አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10፣2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ
ክርስቲያን የአፋን ኦሮሞ የቅዳሴ መጽሀፍን ዛሬ አስመረቀች። መጽሀፈ ቅዳሴው የቋንቋው ተናጋሪ የሆኑ የክልሉ ተወላጆች በቀላሉ እንዲረዱትና እንዲያስቀድሱ የተዘጋጀ ነው። 10
ዓመት ያህል
በፈጀው በዚህ
የትርጉም ስራ
ላይ የቤተ
ክርስቲያኗ ብጹዓን አበው ሊቃነ ጻጻሳትና ሊቃውንት እንድሁም የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ተሳትፈውበታል። 516
ገጾች ያሉት
መጽሀፈ ቅዳሴው 14ቱን የቅዳሴ ሂደቶች ያካተተ መሆኑም ተነግሯል።
ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በምረቃ ስነ
ስርዓቱ ላይ
ባስተላለፉት መልእክት ቤተ ክርስቲያን ሁሉን
አቀፍ ሆና
በእኩልነት የምታገለግል መሆኑን ገልጸው፥ በቀጣይ በሌሎች ቋንቋዎች ይሀው
ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በምረቃው ላይ የቀድሞ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎችና የክልሉ ተወላጆች ተገኝተዋል።
No comments:
Post a Comment