Sunday, September 4, 2011


 አባ ናትናኤል ወደ ሱዳን ፈረጠጡ”

በሸዊት ገ/ኪዳን (shewitgbrkdn95@gmail.com)
  • ጸሎት በእንተ ማኅበረ ቅዱሳን የሚል አነስተኛ ጽሑፍ በትነዋል፡፡
  • ወደ ሱዳን ለመውጣታቸው የቅዱስ ፓትርያርኩና የአቡነ ፋኑኤል እርዳታ እንዳለበት እየተወራ ነው::
  • አዋሳ ላይ ይኽንን ጽሐፍ የሚያሰራጩት በሕግ አካላት እየታደኑ ነው::ጥቂት የማይባሉ ወዳጆቻቸው በመፈረጠጣቸውና በበተኑት ተራ ጽሑፍ እጅ ግ በጣም አዝነዋል የአዋሳ ምዕመናን ግን ይኽ እንደሚሆነ እናውቅ ነበር ይላሉ::

“አባ” ናትናኤል
እነ በጋሻውና ትዝታው ባለቤቱ አይታወቅም እያሉ ማስተባበያ ለመስጠት ላይ ታች የሚሉለትና ነገር ግን በአዋሳ ምዕመናን እንደተዘጋጀና አዲስ አበባ ለአቤቱታ በሚመላለሱበት ጊዜ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስነታቸውን ጨምሮ ለብፁዐን አበው በነጻና በስፍራው ለተገኘው ምዕመን በአነስተኛ ዋጋ ያሰራጩት ቁጥር አንድ ቪሲዲ ካሴት ላይ ሦስቱ ወፎቹ ተበለው ከተጠቀሱት “መነኮሳት” አንዱ የሆነውና በወቅቱ  የአዋሳ ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን “አስተዳዳሪ”የነበረው “አባ” ናትናኤል በቅርቡ ምእመናን በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ይጸልዩበት በሚል “ጸሎት በእንተ ማኅበረ ቅዱሳን”የሚል በይዘትም ሆነ በቅርጽ  አነስተኛ የሆነ ጽሑፍ አዘጋጅቶ በመበተን የሚከተለውን በመገመት ይመስላል ወደ ሱዳን ኮብልሏል ሲሉ የአዋሳዎቹ ገብርኄራውያን ገልጸውልናል፡


መታሰቢያነቱ “በተቀነባበረ የሐሰት ክስ ያለጥፋታቸው ተፈረዶባቸው በወኅኒ ለሚማቅቁት ለወጣት ገዛኸኝ አበራ/በአዋሳው ብጥብጥ ቀንደኛ ተዋናይና የተሐድሶ እንቅስቃሴ አራማጅ ከመሆኑም ሌላ ራሱን አንድ ጊዜ የተስፋ ኪዳነ ምህረት ፀረ ኤድስ ማኅበር ሰብሳቢ፤ሌላ ጊዜ የማኅበሩ ሰብሳቢና የእድሩ መሪ እያለ ከአረጋውያን መርጃ(ሜሪጆይ)ሳይቀር ከበርካታ ማኅበራትና ግለሰቦች ላይ በርካታ ገንዘብ በማጭበርበሩ በሕግ እንደ ተፈረደበት ይታወቃል)እና ለሌሎቹም፡፡.እንዲሁም በአመጸኞች እብሪት  የተነሳ ከሀገረ ስብከታቸው ለተነሱት ለብፁዕ አቡነ ፋኑኤ እና ለሌሎችም ግብረ አበሮቹ ባደረገው በዚህ ጽሑፉ ሙሉ ለሙሉ ማኅበረ ቅዱሳንን የሚዘልፍ ሲሆን
ለምሳሌ”አቤቱ ጌታ ሆይ ይኽ ማኅበር ማን እንደሆነ ስራውና ዓላማው ምን እንደሆነ አንተ ታውቃለህና ካንተ የሚሰወር ምንም ነገር የለም ነገር ግን አምላኬ ለምን ዝም አልክ ተነስ እንጂ ጠላቶችህ ይበተኑ”ይላል፡፡ አቡነ ጳውሎስን ደግሞ “አቤቱ የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ሆይ በዘመናችን አባት አድርገህ የሰጠህንን የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪካዊ አባት የእኛም አማላጅ የሆኑትን ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ጳውሎስን….መንፈሳዊ ስልጣናቸውን ጠብቅልን ሞገስ ሰጥተህ ለዘልአለም አኑርልን አሜን፡፡”ብሎ ያመሰግናል፡፡ ሌሎች ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳትን ግን “ቅዱስ እግዚአብሔር ሆይ ልባቸው በዚህ እርኩስ ማኅበር ልዩ ልዩ ስጦታ የሸፈተባቸውን ሊቃነ ጳጳሳት ልቦናቸውን መልስ….” እያለ ይወቅሳል፡፡ይህንን አነስተኛ ጽሑፍ በአዋሳ ከተማ በምዕመኑ መሃል እየተሽለኮለኩ የሚበትኑትን አስመልክቶ የክልሉ መንግስት የፀጥታ አባላት ጥቆማው ከደረሳቸው ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስዱ በመናገራቸው ምዕመናን በዐይነ ቁራኛ እየጠበቁ መሆኑን ምነጮቻችን ገልጸውልናል፡፡በቅዱስ ሲኖዶስ ሕጋዊ ፈቃድ ተሰጥቶት በአገር ውሰጥና በውጪው ዓለም በስፋት እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ማኅበረ ቅዱሳን ይህንን ጉዳይ በቸልታ ሳይመለከተው በተፈጸመው የስም ማጥፋት ወንጀል ምክንያት“አባ”ናትናኤልን ተከታትሎ ለፍርድ አቅርቦ እንደሚያሳየን እምነታችን ነው የሚሉት የአዋሳ ምዕመናን ይህ ድርጊት የሚያሳየን እነ ያሬድ አደመና በጋሻው ደሳለኝ ወዘተ….ሲክቡት የኖረው ሐረር ላይ እራሱ በጋሻው ከነሐሴ 13-15ቀን 2003 ዓ.ም “የአዲስ አበባ ህዝብ ወሬኛ ነው በኛ ጉዳይ ተፈትኖ ወድቋል” ብሎ ማለት ነው የተሐድሶ ካብ የመፈራረሱ ምልክትን ሆኖል ይኽም እንደሚሆን እንጠብቅ ነበር ብለዋል፡፡ በተያያዘ ዜና በአዋሳ ከተማ ልዩ ስሙ ሞኖፖል በሚባለው አካባቢ ያለው የደብረ መንክራት ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን “አስተዳዳሪ”የነበሩትና የተሐድሶ አቀንቃኝ የነበሩት “አባ”ሲሳይ የተባሉት መነኩሴ የቤተ ክርስቲያኑን 30፣000( ሠላሳ ሺህ) ብር ዘርፈው  የተሰወሩ መሆኑን ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸዋል፡፡የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል እየወሰዱት ባለው እርምጃና እያስተካከሉት ባለው የአስተዳደር ሥራ የተደሰቱ በርካታ የአዋሳ ምዕመናን እነዚህ ከተሐድሶ ጋር ይሠሩ የነበሩትና ለአዋሳው ብጥብጥ በአንድም በሌላም መንገድ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ሲያደርጉ የነበሩት ምንደኞች አሁን የተፈጠረው ሰላማዊ ሁኔታ ስለማይመቻቸው እየወሰዱ ባሉት ዘርፎና ተሳድቦ የመፈርጠጥ እርምጃ እንደሚገፉበት የታመነ ነው፡፡
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን!!!

1 comment:

  1. Ewinet new.Yefertirtu beyalubet.Giberachew asadwachewim ayileqachiu zewtir hilinachew wist yaqachilal::

    ReplyDelete