Wednesday, March 30, 2016

አንድ ካሬ 305 ሺህ ብር በሊዝ በሚሸጥበት ወቅት ፤ አንድ ካሬ በ5 ብር የምታከራይ ቤተክርስቲያን



(አንድ አድርገን መጋቢት 21 2008 ዓ.ም ፡- የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኝ ሲሆን ይህ / 1986 . በአካባቢው ምዕመናን እንደተመሰረተ ይነነገራል፡፡ የቤተክርስቲያኑ ይዞታ ወደ 80ሺ ካሬ የሚጠጋ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተሰሩ ወይም በመሰራት ላይ ከሚገኙ እጅግ ግዙፍ ከሚባሉ አብያተክርስቲያናት ውስጥ አንዱ ሊሆን የሚችል ሕንጻ ቤተክርስቲያን እያስገነባ ይገኛል፡፡

የቤተክርስቲያኒቱ አስተዳደር በተለያዩ ስራዎች ለተሰማሩ አስራ ሁለት ግለሰቦች  በወር 157,332 ወርሐዊ ኪራይ የሚያገኝ ሲሆን ከ7ሺህ ካሬ በላይ የሚገኝውን ቦታ ደግሞ  በካሬ ሜትር 5 ብር እስከ  8 ብር ከግለሰቦች እንዳከራየና   ወርሃዊ ኪራይ እንደሚሰበስብ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ድረ-ገጽ ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ 

ከዓመት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ቤቶችን ከቤተክርስቲያኒቱ ከ30 ዓመት በፊት በተሰላ ሂሳብ በወር እስከ 150 ብር ተከራይተው ለሦስተኛ ወገን በወር እስከ 10ሺህ ብር ድረስ የሚያከራዩ  ሰዎች ስም ዝርዝርና በኪራይ ውል በስማቸው የሚገኙ ቤቶች እና የሚገኙበት አካባቢ ፤ የተከራዩበት ወርሃዊ ሂሳብ በሚመለከት  ጥቅት ግለሰቦች  ቤተክርስቲያኒቱን የኪራይ መሰብሰቢያ መድረክ እንዳደረጓት እና ይህን ጉዳይ ለጠቅላይ ቤተክህነት ቢያሳውቁ መልስ እንዳላገኙ በመግለጽ ለተወካዮች ምክር ቤት ጉዳዩ ይመለከተናል ያሉ ሰዎች የአቤቱታ ደብዳቤ  ያስገቡ ሲሆን ምክር ቤቱም ጉዳዩን በወቅቱ ለነበሩት የአፈጉባኤ ከፍተኛ የሕግ አማካሪ አቶ መሀመድ አህመድ ልኮ መልስ ሰጥቶበታል፡፡ 

ምክር ቤቱ የቀረበውን አቤቱታ እንደተመለከተው እና ይህ በቤተክርስቲያኒቱ የበላይ አካል መታየት እንዳለበት ፤ መልስ መስጠት እና ማስተካከል ያለባት ቤተክርስቲያኒቷ እንደሆነች ፤ ምክር ቤቱ ይህን ጉዳይ አጣርቶ እርምጃ መውሰድ እንደማይችልና ከተቋቋመበት አላማ ውጪ መሆኑን ገልጾ ለጠያቂዎች መልስ ሰጥቷል፡፡

አሁን አንድ ካሬ መንግስት ከ305ሺህ ብር የሊዝ ዋጋ የሚሸጥበት ሰዓት ቤተክርስቲያን ግን በካሬ ከ5ብር እስከ ስምንት ብር ድረስ ቦታዋን ለግለሰቦች አከራይታ ትገኛለች፡፡

1 comment:

  1. ewenet ande ken mewtato ahyekerem Egizahber bezegeyem yemekedemewe yelem firedon yeferedale

    ReplyDelete