተኛ ፡ እኔም እያለቀስኩ እኖር ነበር፡፡ አስቡት ጆሮውንኳ ባይሰማ አይን ቢኖረው በምልክት እንግባባ ነበር ፡ ወይንም አይኑ ባይኖርና ጆሮው ቢሰማ በድምፅ እንግባባ ነበር አሁን ግን እጅግ ችግር ሆነብኝ፡፡ ከሁሉ የሚያስጨንቀኝ ግን እመቤቴን መክዳቱ ነበር፡፡ 
አንድ ቀን ቤተክርስቲያን ምስክርነት ሲሰጥ ሰምቼ እኔም በሃይላንድ ፀበል ይዜ ወደቤት ሄድኩኝ፡፡ በሁለቱ ጆሮወቹ ፀበሉን አፈሰስኩበት፡፡ የእመቤቴ ስእል ፊትም ተንበርክኬ “እመቤቴ ሆይ ጆሮውም አይስማ ፡ አይኑም አይይ ፡ ነገር ግን ልቡን መልሺልኝ” እያልኩ አልቅሼ ፀልየ ወደ መኝታየ ሄድኩኝ ሌሊት 10፡00 ላይ ልጄ “እማየ” ብሎ ጠራኝ እኔም “አቤት” አልኩት “ጆሮወቼ ሰሙልኝ” አለኝ፡፡ እኔም “ልብህ ቢሰማ ነውንጅ የሚሻለው” አልኩት፡፡ አሁንም ትንሽ ቆይቶ 11፡00 ላይ “ እማየ የእመቤታችንን ስእሏን ስጭኝ” አለኝ ፡ እኔም ሰጠሁት እሱም ስእሏን አቅፎ ለአንድ ሰአት ያክል አለቀሰ፡፡ ትንሽ ቆይቶም “እማየ” አለኝ ፡ እኔም “አቤት ልጄ” አልኩት ፡ እርሱም ”ሁለቱም አይኖቼ በሩልኝ” አለኝ፡፡ ደስታየን እንዴት እንደምገልፀው አላውቅም ፡ የኔ እመቤት የልጄን የነፍሱንም የስጋውንም ህመም ፈወሰችልኝ፡፡ አሁንም ልጄ እዚሁ ቤተክርስቲያን ከእመቤቴ ስእል ፊት ተንበርክኮ እየፀለየ ነው፡፡ እኔን የሰማች እናንተንም ትስማልኝ” ይህ ታአምር እንዴት ደስ ይላል፡፡ እመቤታችን ሆይ ስለዚህ እንወድሻለን ፡ ከፍ ከፍ እናደርግሻለን ፡ በልጅሽ አምነው በአማላጅነሽ ተማምነው ስምሽን የሚጠሩትን እንደማትተያቸው እናውቃለን፡፡ ድንግል ሆይ ስለዚህ ክብር ምስጋና ይገባሻል፡፡ አንቺን ለእናትነትና ለአማላጅነት የሰጠን ጌታችን አምላካችንና መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፍቅሩ ነገር ምን ይረቅ?


Source:- Mahlet Girma's post on Mehal zege Giorgis rebulding committee face book pagehttp://www.facebook.com/groups/giorgis/. (It is inactive to share. )

2 comments:

  1. ligune yesemache enatachine egnanime tisimane.amene

    ReplyDelete
  2. YeOrthodox teamerua ayalkim ewonetim andadirgen geta. Egzihaber emembetachinen seten bizowochim alawequatim. Des yemil misikirinet ena lehiwotachinim tesfa yemistet newe. Egzihabere yimesegen yemebetachinim milijana tselot ayileyen amen.

    ReplyDelete